Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ ያሲን (የያሲን ምዕራፍ)

36:1
የ.ሰ. (ያ ሲን) (1)

Ya, Seen.

36:2
ጥበብ በተመላበት ቁርአን እምላለሁ ፤

By the wise Qur'an.

36:3
አንተ በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ ።

Indeed you, [O Muhammad], are from among the messengers,

36:4
በቀጥታው መንገድ ላይ ነህ ።

On a straight path.

36:5
አሸናፊ አዛኝ ከሆነው አምላክ መውረድን ተወረደ።

[This is] a revelation of the Exalted in Might, the Merciful,

36:6
አባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ሕዝቦች ልታስጠነቅቅበት (ተወረደ) ። እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና።

That you may warn a people whose forefathers were not warned, so they are unaware.

36:7
በአብዛኞቻቸው ላይ ቃሉ በውነት ተረጋገጠ ፤ ስለዚህ እነርሱ አያምኑም።

Already the word has come into effect upon most of them, so they do not believe.

36:7
እኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዘዝላዎችን አደረግን ፤ እርሷም (እንዘዝላይቱ) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት፤ እነርሱም ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው። (2)

Indeed, We have put shackles on their necks, and they are to their chins, so they are with heads [kept] aloft.

36:9
ከስተፊታቸው ግርዶን ከስተኋላቸው ግርዶን አደረግን ፤ ሸፋፈንናቸውም ፤ ስለዚህ እነሱ አያዩም።

And We have put before them a barrier and behind them a barrier and covered them, so they do not see.

36:10
በታስጠነቅቃቸውም ብታስጠነቅቃቸውም በነርሱ ላይ እኩል ነው ፤ አያምኑም::

And it is all the same for them whether you warn them or do not warn them - they will not believe.

36:11
የምታስጠነቅቀው ግሣጼን የተከተለንና አልረሕማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው ፤ በምሕረትና በመልካም ምንዳም አብስረው።

You can only warn one who follows the message and fears the Most Merciful unseen. So give him good tidings of forgiveness and noble reward.

36:12
እኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን ፤ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን ፤ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በሆነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው።

Indeed, it is We who bring the dead to life and record what they have put forth and what they left behind, and all things We have enumerated in a clear register.

36:13
ለነሱም የከተማይቱን (የአንጣኪያን) ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ፣ (የሆነውን) ግለጽላቸው።

And present to them an example: the people of the city, when the messengers came to it -

36:14
ወደነርሱ ሁለት ሰዎችን በላክንና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ፣ በሦስተኛው አበረታንና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ፣ (የሆነውን ምሳሌ ግለጽላቸው) ።

When We sent to them two but they denied them, so We strengthened them with a third, and they said, "Indeed, we are messengers to you."

36:15
እናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም ፤ አልረህማንም ምንም ነገር አላወረደም ፤ እናንተ የምትዋሹ እንጂ ሌላ አይደላችሁም አሉዋቸው።

They said, "You are not but human beings like us, and the Most Merciful has not revealed a thing. You are only telling lies."

36:16
(መልክተኞቹም) አሉ፦ ጌታችን ያውቃል፤ እኛ ወደናንተ በእርግጥ መልክተኞች ነን ፤

They said, "Our Lord knows that we are messengers to you,

36:17
በኛ ላይም ግልጽ የሆነ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብንም።

And we are not responsible except for clear notification."

36:18
ሕዝቦቹም) ፦ እኛ በናንተ ገደቢሶች ሆን ፤ ባትከለከሉ በእርግጥ እንወግራችሁዋለን፤ ከኛም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ያገኛችኋል ፤ አሉ።

They said, "Indeed, we consider you a bad omen. If you do not desist, we will surely stone you, and there will surely touch you, from us, a painful punishment."

36:19
ገደ ቢስነታቸው ከናንተው ጋር ነው ፤ ብትግገሠጹ (ትዝታላችሁን?) በውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ አሏቸው።

They said, "Your omen is with yourselves. Is it because you were reminded? Rather, you are a transgressing people."

36:20
ከከተማይቱም ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣ፤ ወገኖቼ ሆይ! መልክተኞቹን ተከተሉ አለ።

And there came from the farthest end of the city a man, running. He said, "O my people, follow the messengers.

36:21
እነርሱ ቅኑን መንገድ የተመሩ ሲሆኑዋጋንም የማይጠይቋችሁ ሰዎች ተከተሉ (አላቸው) ።

Follow those who do not ask of you [any] payment, and they are [rightly] guided.

36:22
ያንንም የፈጠረኝን ፤ ወደርሱም የምትመለሱበትን (ጌታ) የማልግገዛ ለኔ ምን አለኝ? (አለ) ።

And why should I not worship He who created me and to whom you will be returned?

36:23
ከርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረሕማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከኔ (ለመመለስ) ምንም አትጠቅመኝም፤ አያድኑኝም።

Should I take other than Him [false] deities [while], if the Most Merciful intends for me some adversity, their intercession will not avail me at all, nor can they save me?

36:24
እኔ ያን ጊዜ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ነኝ ፤

Indeed, I would then be in manifest error.

36:25
እኔ በጌታችሁ አመንኩ ፤ ስሙኝም (አለ) ።

Indeed, I have believed in your Lord, so listen to me."

36:26
ገነትን ግባ ተባለ ፤ (እርሱም) አለ ፦ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ ፤

It was said, "Enter Paradise." He said, "I wish my people could know

36:27
ጌታዬ ለኔ ምሕረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መሆኑን።

Of how my Lord has forgiven me and placed me among the honored."

36:28
ከርሱም በኋላ በሕዝቦቹ ላይ (ልናጠፋቸው) ሰራዊትን ከሰማይ አላወረድንም ፤ (በማንም ላይ) አውራጆች አልነበርንም።

And We did not send down upon his people after him any soldiers from the heaven, nor would We have done so.

36:29
(ቅጣታቸው) አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አልነበረችም ፤ ወዲያውኑም እነርሱ ጠፊዎች ሆኑ።

It was not but one shout, and immediately they were extinguished.

36:30
በባሮቹ ላይ ዋ ቁልጭት! ከመልክተኛ አንድም አይመጣቸውም በርሱ የሚሳለቁበት ቢሆኑ እንጅ።

How regretful for the servants. There did not come to them any messenger except that they used to ridicule him.

36:31
ከነሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንና እነሱ ወደነርሱ የማይመለሱ መሆናቸውን አላወቁምን?

Have they not considered how many generations We destroyed before them - that they to them will not return?

36:32
ሁሉም እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀረቡ እንጂ ሌላ አይደሉም።

And indeed, all of them will yet be brought present before Us.

36:33
የሞተችውም ምድር ለነሱ ምልክት ናት! ሕያው አደረግናት ፤ ከርሷም ፍሬን አወጣን፤ ከርሱም ይበላሉ።

And a sign for them is the dead earth. We have brought it to life and brought forth from it grain, and from it they eat.

36:34
በርሷም ውስጥ ከዘምባባዎችና ከወይኖች የሆኑ አትክልተኞችን አደረግን ፤ በርሷም ውስጥ ምንጮችን አፈለቅን።

And We placed therein gardens of palm trees and grapevines and caused to burst forth therefrom some springs -

36:35
ከፍሬውና እጆቻቸው ከሠሩትም ይበሉ ዘንድ (ይህን አደረግን)፤ አያመሰግኑምን?

That they may eat of His fruit. And their hands have not produced it, so will they not be grateful?

36:36
ያ ምድር ከምታበቅለው ከነፍሶቻቸውም ከማያውቁትም ነገር ዓይነቶችን ሁሏንም የፈጠረ (አምላክ)፣ ጥራት ይገባው።

Exalted is He who created all pairs - from what the earth grows and from themselves and from that which they do not know.

36:37
ሌሊቱም ለነሱ ምልክት ነው፤ ከርሱ ላይ ቀንን እንገፍፋለን ወዲያውኑም እነሱ በጨለማ ውስጥ ይገባሉ።

And a sign for them is the night. We remove from it [the light of] day, so they are [left] in darkness.

36:38
ፀሐይም ለርሷ ወደሆነው መርጊያ ትሮጣለችይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው።

And the sun runs [on course] toward its stopping point. That is the determination of the Exalted in Might, the Knowing.

36:39
ጨረቃንም መስፈሪያዎች (1) ባለቤት ሲሆን እንደ ዘንባባ አሮጌ ቀንዘል እስኪሆን ድረስ (መኼዱን) ለካነው።

And the moon - We have determined for it phases, until it returns [appearing] like the old date stalk.

36:40
ፀሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም፤ ሌሊትም ቀንን (ያለጊዜው) ቀዳሚ አይሆንም፤ ሁሉም በመዞርያቸው ውስጥ ይዋኛሉ።

It is not allowable for the sun to reach the moon, nor does the night overtake the day, but each, in an orbit, is swimming.

36:41
እኛም (የቅድም) ትውልዳቸውን በተመላች መርከብ ውስጥ የጫን መሆናችን ለነርሱ ምልክት ነው።

And a sign for them is that We carried their forefathers in a laden ship.

36:42
ከመሰሉም በርሱ የሚሳፈሩበትን ለነርሱ ፈጠርንላቸው።

And We created for them from the likes of it that which they ride.

36:43
ብንሻም እናሰጥማቸዋለን፤ ለነርሱም ረዳት የላቸውም፤ እነርሱም የሚድዳኑ አይደሉም።

And if We should will, We could drown them; then no one responding to a cry would there be for them, nor would they be saved

36:44
ግን ከኛ ለሆነው ችሮታና እስከ ጊዜ ሞታቸው ለማጣቀም (አዳናቸው)።

Except as a mercy from Us and provision for a time.

36:45
ለነርሱም በስተ-ፊታችሁና በኋላችሁ ያለውን ነገር ተጠንቀቁይታዘንላችኋልና በተባሉ ጊዜ (ፊታቸውን ያዞራሉ)። ቁም

But when it is said to them, "Beware of what is before you and what is behind you; perhaps you will receive mercy... "

36:46
ከጌታቸውም ታምራት ማንኛይቱም ታምር አትመጣላቸውም፤ ከርሷ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ

And no sign comes to them from the signs of their Lord except that they are from it turning away.

36:47
ለነሱም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ለግሱ በተባሉ ጊዜ እነዚያ የካዱት ለነዚያ ላመኑት፦ አላህ ቢሻ ኖሮ የሚያበላውን ሰው እናበላለን? እናንተ በግልጽ ሰሕተት ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደላችሁም ይላሉ።

And when it is said to them, "Spend from that which Allah has provided for you," those who disbelieve say to those who believe, "Should we feed one whom, if Allah had willed, He would have fed? You are not but in clear error."

36:48
እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው? ይላሉ፤

And they say, "When is this promise, if you should be truthful?"

36:49
እነርሱ የሚከራከሩ ሲሆኑ በድንገት የምትይዛቸው የሆነችን አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላን አይጠባበቁም።

They do not await except one blast which will seize them while they are disputing.

36:50
(ያን ጊዜ) መናዘዝንም አይችሉም፤ ወደ ቤተሰቦቻቸውም አይመለሱም።

And they will not be able [to give] any instruction, nor to their people can they return.

36:51
በቀንዱም ይነፍፋል፤ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሠግሣሉ።

And the Horn will be blown; and at once from the graves to their Lord they will hasten.

36:52
ወይ ጥፋታችን ! ከምኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ (በርሱ) የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩ ነው ይላሉ።

They will say, "O woe to us! Who has raised us up from our sleeping place?" [The reply will be], "This is what the Most Merciful had promised, and the messengers told the truth."

36:53
(እርሷ) አንዲት ጩኸት እንጂ አይደለችም፤ ወዲያውኑም እንርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው።

It will not be but one blast, and at once they are all brought present before Us.

36:54
ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንም አትበደል፤ ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም (ይባላሉ)።

So today no soul will be wronged at all, and you will not be recompensed except for what you used to do.

36:55
የገነት ሰዎች ዛሬ በእርግጥ በሥራዎች ውስጥ ተደሳቾች ናቸው፤

Indeed the companions of Paradise, that Day, will be amused in [joyful] occupation -

36:56
እነርሱም ሚስቶቻቸውም በጥላዎች ውስጥ ናቸው፤ ባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ናቸው።

They and their spouses - in shade, reclining on adorned couches.

36:57
በውስጧ ለርነሱ ፍራፍሬዎች አሏቸው፤ ለነርሱም የሚፈልጉት ሁሉ አላቸው።

For them therein is fruit, and for them is whatever they request [or wish]

36:58
(ለነሱም) አዛኝ ከሆነው ጌታ ቃል በቃል ሰላምታ አላቸው።

[And] "Peace," a word from a Merciful Lord.

36:59
(ይላልም) እላንተ አመጠኞች ሆይ ! ዛሬ (ከምእመናን) ተለዩ፤

[Then He will say], "But stand apart today, you criminals.

36:60
የአደም ልጆች ሆይ ! ሰይጣንን አትግገዙ፤ እርሱ ለናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደናንተ አላዘዝኩምን?

Did I not enjoin upon you, O children of Adam, that you not worship Satan - [for] indeed, he is to you a clear enemy -

36:61
ተገዙኝም፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፤ (በማለትም)

And that you worship [only] Me? This is a straight path.

36:62
ከናንተ ብዙን ፍጡር በርግጥ አሳስቷል፤ የምታውቁም አልነበራችሁምን?

And he had already led astray from among you much of creation, so did you not use reason?

36:63
ይህቺ ያቺ ትቅቀጠሩዋት የነበረችው ገሀነም ናት፤

This is the Hellfire which you were promised.

36:64
ትክዱ በነበራችሁ ምክንያት ዛሬ ግቡዋት (ይባላሉ)።

[Enter to] burn therein today for what you used to deny."

36:65
ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፤ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ።

That Day, We will seal over their mouths, and their hands will speak to Us, and their feet will testify about what they used to earn.

36:66
ብንሻም ኖሮ በዐይኖቻቸው ላይ በአበስን ነበር፤ መንገድንም (እንደ ልማዳቸው) በተሽቀዳደሙ ነበር፤ እንዴትም ያያሉ?

And if We willed, We could have obliterated their eyes, and they would race to [find] the path, and how could they see?

36:67
ብንሻም ኖሮ በስፍራቸው ላይ እንዳሉ ወደ ሌላ ፍጥረት በለወጥናቸው ነበር፤ መኼድንም መመለስንም ባልቻሉም ነበር።

And if We willed, We could have deformed them, [paralyzing them] in their places so they would not be able to proceed, nor could they return.

36:68
ዕድሜውንም የምናረዝመውን ሰው በፍጥረቱ (ወደ ደካማነት) እንመልሰዋለን፤ አያውቁምን?

And he to whom We grant long life We reverse in creation; so will they not understand?

36:69
(ሙሐመድን) ቅኔን አላስተማርነውም፤ ለርሱም አይገባውም እርሱ (መጽሐፉ) መገሠጫና ገላጭ ቁርአን እንጂ ቅኔ አይደለም።

And We did not give Prophet Muhammad, knowledge of poetry, nor is it befitting for him. It is not but a message and a clear Qur'an

36:70
(ግሣጼነቱም ልቡ) ሕያው የሆነን ሰው ሊያስፈራራበትና ቃሉም በከሐዲዎች ላይ ይፈጸም ዘንድ ነው።

To warn whoever is alive and justify the word against the disbelievers.

36:71
እኛ እጆቻችን (ኃይሎቻችን) ከሠሩት ለነርሱ እንሰሳዎችን መፈጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ልርሷ ባለ መብቶች ናቸው።

Do they not see that We have created for them from what Our hands have made, grazing livestock, and [then] they are their owners?

36:72
ለነርሱም ገራናት ስለዚህ ከርሷም ይበላሉ።

And We have tamed them for them, so some of them they ride, and some of them they eat.

36:73
ለነርሱም በርሷ ውስጥ (ሌሎች) ጥቅሞች መጠጦችም አሉዋቸው ፣ ታዲያ አያመሰግኑምን?

And for them therein are [other] benefits and drinks, so will they not be grateful?

36:74
መረዳትንም በመከጀል ከአላህ ሌላ አማልክትን ያዙ፤

But they have taken besides Allah [false] deities that perhaps they would be helped.

36:75
መርዳታቸውን አይችሉም፤ እነርሱም ለርሳቸው (ወደ እሳት) የተቀረቡ ሰራዊት ሰራዊት ናቸው።

They are not able to help them, and they [themselves] are for them soldiers in attendance.

36:76
ንግግራቸውም አያሳዝንህ፤ እኛ የሚደብቁትንም የሚደብቁትንም የሚገልጹትንም እናውቃለንና።

So let not their speech grieve you. Indeed, We know what they conceal and what they declare.

36:77
ሰውየው እኛ ከፍቶት ጠብታ የፈጠርነው መሆናችን አላወቀምን? ወዲያውም እርሱ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይሆናልን?

Does man not consider that We created him from a [mere] sperm-drop - then at once he is a clear adversary?

36:78
ለኛም ምሳሌን አደረገልን፤ መፈጠሩንም ረሳ አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲሆኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው? አለ።

And he presents for Us an example and forgets his [own] creation. He says, "Who will give life to bones while they are disintegrated?"

36:79
ያ በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ሕያው ያደርጋታል፤ እርሱም በፍጡሩ ሁሉ (ሁነታ) ዐዋቂ ነው በለው።

Say, "He will give them life who produced them the first time; and He is, of all creation, Knowing."

36:80
ያ ለናንተ ከእርጥብ ዛፍ እሳትን ያደረገላችሁ ነው ወዲያውኑም እናንተ ከርሱ ታቀጣጥላላችሁ።

[It is] He who made for you from the green tree, fire, and then from it you ignite.

36:81
ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? ነውንጂ እርሱም በብዙ ፈጣሪው ዐዋቂ ነው።

Is not He who created the heavens and the earth Able to create the likes of them? Yes, [it is so]; and He is the Knowing Creator.

36:82
ነገሩም አንዳች ባሻ ጊዜ ሁን ማለት ነው ወዲያው ይሆናልም።

His command is only when He intends a thing that He says to it, "Be," and it is.

36:83
ያ የነገሩ ሁሉ ስልጣን በጁ የሆነው ጌታ ጥራት ይግባው፤ ወደርሱም ትመለሳላችሁ።

So exalted is He in whose hand is the realm of all things, and to Him you will be returned.

Copyright 2013, AmharicQuran.com