Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ጃሢያህ፣ (የተንበርካኪ ምዕራፍ)

45:1
ሐ.መ. (ሐ.ሚም)።

Ha, Meem.

45:2
የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ፣ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው።

The revelation of the Book is from Allah , the Exalted in Might, the Wise.

45:3
በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእመናን ሁሉ (ለችሎታው) እርግጠኛ ምልክቶች አልሉ።

Indeed, within the heavens and earth are signs for the believers.

45:4
እናንተንም በመፍጠር ከተንቀሳቃሽም (በምድር ላይ) የሚበትነውን ሁሉ፣ (በመፍርጠሩ) ለሚያረጋግጡ ሕዝቦች ታምራቶች አልሉ።

And in the creation of yourselves and what He disperses of moving creatures are signs for people who are certain [in faith].

45:5
በሌሊትና መዓልት መተካከትም፣ ከሲሳይም (ከዝናም) አላህ ከሰማይ ባወረደው፣ በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ፣ ነፋሶችንም (በያቅጣጫቸው) በማዘዋወሩ፣ ለሚያውቁ ሕዝቦች ማስረጃ አልሉ።

And [in] the alternation of night and day and [in] what Allah sends down from the sky of provision and gives life thereby to the earth after its lifelessness and [in His] directing of the winds are signs for a people who reason.

45:6
እነዚህ፣ ባንተ ላይ በውነት የምናነባቸው ሲኾኑ፣ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፤ ከአላህና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?

These are the verses of Allah which We recite to you in truth. Then in what statement after Allah and His verses will they believe?

45:7
ውሸታም ኀጢአተኛ ለሆነ ሁሉ ወዮለት። (ጥፋት ተገባው)።

Woe to every sinful liar

45:8
የአላህን አንቀጾች በርሱ ላይ የሚነበቡለት ሲሆኑ፣ ይሰማል፤ ከዚያም የኮራ ሲሆን እንዳልሰማት ኾኖ፣ (በክሕደቱ ላይ) ይዘወትራል፤ በአሳማሚም ቅጣት አብስረው።

Who hears the verses of Allah recited to him, then persists arrogantly as if he had not heard them. So give him tidings of a painful punishment

45:9
ከአንቀጾቻችንም አንዳችን ባወቀ ጊዜ፣ መሳለቂያ አድርጎ ይይዛታል፤ እነዚያ ለነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው።

And when he knows anything of Our verses, he takes them in ridicule. Those will have a humiliating punishment.

45:10
ከፊታቸውም ገሃነም አለች፤ የሰበሰቡትም ሀብት ከነርሱ ላይ ምንንም አይመልስላቸውም፤ ከአላህ ሌላም ረዳቶች አድርገው የያዙዋቸው፣ (አይጠቅሟቸውም)፤ ለነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸው።

Before them is Hell, and what they had earned will not avail them at all nor what they had taken besides Allah as allies. And they will have a great punishment.

45:11
ይህ (ቁርአን) መሪ ነው፤ እነዚያም በጌታቸው አንቀጾች የካዱት፣ ለነሱ ከብርቱ ቅጣት የሆነ አሳማሚ ስቃይ አላቸው።

This [Qur'an] is guidance. And those who have disbelieved in the verses of their Lord will have a painful punishment of foul nature.

45:12
አላህ ያ ባሕርን በውስጡ ታንኳዎች በፈቃዱ እንዲንሻለሉበት፣ ከችሮታውም እንድትፈልጉበት፣ እንድታመሰግኑትም፣ ለናንተ የገራላችሁ ነው።

It is Allah who subjected to you the sea so that ships may sail upon it by His command and that you may seek of His bounty; and perhaps you will be grateful.

45:13
ለናንተም በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ ከርሱ ሲኾን የገራላችሁ ነው፤ በዚህ ለሚያስተነኑ ሕዝቦች ታምራት አለበት።

And He has subjected to you whatever is in the heavens and whatever is on the earth - all from Him. Indeed in that are signs for a people who give thought.

45:14
ለነዚያ ለአመኑት ሰዎች፣ (ምሕረት አድርጉ)፣ በላቸው፤ ለነዚያ የአላህን ቀኖች ለማይፈሩት ይምራሉና፣ ሕዝቦችን ይሠሩት በነበሩት ነገር ይመነዳ ዘንድ፣ (ምሕረት አድርጉ በላቸው)።

Say, [O Muhammad], to those who have believed that they [should] forgive those who expect not the days of Allah so that He may recompense a people for what they used to earn.

45:15
መልካምን የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው፤ ያከፋም ሰው በርሷ ላይ ነው፤ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ።

Whoever does a good deed - it is for himself; and whoever does evil - it is against the self. Then to your Lord you will be returned.

45:16
ለእስራኤል ልጆችም መጽሐፍንና ሕግን፣ ነቢይነትንም በእርግጥ ሰጠናቸው፤ ከመልካም ሲሳዮችም ለገስንላቸው በአለማት ላይም አበለጥናቸው።

And We did certainly give the Children of Israel the Scripture and judgement and prophethood, and We provided them with good things and preferred them over the worlds.

45:17
ከትእዛዝም ግልጾችን ሰጠናቸው፤ ዕውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም፤ ጌታህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል።

And We gave them clear proofs of the matter [of religion]. And they did not differ except after knowledge had come to them - out of jealous animosity between themselves. Indeed, your Lord will judge between them on the Day of Resurrection concerning that over which they used to differ.

45:18
ክዚያም ከነገሩ፣ (ከሃይማኖት)፣ በትክክለኛይቱ ሕግ ላይ አደረግንህ፤ ስለዚህ ተከተላት፤ የነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል።

Then We put you, [O Muhammad], on an ordained way concerning the matter [of religion]; so follow it and do not follow the inclinations of those who do not know.

45:19
እነርሱ ከአላህ (ቅጣት) ምንንም ከአንተ አይገፈትሩልህምና፤ በደለኞችም ከፊላቸው የከፊሉ ረዳቶች ናቸው፤ አላህም የጥንቁቆች ረዳት ነው።

Indeed, they will never avail you against Allah at all. And indeed, the wrongdoers are allies of one another; but Allah is the protector of the righteous.

45:20
ይህ (ቁርአን) ለሰዎች የልብ ብርሃኖች ነው። ለሚያረጋግጡም ሕዝቦች መሪና እዝነት ነው።

This [Qur'an] is enlightenment for mankind and guidance and mercy for a people who are certain [in faith].

45:21
እነዚያ ኀጢያቶችን የሠሩ፣ ሕይወታቸውም ሞታቸውም ትክክል ሲኾን፤ እንደዚያ እንደ አመኑትና መልካሞችን እንደሠሩት ልናደርጋቸው ይጠረጥራሉን? (አይጠርጥሩ)፤ የሚፈርዱት ምንኛ ከፋ!

Or do those who commit evils think We will make them like those who have believed and done righteous deeds - [make them] equal in their life and their death? Evil is that which they judge.

45:22
አላህም ሰማያትንና ምድርን (ለችሎታው እንዲያመለክትባቸውና) ነፍስም ሁሉ በሠራችው ሥራ ትመነዳ ዘንድ፣ በትክክል ፈጠረ፤ እነሱም አይበደሉም።

And Allah created the heavens and earth in truth and so that every soul may be recompensed for what it has earned, and they will not be wronged

45:23
ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣ አላህም ከዕውቀት ጋር ያጠመመውን፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣ በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን፣ ሰው አየህን! ታዲያ ከአላህ ኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሠጹምን?

Have you seen he who has taken as his god his [own] desire, and Allah has sent him astray due to knowledge and has set a seal upon his hearing and his heart and put over his vision a veil? So who will guide him after Allah ? Then will you not be reminded?

45:24
እርሷም (ሕይወት) የቅርቢቱ ሕይወታችን እንጅ ሌላ አይደለችም፤ እንሞታለን፤ ሕያውም እንሆናለን፤ (1) ከጊዜም (ማለፍ) በስተቀር ሌላ አያጠፋንም አሉ፤ ለነርሱም በዚህ (በሚሉት) ምንም ዕውቀት የላቸውም፤ እነርሱ የሚጠራጠሩ እንጅ ሌላ አይደሉም።

And they say, "There is not but our worldly life; we die and live, and nothing destroys us except time." And they have of that no knowledge; they are only assuming.

45:25
አንቀጾቻችንም ግልጾች ሆነው በነሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ፣ ክርክራቸው እውነተኞች እንደ ሆናችሁ፣ አባቶቻችንን አምጡ ማለት እንጅ፣ ሌላ አልነበረም።

And when Our verses are recited to them as clear evidences, their argument is only that they say, "Bring [back] our forefathers, if you should be truthful."

45:26
፦አላህ ሕያው ያደርጋችኋል፤ ከዚያም ያሞታችኋል፤ ከዚያም ወደ ትንሣኤ ቀን ይሰበስባችኋል፤ በርሱ ጥርጥር የለበትም፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም በላቸው።

Say, " Allah causes you to live, then causes you to die; then He will assemble you for the Day of Resurrection, about which there is no doubt, but most of the people do not know."

45:27
የሰማያትና የምድር ግዛት የአላህ ብቻ ነው፤ ሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን ያን፣ ጊዜ አጥፊዎች ይከስራሉ።

And to Allah belongs the dominion of the heavens and the earth. And the Day the Hour appears - that Day the falsifiers will lose.

45:28
ሕዝብንም ሁሉ ተንበርካኪ ሆና ታያታለህ፤ ሕዝብ ሁሉ፣ ወደ መጽሐፏ ትጠራለች፤ ዛሬ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ፣ (ይባላሉ)።

And you will see every nation kneeling [from fear]. Every nation will be called to its record [and told], "Today you will be recompensed for what you used to do.

45:29
ይህ መጽሐፋችን ነው፤ በናንተ ላይ በውነት ይናገራል፤ እኛ ያንን ትሠሩት የነበራችሁትን እናስገለብጥ ነበርን፣ (ይባላሉ)።

This, Our record, speaks about you in truth. Indeed, We were having transcribed whatever you used to do."

45:30
እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩትማ ጌታቸው በእዝነቱ ውስጥ ያገባቸዋል፤ ይህ እርሱ ግልጽ የሆነ ማግኘት ነው።

So as for those who believed and did righteous deeds, their Lord will admit them into His mercy. That is what is the clear attainment

45:31
እነዚያም የካዱትማ (ለነርሱ ይባላሉ)፦ አንቀጾቼ በናንተ ላይ ይነበቡ አልነበሩምን? ኮራችሁም፤ ከሐዲዎች ሕዝቦችም ነበራችሁ።

But as for those who disbelieved, [it will be said], "Were not Our verses recited to you, but you were arrogant and became a people of criminals?

45:32
የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው፤ ሰአቲቱም በርሷ (መምጣት) ጥርጥር የለም፤ በተባለ ጊዜም ሰዓቲቱ ምን እንደ ሆነች አናውቅም፤ መጠራጠርን የምንጠራጠር እንጅ ሌላ አይደለንም፤ እኛም አረጋጋጮች አይደለንም አላችሁ።

And when it was said, 'Indeed, the promise of Allah is truth and the Hour [is coming] - no doubt about it,' you said, 'We know not what is the Hour. We assume only assumption, and we are not convinced.' "

45:33
የሠሩዋቸውም ኀጢአቶች ለነርሱ ይገለጹላቸዋል፤ ያም በርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት በነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል።

And the evil consequences of what they did will appear to them, and they will be enveloped by what they used to ridicule.

45:34
ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን እንደረሳችሁ፣ ዛሬ እንረሳችኋለን፤ (እንተዋችኋለን)፤ መኖሪያችሁም እሳት ናት፤ ለናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም ይባላል።

And it will be said, "Today We will forget you as you forgot the meeting of this Day of yours, and your refuge is the Fire, and for you there are no helpers

45:35
ይሃችሁ እናንተ የአላህን አንቀጾች መቀለጃ አድርጋችሁ በመያዛችሁና ቅርቢቱም ሕይወት ስለ አታለለቻችሁ ነው (ይባላሉ)። ዛሬ ከርሷ አይወጥጡም፤ እነሱም በወቀሳ አይታለፉም።

That is because you took the verses of Allah in ridicule, and worldly life deluded you." So that Day they will not be removed from it, nor will they be asked to appease [ Allah ].

45:36
ምስጋናም ለአላህ፣ ለሰማያት ጌታ፣ ለምድርም ጌታ፣ ለአለማት ጌታ የተገባው ነው።

Then, to Allah belongs [all] praise - Lord of the heavens and Lord of the earth, Lord of the worlds.

45:37
ኩራትም በሰማያትም በምድርም ለርሱ ብቻ ነው፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።

And to Him belongs [all] grandeur within the heavens and the earth, and He is the Exalted in Might, the Wise.

Copyright 2013, AmharicQuran.com