Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ ሙሐመድ (የሙሐመድ ምዕራፍ)

47:1
እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድም የከለከሉ (አላህ) ሥራዎቻቸውን አጠፋባቸው።

Those who disbelieve and avert [people] from the way of Allah - He will waste their deeds.

47:2
እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ በሙሐመድ ላይም በተወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት ስለ ሆነ ያመኑ ከነርሱ ላይ ኃጢያቶቻቸውን ያብብሳል፤ ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል።

And those who believe and do righteous deeds and believe in what has been sent down upon Muhammad - and it is the truth from their Lord - He will remove from them their misdeeds and amend their condition.

47:3
ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመሆናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የሆነን እውነት ስለ ተከተሉ ነው። እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል።

That is because those who disbelieve follow falsehood, and those who believe follow the truth from their Lord. Thus does Allah present to the people their comparisons.

47:4
እነዚያንም የካዱትን (በጦር ላይ) ባገኛችሁት ጊዜ ጫንቃዎችን በኃይል ምቱ፤ ባደከማችኋቸው ጊዜ (አትግደሏቸው ማርኳቸው)፤ ማሠሪያውንም አጥብቁ፤ በኃላም ወይንም በነጻ ትለቁዋላችሁ ወይም ትበዧቸዋላችሁ፤ (ይህም) ጦሪቱ መሣሪያዋን እስክምትጥል ድረስ ነው፤ (ነገሩ) ይህ ነው፤ አላህም ቢሻ ከነሱ (ያለጦር) በተበቀለ ነበር፤ ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር፣ (በዚህ አዘዛችሁ)፤ እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉትን ሥርዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸውም።

So when you meet those who disbelieve [in battle], strike [their] necks until, when you have inflicted slaughter upon them, then secure their bonds, and either [confer] favor afterwards or ransom [them] until the war lays down its burdens. That [is the command]. And if Allah had willed, He could have taken vengeance upon them [Himself], but [He ordered armed struggle] to test some of you by means of others. And those who are killed in the cause of Allah - never will He waste their deeds.

47:5
በእርግጥ ይመራቸዋል፤ ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል።

He will guide them and amend their condition

47:6
ገነትንም ያገባቸዋል፤ ለነሱ አስታውቋታል።

And admit them to Paradise, which He has made known to them.

47:7
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ሃይማኖቱን) ብትረዱ ይረዳችኋል፤ ጫማዎቻቸሁንም ያደላድላልል።

O you who have believed, if you support Allah , He will support you and plant firmly your feet.

47:8
እነዚያም የካዱት ለነሱ ጥፋት ተገባቸው፤ ሥራዎቻቸውንም አጠፋባቸው።

But those who disbelieve - for them is misery, and He will waste their deeds.

47:9
ይህ እነሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው፤ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው።

That is because they disliked what Allah revealed, so He rendered worthless their deeds.

47:10
የነዚያ ከነሱ በፊት የነበሩት (ከሐዲዎች) መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ያዩ ዘንድ በምድር ላይ አልኼዱምን? አላህ በነርሱ ላይ (ያላቸውን ሁሉ) አጠፋባቸው፤ ለከሐዲዎች ሁሉ ብጤዎችዋ አልሏቸው።

Have they not traveled through the land and seen how was the end of those before them? Allah destroyed [everything] over them, and for the disbelievers is something comparable.

47:11
ይህ አላህ የነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ስለ ኾነና ከሐዲዎችም ለነሱ ረዳት ስለሌላቸው ነው።

That is because Allah is the protector of those who have believed and because the disbelievers have no protector.

47:12
አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን፣ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያገባቸዋል፤ እነዚያም የካዱት (በቅርቢቱ ዓለም) ይጣቀማሉ፤ እንሰሳዎችም እንደሚበሉ ይበላሉ፤ እሳትም ለነርሱ መኖሪያቸው ናት።

Indeed, Allah will admit those who have believed and done righteous deeds to gardens beneath which rivers flow, but those who disbelieve enjoy themselves and eat as grazing livestock eat, and the Fire will be a residence for them.

47:13
ከከተማም እርሷ ከዚያች ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በኀይል ጠንካራ የኾነች (ባለቤቶችዋን) ያጠፋናቸው ብዙ ናት፤ ለነርሱም ረዳት አልነበራቸውም።

And how many a city was stronger than your city [Makkah] which drove you out? We destroyed them; and there was no helper for them.

47:14
ከጌታው በኾነች አስረጅ ላይ የኾነ ምእመን ክፉ ስራቸው ለነርሱ እንደ ተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉት ነውን?

So is he who is on clear evidence from his Lord like him to whom the evil of his work has been made attractive and they follow their [own] desires?

47:15
የዚያች ጥንቁቆች ተስፋ የተሰጧት ገነት ምስል በውስጧ ሺታው ከማይለወጥ ውሃ ወንዞች ጣዕሙ ከማይለውጥ ወተትም ወንዞች ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች,ከተነጠረ ማርም ወንዞች አሉባት፤ ለነሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ (በያይነቱ) ከጌታቸው ምሕረትም አላቸው፣ (በዚች ገነት ውስጥ ዘውታሪ የሆነ ሰው) እርሱ በእሳት ውስጥ ዘውታሪ የሆነ ሰው ሞቃትንም ውሃ እንደ ተጋቱ፣ አንጀቶቻቸውንም ወዲያውኑ እንደ ቆራረጠው ነውን? (አይደለም)።

Is the description of Paradise, which the righteous are promised, wherein are rivers of water unaltered, rivers of milk the taste of which never changes, rivers of wine delicious to those who drink, and rivers of purified honey, in which they will have from all [kinds of] fruits and forgiveness from their Lord, like [that of] those who abide eternally in the Fire and are given to drink scalding water that will sever their intestines?

47:16
ከነሱም ወዳንተ የሚያዳምጡ አልሉ፤ ከአንተም ዘንድ በወጡ ጊዜ ለነዚያ ዕውቀት ለተሰጡት አሁን ምን አለ? ይላሉ። እነዚህ እነዚያ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተመባቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ናቸው።

And among them, [O Muhammad], are those who listen to you, until when they depart from you, they say to those who were given knowledge, "What has he said just now?" Those are the ones of whom Allah has sealed over their hearts and who have followed their [own] desires.

47:17
እነዚያም የተመሩት፣ (አላህ) መመራትን ጨመረላቸው፤ (ከእሳት) መጠበቂያቸውንም ሰጣቸው።

And those who are guided - He increases them in guidance and gives them their righteousness.

47:18
ሰዓቲቱንም ድንገት የምትመጣባቸው መሆንዋን እንጅ ይጠባበቃሉን? ምልክቶችዋም በእርግጥ መጥተዋል፤ በመጣቻቸውም ጊዜ ማስታወሳቸው ለነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል?

Then do they await except that the Hour should come upon them unexpectedly? But already there have come [some of] its indications. Then what good to them, when it has come, will be their remembrance?

47:19
እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ዕወቅ፤ ስለ ስሕተትም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፤ አላህም መዘዋወሪያችሁን መርጊያችሁንም ያውቃል።

So know, [O Muhammad], that there is no deity except Allah and ask forgiveness for your sin and for the believing men and believing women. And Allah knows of your movement and your resting place.

47:20
እነዚያም ያመኑት ሰዎች (መታገል ያለባት) ሱራ አትወርድም ኖሮአልን? ይላሉ፤ የጠነከረችም ሱራ በተወረደችና በውስጧም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሺታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የሆነ መከራ በርሱ ላይ እንደ ወደቀበት ሰው አስተያየት ወዳንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፤ ለነሱም ወዮላቸው።

Those who believe say, "Why has a surah not been sent down? But when a precise surah is revealed and fighting is mentioned therein, you see those in whose hearts is hypocrisy looking at you with a look of one overcome by death. And more appropriate for them [would have been]

47:21
ታዛዥነትና መልካም ንግግር (ይሻላቸዋል) ትዕዛዙም ቁርጥ በሆነ ጊዜ ለአላህ (ትዕዛዝ) እውነተኞች በሆኑ ኖሮ ለነሱ የተሻለ በሆነ ነበር።

Obedience and good words. And when the matter [of fighting] was determined, if they had been true to Allah , it would have been better for them.

47:22
ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?

So would you perhaps, if you turned away, cause corruption on earth and sever your [ties of] relationship?

47:23
እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው፤ ያደንቆራቸውም ዓይኖቻቸውንም ያወራቸው ናቸው።

Those [who do so] are the ones that Allah has cursed, so He deafened them and blinded their vision.

47:24
ቁራንንም አያስተነትኑምን? በውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አልሉባትን?

Then do they not reflect upon the Qur'an, or are there locks upon [their] hearts?

47:25
እነዚያ ለነሱ ቅን መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን ለነሱ መመለሳቸው ሸለመላቸው፤ ለነሱም አዝዘናጋቸው።

Indeed, those who reverted back [to disbelief] after guidance had become clear to them - Satan enticed them and prolonged hope for them.

47:26
ይህ እነሱ ለነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት በነገሩ ከፊል እንታዘዛችኋለን ያሉ በመሆናቸው ነው፤ አላህም መደበቃቸውን ያውቃል።

That is because they said to those who disliked what Allah sent down, "We will obey you in part of the matter." And Allah knows what they conceal.

47:27
መላእክትም ፊቶቻቸውንና ጀርቦቻቸውን የሚመቱ ሲሆኑ በገደሉዋቸው ጊዜ (ሁኔታቸው) እንዴት ይሆናል?

Then how [will it be] when the angels take them in death, striking their faces and their backs?

47:28
ይህ እርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ስለ ተከተሉ ውዴታውንም ስለ ጠሉ ነው። ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው።

That is because they followed what angered Allah and disliked [what earns] His pleasure, so He rendered worthless their deeds.

47:29
እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አላህ ቂሞቻቸውን አለማውጣቱን ጠረጠሩን?

Or do those in whose hearts is disease think that Allah would never expose their [feelings of] hatred?

47:30
በሻንም ኖሮ እነሱን ባሳየንህና በምልክታቸውም በእርግጥ ባወቅሀቸው ነበር፤ ንግግርንም በማሸሞራቸው በእርግጥ ታውቃቸዋለህ። አላህም ሥራዎቻችሁን ያውቃል።

And if We willed, We could show them to you, and you would know them by their mark; but you will surely know them by the tone of [their] speech. And Allah knows your deeds.

47:31
ከናንተም ታጋዮቹንና ታጋሾቹን እስከምናውቅ ወሬዎቻችሁንም እስከምንገልፅ ወሬዎቻችሁንም እስከምንገልፅ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን።

And We will surely test you until We make evident those who strive among you [for the cause of Allah ] and the patient, and We will test your affairs.

47:32
እነዚያ የካዱና ከአላህም መንገድ ያገዱ ለነርሱም ቅኑ መንገድ ከተገለጸላቸው በኋላ መልክተኛውን የተከራከሩ አላህን በምንም አይጎዱትም፤ ሥራዎቻቸውን በእርግጥ ያበላሻል።

Indeed, those who disbelieved and averted [people] from the path of Allah and opposed the Messenger after guidance had become clear to them - never will they harm Allah at all, and He will render worthless their deeds.

47:33
እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ተገዙ፤ መል ክተኛውንም ታዘዙ፤ ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ።

O you who have believed, obey Allah and obey the Messenger and do not invalidate your deeds.

47:34
እነዚያ የካዱ ከአላህም መንገድ ያገዱ ከዚያም እነሱ ከሐዲዎች ሆነው የሞቱ አላህ ለነሱ በፍጹም አይምርም።

Indeed, those who disbelieved and averted [people] from the path of Allah and then died while they were disbelievers - never will Allah forgive them.

47:35
እናንተም አሸናፊዎቹ ስትሆኑ አላህም ከናንተጋር ሲሆን አትድከሙ፤ ወደ ዕርቅም አትጥሩ፤ ስራዎቻችሁንም ፈጽሞ አያጎድልባችሁም።

So do not weaken and call for peace while you are superior; and Allah is with you and will never deprive you of [the reward of] your deeds.

47:36
ቅርቢቱ ሕይወት ጫወታና ዛዛታ ብቻ ናት፤ ብታምኑም ብትጠነቀቁም ምንዳዎቻችሁን ይሰጣችኋል፤ገንዘቦቻችሁንም (ሁሉ) አይጠይቃችሁም።

[This] worldly life is only amusement and diversion. And if you believe and fear Allah , He will give you your rewards and not ask you for your properties.

47:37
እርሷን በጠይቃችሁና ችክ ቢልባችሁ ትሰስታላችሁ፤ ቂሞቻችሁንም ያወጣል።

If He should ask you for them and press you, you would withhold, and He would expose your unwillingness.

47:38
ንቁ እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጠሩ ናችሁ፤ ከናንተም ውስጥ የሚሰሰት ሰው አለ፤ የሚሰስትም ሰው የሚሰስተው በራሱ ብቻ ነው፤ አላህም ከበርቴ ነው፤ እናንተም ድሆች ናችሁ፤ ብትሸሹም ሌሎችን ሕዝቦች ይለውጣል፤ ከዚያም (ባለመታዘዝ) ብጤዎቻችሁ አይሆኑም።

Here you are - those invited to spend in the cause of Allah - but among you are those who withhold [out of greed]. And whoever withholds only withholds [benefit] from himself; and Allah is the Free of need, while you are the needy. And if you turn away, He will replace you with another people; then they will not be the likes of you.

Copyright 2013, AmharicQuran.com