Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ ሰበእ፤ (የሰበእ ምዕራፍ)

34:1
ምስጋና ለዚያ በሰማያትም ያለ፣ በምድርም ያለ ሁሉ፣ የርሱ ለሆነው ለአላህ ይገባው፤ በመጨረሻይቱም ዓለም ምስጋና ለርሱ ብቻ ነው፤ እርሱም ብልሃተኛው ውስጠ ዐዋቂው ነው።

[All] praise is [due] to Allah , to whom belongs whatever is in the heavens and whatever is in the earth, and to Him belongs [all] praise in the Hereafter. And He is the Wise, the Acquainted.

34:2
በምድር ውስጥ የሚገባውን ሁሉ፣ ክከሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይ የሚወርደውን፣ በርሷም ውስጥ የሚያርገውን ሁሉ ያውቃል፤ እርሱም አዛኙ መሐሪው ነው።

He knows what penetrates into the earth and what emerges from it and what descends from the heaven and what ascends therein. And He is the Merciful, the Forgiving.

34:3
እነዚያ የካዱትም፣ ሰዓቲቱ አትመጣብንም አሉ፤ በላቸው ፡- አይደለም ሩቁን ሁሉ አዋቂ በሆነው ጌታዬ እምላለሁ፤ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፤ የብናኝ ክብደት ያክል ክብደት እንኳን በሰማይና በምድር ውስጥ ከርሷ አይርቅም፤ ከዚህ ያነሰም ሆነ የበለጠም የለም፣ በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጅ።

But those who disbelieve say, "The Hour will not come to us." Say, "Yes, by my Lord, it will surely come to you. [ Allah is] the Knower of the unseen." Not absent from Him is an atom's weight within the heavens or within the earth or [what is] smaller than that or greater, except that it is in a clear register -

34:4
እነዚያ ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ሊመነዳ፣ (ሰዓቲቱ ትመጣባችኋለች)፤ እነዚያ፣ ለነሱ ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው።

That He may reward those who believe and do righteous deeds. Those will have forgiveness and noble provision.

34:5
እነዚያም የሚያመልጡ መስሏቸው አንቀጾቻችንን ለማፍረስ የጣሩ፣ እነዚያ ለነርሱ ከመጥፎ ቅጣት የሆነ አሳማሚ ስቃይ አላቸው።

But those who strive against Our verses [seeking] to cause failure - for them will be a painful punishment of foul nature.

34:6
እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት፣ ያንን ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን፣ እርሱ እውነትና አሸናፊ ምስጉን ወደ ሆነው አላህ መንገድ የሚመራ መሆኑን ያውቃሉ።

And those who have been given knowledge see that what is revealed to you from your Lord is the truth, and it guides to the path of the Exalted in Might, the Praiseworthy.

34:7
እነዚያም የካዱት፦ (ሙታችሁ) መበጣጠስን ሁሉ በተበጣጠሳችሁ ጊዜ እናንተ በአዲስ መፈጠር ውስጥ ትሆናላችሁ ብሎ የሚነግራችሁን ሰው እናሳያችሁን? አሉ።

But those who disbelieve say, "Shall we direct you to a man who will inform you [that] when you have disintegrated in complete disintegration, you will [then] be [recreated] in a new creation?

34:8
በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈን? ወይስ በርሱ ዕብደት አለበትን? (አሉ)፤ እንዳሉት አይደለም፤ እነዚያ በመጨረሻይቱ (ዓለም) የማያምኑት (በርሷ) በቅጣት ውስጥ (አሁን) በራቀ ስሕተትም ውስጥ ናቸው።

Has he invented about Allah a lie or is there in him madness?" Rather, they who do not believe in the Hereafter will be in the punishment and [are in] extreme error.

34:9
ከሰማይና ከምድር በፊታቸውና በኋላቸው ወዳለው ሁሉ አይመለከቱምን? ብንሻ በነርሱ፣ ምድርን እንደርባባቸዋለን፤ ወይም በነርሱ ላይ ከሰማይ ቁራጭን እንጥልባቸዋለን፤ በዚህ ውስጥ፣ (ወደ ጌታው) ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ምልክት አለበት።

Then, do they not look at what is before them and what is behind them of the heaven and earth? If We should will, We could cause the earth to swallow them or [could] let fall upon them fragments from the sky. Indeed in that is a sign for every servant turning back [to Allah ].

34:10
ለዳውድም ከኛ የሆነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው፤(አልንም)፦ ተራራዎች ሆይ! ከርሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ፤ በራሪዎችንም፣ (ገራንለት)፤ ብረትንም ለርሱ አለዘብንለት።

And We certainly gave David from Us bounty. [We said], "O mountains, repeat [Our] praises with him, and the birds [as well]." And We made pliable for him iron,

34:11
ሰፋፊዎችን ጥሩሮች (1) ሥራ፤ በአሠራርዋም መጥን፤ መልካምንም ሥራ ሥሩ፤ እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና (አልነው)።

[Commanding him], "Make full coats of mail and calculate [precisely] the links, and work [all of you] righteousness. Indeed I, of what you do, am Seeing."

34:12
ለሱለይማንም ነፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ ፣ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲሆን ገራንለት፤ የነሐስንም ምንጭ ለርሱ አፈሰስንለት፤ ከጋኔኖችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሰሩን፣ (አደረግንለት)፤ ከነሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዲድ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን።

And to Solomon [We subjected] the wind - its morning [journey was that of] a month - and its afternoon [journey was that of] a month, and We made flow for him a spring of [liquid] copper. And among the jinn were those who worked for him by the permission of his Lord. And whoever deviated among them from Our command - We will make him taste of the punishment of the Blaze.

34:13
ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከሆኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም፣ የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል፤ (አልናቸውም)፦ የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ! አመስጋኞች ሆናችሁ (ለጌታችሁ) ሥሩ፤ ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው።

They made for him what he willed of elevated chambers, statues, bowls like reservoirs, and stationary kettles. [We said], "Work, O family of David, in gratitude." And few of My servants are grateful.

34:14
በርሱም ላይ ሞትን በፈጸምንበት ጊዜ መሞቱን በትሩን የምትበላ ተንቀሳቃሽ ምስጥ እንጂ ሌላ አላመለከታቸውም፤ በወደቀ ጊዜም ጋኔኖች ሩቅን ሚስጢር የሚያውቁ በሆኑ ኖሮ፣ በአዋራጅ ስቃይ ውስጥ የማይቆዩ እንደነበሩ ተረዱ።

And when We decreed for Solomon death, nothing indicated to the jinn his death except a creature of the earth eating his staff. But when he fell, it became clear to the jinn that if they had known the unseen, they would not have remained in humiliating punishment.

34:15
ለሰበእ (1) በመኖሪያቸው በውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች (ነበሩዋቸው)፤ ከጌታችሁ ሲሳይ ብሉ፤ ለርሱም አመስግኑ፤ ሀገራችሁ ውብ ሀገር ናት፤ (ጌታችሁ) መሐሪ ጌታም ነው፤ (ተባሉ)።

There was for [the tribe of] Saba' in their dwelling place a sign: two [fields of] gardens on the right and on the left. [They were told], "Eat from the provisions of your Lord and be grateful to Him. A good land [have you], and a forgiving Lord."

34:16
(ከማመስገን) ዞሩም፤ በነርሱም ላይ የግድቡን ጎርፍ ለቀቅንባቸው፤ በአትክልቶቻቸውም ሁለትን አትክልቶች፣ ባለ መርጋጋ ፍሬዎችን ባለጠደቻና ከቁርቁራም ባለ ጥቂት ዛፎችን፣ ለወጥናቸው።

But they turned away [refusing], so We sent upon them the flood of the dam, and We replaced their two [fields of] gardens with gardens of bitter fruit, tamarisks and something of sparse lote trees.

34:17
በመከዳቸው ይህንን መነዳናቸው፤ (እንዲህ ያለውን ቅጣት) በጣም ከሐዲን እንጂ ሌላውን እንቀጣለን?

But [insolently] they said, "Our Lord, lengthen the distance between our journeys," and wronged themselves, so We made them narrations and dispersed them in total dispersion. Indeed in that are signs for everyone patient and grateful.

34:18
በነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን፤ በርሷም ጉዞን ወሰንን፤ ጸጥተኞች ሆናችሁ፣ በሌሊቶችም በቀኖችም ተጓዙ፤ (አልን)።

And Iblees had already confirmed through them his assumption, so they followed him, except for a party of believers.

34:19
ጌታችን ሆይ! በጉዞዎቻችን መካከል አራርቅልን አሉም፤ ነፍሶቻቸውንም በደሉ፤ (መገረሚያ) ወሬዎችም አደረግናቸው፤ መበታተንንም ሁሉ በታተንናቸው፤ በዚህ ውስጥ፣ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ መገሠጫዎች አሉበት።

But [insolently] they said, "Our Lord, lengthen the distance between our journeys," and wronged themselves, so We made them narrations and dispersed them in total dispersion. Indeed in that are signs for everyone patient and grateful.

34:20
ኢብሊስም በነሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈጸመ፤ ከአመኑትም የሆኑት ጭፍሮች በስተቀር ተከተሉት።

And Iblees had already confirmed through them his assumption, so they followed him, except for a party of believers.

34:21
በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያምነውን፣ ከዚያ እርሱ ከርሷ በመጠራጠር ውስጥ ከሆነው ሰው ለይተን እንድናውቅ እንጅ፣ በነርሱ ላይ ለርሱ ምንም ስልጣን አልነበረውም ጌታህም በነገሩ ላይ ተጠባባቂ ነው።

And he had over them no authority except [it was decreed] that We might make evident who believes in the Hereafter from who is thereof in doubt. And your Lord, over all things, is Guardian.

34:22
እነዚያን ከአላህ ሌላ (አማልክት ብላችሁ) የምታስስቧቸውን ጥሩ፤ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፤ ለነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፤ ከነርሱም ለርሱ ምንም አጋዥ የለውም በላቸው።

Say, [O Muhammad], "Invoke those you claim [as deities] besides Allah ." They do not possess an atom's weight [of ability] in the heavens or on the earth, and they do not have therein any partnership [with Him], nor is there for Him from among them any assistant.

34:23
ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ፣ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፤ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጠም ጊዜ (ተማላጆቹ) ጌታችሁ ምን አለ? ይላሉ፤ (አማላጆቹ) እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው ይላሉ።

And intercession does not benefit with Him except for one whom He permits. [And those wait] until, when terror is removed from their hearts, they will say [to one another], "What has your Lord said?" They will say, "The truth." And He is the Most High, the Grand.

34:24
፦ ከሰማያትና ከምድር (ዝናምንና በቃይን) የሚሰጣችሁ ማነው? በላቸው፤ አላህ ነው፣ እኛ ወይንም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልፅ መሳሳት ውስጥ ነን በላቸው።

Say, "Who provides for you from the heavens and the earth?" Say, " Allah . And indeed, we or you are either upon guidance or in clear error."

34:25
ከአጠፋነውም ጥፋት አትጠየቁም፤ ከምትሠሩትም ሥራ አንጠየቅም፤ በላቸው።

Say, "You will not be asked about what we committed, and we will not be asked about what you do."

34:26
፦ ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፤ ከዚያም በመካከላችን በውነት ይፈርዳል፤ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው በላቸው።

Say, "Our Lord will bring us together; then He will judge between us in truth. And He is the Knowing Judge."

34:27
እነዚያን ተጋሪዎች አድርጋችሁ በርሱ ያስጠጋችኋቸውን (ጣዖታት) አሳዩኝ፣ ተዉ፣ (አታጋሩ)፤ በውነቱ እርሱ አሸናፊው፣ ብልሃተኛው፣ አላህ ነው፤ በላቸው።

Say, "Show me those whom you have attached to Him as partners. No! Rather, He [alone] is Allah , the Exalted in Might, the Wise."

34:28
አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ፣ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አልላክንህም፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።

And We have not sent you except comprehensively to mankind as a bringer of good tidings and a warner. But most of the people do not know.

34:29
፦እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው? ይላሉ።

And they say, "When is this promise, if you should be truthful?"

34:30
ለናንተ ከርሱ አንዲትንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበት የቀጠሮ ቀን ነው አላችሁ፣ በላቸው።

Say, "For you is the appointment of a Day [when] you will not remain thereafter an hour, nor will you precede [it]."

34:31
እነዚያ የካዱትም በዚህ ቁርአን በዚያ ከበፊቱ ባለውም፣ (መጽሐፍ) በጭራሽ አናምንም አሉ በዳዮችም ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ንግግርን የሚመላለሱ ሆነው በጌታቸው ዘንድ በሚቆሙ ጊዜ ብታይ ኖሮ፤ (አስደናቂን ነገር ታይ ነበር) እነዚያ የተዋረዱት ለነዚያ ለኮሩት፣ እናንተ ባልነበራችሁ ኖሮ አማኞች በሆን ነበር ይላሉ።

And those who disbelieve say, "We will never believe in this Qur'an nor in that before it." But if you could see when the wrongdoers are made to stand before their Lord, refuting each other's words... Those who were oppressed will say to those who were arrogant, "If not for you, we would have been believers."

34:32
እነዚያ የኮሩት ለነዚያ ለተዋረዱት ከትክክለኛው እምነት ከመጣላችሁ በኋላ እኛ ከለከልናችሁን? አይደለም (እናንተው) ከሐዲዎች ነበራችሁ ይሏቸዋል።

Those who were arrogant will say to those who were oppressed, "Did we avert you from guidance after it had come to you? Rather, you were criminals."

34:33
እነዚያ የተዋረዱት ለነዚያ ለኮሩት አይደለም በአላህ እንድንክድና ለርሱ ባላንጣዎችን እንድናደርግ ስታዙን፣ (የከለከለን) የሌሊትና የቀን ዱለታችሁ ነው፣ ይላሉ፤ ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጣሉ፤ በነዚያም በካዱት አንገቶች ላይ እንዛዝሎችን እናደርጋለን፤ ይሠሩት የነበሩትን እንጂ ሌላን ይመነዳሉን?

Those who were oppressed will say to those who were arrogant, "Rather, [it was your] conspiracy of night and day when you were ordering us to disbelieve in Allah and attribute to Him equals." But they will [all] confide regret when they see the punishment; and We will put shackles on the necks of those who disbelieved. Will they be recompensed except for what they used to do?

34:34
በከተማም አስፈራሪን አልላክንም፣ ነዋሪዎችዋ እኛ በዚያ በርሱ በተላካችሁበት ከሐዲዎች ነን ያሉ ቢሆኑ እንጂ።

And We did not send into a city any warner except that its affluent said, "Indeed we, in that with which you were sent, are disbelievers."

34:35
እኛም በገንዘቦችና በልጆች ይበልጥ የበዛን ነን፤ እኛም የምንቀጥጣ አይደለንም አሉ።

And they said, "We are more [than the believers] in wealth and children, and we are not to be punished."

34:36
በላቸው፦ ጌታዬ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።

Say, "Indeed, my Lord extends provision for whom He wills and restricts [it], but most of the people do not know."

34:37
ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ያች እኛ ዘንድ መቅረብን የምታቀርባችሁ አይደለችም፤ ያመነና መልካምን የሠራ ብቻ ሲቀር እነዚያ ለነርሱ በሠሩት መልካም ሥራ እጥፍ ምንዳ አላቸው፤ እነሱም በገነት ሰገነቶች ውስጥ ጸጥተኞች ናቸው።

And it is not your wealth or your children that bring you nearer to Us in position, but it is [by being] one who has believed and done righteousness. For them there will be the double reward for what they did, and they will be in the upper chambers [of Paradise], safe [and secure].

34:38
እነዚያም የሚያቅቱ መስሏቸው አንቀጾቻችንን ለማበላሸት የሚጥሩት እነዚያ በቅጣቱ ውስጥ የሚጣዱ ናቸው።

And the ones who strive against Our verses to cause [them] failure - those will be brought into the punishment [to remain].

34:39
፦ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ለርሱም ያጠባል፤ ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል፤ እርሱም ከሲሳይ ሰጭዎች ሁሉ በላጭ ነው በላቸው።

Say, "Indeed, my Lord extends provision for whom He wills of His servants and restricts [it] for him. But whatever thing you spend [in His cause] - He will compensate it; and He is the best of providers."

34:40
ሁሉንም በሚሰበስባቸውና ከዚያም ለመላእክቶቹ እነዚህ፣ እናንተን ይግገዙ ነበሩን? በሚላቸው ቀን፣ (የሚሆነውን አስታውስ)።

And [mention] the Day when He will gather them all and then say to the angels, "Did these [people] used to worship you?"

34:41
(መላእክቶቹም) ጥራት ይገባህ፣ ከነሱ ሌላ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፤ (እንደሚሉት) አይደለም፣ ይልቁንም ጋኔን ይግገዙ ነበሩ፤ አብዛኞቻቸው በነርሱ አማኞች ናቸው ይላሉ።

They will say, "Exalted are You! You, [O Allah ], are our benefactor not them. Rather, they used to worship the jinn; most of them were believers in them."

34:42
ዛሬም ከፊላችሁ ለከፊሉ መጥቀምን ኾነ መጉዳትን አይችሉም፤ ለነዚያም ለበደሉት፣ ያችን በርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁትን፣ የእሳት ቅጣት፣ ቅመሱ እንላቸዋለን።

But today you do not hold for one another [the power of] benefit or harm, and We will say to those who wronged, "Taste the punishment of the Fire, which you used to deny."

34:43
በነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጽ ሆነው በተነበቡላቸው ጊዜ፣ ይህ አባቶቻችሁ ይግገዙት ከነበሩት ነገር ሊከለክላችሁ የሚፈልግ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም አሉ፤ ይህም (ቁርአን) የተቀጣጠፈ ውሸት ነው፤ እንጂ ሌላ አይደለም አሉ፤ እነዚያም የካዱት እውነቱ በመታላቸው ጊዜ፣ ይህ ግልጥ ድግምት ነው፣ እንጂ ሌላ አይደለም አሉ።

And when our verses are recited to them as clear evidences, they say, "This is not but a man who wishes to avert you from that which your fathers were worshipping." And they say, "This is not except a lie invented." And those who disbelieve say of the truth when it has come to them, "This is not but obvious magic."

34:44
የሚያጠኑዋቸው የሆኑ መጽሐፎችንም ምንም አልሰጠናቸውም፤ ከአንተ በፊትም አስፈራሪ ነቢይን ወደነርሱ አልላክንም።

And We had not given them any scriptures which they could study, and We had not sent to them before you, [O Muhammad], any warner

34:45
እነዚያም ከነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፤ የሰጠናቸውንም ከዐሥር አንዱን (እነዚህ) አልደረሱም፤ መልክተኞቼንም አስተባበሉ፤ (ነቀፍኳቸውም)፤ መንቀፌም እንዴት ነበር!

And those before them denied, and the people of Makkah have not attained a tenth of what We had given them. But the former peoples denied My messengers, so how [terrible] was My reproach.

34:46
የምገሥጻችሁ ባንዲት ነገር ብቻ ነው፤ (እርሷም) ሁለት ሁለት፣ አንድ አንድም፣ ኾናችሁ ለአላህ እንድትነሱ፣ ከዚያም በጓደኛችሁ (በሙሐመድ) ምንም ዕብደት የሌለበት መሆኑን መርምራችሁ እንድትረዱ ነው፤ እርሱ ለናንተ ከብርቱ ቅጣት በስተፊት አስጠንቃቂ ነው እንጂ ሌላ አይደለም፣ በላቸው።

Say, "I only advise you of one [thing] - that you stand for Allah , [seeking truth] in pairs and individually, and then give thought." There is not in your companion any madness. He is only a warner to you before a severe punishment.

34:47
ከዋጋ ማንኛውም የጠየቅኋችሁ ቢኖር እርሱ ለናንተው ነው፤ ዋጋዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነው፣ በላቸው።

Say, "Whatever payment I might have asked of you - it is yours. My payment is only from Allah , and He is, over all things, Witness."

34:48
፦ጌታዬ እውነትን ያወርዳል፤ ሩቅ የኾኑትን ሚስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው በላቸው።

Say, "Indeed, my Lord projects the truth. Knower of the unseen."

34:49
እውነቱ መጣ፤ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ) በላቸው።

Say, "The truth has come, and falsehood can neither begin [anything] nor repeat [it]."

34:50
ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው፤ ብመራም፣ ጌታዬ ወደኔ በሚያወርደው ነው፤ እርሱ ሰሚ ቅርብ ነውና በላቸው።

Say, "If I should err, I would only err against myself. But if I am guided, it is by what my Lord reveals to me. Indeed, He is Hearing and near."

34:51
በደነገጡና ማምለጫ በሌላቸው ጊዜ፣ ከቅርብ ስፍራም በተያዙ ጊዜ (ሁኔታቸውን) ብታይ ኖሮ፣ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)።

And if you could see when they are terrified but there is no escape, and they will be seized from a place nearby.

34:52
በርሱም (አሁን) አመንን ይላሉ፤ ለነርሱም ከሩቅ ስፍራ (እምነትን) በቀላል ማግኘት ከየታቸው?

And they will [then] say, "We believe in it!" But how for them will be the taking [of faith] from a place far away?

34:53
በፊትም በርሱ በርግጥ ክደዋል፣ ከሩቅ ስፍራም በግምት ንግግርን ይጥላሉ።

And they had already disbelieved in it before and would assault the unseen from a place far away.

34:54
ከዚህ ቀደም በመሰሎቻቸው እንደ ተሠራውም ብጤ፣ በነርሱና በሚፈልጉት መካከል ተጋረደ፤ እነርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ነበሩና።

And prevention will be placed between them and what they desire, as was done with their kind before. Indeed, they were in disquieting denial.

Copyright 2013, AmharicQuran.com