Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ሰጅዳህ፣ (የስግደት ምዕራፍ)

32:1
አ. ለ. መ. ( አሊፍ ላም ሚም)።

Alif, Lam, Meem

32:2
የመጽሐፉ መወረድ ጥርጥር የለበትም፤ ከዓለማት ጌታ ነው።

[This is] the revelation of the Book about which there is no doubt from the Lord of the worlds.

32:3
ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? አይደለም፤ እርሱ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት ነው፤ በርሱ ከአንተ በፊት አስፈራሪ (ነቢይ)፤ ያልመጣባቸውን ህዝቦች ልታስፈራራበት (ያወረደልህ ነው)፤ እነርሱ ሊመረምሩ ይከጅላልና።

Or do they say, "He invented it"? Rather, it is the truth from your Lord, [O Muhammad], that you may warn a people to whom no warner has come before you [so] perhaps they will be guided.

32:4
አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ)፤ የተደላደላ ነው፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ ረዳትም አማላጅም ምንም የላችሁም፤ አትገሠጹምን?

It is Allah who created the heavens and the earth and whatever is between them in six days; then He established Himself above the Throne. You have not besides Him any protector or any intercessor; so will you not be reminded?

32:5
ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፤ ከዚያም ከምትቆጥሩት (ዘመን)፣ ልኩ ሺሕ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደርሱ ይወጣል፤ (ይመለሳል)።

He arranges [each] matter from the heaven to the earth; then it will ascend to Him in a Day, the extent of which is a thousand years of those which you count.

32:6
ይህ (ይህንን የሠራው) ሩቅንም ቅርቡንም ሁሉ ዐዋቂዉ፣ አሸናፊው፣ አዛኙ፣ (ጌታ) ነው።

That is the Knower of the unseen and the witnessed, the Exalted in Might, the Merciful,

32:7
ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው፣ የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው፥ ነው።

Who perfected everything which He created and began the creation of man from clay.

32:8
ከዚያም ዘሮቹን፣ ከተጣለለ ከደካማ ውሃ ያደረገ፣ ነው።

Then He made his posterity out of the extract of a liquid disdained

32:9
ከዚያም (ቅረጹን) አስተካከለው፤ በርሱ ውስጥም ከመንፈሱ ነፋበት፣ (ነፋስ ዘራበት)፤ ለናንተም ጆሮዎችን፣ ዓይኖችንና ልቦችንም አደረገላቸው፣ በጣም ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ።

Then He proportioned him and breathed into him from His [created] soul and made for you hearing and vision and hearts; little are you grateful.

32:10
በምድርም ውስጥ (በስብሰን) በጠፋን ጊዜ፣ እኛ በአዲስ መፈጠር ውስጥ እንኾናለን? አሉ በውነቱ ነርሱ በጌታቸው መገናኘት ከሐዲዎች ናቸው።

And they say, "When we are lost within the earth, will we indeed be [recreated] in a new creation?" Rather, they are, in [the matter of] the meeting with their Lord, disbelievers

32:11
፦ በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችሗል፤ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ፣ በላቸው።

Say, "The angel of death will take you who has been entrusted with you. Then to your Lord you will be returned."

32:12
አመጠኞችም በጌታቸው ዘንድ እራሳችውን ያቀረቀሩ ኾነው ፦ጌታችን ሆይ አየን፤ ሰማንም፤ መልካምን እንሰራለንና (ወደ ምድረ ዓለም) መልሰን፤ እኛ አረጋጋጮች ነን፤ ( የሚሉ ሲሆኑ)፤ ብታይ ኖሮ፣ (አስድንጋጪን ነገር ታይ ነበር)

If you could but see when the criminals are hanging their heads before their Lord, [saying], "Our Lord, we have seen and heard, so return us [to the world]; we will work righteousness. Indeed, we are [now] certain."

32:13
በሻንም ኑሮ ነፍስን ሁሉ ቅንነቷን (እምነቷንም) በሰጠናት ነበር፤ ግን ገሀነምን አጋንንትና ከሰዎች የተሰባሰቡ ሆነው በእርግጥ እመላለሁ ማለት ቃሉ ከኔ ተረጋግጧል

And if we had willed, We could have given every soul its guidance, but the word from Me will come into effect [that] "I will surely fill Hell with jinn and people all together

32:14
ይህንንም ቀናችሁንም መገናኘትን በመርሳታችሁ ምክኒያት (ቅጣትን) ቅመሱ! እኛም ተውናችሁ፤ ትሠሩት በነበራችሁትም ጥፋት ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ፣ (ይባላሉ)።

So taste [punishment] because you forgot the meeting of this, your Day; indeed, We have [accordingly] forgotten you. And taste the punishment of eternity for what you used to do."

32:15
አንቀጾቻችን የሚያምኑት እነዚያ በርሷ የተገሰጹት ጊዜ ሰጋጆች ኾነው የሚውድቁትና እነሱም የማይኮሩ ሆነው በጌታቸው ምስጋና (ተጎናጽፈው) የሚያወድሱት ብቻ ናቸው።

Only those believe in Our verses who, when they are reminded by them, fall down in prostration and exalt [ Allah ] with praise of their Lord, and they are not arrogant

32:16
ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ፤ ከሰጠናቸውም (ጸጋ) ይለገሳሉ።

They arise from [their] beds; they supplicate their Lord in fear and aspiration, and from what We have provided them, they spend.

32:17
ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት፣ ከዓይኖች መርጊያ ለነሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።

And no soul knows what has been hidden for them of comfort for eyes as reward for what they used to do

32:18
አማኝ የኾነ ሰው አመጠኛ እንድ ሆነ ሰው ነውን? አይተካከሉም

Then is one who was a believer like one who was defiantly disobedient? They are not equal.

32:19
እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩማ፣ ለነሱ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መስተነግዶ ሲኾኑ መኖሪያ ገነቶች አሏቸው።

As for those who believed and did righteous deeds, for them will be the Gardens of Refuge as accommodation for what they used to do

32:20
እነዚያ ያምመጡትማ፤ መኖሪያቸው እሳት ናት፤ ከርሷ መውጣትን በፈለጉ ቁጥር በርሷ ውስጥ ይመለሳሉ፤ ለነርሱም ያንን በርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ ይባላሉ።

But as for those who defiantly disobeyed, their refuge is the Fire. Every time they wish to emerge from it, they will be returned to it while it is said to them, "Taste the punishment of the Fire which you used to deny."

32:21
ይመለሱ ዘንድም፣ ከትልቁ ቅጣት በፊት (በዚህ ዓለም) ከትንሹ ቅጣት በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን

And we will surely let them taste the nearer punishment short of the greater punishment that perhaps they will repent.

32:22
በጌታቸውም አንቀጾች ከተገሠጸና ከዚያም ከተዋት ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? (የለም)፤ እኛ ከተንኮለኞቹ ተበቃዮች ነን።

And who is more unjust than one who is reminded of the verses of his Lord; then he turns away from them? Indeed We, from the criminals, will take retribution

32:23
ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፤ እርሱን ከመገናኘትም በመጠራጠር ውስጥ አትኹን፤ ለእስራኤል ልጆችም መሪ አደረግነው።

And We certainly gave Moses the Scripture, so do not be in doubt over his meeting. And we made the Torah guidance for the Children of Israel.

32:24
በታገሡና በታምራቶቻችን የሚያረጋግጡ በሆኑም ጊዜ፣ ከነርሱ በትዛዛዛችን በሚመሩ መሪዎች አደረግን።

And We made from among them leaders guiding by Our command when they were patient and [when] they were certain of Our signs.

32:25
ጌታህ እርሱ በዚያ በርሱ ያለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው (በፍርድ) ይለያል፤

Indeed, your Lord will judge between them on the Day of Resurrection concerning that over which they used to differ

32:26
ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመሪያዎቻቸው የሚኼዱ ሲሆኑ ለነርሱ አልተገለጸላችውምን? በዚህ ውስጥ ምልክቶች አሉበት፤ አይሰሙምን?

Has it not become clear to them how many generations We destroyed before them, [as] they walk among their dwellings? Indeed in that are signs; then do they not hear?

32:27
እኛ ውሃን ወደ ደረቅ ምድር የምንነዳ፣ እንሰሶቻቸውና ነፍሶቻቸው ከርሱ የሚበሉትንም አዝመራ በርሱ የምናወጣ መሆናችንን አያዩንም? አይመለከቱንም?

Have they not seen that We drive the water [in clouds] to barren land and bring forth thereby crops from which their livestock eat and [they] themselves? Then do they not see?

32:28
ከውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ፍርድ፣ መቸ ነው? ይላሉ።

And they say, "When will be this conquest, if you should be truthful?"

32:29
በፍርዱ ቀን፣ እነዚያን የካዱት ሰዎች እምነታቸው አይጠቅማቸውም፤ እነሱም ጊዜን አይስጡም፤ በላቸው።

Say, [O Muhammad], "On the Day of Conquest the belief of those who had disbelieved will not benefit them, nor will they be reprieved."

32:30
እነሱንም ተዋቸው፤ ተጠባበቅም ፤ እነሱ ተጠባናቂዎች ናቸውና።

So turn away from them and wait. Indeed, they are waiting

Copyright 2013, AmharicQuran.com