Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ሙእሚን (የምእመን ምዕራፍ)

40:1
ሐ.መ. (ሐ ሚም)፤ (1)

Ha, Meem.

40:2
የመጽሐፉ መወረድ፣ አሸናፊ ዐዋቂ ከኾነው አላህ ነው።

The revelation of the Book is from Allah , the Exalted in Might, the Knowing.

40:3
ኀጢአትን መሐሪ፣ ጸጸትንም ተቀባይ፣. ቅጣተ ብርቱ፣ የልግስና ባለቤት ከሆነው (አላህ የወረደ ነው)፤ ከርሱ በቀር አምላክ የለም፤ መመለሻው ወደርሱ ብቻ ነው።

The forgiver of sin, acceptor of repentance, severe in punishment, owner of abundance. There is no deity except Him; to Him is the destination.

40:4
በአላህ አንቀጾች፣ እነዚያ የካዱት ቢሆኑ እንጂ ማንም (በመዝለፍ) አይከራከርም። በያገሮችም ውስጥ መዘዋወራቸው አይሸንግልህ።

No one disputes concerning the signs of Allah except those who disbelieve, so be not deceived by their [uninhibited] movement throughout the land.

40:5
ከነሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች፣ ከኋላቸውም አሕዛቦቹ አስተባበሉ፤ ህዝቦችም ሁሉ መልክተኛቸውን ሊይዙ አሰቡ፤ በውሸትም በርሱ እውነትን ሊያጠፉበት ተከራከሩ፤ ያዝኳቸውም፤ ታዲያ ቅጣቴ እንዴት ነበር?

The people of Noah denied before them and the [disbelieving] factions after them, and every nation intended [a plot] for their messenger to seize him, and they disputed by [using] falsehood to [attempt to] invalidate thereby the truth. So I seized them, and how [terrible] was My penalty.

40:6
እንደዚሁም የጌታህ ቃል፣ በነዚያ በካዱት ላይ፣ እነሱ የእሳት ጓዶች ናቸው ማለት ተረጋገጠች።

And thus has the word of your Lord come into effect upon those who disbelieved that they are companions of the Fire.

40:7
እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት፣ እነዚያም በዙሪያው ያሉት፣ በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፤በርሱም ያምናሉ፤ ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በዕውቀት ከበሃል፤ ስለዚህ ለነዚያ ለተጸጸቱት፣ መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፣ እያሉ ለነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ።

Those [angels] who carry the Throne and those around it exalt [ Allah ] with praise of their Lord and believe in Him and ask forgiveness for those who have believed, [saying], "Our Lord, You have encompassed all things in mercy and knowledge, so forgive those who have repented and followed Your way and protect them from the punishment of Hellfire.

40:8
ጌታችን ሆይ! እነርሱንም ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸውም ከዝርዮቻቸውም የበጀውን ሁሉ፣ እነዚያን ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አግባቸው፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ነህና።

Our Lord, and admit them to gardens of perpetual residence which You have promised them and whoever was righteous among their fathers, their spouses and their offspring. Indeed, it is You who is the Exalted in Might, the Wise.

40:9
ከቅጣቶችም ጠብቃቸው፤ በዚያ ቀንም የምትጠብቀውን ሰው በእርግጥ አዘንክለት፤ ይህም እርሱ ታላቅ ማግኘት ነው።

And protect them from the evil consequences [of their deeds]. And he whom You protect from evil consequences that Day - You will have given him mercy. And that is the great attainment."

40:10
እነዚያ የካዱት ሰዎች፣ ወደ በእምነት በምትጥጠሩና በምትክዱ ጊዜ አላህ (እናንተን) መጥላቱ፣ ነፍሶቻችሁ (ዛሬ) ከመጥላታችሁ የበለጠ ነው፤ በማለት ይጥጠራሉ።

Indeed, those who disbelieve will be addressed, "The hatred of Allah for you was [even] greater than your hatred of yourselves [this Day in Hell] when you were invited to faith, but you refused."

40:11
ጌታችን ሆይ! ሁለትን ሞት አሞትከን፣ ሁለትንም ሕይወት ሕያው አደረግከን፤ በኃጢአቶቻችንም መሰከርን፤ ታዲያ (ከእሳት) ወደ መውጣት መንገድ አለን? ይላሉ።

They will say, "Our Lord, You made us lifeless twice and gave us life twice, and we have confessed our sins. So is there to an exit any way?"

40:12
ይሃችሁ፣ እነሆ አላህ ብቻውን በተጠራ ጊዜ ስለ ካዳችሁ፣ በርሱም ተጋሪ ቢደረግ የምታምኑ ስለ ሆናችሁ ነው፤ ስለዚህ ፍርዱ፣ ከፍተኛ ታላቅ ለሆነው አላህ ብቻ ነው

[They will be told], "That is because, when Allah was called upon alone, you disbelieved; but if others were associated with Him, you believed. So the judgement is with Allah , the Most High, the Grand."

40:13
እርሱ ያ (ለአምላክነቱ) ምልክቶቹን የሚያሳያችሁ፣ ለናንተም ከሰማይ ሲሳይን የሚያወርድላችሁ ነው፤ ወደርሱም የሚመለስ ሰው ቢሆን እንጂ ሌላው አይገሠጽም።

It is He who shows you His signs and sends down to you from the sky, provision. But none will remember except he who turns back [in repentance].

40:14
አላህንም ከሐዲዎች ቢጠሉም ሃይማኖትን ለርሱ አጥሪዎች ሆናችሁ ተገዙት።

So invoke Allah , [being] sincere to Him in religion, although the disbelievers dislike it.

40:15
(እርሱ) ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው፤ የመገናኛውን ቀን ያስፈራራ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከት እዛዙ መንፈስን ( ራእይን) ያወርዳል።

[He is] the Exalted above [all] degrees, Owner of the Throne; He places the inspiration of His command upon whom He wills of His servants to warn of the Day of Meeting.

40:16
እነርሱ ከመቃብር (በሚወጡበት) ቀን፣ በአላህ ላይ ከነሱ ምንም ነገር አይደበቅም፤ ንግሥናው ዛሬ ለማን ነው? (ይባላል)፤ ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው (ይባላል)።

The Day they come forth nothing concerning them will be concealed from Allah . To whom belongs [all] sovereignty this Day? To Allah , the One, the Prevailing.

40:17
ዛሬ ነፍስ በሠራችው ሥራ ትመነዳለች፤ ዛሬ በደል የለም፤ አላህ በእርግጥ ምርመራው ፈጣን ነው፣ (ይባላል)

This Day every soul will be recompensed for what it earned. No injustice today! Indeed, Allah is swift in account.

40:18
ቅርቢቱንም (የትንሣኤን) ቀን ልቦች ጭንቀትን የተመሉ ሆነው ላንቃዎች ዘንድ የሚደርሱበትን ጊዜ፣ አስጠንቅቃቸው፤ ለበዳዮች ምንም ወዳጅና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም።

And warn them, [O Muhammad], of the Approaching Day, when hearts are at the throats, filled [with distress]. For the wrongdoers there will be no devoted friend and no intercessor [who is] obeyed.

40:19
(አላህ) የአይኖችን ክዳት፣ ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል።

He knows that which deceives the eyes and what the breasts conceal.

40:20
አላህም በእውነት ይፈርዳል፤ እነዚያም ከርሱ ሌላ የሚግገዟቸው፣ በምንም አይፈርዱም፤ አላህ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው።

And Allah judges with truth, while those they invoke besides Him judge not with anything. Indeed, Allah - He is the Hearing, the Seeing.

40:21
የነዚያን ከነሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይኼዱምን? በኃይልና በምድር ላይ በተዉዋቸው ምልክቶች፤ ከነሱ ይበልጥ የበረቱ ነበሩ፤ አላህም በኅጢአቶቻቸው ያዛቸው፤ ለነሱም ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ አልነበራቸውም።

Have they not traveled through the land and observed how was the end of those who were before them? They were greater than them in strength and in impression on the land, but Allah seized them for their sins. And they had not from Allah any protector.

40:22
ይህ (መያዝ) እነሱ መልክተኞቻቸው በታምራቶች ይመጡባቸው ስለ ነበሩና ስለ ካዱ ነው፤ አላህም ያዛቸው፤ እርሱ ኀያል፣ ቅጣተ ብርቱ ነውና።

That was because their messengers were coming to them with clear proofs, but they disbelieved, so Allah seized them. Indeed, He is Powerful and severe in punishment.

40:23
ሙሳንም በታምራቶቻችንና በግልጽ ማሥረጃ በእርግጥ ላክነው።

And We did certainly send Moses with Our signs and a clear authority

40:24
ወደ ፈርዖንና ወደ ሃማን፤ ወደ ቃሩንም፣ (ላክነው)፤ ድግምተኛ ውሸታም ነው አሉም።

To Pharaoh, Haman and Qarun; but they said, "[He is] a magician and a liar."

40:25
ከኛ ዘንድ እውነትን ይዞ በመጣላቸውም ጊዜ ፦ የነዚያን ከርሱ ጋር ያመኑትን ሰዎች ወንዶች ልጆች ግደሉ ሴቶቻቸውንም አስቀሩ አሉ፤ የከሐዲዎችም ተንኮል በጥፋት ውስጥ እንጅ አይደለም።

And when he brought them the truth from Us, they said, "Kill the sons of those who have believed with him and keep their women alive." But the plan of the disbelievers is not except in error.

40:26
ፈርዖንም ፦ ተዉኝ፤ ሙሳን ልግደል፤ ጌታውንም ይጥራ፤ ያድነውም እንደሆነ)፤ እኔ ሃይኖታችሁን ሊለውጥ፤ ወይም በምድር ውስጥ ጥፋትን ሊያሰራጭ፣ እፈራለሁና አለ።

And Pharaoh said, "Let me kill Moses and let him call upon his Lord. Indeed, I fear that he will change your religion or that he will cause corruption in the land."

40:27
ሙሳም፣ እኔ በምርመራው ቀን ከማያምን ትዕቢተኛ ሁሉ፣ በጌታየና በጌታችሁ ተጠበቅሁ አለ።

But Moses said, "Indeed, I have sought refuge in my Lord and your Lord from every arrogant one who does not believe in the Day of Account."

40:28
ከፈርዖንም ቤተሰቦች አንድ እምነቱን የሚደብቅ ምእምን ሰው አለ፦ ሰውየውን ከጌታችሁ በታምራቶች በእርግጥ የመጣላችሁ ሲሆን ጌታዬ አላህ ነው፣ ስለሚል ትገድላላችሁን? ውሸታምም ቢሆን ውሸቱ በርሱው ላይ ነው፤ እውነተኛ ቢሆን ግን የዚያ የሚያስፈራራችሁ ከፊሉ ያገኛችኋል፤ አላህ ያንን እርሱ ድንበር አላፊ ውሸታም የሆነውን አይመራምና።

And a believing man from the family of Pharaoh who concealed his faith said, "Do you kill a man [merely] because he says, 'My Lord is Allah ' while he has brought you clear proofs from your Lord? And if he should be lying, then upon him is [the consequence of] his lie; but if he should be truthful, there will strike you some of what he promises you. Indeed, Allah does not guide one who is a transgressor and a liar.

40:29
ወገኖቼ ሆይ! በምድር ላይ አሸናፊዎች ስትሆኑ ዛሬ መንግሥቱ የናንተ ነው፤ ታዲያ ከአላህ ቅጣት ቢመጣብን የሚያድነን ማነው? (አለ)። ፈርዖን የማየውን ነገር እንጅ፤ አላመለከታችሁም፤ ቅኑንም መንገድ እንጅ አልመራችሁም አላቸው።

O my people, sovereignty is yours today, [your being] dominant in the land. But who would protect us from the punishment of Allah if it came to us?" Pharaoh said, "I do not show you except what I see, and I do not guide you except to the way of right conduct."

40:30
ያም ያመነው ሰው አለ፦ እኔ በናንተ ላይ የአሕዛቦቹን ቀን ብጤ እፈራላችኋለሁ።

And he who believed said, "O my people, indeed I fear for you [a fate] like the day of the companies -

40:31
የኑሕን ሕዝቦች የዓድንና የሠሙድንም የነዚያንም ከኋላቸው የነበሩትን ልማድ ብጤ (እፈራላቸውዋለሁ)፤ አላህም ለባሮቹ መበደልን የሚሻ አይደለም።

Like the custom of the people of Noah and of 'Aad and Thamud and those after them. And Allah wants no injustice for [His] servants.

40:32
ወገኖቼ ሆይ! እኔ በናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን (1) እፈራለሁ።

And O my people, indeed I fear for you the Day of Calling -

40:33
ወደኋላ ዞራችሁ በምትሸሹበት ቀን፤ ለናንተ ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ የላችሁም፤ አላህም የሚያጠመው ሰው ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም።

The Day you will turn your backs fleeing; there is not for you from Allah any protector. And whoever Allah leaves astray - there is not for him any guide.

40:34
ዩሱፍም ከዚህ በፊት ግልጽ ማስረጃዎችን በእርግጥ አመጣላችሁ፤ ከዚያም እርሱ ካመጣላችሁ ነገር ከመጠራጠር አልተወገዳችሁም፤ በጠፋም ጊዜ አላህ ከርሱ ኋላ መልክተኛን በጭራሽ አይልክም፣ አላችሁ፤ አላህ እንደዚሁ ድንበር አላፊ፣ ተጠራጣሪ የሆነን ሰው ያሳስታል።

And Joseph had already come to you before with clear proofs, but you remained in doubt of that which he brought to you, until when he died, you said, 'Never will Allah send a messenger after him.' Thus does Allah leave astray he who is a transgressor and skeptic."

40:35
እነዚያ፤ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር፣ በአላህ ታምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም አመኑት ዘንድ መጠላቱ፣ በጣም ተለቀ፤ እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ (ሰው) ልብ ሁሉ ላይ ያትማል።

Those who dispute concerning the signs of Allah without an authority having come to them - great is hatred [of them] in the sight of Allah and in the sight of those who have believed. Thus does Allah seal over every heart [belonging to] an arrogant tyrant.

40:36
ፈርዖንም አለ፦ ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ፣ ረዢም ሕንጻን ለኔ ካብልኝ።

And Pharaoh said, "O Haman, construct for me a tower that I might reach the ways -

40:37
የሰማያትን መንገዶች፣ (እደርስ ዘንድ)፤ ወደ ሙሳም አምላክ እመለከት ዘንድ እኔ ውሸታም ነው ብዬ በእርግጥ እጠረጥረዋለሁ፣ (አለ)፤ እንደዚሁም ለፈርዖን መጥፎ ሥራው ተሸለመለት፤ ከቅን መንገድም ታገደ፤ የፈርዖንም ተንኮል በከሳራ ውስጥ እንጅ አይደለም።

The ways into the heavens - so that I may look at the deity of Moses; but indeed, I think he is a liar." And thus was made attractive to Pharaoh the evil of his deed, and he was averted from the [right] way. And the plan of Pharaoh was not except in ruin.

40:38
ያም ያመነው አለ፦ ወገኖቼ ሆይ! ተከተተሉኝ፤ ቀጥታውን መንገድ እመራችኋለሁና።

And he who believed said, "O my people, follow me, I will guide you to the way of right conduct.

40:39
ወገኖቼ ሆይ! ይህቺ ቅርቢቱ ሕይወት (ጥቂት) መጣቀሚያ ብቻ ናት፤ መጨረሻይቱም ዓለም እርሷ መርጊያ አገር ናት።

O my people, this worldly life is only [temporary] enjoyment, and indeed, the Hereafter - that is the home of [permanent] settlement.

40:40
መጥፎን የሠራ ሰው፣ ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፤ እርሱ መእምን ሆኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው፣ እነዚያ ገነትን ይገባሉ፤ በርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ።

Whoever does an evil deed will not be recompensed except by the like thereof; but whoever does righteousness, whether male or female, while he is a believer - those will enter Paradise, being given provision therein without account.

40:41
ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስሆን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትሆኑ ለኔ ምን አለኝ! (1)

And O my people, how is it that I invite you to salvation while you invite me to the Fire?

40:42
በአላህ ልክድና በርሱም ለኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር በርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ፤ እኔም ወደ አሸናፊው፣ መሐሪው፣ (አላህ) እጠራችችኋለሁ።

You invite me to disbelieve in Allah and associate with Him that of which I have no knowledge, and I invite you to the Exalted in Might, the Perpetual Forgiver.

40:43
በእርግጥ ወደርሱ የምትጠሩብኝ፣ (ጣዖት) ለርሱ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም (ተሰሚ) ጥሪ የለውም፤ መመለሻችንም በእርግጥ ወደ አላህ ነው፤ ወሰን አላፊዎቹም እነሱ የእሳት ጓዶች ናቸው።

Assuredly, that to which you invite me has no [response to a] supplication in this world or in the Hereafter; and indeed, our return is to Allah , and indeed, the transgressors will be companions of the Fire.

40:44
ወደ ፊትም፣ ለናንተ የምላችሁን ምክር፣ (ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሳላችሁ፤ ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ፤ አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።

And you will remember what I [now] say to you, and I entrust my affair to Allah . Indeed, Allah is Seeing of [His] servants."

40:45
ከመከሩዋቸውም መጥፎዎች አላህ ጠበቀው፤ በፈርዖን ቤተሰቦችም፣ ላይ ክፉ ቅጣት ሰፈረባቸው።

So Allah protected him from the evils they plotted, and the people of Pharaoh were enveloped by the worst of punishment -

40:46
እሳት በጧትና በማታ በርሷ ላይ ይቀርባሉ፤ ሰዓቲቱም በምትሆንበት ቀን የፈርዖንን ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት (ገሀነምን) አግቡዋቸው (ይባላል)።

The Fire, they are exposed to it morning and evening. And the Day the Hour appears [it will be said], "Make the people of Pharaoh enter the severest punishment."

40:47
በእሳትም ውስጥ የሚከራከሩበትን ጊዜ (አስታውስ) ደካማዎቹም ለነዚያ ለኮሩት እኛ ለናንተ ተከታዮች ነበርንና እናንተ (አሁን) ከእሳት ከፊሉን ከኛ ላይ ገፍታሪዎች ናችሁን? ይላሉ።

And [mention] when they will argue within the Fire, and the weak will say to those who had been arrogant, "Indeed, we were [only] your followers, so will you relieve us of a share of the Fire?"

40:48
እነዚያም የኮሩት እኛ ሁላችንም በውስጧ ነን፤ አላህ በባሮቹ መካከል በእርግጥ ፈረደ ይላሉ።

Those who had been arrogant will say, "Indeed, all [of us] are in it. Indeed, Allah has judged between the servants."

40:49
እነዚያም በእሳት ውስጥ ያሉት፣ ለገሀነም ዘበኞች ጌታችሁን ለምኑልን፤ ከኛ ላይ ከቅጣቱ አንድን ቀን ያቃልልን፤ ይላሉ።

And those in the Fire will say to the keepers of Hell, "Supplicate your Lord to lighten for us a day from the punishment."

40:50
(ዘበኞቹም) መልክተኞቻችሁ በታምራቶች ይመጡላችሁ አልነበሩምን? ይላሉ፤ (ከሐዲዎቹም) እንዴታ መጥተውናል እንጅ፤ (ግን አስተባበልናቸው)፣ ይላሉ፤ እንግዲያውስ ጸልዩ የከሐዲዎችም ጸሎት፣ የከሐዲዎችም ጸሎት በከንቱ እንጅ አይደለም ይሏቸዋል።

They will say, "Did there not come to you your messengers with clear proofs?" They will say, "Yes." They will reply, "Then supplicate [yourselves], but the supplication of the disbelievers is not except in error."

40:51
እኛ መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ሕይወት ምስክሮችም በሚቆሙበት ቀን በእርግጥ እንረዳለን።

Indeed, We will support Our messengers and those who believe during the life of this world and on the Day when the witnesses will stand -

40:52
በደለኞችን ምክንያታቸው በማይጠቅማቸው ቀን (እንረዳለን)፤ ለነርሱም ርግማን አላቸው፤ ለነርሱም መጥፎ አገር አላቸው።

The Day their excuse will not benefit the wrongdoers, and they will have the curse, and they will have the worst home.

40:53
ሙሳንም መምሪያን በእርግጥ ሰጠነው፤ የእስራኤልንም ልጆች መጽሐፉን አወረስናቸው።

And We had certainly given Moses guidance, and We caused the Children of Israel to inherit the Scripture

40:54
ለባለ አእምሮዎች መሪና ገሣጭ ሲሆን።

As guidance and a reminder for those of understanding.

40:55
(ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም፤ የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፤ ለስሕተትህም ምሕረትን ለምን፤ ከቀትር በኋላም በማለዳም ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው።

So be patient, [O Muhammad]. Indeed, the promise of Allah is truth. And ask forgiveness for your sin and exalt [ Allah ] with praise of your Lord in the evening and the morning.

40:56
እነዚያ የመጣላቸውን አስረጅ ሳይኖር፣ በአላህ አንቀጾች የሚከራከሩ፣ በልቦቻቸው ውስጥ፣ እነርሱ ደራሾቹ ያልሆኑት ኩራት ብቻ እንጅ፣ ምንም የለም፤ በአላህም ተጠበቅ፤ እነሆ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነውና።

Indeed, those who dispute concerning the signs of Allah without [any] authority having come to them - there is not within their breasts except pride, [the extent of] which they cannot reach. So seek refuge in Allah . Indeed, it is He who is the Hearing, the Seeing.

40:57
ሰማያትንና ምድርን መፍጠር፣ ሰዎችን ከመፍጠር ይልቅ ታላቅ ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።

The creation of the heavens and earth is greater than the creation of mankind, but most of the people do not know.

40:58
ዕውርና የሚያይ፣ እነዚያም አምነው መልካሞችን የሠሩና መጥፎ ሠሪው አይተካከሉም፤ በጣም ጥቂትን ብቻ ትገሠጻላችሁ።

And not equal are the blind and the seeing, nor are those who believe and do righteous deeds and the evildoer. Little do you remember.

40:59
ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት፤ በርሷ ጥርጥር የለም፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም።

Indeed, the Hour is coming - no doubt about it - but most of the people do not believe.

40:60
ጌታችሁም አለ፦ ለምኑኑኝ እቀበላችኋለሁና፤ እነዚያም እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።

And your Lord says, "Call upon Me; I will respond to you." Indeed, those who disdain My worship will enter Hell [rendered] contemptible.

40:61
አላህ ያ ለናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ) ቀንንም (ልትሠሩበት) የሚያሳይ ያደረገላችሁ ነው። አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነውና። ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም።

It is Allah who made for you the night that you may rest therein and the day giving sight. Indeed, Allah is full of bounty to the people, but most of the people are not grateful.

40:62
ይሃችሁ፣ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ትመለሳላችሁ።

That is Allah , your Lord, Creator of all things; there is no deity except Him, so how are you deluded?

40:63
እንደዚሁ እነዚያ በአላህ አንቀጾች ይክዱ የነበሩት (ከእምነት ይመለሳሉ)።

Thus were those [before you] deluded who were rejecting the signs of Allah .

40:64
አላህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም ጣሪያ ያደረገላችሁ ነው፤ የቀረጻችሁም ቅርጻችሁንም ያሳመረ፣ ከጣፋጮችም ሲሳዮች የሰጣችሁ ነው፤ ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ።

It is Allah who made for you the earth a place of settlement and the sky a ceiling and formed you and perfected your forms and provided you with good things. That is Allah , your Lord; then blessed is Allah , Lord of the worlds.

40:65
እርሱ ብቻ (ሁል ጊዜ) ሕያው ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ሃይማኖትንም ለርሱ ያጠራችሁ ስትሆኑ፣ ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፣ የምትሉ ሆናችሁ ተገዙት።

He is the Ever-Living; there is no deity except Him, so call upon Him, [being] sincere to Him in religion. [All] praise is [due] to Allah , Lord of the worlds.

40:66
እኔ ከጌታዬ አስረጅዎች በመጡልኝ ጊዜ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን እንዳልገዛ ተከልክያለሁ፤ ለዓለማት ጌታም እንድግገዛ ታዝዣለሁ በላቸው።

Say, [O Muhammad], "Indeed, I have been forbidden to worship those you call upon besides Allah once the clear proofs have come to me from my Lord, and I have been commanded to submit to the Lord of the worlds."

40:67
እርሱ ያ ከዐፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ የፈጠራችሁ ነው። ከዚያም ሕጻናት አድርጎ ያወጣችኋል፤ ከዚያም ጥንካሬአችሁን ትደርሱ ዘንድ፤ ከዚያም ሽማግሌዎች ትሆኑ ዘንድ፣ (ያቆያችኋል)፤ ከናንተም ውስጥ ከዚህ በፊት የሚሞት አለ፤ (ይህንንም ያደረገው ልትኖሩና) የተወሰነ ጊዜንም ልትደርሱ፣ ታውቁም ዘንድ ነው።

It is He who created you from dust, then from a sperm-drop, then from a clinging clot; then He brings you out as a child; then [He develops you] that you reach your [time of] maturity, then [further] that you become elders. And among you is he who is taken in death before [that], so that you reach a specified term; and perhaps you will use reason.

40:68
እርሱ ያ ሕያው የሚያደርግ፣ የሚያሞትም ነው፤ አንዳችን ነገር ባሻም ጊዜየሚለው ሁን ነው፤ ወዲያውም ይሆናል።

He it is who gives life and causes death; and when He decrees a matter, He but says to it, "Be," and it is.

40:69
ወደነዚያ በአላህ አንቀጾች ወደሚከራከሩት (ከእምነት) እንዴት እንደሚመለሱ አታይምን?

Do you not consider those who dispute concerning the signs of Allah - how are they averted?

40:70
ወደነዚያ በመጽሐፉ፣ በዚያም መልክተኞቻችንን በርሱ በላክንበት ወዳስተባበሉት (አታይምን?) ያውቃሉ።

Those who deny the Book and that with which We sent Our messengers - they are going to know,

40:71
እንዛዝላዎቹና ሰንሰለቶቹ በአንገቶቻቸው ላይ በተደረጉ ጊዜ (በርሷ) ይጎተታሉ።

When the shackles are around their necks and the chains; they will be dragged

40:72
በገሀነም ውስጥ (ይጎተታሉ)፤ ከዚያም በእሳት ውስጥ ይማገዳሉ።

In boiling water; then in the Fire they will be filled [with flame].

40:73
ከዚያም ለነርሱ ይባላሉ፦ (በአላህ) ታጋሩዋቸው የነበራችሁት የታሉ?

Then it will be said to them, "Where is that which you used to associate [with Him in worship]

40:74
ከአላህ ሌላ (የምታጋሩዋቸው) ከኛ ተሰወሩን፤ ከቶ ከዚህ በፊት ምንንም የምንግገዛ አልነበርንም ይላሉ፤ እንደዚሁ አላህ ከሀዲዎችን ያሳስታል።

Other than Allah ?" They will say, "They have departed from us; rather, we did not used to invoke previously anything." Thus does Allah put astray the disbelievers.

40:75
ይሃችሁ (ቅጣት) ያለ አግባብ በምድር ውስጥ ትደሰቱ በነበራችሁትና ትንበጣረሩ በነበራችሁት ነው (ይባላሉ)።

[The angels will say], "That was because you used to exult upon the earth without right and you used to behave insolently.

40:76
የገሀነምን በርሮች፣ በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ (ይባላሉ)፤ የትዕቢተኞችም መኖሪያ (ገሀነም) ምን ትከፋ! ከሐዲዎች ከሰሩ።

Enter the gates of Hell to abide eternally therein, and wretched is the residence of the arrogant."

40:77
ታገሥም የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፤ የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ፣ (መልካም ነው)፤ ወይም ብንገድልህ ወደኛ ይመለሳሉ።

So be patient, [O Muhammad]; indeed, the promise of Allah is truth. And whether We show you some of what We have promised them or We take you in death, it is to Us they will be returned.

40:78
ካንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፤ ከነሱ ባንተ ላይ የተረክንልህ አልለ፤ ከነሱም ባንተ ላይ ያልተረክነው አልለ፤ ለማንኛውም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ ታምርን ሊያመጣ አይገባውም። የአላህም ትእዛዝ በመጣ ጊዜ በውነት ይፈረዳል፤ እዚያ ዘንድም አጥፊዎቹ ይከስራሉ።

And We have already sent messengers before you. Among them are those [whose stories] We have related to you, and among them are those [whose stories] We have not related to you. And it was not for any messenger to bring a sign [or verse] except by permission of Allah . So when the command of Allah comes, it will be concluded in truth, and the falsifiers will thereupon lose [all].

40:79
አላህ፣ ያ ለናንተ ግመልን ከብትንና ፍየልን፣ ከርሷ ( ከፊሏን) ልትጋልቡ የፈጠረላችሁ ነው፤ ከርሷም ትበላላችሁ።

It is Allah who made for you the grazing animals upon which you ride, and some of them you eat.

40:80
ለናንተም በርሷ ውስጥ ጥቅሞች አሏችሁ፤ በርሷም ላይ (ዕቃን በመጫን) በልቦቻችሁ ያሰባችሁበትን ጉዳይ ትደርሱ ዘንድ (ፈጠረላችሁ)፤ በርሷም ላይ መርከቦችም ላይ ትሳፈራላችሁ።

And for you therein are [other] benefits and that you may realize upon them a need which is in your breasts; and upon them and upon ships you are carried.

40:81
ታምራቱንም ያሳያችኋል፤ ታዲያ ከአላህ ታምራት የትኛውን ትክዳላችሁ?

And He shows you His signs. So which of the signs of Allah do you deny?

40:82
የዚያን ከነሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይኼዱምን? ከነሱ ይበልጥ ብዙዎች በኀይልና በምድር ላይ በተዉዋቸው ምልክቶችም በጣም ብርቱዎች ነበሩ። ያም ይሠሩት የነበሩት ከነሱ ምንም አልጠቀማቸውም።

Have they not traveled through the land and observed how was the end of those before them? They were more numerous than themselves and greater in strength and in impression on the land, but they were not availed by what they used to earn.

40:83
መልክተኞቻቸውም ታምራቶችን ባመጡላቸው ጊዜ፣ እነርሱ ዘንድ ባለው ዕውቀት ተደሰቱ፤ በርሱ ይሳለቁበትየነበሩት ቅጣትም በነርሱ ላይ ሰፈረባቸው።

And when their messengers came to them with clear proofs, they [merely] rejoiced in what they had of knowledge, but they were enveloped by what they used to ridicule.

40:84
ብርቱ ቅጣታችንንም ባዩ ጊዜ፣ በአላህ አንድ ሲሆን አምነናል፤ በርሱም እናጋራ በነበርነው (ጣዖታት) ክደናል አሉ።

And when they saw Our punishment, they said," We believe in Allah alone and disbelieve in that which we used to associate with Him."

40:85
ብርቱ ቅጣታችንን ባዩ ጊዜ ማመናቸውም፣ የሚጠቅማቸው አልነበረም፤ የአላህን ደንብ ያችን በባሮቹ ውስጥ ያለፈችውን (ተጠንቀቁ) በዚያ ጊዜም ከሐዲዎች ከሰሩ።

But never did their faith benefit them once they saw Our punishment. [It is] the established way of Allah which has preceded among His servants. And the disbelievers thereupon lost [all].

Copyright 2013, AmharicQuran.com