Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አልሷፍፋት (የተሰላፊዎቹ ምዕራፍ)

37:1
መሰለፍን በሚሰለፉት።

By those (angels) ranged in ranks (or rows).

37:2
መገሠጽንም በሚገሥጹት፤

By those (angels) who drive the clouds in a good way.

37:3
ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ።

By those (angels) who bring the Book and the Qur'ân from Allâh to mankind

37:4
አምላካችሁ በእርግጥአንድ ነዉ።

Verily your Ilâh (God) is indeed One (i.e. Allâh)

37:5
የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉ ያለዉም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነዉ። የምሥራቆችም ጌታ ነዉ።

Lord of the heavens and the earth and that between them and Lord of the sunrises.

37:6
እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት።

Indeed, We have adorned the nearest heaven with an adornment of stars

37:7
አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት።

And as protection against every rebellious devil

37:8
ወደላይኛዉ ሰራዊት አያዳምጡም። ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል።

[So] they may not listen to the exalted assembly [of angels] and are pelted from every side

37:9
የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)።ለእነሱም ዘዉታሪ ቅጣት አላቸዉ።

Repelled; and for them is a constant punishment,

37:10
ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያዉም አብሪ ኮከብ የተከተለዉ ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)።

Except one who snatches [some words] by theft, but they are pursued by a burning flame, piercing [in brightness].

37:11
. ጠይቃቸዉም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸዉን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነዉ? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው።

Then inquire of them, [O Muhammad], "Are they a stronger [or more difficult] creation or those [others] We have created?" Indeed, We created men from sticky clay.

37:12
“በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?

When we have died and become dust and bones, are we indeed to be resurrected?

37:13
በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም።

And when they are reminded, they remember not.

37:14
ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ።

And when they see a sign, they ridicule

37:15
ይላሉም <ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።

And say, "This is not but obvious magic.

37:16
“በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?

When we have died and become dust and bones, are we indeed to be resurrected?

37:17
“የቀድሞዎቹ አባቶችንም ? (ይላሉ)።

And our forefathers [as well]?"

37:18
“አዎን አናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)” በላቸዉ።

Say, "Yes, and you will be [rendered] contemptible."

37:19
እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት። እነርሱም ወዲያዉኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸዉ) ያያሉ።

It will be only one shout, and at once they will be observing.

37:20
“ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነዉ” ይላሉም።

They will say, "O woe to us! This is the Day of Recompense."

37:21
“ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያዉ ቀን ነዉ” (ይባላሉ)።

[They will be told], "This is the Day of Judgement which you used to deny."

37:22
(ለመላእክቶችም) “እነዚያን ነፍሶቻቸዉን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸዉንም ይግገዟቸዉ የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ።

[The angels will be ordered], "Gather those who committed wrong, their kinds, and what they used to worship

37:23
ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸዉን ሰብስቧቸዉ) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸዉ።

Other than Allah , and guide them to the path of Hellfire

37:24
“አቁሟቸዉም።እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸዉና “ (ይባላል)።

And stop them; indeed, they are to be questioned."

37:25
(ለእነርሱም) “ የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)።

[They will be asked], "What is [wrong] with you? Why do you not help each other?"

37:26
በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸዉን የሰጡ ወራዳዎች ናቸዉ።

But they, that Day, are in surrender.

37:27
የሚወቃቀሱም ሆነዉ ከፊላቸዉ በከፈሉ ላይ ይመጣሉ።

And they will approach one another blaming each other.

37:28
(ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር1 ይላሉ።

They will say, "Indeed, you used to come at us from the right."

37:29
አስከታዮቹም) ይላሉ “ አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁሞ።

The oppressors will say, "Rather, you [yourselves] were not believers,

37:30
“ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም። በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ።

And we had over you no authority, but you were a transgressing people.

37:31
“በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን።

So the word of our Lord has come into effect upon us; indeed, we will taste [punishment].

37:32
” ወደ ጥምመት ጠራናችሁም። እኛጠማሞች ነበርንና” (ይላሉ)።

And we led you to deviation; indeed, we were deviators."

37:33
ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸዉ።

So indeed they, that Day, will be sharing in the punishment.

37:34
እኛ በአመጻኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን።

Indeed, that is how We deal with the criminals.

37:35
እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ በነሩ።

Indeed they, when it was said to them, "There is no deity but Allah ," were arrogant

37:36
እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተዉ ነን? ይሉም ነበር።

And were saying, "Are we to leave our gods for a mad poet?"

37:37
አይደለም እዉነቱን (ሃይማኖት) አመጣ። መልክተኞቹንም እዉነተኛ ነታቸዉን አረጋገጠ።

Rather, the Prophet has come with the truth and confirmed the [previous] messengers.

37:38
እናንተ አሳማሚዉን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ።

Indeed, you [disbelievers] will be tasters of the painful punishment,

37:39
ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም።

And you will not be recompensed except for what you used to do -

37:40
ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)።

But not the chosen servants of Allah .

37:42
ፍራፍሬዎች (አሏቸል) እነርሱም የተከበሩ ናቸዉ፤

Fruits; and they will be honored

37:43
በድሎት ገነቶች ዉስጥ።

In gardens of pleasure

37:44
ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)።

On thrones facing one another.

37:45
ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል።

There will be circulated among them a cup [of wine] from a flowing spring,

37:46
ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች።

White and delicious to the drinkers;

37:47
በእርሷ ዉስጥም ምታት የለባትም። እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም።

No bad effect is there in it, nor from it will they be intoxicated.

37:48
እነርሱም ዘንድ ዓይናቸዉን (በባሎቻቸዉ ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ(1)ዓይናማዎች አልሉ።

And with them will be women limiting [their] glances, with large, [beautiful] eyes,

37:49
እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ።

As if they were [delicate] eggs, well-protected.

37:50
የሚጠያየቁም ሆነዉ ከፊላቸዉ ወደ ከፊሉ ይመጣሉ።

And they will approach one another, inquiring of each other.

37:51
ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላሉ <እኔጓደኛ ነበረኝ።

A speaker among them will say, "Indeed, I had a companion [on earth]

37:52
” በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን?" የሚል።

Who would say, 'Are you indeed of those who believe

37:53
“በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?” (የሚል)።

That when we have died and become dust and bones, we will indeed be recompensed?'"

37:54
እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላሉ።(ጓደኛዉን) ያየዋል።

He will say, "Would you [care to] look?"

37:55
ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛዉን ጓ) ያየዋል።

And he will look and see him in the midst of the Hellfire.

37:56
ይላል “በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታ ጠፋኝ ቀርበህ ነበር።

He will say, "By Allah , you almost ruined me.

37:57
“የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር።”

If not for the favor of my Lord, I would have been of those brought in [to Hell].

37:58
(የገነት ሰዎች ይላሉ) “እኛ የምንሞት አይደለንምን?

Then, are we not to die

37:59
”የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር። እኛም የምንቅቀጣ አይደለን ምን?” (ይላሉ)።

Except for our first death, and we will not be punished?"

37:60
ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳዉ) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው።

Indeed, this is the great attainment.

37:61
ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ።

For the like of this let the workers [on earth] work.

37:62
በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?

Is Paradise a better accommodation or the tree of zaqqum?

37:63
እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል።

Indeed, We have made it a torment for the wrongdoers.

37:64
እርሷ በገሀነም አዘቅት ዉስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት።

Indeed, it is a tree issuing from the bottom of the Hellfire,

37:65
እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች መስላሉ።

Its emerging fruit as if it was heads of the devils.

37:66
እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸዉ፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸዉ።

And indeed, they will eat from it and fill with it their bellies.

37:67
ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኻሳ ዉሃ ቅልቅል (መጠጥ ) አልላቸዉ።

Then indeed, they will have after it a mixture of scalding water.

37:68
ከዚያም መመለሻቸዉ ወደ ተጋጋመች እሳት ነዉ።

Then indeed, their return will be to the Hellfire.

37:69
እነሱ አባቶቻቸዉን የተሳሳቱ ሆነዉ አግኝተዋልና።

Indeed they found their fathers astray.

37:70
እነሱም በፈለጎቻቸዉ ላይ ይገሰግሳሉና።

So they hastened [to follow] in their footsteps.

37:71
ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል።

And there had already strayed before them most of the former peoples,

37:72
በዉስጣቸዉም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል።

And We had already sent among them warners.

37:73
የተስፈራሪዎችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት።

Then look how was the end of those who were warned -

37:74
ምርጥ የሆነት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ።

But not the chosen servants of Allah .

Copyright 2013, AmharicQuran.com