Amharic Quran
Chapters/Surah

አል-ዙመር፤ (የጭፍራዎች ምዕራፍ)

39:1
የመጽሐፉ መወረድ፣ አሸናፊው ጥበበኛው ከሆነው አላህ ነው።

The revelation of the Qur'an is from Allah , the Exalted in Might, the Wise.

39:2
እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በውነት (የተመላ) ሲሆን አወረድነው፤ አላህንም ሀይማኖትን እርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው።

Indeed, We have sent down to you the Book, [O Muhammad], in truth. So worship Allah , [being] sincere to Him in religion.

39:3
ንቁ፤ ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው። እነዚያም ከርሱ ሌላ (ጣዖታትን) ረዳቶች የያዙት ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን እንጅ ለሌላ አንግገዛቸውም፣ (ይላሉ)፤ አላህ በዚያ እነርሱ በርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል፤ አላህ እርሱ ውሸታም ከሐዲ የሆነን ሰው አያቀናም።

Unquestionably, for Allah is the pure religion. And those who take protectors besides Him [say], "We only worship them that they may bring us nearer to Allah in position." Indeed, Allah will judge between them concerning that over which they differ. Indeed, Allah does not guide he who is a liar and [confirmed] disbeliever.

39:4
አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ፣ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር፤ ጥራት ተገባው እርሱ አሸናፊው አንዱ አላህ ነው።

If Allah had intended to take a son, He could have chosen from what He creates whatever He willed. Exalted is He; He is Allah , the One, the Prevailing.

39:5
ሰማያትንና ምድርን በውነት ፈጠረ፤ ሌሊትንም በቀን ላይ ይጠቀልላል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፤ ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ፤ ንቁ እርሱ አሸናፊው መሐሪው ነው።

He created the heavens and earth in truth. He wraps the night over the day and wraps the day over the night and has subjected the sun and the moon, each running [its course] for a specified term. Unquestionably, He is the Exalted in Might, the Perpetual Forgiver.

39:6
ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ከርሷ መቀናጆዋን አደረገ። ለናንተም ከግመልና ከከብት፣ ከፍየል፣ ከበግ፣ ስምንት አይነቶችን (ወንድና ሴት) አወረደ፤ በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ፣ በሦስት ጨለማዎች ውስጥ፣ (1) ከመፍጠር በኋላ፣ (ሙሉ) መፍጠርን ይፈጥራችኋል፤ (2) ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው። ሥልጣኑ የርሱ ብቻ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ።

He created you from one soul. Then He made from it its mate, and He produced for you from the grazing livestock eight mates. He creates you in the wombs of your mothers, creation after creation, within three darknesses. That is Allah , your Lord; to Him belongs dominion. There is no deity except Him, so how are you averted?

39:7
ብትክዱ አላህ ከናንተ የተብቃቃ ነው። ለባሪያዎቹም ክህደትን አይወድም፤ ብታመሰግኑም፤ እርሱን ይወድላችኋል፤ ማንኛይቱም ኀጢአትን ተሸካሚ ነፍስ፣ የሌላይቱን ኃጢያት አትሸከምም፤ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው፤ ትሠሩት የነበራችሁትንም ይነግራችኋል፤ እርሱ በልቦች ውስጥ ያሉትን ዐዋቂ ነውና።

If you disbelieve - indeed, Allah is Free from need of you. And He does not approve for His servants disbelief. And if you are grateful, He approves it for you; and no bearer of burdens will bear the burden of another. Then to your Lord is your return, and He will inform you about what you used to do. Indeed, He is Knowing of that within the breasts.

39:8
ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ፣ ጌታውን ወደርሱ ተመላሽ ሆኖ ይጠራል። ከዚያም ከርሱ ዘንድ ጸጋን በሰጠው ጊዜ፣ ያንን ከዚያ በፊት ወደርሱ ይጸልይበት የነበረውን መከራ ይረሳል፤ ከመንገዱ ለማሳሳትም ለአላህ ባላንጣዎችን ያደርጋል፤ በክሕደትህ ጥቂትን ተጣቀም፤ አንተ በእርግጥ ከእሳት ጓዶች ነህ በለው።

And when adversity touches man, he calls upon his Lord, turning to Him [alone]; then when He bestows on him a favor from Himself, he forgets Him whom he called upon before, and he attributes to Allah equals to mislead [people] from His way. Say, "Enjoy your disbelief for a little; indeed, you are of the companions of the Fire."

39:9
እርሱ የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) የሚፈራ የጌታውንም ችሮታ የሚከጅል ሲሆን በሌሊት ሰዓቶች ሰጋጅና ቋሚ ሆኖ ለጌታው የመግገዛ ሰው (እንደ ተስፋ ቢሱ ከሐዲ ነውን?በለው)፤ እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይተካከላሉን? በላቸው፤ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ናቸው።

Is one who is devoutly obedient during periods of the night, prostrating and standing [in prayer], fearing the Hereafter and hoping for the mercy of his Lord, [like one who does not]? Say, "Are those who know equal to those who do not know?" Only they will remember [who are] people of understanding.

39:10
(ጌታችሁ) እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፤ ለነዚያ በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት፣ መልካም ምንዳ አላቸው። የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ፣ ተሰደዱ)፤ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሠጡት ያለ ግምት ነው፤ (ይላል) በላቸው።

Say, "O My servants who have believed, fear your Lord. For those who do good in this world is good, and the earth of Allah is spacious. Indeed, the patient will be given their reward without account."

39:11
በል፦ እኔ አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ያጠራሁ ሆኜ እንድግገዛው ታዘዝኩ፤

Say, [O Muhammad], "Indeed, I have been commanded to worship Allah , [being] sincere to Him in religion.

39:12
የሙስሊሞችም መጀመሪያ እንድሆን ታዘዝኩ።

And I have been commanded to be the first [among you] of the Muslims."

39:13
እኔ ከጌታዬ ባምጥ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ በል።

Say, "Indeed I fear, if I should disobey my Lord, the punishment of a tremendous Day."

39:14
አላህን ሃይማኖቴን ለርሱ ያጠራሁ ሆኜ እግገዛዋለሁ በል።

Say, " Allah [alone] do I worship, sincere to Him in my religion,

39:15
ከርሱ ሌላ የሻችሁትን ተገዙ፤ ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሣኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፤ ንቁ፤ ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ናቸው በላቸው።

So worship what you will besides Him." Say, "Indeed, the losers are the ones who will lose themselves and their families on the Day of Resurrection. Unquestionably, that is the manifest loss."

39:16
ለነርሱ ከበላያቸው ከእሳት የሆኑ (ድርብርብ) ጥላዎች አሏቸው፤ ከበታቻቸውም ጥላዎች አሏቸው። ይህ አላህ ባሮቹን (እንዲጠነቀቁ) በርሱ ያስፈራራበታል፤ ባሮቼ ሆይ! ስለዚህ ፍሩኝ።

They will have canopies of fire above them and below them, canopies. By that Allah threatens His servants. O My servants, then fear Me

39:17
እነዚያም ጣዖታትን የሚግገዟት ከመሆን የራቁ ወደ አላህም የዞሩ ለነርሱ ብስራት አላቸው፤ ስለዚህ ባሮቼን አብስር።

But those who have avoided Taghut, lest they worship it, and turned back to Allah - for them are good tidings. So give good tidings to My servants

39:18
እነዚያን ንግግርን የሚያዳምጡትንና መልካሙን የሚከተሉትን፣ (አብስር)፤ እነዚያ፣ እነርሱ አላህ የመራቸው ናቸው። እነዚያም እነሱ ባለ አእምሮዎች ናቸው።

Who listen to speech and follow the best of it. Those are the ones Allah has guided, and those are people of understanding.

39:19
በርሱ ላይ የቅጣት ቃል የተረጋገጠችበት ሰው (ትመራዋለህን?) አንተ በእሳት ውስጥ ያለን ሰው ታድናለህን?

Then, is one who has deserved the decree of punishment [to be guided]? Then, can you save one who is in the Fire?

39:20
ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ ለነርሱ ከበላያቸው የታነጹ ሰገነቶች ያሏቸው ሰገነቶች ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ አሏቸው፤ (ይህንን) አላህ ቃል ገባላቸው፤ አላህ ቃሉን አያፈርስም።

But those who have feared their Lord - for them are chambers, above them chambers built high, beneath which rivers flow. [This is] the promise of Allah . Allah does not fail in [His] promise.

39:21
አላህ ከሰማይ ውሃን እንዳወረደና በምድርም ውስጥ ምንጮች አድርጎ እንዳስገባው አላየህምን? ከዚያም በርሱ ዓይነቶቹ የተለያዩን አዝመራ ያወጣል፤ ከዚያም ይደርቃል፤ ገርጥቶም ታየዋለህ፤ ከዚያም ስብርብር ያደርገዋል፤ በዚህ ውስጥ ለባለ አ እምሮዎች ግሣጼ አለበት።

Do you not see that Allah sends down rain from the sky and makes it flow as springs [and rivers] in the earth; then He produces thereby crops of varying colors; then they dry and you see them turned yellow; then He makes them [scattered] debris. Indeed in that is a reminder for those of understanding.

39:22
አላህ ደረቱን ለእስልምና ያሰፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የሆነ ሰው (ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን?) ልቦቻቸውም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወዮላቸው፤ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው።

So is one whose breast Allah has expanded to [accept] Islam and he is upon a light from his Lord [like one whose heart rejects it]? Then woe to those whose hearts are hardened against the remembrance of Allah . Those are in manifest error

39:23
አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን ተመሳሳይ ተደጋጋሚ የሆነን መጽሐፍ አወረደ፤ ከርሱ፣ (ግሣጼ) የነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ (ተስፋ) ማስታወስ ይለዝባሉ። ይህ የአላህ መምሪያ ነው፤ በርሱ የሚሻውን ሰው ይመራበታል፤ አላህም የሚያጠመው ሰው ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም።

Allah has sent down the best statement: a consistent Book wherein is reiteration. The skins shiver therefrom of those who fear their Lord; then their skins and their hearts relax at the remembrance of Allah . That is the guidance of Allah by which He guides whom He wills. And one whom Allah leaves astray - for him there is no guide.

39:24
በትንሣኤ ቀን ክፉን ቅጣት በፊቱ የሚመክት ሰው፣ (ከቅጣት እንደሚድን ነውን?) ለበዳዮችም ትሠሩት የነበራችሁትን (ቅጣቱን) ቅመሱ ይባላሉ።

Then is he who will shield with his face the worst of the punishment on the Day of Resurrection [like one secure from it]? And it will be said to the wrongdoers, "Taste what you used to earn."

39:25
ከነሱ በፊት የነበሩት አስተባበሉ፤ ቅጣቱም ከማያውቁት በኩል መጣባቸው።

Those before them denied, and punishment came upon them from where they did not perceive.

39:26
አላህም በቅርቢቱ ሕይወት ውርደትን አቀመሳቸው። የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም ትልቅ፣ ነው። የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ፣ (አያስተባብሉም ነበር)።

So Allah made them taste disgrace in worldly life. But the punishment of the Hereafter is greater, if they only knew.

39:27
በዚህ ቁርአን ውስጥ ለሰዎች ይገሠጸ ዘንድ ከየምሳሌው ሁሉ በእርግጥ አብራራን፤

And We have certainly presented for the people in this Qur'an from every [kind of] example - that they might remember.

39:28
መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርአን ሲኾን፣ (አብራራነው)፤ ሊጠነቀቁ ይከጀላልና።

[It is] an Arabic Qur'an, without any deviance that they might become righteous.

39:29
አላህ በርሱ ተጨቃጫቂዎች የሆኑ ተጋሪዎች ያሉትን ባሪያና፣ ለአንድ ሰው ብቻ ንጹሕ የሆነን ባሪያ (ለሚያጋራና ባንድነቱ ለሚያምን ሰው) ምሳሌ አደረገ፤ በምሳሌ ይተካከላሉን?፤ ምስጋና ለአላህ ይግባው። በውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም።

Allah presents an example: a slave owned by quarreling partners and another belonging exclusively to one man - are they equal in comparison? Praise be to Allah ! But most of them do not know.

39:30
አንተ ሟች ነህ፤ እነሱም ሟቾች ናቸው።

Indeed, you are to die, and indeed, they are to die.

39:31
ከዚያም እናንተ በትንሣኤ ቀን እጌታችሁ ዘንድ ትከራከራላችሁ።

Then indeed you, on the Day of Resurrection, before your Lord, will dispute.

39:32
በአላህ ላይም ከዋሸ እውነቱንም በመጣለት ጊዜ ከአስተባበለ ሰው ይበልጥ በላይ በዳይ ማን ነው? በገሀነም ውስጥ ለከሐዲዎች መኖሪያ የለምን? (አልለ እንጅ)።

So who is more unjust than one who lies about Allah and denies the truth when it has come to him? Is there not in Hell a residence for the disbelievers?

39:33
ያም በውነት የመጣው፣ በርሱ ያመነውም፣ እነዚያ እነርሱ አላህን ፈሪዎች ናቸው።

And the one who has brought the truth and [they who] believed in it - those are the righteous.

39:34
ለነሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አላቸው፤ ይህ የበጎ አድራጊዎች ምንዳ ነው።

They will have whatever they desire with their Lord. That is the reward of the doers of good -

39:35
አላህ ያንን (በስሕተ) የሠሩትን መጥፎ ሥራ ከነርሱ ሊሰርይላቸው በዚያም ይሠሩት በነበሩት በመልካሙ ሥራ ምንዳቸውን ሊመነዳቸው፣ (ይህንን አደረገ)።

That Allah may remove from them the worst of what they did and reward them their due for the best of what they used to do.

39:36
አላህ ባሪያውን በቂ አይደለምን? በነዚያ ከርሱ ሌላ በሆኑትም፣ (ጣዖታት)፣ ያስፈራሩሃል፤ አላህ የሚያጠመውም እርሱ ምንም አቅኚ የለውም።

Is not Allah sufficient for His Servant [Prophet Muhammad]? And [yet], they threaten you with those [they worship] other than Him. And whoever Allah leaves astray - for him there is no guide.

39:37
አላህ የሚያቀናውም ሰው ለርሱ ምንም አጥማሚ የለውም፤ አላህ አሸናፊ፣ የመበቀል ባለቤት አይደለምን?

And whoever Allah guides - for him there is no misleader. Is not Allah Exalted in Might and Owner of Retribution?

39:38
ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደ ሆነ ብትጠይቃቸው አላህ ነው፣ ይሉሃል።ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን (ጣዖታት) አያችሁን? (ነገሩኝ) አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈቅደኝ እነርሱ ችሮታውን አዘጋጆች ናቸውን? በላቸው። አላህ በቂዬ ነው፤ በርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ፤ በል።

And if you asked them, "Who created the heavens and the earth?" they would surely say, " Allah ." Say, "Then have you considered what you invoke besides Allah ? If Allah intended me harm, are they removers of His harm; or if He intended me mercy, are they withholders of His mercy?" Say, "Sufficient for me is Allah ; upon Him [alone] rely the [wise] reliers."

39:39
(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፦ ሕዝቦቼ ሆይ! ባላችሁበት ሁነታ ላይ ሥሩ፤ እኔ ሠሪ ነኝና፤ ወደፊትም ታውቃላችሁ፤

Say, "O my people, work according to your position, [for] indeed, I am working; and you are going to know

39:40
ያንን፣ የሚያሳፍረውን ቅጣት የሚመጣበትንና በርሱ ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን፣ (ታውቃላችሁ)?

To whom will come a torment disgracing him and on whom will descend an enduring punishment."

39:41
እኛ መጽሐፉን ባንተ ላይ ለሰዎች (ጥቅም) በውነት አወረድነው፤ የተመራም ሰው ለነፍሱ ነው፤ የጠመመም ሰው የሚጠመው (ጉዳቱ) በርሷ ላይ ነው፤ አንተም (ታስገድዳቸው ዘንድ) በነርሱ ላይ ጠባቂ አይደለህም።

Indeed, We sent down to you the Book for the people in truth. So whoever is guided - it is for [the benefit of] his soul; and whoever goes astray only goes astray to its detriment. And you are not a manager over them.

39:42
አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ፣ ይወስዳል፤ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ (ይወስዳታል)፤ ታዲያ ያችን ሞትን የፈረደባትን ይይዛታል፤ ሌላይቱንም እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ይለቃታል፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ምልክቶች አሉበት።

Allah takes the souls at the time of their death, and those that do not die [He takes] during their sleep. Then He keeps those for which He has decreed death and releases the others for a specified term. Indeed in that are signs for a people who give thought.

39:43
ይልቁንም (ቁረይሾች) ከአላህ ሌላ አማላጆችን ያዙ፤ እነርሱ ምንንም የማይችሉና የማያውቁ ቢሆኑም? በላቸው።

Or have they taken other than Allah as intercessors? Say, "Even though they do not possess [power over] anything, nor do they reason?"

39:44
ምልጃ መላውም የአላህ ብቻ ነው፤ የሰማያትና የምድር ሥልጣን የርሱ ብቻ ነው፤ ከዚያም ወደርሱ ትመለሳላችሁ፤ በላቸው።

Say, "To Allah belongs [the right to allow] intercession entirely. To Him belongs the dominion of the heavens and the earth. Then to Him you will be returned."

39:45
አላህም ብቻውን በተወሳ ጊዜ፣ የነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይሸመቀቃሉ፤ (ይደነብራሉ)፤ እነዚያም ከርሱ ሌላ የሆኑት (ጣዖታት) በተወሱኑ ጊዜ እነርሱ ወዲያውን ይደሰታሉ።

And when Allah is mentioned alone, the hearts of those who do not believe in the Hereafter shrink with aversion, but when those [worshipped] other than Him are mentioned, immediately they rejoice.

39:46
ሰማያትንና ምድርን የፈጠርክ፣ ሩቁንም ቅርቡም ዐዋቂ የኾንክ አላህ ሆይ! አንተ በባሮችህ መካከል በዚያ በርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ትፈርዳለህ፤ በል።

Say, "O Allah , Creator of the heavens and the earth, Knower of the unseen and the witnessed, You will judge between your servants concerning that over which they used to differ."

39:47
ለነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላውም፤ ከርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ ትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በርሱ ነፍሶቻቸውን በተበዡበት ነበር። ከአላህ ዘንድ ያስብት ያልነበሩት ሁሉ ይገለጽላቸዋል።

And if those who did wrong had all that is in the earth entirely and the like of it with it, they would [attempt to] ransom themselves thereby from the worst of the punishment on the Day of Resurrection. And there will appear to them from Allah that which they had not taken into account.

39:48
ለነሱም የሠሩዋቸው መጥፎዎቹ፣ ይገለጹላቸዋል። በነርሱም ላይ በርሱ ያላግጡበት የነበሩት ቅጣት ይሰፍርባቸዋል።

And there will appear to them the evils they had earned, and they will be enveloped by what they used to ridicule.

39:49
ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ፣ ይጠራናል፤ ከዚያም ከኛ የኾነውን ጸጋ በሠጠነው ጊዜ፣ እርሱን የተሰጠሁት፣ በእውቀት ብቻ ነው ይላል፤ ይልቁንም እርሷ (ጸጋዪቱ) መፈተኛ ናት፤ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።

And when adversity touches man, he calls upon Us; then when We bestow on him a favor from Us, he says, "I have only been given it because of [my] knowledge." Rather, it is a trial, but most of them do not know.

39:50
እነዚያ ከነሱ በፊት የነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ ብለዋታል፤ ይሠሩት የነበሩትም ነገር ከነሱ አልጠቀማቸውም።

Those before them had already said it, but they were not availed by what they used to earn.

39:51
የሠሩዋቸውም መጥፎዎች፣ (ቅጣት) አገኛቸው። ከነዚህም እነዚያ የበደሉት፣ የሠሩዋቸው መጥፎዎች (ፍዳ) በርግጥ ይነካቸዋል። እነርሱም አምላጮች አይደሉም።

And the evil consequences of what they earned struck them. And those who have wronged of these [people] will be afflicted by the evil consequences of what they earned; and they will not cause failure.

39:52
አላህ ሲሳዩን ለሚሻው ሰው የሚያሰፋ የሚያጠብም፣ መሆኑን አያውቁምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑት ሕዝቦች ግሣጼዎች አሉበት።

Do they not know that Allah extends provision for whom He wills and restricts [it]? Indeed in that are signs for a people who believe.

39:53
በላቸው፦ እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢአቶችን በመላ ይምራልና። እነሆ እርሱ መሐሪው አዛኙ ነውና።

Say, "O My servants who have transgressed against themselves [by sinning], do not despair of the mercy of Allah . Indeed, Allah forgives all sins. Indeed, it is He who is the Forgiving, the Merciful."

39:54
ቅጣቱም ወደ እናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትረዱ ከመሆናችሁ በፊት፣ ወደ ጌታችሁ (በመጸጸት) ተመለሱ፤ ለርሱም ታዘዙ።

And return [in repentance] to your Lord and submit to Him before the punishment comes upon you; then you will not be helped.

39:55
እናንተ የማታውቁ ስትሆኑም ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት፣ ከጌታችሁ ወደናንተ የተወረደውን መልካሙን (መጽሐፍ) ተከተሉ።

And follow the best of what was revealed to you from your Lord before the punishment comes upon you suddenly while you do not perceive,

39:56
(የካደች) ነፍስ፣ እኔ ከሚሳለቁት የነበርኩ ስሆን፣ በአላህ በኩል ባጓድልኩት ዋ ጸጸቴ! ማለቷን፣ (ለመፍራት)

Lest a soul should say, "Oh [how great is] my regret over what I neglected in regard to Allah and that I was among the mockers."

39:56
ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ፣ ለኔ (ወደ ምድረ ዓለም) አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎቹ በሆንኩ ማለቷን (ለመፍራት መልካሙን ተከተሉ)።

Or [lest] it say when it sees the punishment, "If only I had another turn so I could be among the doers of good."

39:57
ወይም አላህ በመራኝ ኖሮ ከሚጠነቀቁት እሆን ነበር ማለቷን፣ (ለመፍራት)

Or [lest] it say, "If only Allah had guided me, I would have been among the righteous."

39:59
የለም፣ ተመርተሃል፤ አንቀጾቼ በእርግጥ መጥተውልሃል፤ በነሱም አስተባበሃል፤ ኮርተሃልም፤ ከከሐዲዎቹም ሆነሃል፤ (ይባላል)።

But yes, there had come to you My verses, but you denied them and were arrogant, and you were among the disbelievers.

39:60
በትንሣኤ ቀንም፣ እነዚያን በአላህ ላይ የዋሹትን፣ ፊቶቻቸው የጠቆሩ ሆነው ታያቸዋለህ፤ በገሀነም ውስጥ ለትዕቢተኞች መኖሪያ የለምን?

And on the Day of Resurrection you will see those who lied about Allah [with] their faces blackened. Is there not in Hell a residence for the arrogant?

39:61
እነዚያን የተጠነቀቁትን በማግኛቸው ስፍራ ሆነው አላህ ያድናቸዋል፤ ክፉ ነገር አይነካቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም።

And Allah will save those who feared Him by their attainment; no evil will touch them, nor will they grieve.

39:62
አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው።

Allah is the Creator of all things, and He is, over all things, Disposer of affairs.

39:63
የሰማያትና የምድር (ድልብ) መክፈቻዎች የርሱ ብቻ ናቸው፤ እነዚያም በአላህ አንቀጾች የካዱት፣ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎቹ ናቸው።

To Him belong the keys of the heavens and the earth. And they who disbelieve in the verses of Allah - it is those who are the losers.

39:64
እላንተ መሃይማን ሆይ! ከአላህ ሌላን እንድንግገዛ ታዙኛላችሁን? በላቸው።

Say, [O Muhammad], "Is it other than Allah that you order me to worship, O ignorant ones?"

39:65
ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፤ በእርግጥም ከከሐዲዎቹ ትሆናለህ ማለት ወደ አንተም ወደነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል።

And it was already revealed to you and to those before you that if you should associate [anything] with Allah , your work would surely become worthless, and you would surely be among the losers."

39:66
ይልቅ አላህን ብቻ ተገዛም፤ ከአመስጋኞቹም ኹን።

Rather, worship [only] Allah and be among the grateful.

39:67
አላህንም በትንሣኤ ቀን ምድርን በመላ ጭብጡ (1) ስትሆን፤ ሰማያትም በኀይሉ የሚጠቀለሉ ሲሆኑ (ከርሱ ጋር ሌላን በማጋራታቸው) ተገቢ ክብሩንም አላከበሩትም። ከሚያጋሩት ጠራ ላቀም።

They have not appraised Allah with true appraisal, while the earth entirely will be [within] His grip on the Day of Resurrection, and the heavens will be folded in His right hand. Exalted is He and high above what they associate with Him.

39:68
በቀንዱም ይነፍፋል፤ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡርና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ፣ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፤ ከዚያም በርሱ ሌላ (መነፋት) ይነፋል፤ ወዲያውም እነርሱ (የሚሠራባቸውን) የሚጠባበቁ ሆነው ቋሚዎች ይሆናሉ።

And the Horn will be blown, and whoever is in the heavens and whoever is on the earth will fall dead except whom Allah wills. Then it will be blown again, and at once they will be standing, looking on

39:69
ምድርም በጌታዋ ብርሃን ታበራለች፤ መጽሐፉም ይቀረባል፤ ነቢያቱና ምስክሮቹም ይምመጣሉ፤ በመካከላቸውም በውነት ይፈረዳል፤ እነርሱም አይበደሉም።

And the earth will shine with the light of its Lord, and the record [of deeds] will be placed, and the prophets and the witnesses will be brought, and it will be judged between them in truth, and they will not be wronged.

39:70
ነፍስም ሁሉ የሠራችውን ሥራ ትሞላለች፤ (ትሰፈራለች)፤ እርሱም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው።

And every soul will be fully compensated [for] what it did; and He is most knowing of what they do.

39:71
እነዚያ የካዱትም፣ የተከፋፈሉ ጭፍሮች ሆነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፤ በመጧትም ጊዜ ደጃፎችዋ ይከፈታሉ፤ ዘበኞችዋም ከናንተ የሆኑ መልክተኞች የጌታችሁን አንቀጾች በናንተ ላይ የሚያነቡላችሁ የዚህንም ቀን መገናኘት የሚያስጠነቅቋችሁ አልመጡዋችሁምን? ይሏቸዋል፤ የለም መጥተውናል፤ግን የቅጣቲቱ ቃል በከሐዲዎች ላይ ተረጋገጠች ይላሉ።

And those who disbelieved will be driven to Hell in groups until, when they reach it, its gates are opened and its keepers will say, "Did there not come to you messengers from yourselves, reciting to you the verses of your Lord and warning you of the meeting of this Day of yours?" They will say, "Yes, but the word of punishment has come into effect upon the disbelievers.

39:72
የገሀነም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ፤ የትዕቢተኞችም መኖሪያ ምን ትከፋ! ይባላሉ።

[To them] it will be said, "Enter the gates of Hell to abide eternally therein, and wretched is the residence of the arrogant."

39:73
እነዚያ ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ጭፍሮችም ሆነው ወደ ገነት ይነዳሉ፤ በመጧትም ጊዜ፣ ደጃፎችዋ የተከፈቱ ሲሆኑ፣ ዘበኞችዋም ለነርሱ ሰላም በናንተ ላይ ይሁን፤ ተዋባችሁ፤ ዘውታሪዎች ሆናችሁ ግቧት፤ ባሏቸው ጊዜ (ይገቧታል)።

But those who feared their Lord will be driven to Paradise in groups until, when they reach it while its gates have been opened and its keepers say, "Peace be upon you; you have become pure; so enter it to abide eternally therein," [they will enter].

39:74
ምስጋና ለአላህ፣ ለዚያ ተስፋ ቃሉን ለሞላልን፤ የገነትን ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንሆን ላወረሰን ይገባው ይላሉም፤ የሠሪዎችም ምንዳ ምን ያምር!

And they will say, "Praise to Allah , who has fulfilled for us His promise and made us inherit the earth [so] we may settle in Paradise wherever we will. And excellent is the reward of [righteous] workers."

39:75
መላእክትንም በጌታቸው ምስጋና ቀላቅለው የሚያጠሩ ሲሆኑ በዐርሹ ዙሪያ ከባቢዎች ሆነው ታያለህ። በመካከላቸውም (1) በውነት ይፈረዳል፤ ይባላልም፤ ምስጋና ለአላህ፣ ለዓለማት ጌታ ይገባው።

And you will see the angels surrounding the Throne, exalting [ Allah ] with praise of their Lord. And it will be judged between them in truth, and it will be said, "[All] praise to Allah , Lord of the worlds."

Copyright 2013, AmharicQuran.com