Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ሹራ (የመመካከር ምዕራፍ)

42:1
1. ሐ.መ. (ሐ.ሚም)።

Ha, Meem.

42:2
ዐ.ሰ.ቀ. (ዓይን ሲን ቃፍ)፤ (1)

'Ayn, Seen, Qaf.

42:3
እንደዚሁ (በዚህች ሱራ ውስጥ እንዳለው) አሸናፊው፣ ጥበበኛው አላህ ወዳንተ ያወርዳል፤ ወደነዚያም ወደነበሩት ሕዝቦች፣ (አውርዷል)።

Thus has He revealed to you, [O Muhammad], and to those before you - Allah , the Exalted in Might, the Wise.

42:4
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ነው፤ እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው።

To Him belongs whatever is in the heavens and whatever is in the earth, and He is the Most High, the Most Great.

42:5
(ከአላህ ፍራቻ) ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፤ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያወድሳሉ፤ በምድርም ላለው ፍጡር ምሕረትን ይለምናሉ፤ ንቁ አላህ እርሱ መሐሪው አዛኙ ነው።

The heavens almost break from above them, and the angels exalt [ Allah ] with praise of their Lord and ask forgiveness for those on earth. Unquestionably, it is Allah who is the Forgiving, the Merciful.

42:6
እነዚያም ከርሱ ሌላ (የጣዖታት) ረዳቶችን የያዙ፤ አላህ በነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው አንተም በነርሱ ላይ ኀላፊ አይደለህም።

And those who take as allies other than Him - Allah is [yet] Guardian over them; and you, [O Muhammad], are not over them a manager.

42:7
እንደዚሁም የከተሞች እናት የሆነችውን (የመካን ሰዎች)፣ በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስፈራራ፣ የመሰብሰቢያውንም ቀን፣ በርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የሆነን ቁርአን ወደአንተ አወረድን፤ (ከነሱም) ከፊሉ በገነት ውስጥ ከፊሉም በእሳት ውስጥ ነው።

And thus We have revealed to you an Arabic Qur'an that you may warn the Mother of Cities [Makkah] and those around it and warn of the Day of Assembly, about which there is no doubt. A party will be in Paradise and a party in the Blaze.

42:8
አላህም ባሻ ኖሮ (ባንድ ሃይማኖት ላይ) አንድ ሕዝብ ባደረጋቸው ነበር። ግን የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባል፤ በዳዮችም ለነርሱ ወዳጅና ረዳት ምንም የላቸውም።

And if Allah willed, He could have made them [of] one religion, but He admits whom He wills into His mercy. And the wrongdoers have not any protector or helper.

42:9
ከርሱ ሌላ ረዳቶችን ያዙን? (ረዳቶች አይደሉም)።አላህም ረዳት እርሱ ብቻ ነው።እርሱም ሙታንን ሕያው ያደርጋል፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነው።

Or have they taken protectors [or allies] besides him? But Allah - He is the Protector, and He gives life to the dead, and He is over all things competent.

42:10
ከምንም ነገር ያ በርሱ የተለያዩበት ፍርዱ ወደ አላህ ነው፤ ይሃችሁ አላህ ጌታዬ ነው፤ በርሱ ላይ ተጠጋሁ፤ ወደርሱም እመለሳለሁ፤ (በላቸው)።

And in anything over which you disagree - its ruling is [to be referred] to Allah . [Say], "That is Allah , my Lord; upon Him I have relied, and to Him I turn back."

42:11
ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፤ ከነፍሶቻችሁ (1) ሴቶችን፣ ከቤት እንሰሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፤ በርሱ (2) ያበዛችኋል፤ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፤ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው።

[He is] Creator of the heavens and the earth. He has made for you from yourselves, mates, and among the cattle, mates; He multiplies you thereby. There is nothing like unto Him, and He is the Hearing, the Seeing.

42:12
የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መከፈቻዎች የርሱ ናቸው። ሲሳይን ለሚሻ ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፤ እርሱ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና።

To Him belong the keys of the heavens and the earth. He extends provision for whom He wills and restricts [it]. Indeed He is, of all things, Knowing.

42:13
ለናንተ ከሃይማኖት ያንን በርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፤ ያንንም በርሱ ኢብራሂምን፣ ሙሳንና ዒሳንም ያዘዘበትን፣ ሃይማኖትን በትክክል አቋቋሙ፣ በርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን) በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፤ አላህ የሚሻውን ሰው ወደርሱ (እምነት) ይመርጣል፤የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል።

He has ordained for you of religion what He enjoined upon Noah and that which We have revealed to you, [O Muhammad], and what We enjoined upon Abraham and Moses and Jesus - to establish the religion and not be divided therein. Difficult for those who associate others with Allah is that to which you invite them. Allah chooses for Himself whom He wills and guides to Himself whoever turns back [to Him].

42:14
(የሃይማኖት ሰዎች) ዕውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም፤ እስከተወሰነም ጊዜ (በማቆየት) ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በነሱ መካከል (አሁን) በተፈረደ ነበር። እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፉን እንዲወርሱ የተደረጉት ከርሱ፣ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው።

And they did not become divided until after knowledge had come to them - out of jealous animosity between themselves. And if not for a word that preceded from your Lord [postponing the penalty] until a specified time, it would have been concluded between them. And indeed, those who were granted inheritance of the Scripture after them are, concerning it, in disquieting doubt.

42:15
ለዚህም (ድንጋጌ ሰዎችን) ጥራ፤ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፤ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል፤ በላቸውም፦ ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፤ በመካከላችሁም ላስተካክል ታዘዝኩ፤ አላህ ጌታችን፣ ጌታችሁም ነው፤ ለኛ ሥራዎቻችን አልሉን ለናንተም ሥራዎቻችሁ አልሏችሁ፤ በኛና በናንተ መካከል ክርክር የለም፤ አላህ በመካከላችን ይሰበስባል። መመለሻም ወደርሱ ብቻ ነው።

So to that [religion of Allah ] invite, [O Muhammad], and remain on a right course as you are commanded and do not follow their inclinations but say, "I have believed in what Allah has revealed of the Qur'an, and I have been commanded to do justice among you. Allah is our Lord and your Lord. For us are our deeds, and for you your deeds. There is no [need for] argument between us and you. Allah will bring us together, and to Him is the [final] destination."

42:16
እነዚያም በአላህ (ሃይማኖት) ለርሱ ተቀባይ ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት፣ ማስረጃቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ ናት። በነርሱም ላይ ቁጣ አለባቸው፣ ለነርሱም ብርቱ ቅጣት አልላቸው።

And those who argue concerning Allah after He has been responded to - their argument is invalid with their Lord, and upon them is [His] wrath, and for them is a severe punishment.

42:17
አላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው፤ ሚዛንንም፣ (እንደዚሁ)፤ ሰዓቲቱ ምናልባት ቅርብ መሆንዋን ምን ያሳውቅሃል?

It is Allah who has sent down the Book in truth and [also] the balance. And what will make you perceive? Perhaps the Hour is near.

42:18
እነዚያ በርሷ የማያምኑት፣ በርሷ ያቻኩላሉ፤ እነዚያም ያመኑት ከርሷ ፈሪዎች ናቸው፤ እርሷም እውነት መሆንዋን ያውቃሉ፤ንቁ እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩት በእርግጥ (ከውነት) በራቀ ስሕተት ውስጥ ናቸው።

Those who do not believe in it are impatient for it, but those who believe are fearful of it and know that it is the truth. Unquestionably, those who dispute concerning the Hour are in extreme error.

42:19
አላህ በባሮቹ ርኅሩኅ ነው፤ ለሚሻው ሰው (በሰፊው) ሲሳይን ይሰጣል፤ እርሱም ብርቱው አሸናፊ ነው።

Allah is Subtle with His servants; He gives provisions to whom He wills. And He is the Powerful, the Exalted in Might.

42:20
(በሥራው) የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የሆነ ሰው፣ ለርሱ በአዝመራው ላይ እንጨምርለታለን፤ የቅርቢቱንም ዓለም አዝመራ የሚፈልግ የሆነ ሰው ከርሷ (የተወሰነለትን ብቻ) እንሰጠዋለን፤ ለርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ፋንታ የለውም።

Whoever desires the harvest of the Hereafter - We increase for him in his harvest. And whoever desires the harvest of this world - We give him thereof, but there is not for him in the Hereafter any share.

42:21
ከሃይማኖት አላህ በርሱ ያልፈቀደውን ለነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለነርሱ አልሏቸውን? ይፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) በተፈረደ ነበር፤ በደለኞችም ለርሱ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አልላቸው።

Or have they other deities who have ordained for them a religion to which Allah has not consented? But if not for the decisive word, it would have been concluded between them. And indeed, the wrongdoers will have a painful punishment.

42:22
በደለኞችን ከሠሩት ሥራ (ዋጋ በትንሣኤ ቀን) ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ፤ እርሱም በነርሱ ላይ ወዳቂ ነው። እነዚያም ያመኑት፣ መልካሞችን የሠሩት፣ በገነቶች ጨፌዎች ውስጥ ናቸው። ለነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አልላቸው፤ ይህ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው።

You will see the wrongdoers fearful of what they have earned, and it will [certainly] befall them. And those who have believed and done righteous deeds will be in lush regions of the gardens [in Paradise] having whatever they will in the presence of their Lord. That is what is the great bounty.

42:23
ይህ (ታላቅ ችሮታ)፣ ያ አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ባሮቹን የሚያበስርበት ነው፤ በርሱ (መልክቴን በማድረሴ) ላይ በዝምድና (1) ውዴታን እንጂ ዋጋን አልጠይቃችሁም በላቸው፤ መልካሚቱንም ሥራ የሚሠራ ሰው፣ ለርሱ በርሷ መልካም ነገርን እንጨምርለታለን፤ አላህ መሐሪ አመስጋኝ ነውና።

It is that of which Allah gives good tidings to His servants who believe and do righteous deeds. Say, [O Muhammad], "I do not ask you for this message any payment [but] only good will through kinship." And whoever commits a good deed - We will increase for him good therein. Indeed, Allah is Forgiving and Appreciative.

42:24
ይልቁንም በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ ይላሉን? አላህም ቢሻ በልብህ ላይ ያትማል፤ (2) አላህም ውሸቱን ያብብሳል፤ እውነቱንም በቃላቱ ያረጋግጣል፣ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና።

Or do they say, "He has invented about Allah a lie"? But if Allah willed, He could seal over your heart. And Allah eliminates falsehood and establishes the truth by His words. Indeed, He is Knowing of that within the breasts.

42:25
እርሱም ያ ከባሮቹ ንሰሐን የሚቀበል፣ ከሐጢያቶችም ይቅር የሚል የምትሠሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ነው።

And it is He who accepts repentance from his servants and pardons misdeeds, and He knows what you do.

42:26
እነዚያንም ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን፣ ልመናቸውን ይቀበላል፤ ከችሮታውም ይጨምርላቸዋል፤ ከሐዲዎቹም ለነሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው።

And He answers [the supplication of] those who have believed and done righteous deeds and increases [for] them from His bounty. But the disbelievers will have a severe punishment.

42:27
አላህም ለባሮቹ (ሁሉ) ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ (ሁሉም) ወሰን ባለፉ ነበር፤ ግን የሚሻው በልክ ያወርዳል፤ እርሱ በባሮቹ ውስጥ ዐዋቂ ተመልካች ነውና።

And if Allah had extended [excessively] provision for His servants, they would have committed tyranny throughout the earth. But He sends [it] down in an amount which He wills. Indeed He is, of His servants, Acquainted and Seeing.

42:28
እርሱም ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናምን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው፤እርሱም ረዳቱ ምስጉን ነው።

And it is He who sends down the rain after they had despaired and spreads His mercy. And He is the Protector, the Praiseworthy.

42:29
ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን (መፍጠሩ)፣ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። እርሱም በሚሻ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው።

And whatever strikes you of disaster - it is for what your hands have earned; but He pardons much.

42:30
ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር፣ እጆቻችሁ በሰሩት (ኀጢያት) ምክንያት ነው፤ ከብዙውም ይቅር ይላል።

And you will not cause failure [to Allah ] upon the earth. And you have not besides Allah any protector or helper.

42:31
እናንተም በምድር ውስጥ አሣኞች አይደላችሁም፤ ለናንተም ከአላህ ሌላ ከዘመድም ከረዳትም ምንም የላችሁም።

And whatever strikes you of disaster - it is for what your hands have earned; but He pardons much.

42:32
በባህር ላይ እንደ ጋራዎች ሆነው፣ ተንሻላዮቹም፣ (መርከቦች) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው።

And you will not cause failure [to Allah ] upon the earth. And you have not besides Allah any protector or helper.

42:33
ቢሻ ነፋሱን የረጋ ያደርገዋል፤ በባህሩም ጀርባ ላይ ረጊዎች ይሆናሉ፤ በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ፣ በእርግጥ ምልክቶች አሉ።

If He willed, He could still the wind, and they would remain motionless on its surface. Indeed in that are signs for everyone patient and grateful.

42:34
ወይም በሠሩት ኃጢአት ምክንያት (በማስጠም) ያጠፋቸዋል፤ ከብዙም ይቅርታ ያደርጋል።

Or He could destroy them for what they earned; but He pardons much.

42:35
(ከነሱ ለመበቀል)፤ እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚከራከሩትን ለማወቅ (ያጠፋቸዋል)፤ ለነርሱ ምንም መሸሻ የላቸውም።

And [that is so] those who dispute concerning Our signs may know that for them there is no place of escape.

42:36
ከምንም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፤ አላህ ዘንድ ያለውም ምንዳ ለነዚያ ላአመኑትና በጌታቸው ላይ ለሚጠጉት ሁል ጊዜ ነዋሪ ነው።

So whatever thing you have been given - it is but [for] enjoyment of the worldly life. But what is with Allah is better and more lasting for those who have believed and upon their Lord rely

42:37
ለነዚያም የኀጢያትን ታላላቆችና ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነሱ የሚምሩ ለሆኑት።

And those who avoid the major sins and immoralities, and when they are angry, they forgive,

42:38
ለነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፣ ሦላትንም ላዘወተሩት፣ ነገራቸውም በመካከላቸው መመካከር ለሆነው ከሰጠናቸውም ሲሳይ ለሚለግሱት።

And those who have responded to their lord and established prayer and whose affair is [determined by] consultation among themselves, and from what We have provided them, they spend.

42:39
ለነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ እነሱ (በመሰሉ)የሚመልሱ ለሆኑት (በላጭና ኗሪ ነው)።

And those who, when tyranny strikes them, they defend themselves,

42:40
የመጥፎም ነገር ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፤ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው። እርሱ በደለኞችን አይወድም።

And the retribution for an evil act is an evil one like it, but whoever pardons and makes reconciliation - his reward is [due] from Allah . Indeed, He does not like wrongdoers.

42:41
ከተበደሉም በኋላ (በመሰሉ) የተቀበሉ፣ እነዚያ በነርሱ ላይ ምንም (የወቀሳ) መንገድ የለባቸውም።

And whoever avenges himself after having been wronged - those have not upon them any cause [for blame].

42:42
(የወቀሳ) መንገዱ በነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት፣ በምድርም ውስጥ ያለ ሕግ ወሰን በሚያልፉት ላይ ብቻ ነው፤ እነዚያ ለነሱ አሳማሚ ቅጣት አልላቸው።

The cause is only against the ones who wrong the people and tyrannize upon the earth without right. Those will have a painful punishment.

42:43
የታገሰና ምሕረት ያደረገም ሰው፣ ይህ ከምርሮቹ (ከተፈላጊዎቹ) ነገሮች ነው።

And whoever is patient and forgives - indeed, that is of the matters [requiring] determination.

42:44
አላህ የሚያጠመው ሰው ከርሱ በኋላ ለርሱ ምንም ረዳት የለውም፤ በደለኞችንም ቅታቱን ባዩ ጊዜ፣ ወደ መመለስ መንገድ አለን? የሚሉ ሲሆኑ ታያቸዋለህ።

And he whom Allah sends astray - for him there is no protector beyond Him. And you will see the wrongdoers, when they see the punishment, saying, "Is there for return [to the former world] any way?"

42:45
ከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ሆነው፣ በዓይን ስርቆት ወደርሷ (ወደ እሳት) እያስተዋሉ በርሷ ላይ የሚቀርቡ ሲሆኑ ታያቸዋለህ፤ እነዚያም ያመኑት ፣- በእርግጥ ከሳሪዎቹ፣ እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሣኤ ቀን ያከሰሩት ናቸው ይላሉ።

And you will see them being exposed to the Fire, humbled from humiliation, looking from [behind] a covert glance. And those who had believed will say, "Indeed, the [true] losers are the ones who lost themselves and their families on the Day of Resurrection. Unquestionably, the wrongdoers are in an enduring punishment."

42:46
ንቁ በደለኞች በእርግጥ በዘውታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው። ለነሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ዘመዶች ምንም አልነበሩዋቸውም፤ አላህም የሚያጠመው ሰው ለርሱ (ወደ እውነት) ምንም መንገድ የለውም።

And there will not be for them any allies to aid them other than Allah . And whoever Allah sends astray - for him there is no way.

42:47
ለርሱ መመለስ የሌለው ቀን ከአላህ ከመምጣቱ በፊት፣ ለጌታችሁ ታዘዙ፤ በዚያ ቀን ለናንተ ምንም መጠጊያ የላችሁም፤ ለናንተም ምንም መካድ የላችሁም።

Respond to your Lord before a Day comes from Allah of which there is no repelling. No refuge will you have that day, nor for you will there be any denial.

42:48
ቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም)፤ በነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፤ ባንተ ላይ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብህም፤ እኛም ሰውን ከኛ የሆነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ፣ በርሷ ይደሰታል፤ እጆቻቸው ባስቀደሙትም ኀጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው (ተስፋ ይቆርጣሉ)፤ ሰው ውለታን በጣም ከሐዲ ነውና።

But if they turn away - then We have not sent you, [O Muhammad], over them as a guardian; upon you is only [the duty of] notification. And indeed, when We let man taste mercy from us, he rejoices in it; but if evil afflicts him for what his hands have put forth, then indeed, man is ungrateful.

42:49
የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፤ የሚሻውን ይፈጥራል፤ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፤ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል።

To Allah belongs the dominion of the heavens and the earth; He creates what he wills. He gives to whom He wills female [children], and He gives to whom He wills males.

42:50
ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል። የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፤ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና።

Or He makes them [both] males and females, and He renders whom He wills barren. Indeed, He is Knowing and Competent.

42:51
ለሰው አላህ በራእይ፣ ወይም ከግርዶ ወዲያ፣ ወይም መልክተኛን (መልአክን) የሚልክና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢሆን እንጅ፣ (በገሃድ) ሊያናግረው ተገቢው አይደለም። እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና።

And it is not for any human being that Allah should speak to him except by revelation or from behind a partition or that He sends a messenger to reveal, by His permission, what He wills. Indeed, He is Most High and Wise.

42:52
እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲሆን መንፈስን፣ (ቁርአንን) አወረድን፤ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም። ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው። አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ።

And thus We have revealed to you an inspiration of Our command. You did not know what is the Book or [what is] faith, but We have made it a light by which We guide whom We will of Our servants. And indeed, [O Muhammad], you guide to a straight path -

42:53
ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ወደ ሆነው አላህ መንገድ፣ (ትመራለህ)፤ ንቁ ነገሮቹ ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ።

The path of Allah , to whom belongs whatever is in the heavens and whatever is on the earth. Unquestionably, to Allah do [all] matters evolve.

Copyright 2013, AmharicQuran.com