Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ዱኻን፣ (የጭስ ምዕራፍ)

44:1
ሐ.መ. (ሐ ሚም)።

Ha, Meem.

44:2
አብራሪ በሆነው መጽሐፍ እንምላለን።

By the clear Book,

44:3
እኛ (ቁራኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፤ እኛ አስፈሪዎች ነበርንና።

Indeed, We sent it down during a blessed night. Indeed, We were to warn [mankind].

44:4
በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይለያል።

On that night is made distinct every precise matter -

44:5
ከኛ ዘንድ የሆነ ትእዛዝ ሲሆን (አወረድነው) እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን።

[Every] matter [proceeding] from Us. Indeed, We were to send [a messenger]

44:6
ከጌታህ በሆነው ችሮታ (ተላኩ) እነሆ ሰሚው ዐዋቂው ነውና።

As mercy from your Lord. Indeed, He is the Hearing, the Knowing

44:7
የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከሆነው፣ (ተላኩ) የምታረጋግጡ እንደ ሆናችሁ፣ (ነገሩ እንዳልነው መሆኑን እወቁ)።

Lord of the heavens and the earth and that between them, if you would be certain.

44:8
ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ሕያው ያደርጋል፣ ያሞታልም፣ ጌታችሁ፣ የመጀመሪያ አባቶቻችሁም ጌታ ነው።

There is no deity except Him; He gives life and causes death. [He is] your Lord and the Lord of your first forefathers.

44:9
በውነቱ እነሱ፣ የሚጫወቱ ሲሆኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው።

But they are in doubt, amusing themselves.

44:10
ሰማይም በግልፅ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ።

Then watch for the Day when the sky will bring a visible smoke

44:11
ሰዎችን የሚሸፍን (በሆነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው።

Covering the people; this is a painful torment.

44:12
ጌታችን ሆይ! ከኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፤ እኛም አማኞች እንሆናለና፣ (ይላሉም)።

[They will say], "Our Lord, remove from us the torment; indeed, we are believers."

44:13
(ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለነርሱ መገሠጽ እንዴት ይኖራቸዋል፤ አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲሆን (የካዱም ሲሆኑ)።

How will there be for them a reminder [at that time]? And there had come to them a clear Messenger.

44:14
ከዚያም ከርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) የተስተማረ ዕብድ ነው፣ ያሉም ሲሆኑ።

Then they turned away from him and said, "[He was] taught [and is] a madman."

44:15
እኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፤ እናንተ (ወደ ክሕደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ።

Indeed, We will remove the torment for a little. Indeed, you [disbelievers] will return [to disbelief].

44:16
ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን።

The Day We will strike with the greatest assault, indeed, We will take retribution

44:17
ከነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በርግጥ ሞከርን፤ ክቡር መልክተኛም መጣላቸው።

And We had already tried before them the people of Pharaoh, and there came to them a noble messenger,

44:18
የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፤ እኔ ለናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና።

[Saying], "Render to me the servants of Allah . Indeed, I am to you a trustworthy messenger,"

44:19
በአላህም ላይ አትኩሩ፤ እኔ ግልጽ የሆነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)።

And [saying], "Be not haughty with Allah . Indeed, I have come to you with clear authority.

44:20
እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ።

And indeed, I have sought refuge in my Lord and your Lord, lest you stone me.

44:21
በኔም ባታምኑ ራቁኝ፤ (ተዉኝ አለ)።

But if you do not believe me, then leave me alone."

44:22
ቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) እነዚህ አመጠኞች ሕዝቦች ናቸው፤ (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ።

And [finally] he called to his Lord that these were a criminal people

44:23
(ጌታው) ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና።

[ Allah said], "Then set out with My servants by night. Indeed, you are to be pursued.

44:24
ባሕሩንም የተከፈተ ሆኖ ተወው፤ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውና (አለው)።

And leave the sea in stillness. Indeed, they are an army to be drowned."

44:25
ከአትክቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ።

How much they left behind of gardens and springs

44:26
ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም።

And crops and noble sites

44:27
በርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙውን ነገር ተዉ)።

And comfort wherein they were amused.

44:28
(ነገሩ) እንደዚሁ ሆነ፤ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት።

Thus. And We caused to inherit it another people.

44:29
ሰማይና ምድርም በነርሱ ላይ አላለቀሱም፤ የሚቆዩም አልነበሩም።

And the heaven and earth wept not for them, nor were they reprieved.

44:30
የእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከሆነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው።

And We certainly saved the Children of Israel from the humiliating torment -

44:31
ከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ፣ ከወሰን አላፊዎች ነበርና።

From Pharaoh. Indeed, he was a haughty one among the transgressors.

44:32
ከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው።

And We certainly chose them by knowledge over [all] the worlds.

44:33
ከታምራቶችም በውስጡ ግልፅ የሆነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው።

And We gave them of signs that in which there was a clear trial.

44:34
እነዚህ (የመካ ከሐዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፦

Indeed, these [disbelievers] are saying

44:35
እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፤ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም።

"There is not but our first death, and we will not be resurrected.

44:36
እውነተኞች እንደ ሆናችሁ አባቶቻችን አምጡልን።

Then bring [back] our forefathers, if you should be truthful."

44:37
እነርሱ በላጮች ናቸውን? ወይንስ የቱብበዕ ሕዝቦችና። እነዚያ ከነሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፤ እነሱ አመጠኞች ነበሩና።

Are they better or the people of Tubba' and those before them? We destroyed them, [for] indeed, they were criminals.

44:38
ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም።

And We did not create the heavens and earth and that between them in play.

44:39
ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፤ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።

We did not create them except in truth, but most of them do not know.

44:40
የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው።

Indeed, the Day of Judgement is the appointed time for them all -

44:41
ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት፣ እነሱም የማይረዱበት ቀን ነው።

The Day when no relation will avail a relation at all, nor will they be helped -

44:42
አላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፤ (እርሱስ ይረዳል)፤ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና።

Except those [believers] on whom Allah has mercy. Indeed, He is the Exalted in Might, the Merciful.

44:43
የዘቁም ዛፍ(1)

Indeed, the tree of zaqqum

44:44
የኀጣተኛው ምግብ ነው።

Is food for the sinful.

44:45
እንደ ዘይት አተላ ነው፤ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲሆን።

Like murky oil, it boils within bellies

44:46
እንደገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲሆን)።

Like the boiling of scalding water.

44:47
ያዙትም፤ ወደ ገሀነም መካከልም ጎተቱት።

[It will be commanded], "Seize him and drag him into the midst of the Hellfire,

44:48
ከዚያም ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡት።

Then pour over his head from the torment of scalding water."

44:49
ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው፣ ክቡሩ (1) ነህና (ይባላል)።

[It will be said], "Taste! Indeed, you are the honored, the noble!

44:50
ይህ ያ በርሱ ትጠራሩበት የነበራችሁት ነው፤ (ይባላሉ)።

Indeed, this is what you used to dispute."

44:51
ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው።

Indeed, the righteous will be in a secure place;

44:52
በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው።

Within gardens and springs

44:53
ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሆነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ።

Wearing [garments of] fine silk and brocade, facing each other.

44:54
(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናሞች የሆኑን ነጫጭ ሴቶች እናጠናዳቸዋለን።

Thus. And We will marry them to fair women with large, [beautiful] eyes.

44:55
በርሷም ውስጥ የተማመኑ ሆነው፣ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዛሉ።

They will call therein for every [kind of] fruit - safe and secure.

44:56
የፊተኛይቱን ሞት እንጂ (ዳግመኛ) በርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፤ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው።

They will not taste death therein except the first death, and He will have protected them from the punishment of Hellfire

44:57
ከጌታህ በሆነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው።

As bounty from your Lord. That is what is the great attainment.

44:58
(ቁር አኑን) በቋንቋህ ያገራነው፣ (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው።

And indeed, We have eased the Qur'an in your tongue that they might be reminded

44:59
ተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና።

So watch, [O Muhammad]; indeed, they are watching [for your end].

Copyright 2013, AmharicQuran.com