Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ሩም (የሮም ምዕራፍ)

30:1
አ. ለ. መ. (አሊፍ ላም ሚም)።

Alif, Lam, Meem.

30:2
ሩም ተሸነፈች፤

The Byzantines have been defeated

30:3
በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር። እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ።

In the nearest land. But they, after their defeat, will overcome.

30:4
በጥቂት ዓመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)፤ ትእዛዙ በፊትም በኋላም የአላህ ነው። በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ።

Within three to nine years. To Allah belongs the command before and after. And that day the believers will rejoice

30:5
በአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ) የሚሻውን ሰው ይረዳል፥ እርሱም አሸናፊው አዛኙ ነው።

In the victory of Allah . He gives victory to whom He wills, and He is the Exalted in Might, the Merciful.

30:6
አላህ እርዳታን ቀጠረ፤ አላህ ቀጠሮውንም አያፈርስም፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።

[It is] the promise of Allah . Allah does not fail in His promise, but most of the people do not know.

30:7
ከቅርቢቱ ሕይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ፤ እነርሱም ከኋይለኛይቱ ዓለም እነርሱ ዘንጊዎች ናቸው።

They know what is apparent of the worldly life, but they, of the Hereafter, are unaware.

30:8
በነፍሶቻቸው (ሁኔታ) አያስተውሉምን? ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ አላህ በውነትና በተወሰነ ጊዜ እንጂ አልፈጠራቸውም፤ ከሰዎቹም ብዙዎቹ በጌታቸው መገናኘት ከሐዲዎች ናቸው።

Do they not contemplate within themselves? Allah has not created the heavens and the earth and what is between them except in truth and for a specified term. And indeed, many of the people, in [the matter of] the meeting with their Lord, are disbelievers.

30:9
በምድር ላይ አይኼዱምና የነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍጻሜ እንዴት እንደ ነበረ አይመለከቱምን? በኀይል ከነርሱ ይበልጥ የጠነከሩ ነበሩ፤ ምድርንም አረሱ፤ (እነዚህ) ከአለሟትም የበዛ አለሟት፤ መልክተኞቻቸውም በታምራቶች መጡባቸው፤ (አስተባበሉምና ጠፉ)፤ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፤ ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ።

Have they not traveled through the earth and observed how was the end of those before them? They were greater than them in power, and they plowed the earth and built it up more than they have built it up, and their messengers came to them with clear evidences. And Allah would not ever have wronged them, but they were wronging themselves.

30:10
ከዚያም የነዚያ ያጠፉት ሰዎች መጨረሻ፣ በአላህ አንቀጾች በማስተባበላቸውና በርሷ የሚሳለቁ በመሆናቸው ምክንያት መጥፎ ቅጣት ኾነች።

Then the end of those who did evil was the worst [consequence] because they denied the signs of Allah and used to ridicule them.

30:11
አላህ መፍጠርን ይጀምራል፤ ከዚያም ይመልሰዋል፤ ከዚያም ወደርሱ ትመለሳላችሁ።

Allah begins creation; then He will repeat it; then to Him you will be returned.

30:12
ሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን አመጠኞች ጭጭ ይላሉ።

And the Day the Hour appears the criminals will be in despair.

30:13
ለነርሱም ከሚያጋሩዋቸው (ጣዖታት) አማላጆች አይኖሩዋቸውም፤ በሚያጋሩዋቸውም ፣ (ጣዖታት) ከሐዲዎች ይሆናሉ።

And there will not be for them among their [alleged] partners any intercessors, and they will [then] be disbelievers in their partners.

30:14
ሰዓቲቱ በምትቆምበት ቀንም በዚያ ቀን ይለያያሉ።

And the Day the Hour appears - that Day they will become separated.

30:15
እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን ሥራዎች የሠሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ።

And as for those who had believed and done righteous deeds, they will be in a garden [of Paradise], delighted.

30:16
እነዚያማ የካዱትማ በአንቀጾቻችንና በኋለኛይቱም ዓለም መገናኘት ያስተባባሉት እነዚያ በቅጣቱ ውስጥ የሚጣዱ ናቸው።

But as for those who disbelieved and denied Our verses and the meeting of the Hereafter, those will be brought into the punishment [to remain].

30:17
አላህንም፣ በምታመሹ ጊዜ፣ በምታነጉም ጊዜ፣ አጥሩት፤ (ስገዱለት)።

So exalted is Allah when you reach the evening and when you reach the morning.

30:18
ምስጋናም በስማያትና በምድር ውስጥ ለርሱ ብቻ (የተገባው) ነው። በሠርክም (1) በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ፤ (አጥሩት)።

And to Him is [due all] praise throughout the heavens and the earth. And [exalted is He] at night and when you are at noon.

30:19
ሕያውን ከሙት ያወጣል፤ ሙትንም ከሕያው ያወጣል፤ ምድርንም ከሞተች በኋላ ሕያው ያደርጋታል፤ እንደዚሁም (ከመቃብር) ትወጥጣላችሁ።

He brings the living out of the dead and brings the dead out of the living and brings to life the earth after its lifelessness. And thus will you be brought out.

30:20
እናንተንም ከዐፈር መፍጠሩ፥ ከዚያም እናንተ ወዲያውኑ የምትበታተኑ ሰዎች መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው።

And of His signs is that He created you from dust; then, suddenly you were human beings dispersing [throughout the earth].

30:21
ለናንተም፣ ከነፍሶቻችሁ (ከጐሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስውሉ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ።

And of His signs is that He created for you from yourselves mates that you may find tranquillity in them; and He placed between you affection and mercy. Indeed in that are signs for a people who give thought.

30:22
ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፥ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ታምራቶች አሉበት።

And of His signs is the creation of the heavens and the earth and the diversity of your languages and your colors. Indeed in that are signs for those of knowledge.

30:23
በሌሊትና በቀንም መተኛታችሁ፥ ከችሮታውም መፈለጋችሁ ከምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች ታምራቶች አሉበት።

And of His signs is your sleep by night and day and your seeking of His bounty. Indeed in that are signs for a people who listen.

30:24
ብልጭታንም ፈሪዎችና ከጃዮች ስትሆኑ ለናንተ ማሳየቱ ከሰማይም ውሃን ማውረዱ በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ማድረጉ፣ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች ታምራቶች አሉበት።

And of His signs is [that] He shows you the lightening [causing] fear and aspiration, and He sends down rain from the sky by which He brings to life the earth after its lifelessness. Indeed in that are signs for a people who use reason.

30:25
ሰማያትና ምድርም (ያለ ምሶሶ) በት እዛዙ መቆማቸው ከዚያም (መልአኩ ለትንሣኤ) ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መኾናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው።

And of His signs is that the heaven and earth remain by His command. Then when He calls you with a [single] call from the earth, immediately you will come forth.

30:26
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፤ ሁሉም ለርሱ ታዛዦች ናቸው።

And to Him belongs whoever is in the heavens and earth. All are to Him devoutly obedient.

30:27
እርሱም፤ ያ መፍጠርን የሚጀምር፥ ከዚያም የሚመልሰው ነው፤ እርሱም (መመለሱ) በርሱ ላይ በጣም ገር ነው፤ ለርሱም በሰማያትም በምድርም ከፍተኛ ባሕርይ (አንድነትና ለርሱ ብጤ የሌለው መሆን) አልለው፤ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።

And it is He who begins creation; then He repeats it, and that is [even] easier for Him. To Him belongs the highest attribute in the heavens and earth. And He is the Exalted in Might, the Wise.

30:28
ለናንተ ከነፍሶቻችሁ የኾነን ምሳሌ አደርገላችሁ፤ (እርሱም) እጆቻችሁ ከያዙዋቸው (ባሮች) ውስጥ በሰጠናችሁ ጸጋ ለናንተ ተጋሪዎች አሏችሁን? ታዲያ እናንተና እነርሱ በርሱ ትክክል ናችሁን? ነፍቻችሁን (ብጤዎቻችሁን) እንድምትፈሩ ትፈሩዋችዋላችሁን? እንደዚሁ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች፤ አንቀጾችን እንገልጻለን።

He presents to you an example from yourselves. Do you have among those whom your right hands possess any partners in what We have provided for you so that you are equal therein [and] would fear them as your fear of one another [within a partnership]? Thus do We detail the verses for a people who use reason.

30:29
ይልቁንም እነዚያ የበደሉ ስዎች ያለ ዕውቀት ዝንባሌዎቻቸውን ተከተሉ፤ አላህም ያጠመመውን ሰው የሚያቀናው ማነው? ለነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸውም።

But those who wrong follow their [own] desires without knowledge. Then who can guide one whom Allah has sent astray? And for them there are no helpers.

30:30
ወደ እውነት ተዘንባይ ሆነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፤ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በርስዋ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዙዋት)፤ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፤ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።

So direct your face toward the religion, inclining to truth. [Adhere to] the fitrah of Allah upon which He has created [all] people. No change should there be in the creation of Allah . That is the correct religion, but most of the people do not know.

30:31
ወደርሱ ተመላሾች ሆናችሁ፣ (የአላህን ሃይማኖት ያዙ)፤ ፍሩትም፤ ሶላትም አስተካክላችሁ ስገዱ፤ ከአጋሪዎቹም አትሁኑ።

[Adhere to it], turning in repentance to Him, and fear Him and establish prayer and do not be of those who associate others with Allah

30:32
ከነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩትና ክፍልፍሎችም ከኾኑት፥ (አትኹኑ)፤ ሕዝብ ሁሉ እነሱ ዘንድ ባለው ነገር ተደሳቾች ናቸው።

[Or] of those who have divided their religion and become sects, every faction rejoicing in what it has.

30:33
ሰዎችንም ችግር ባገኛቸው ጊዜ፥ ጌታቸውን ወደርሱ ተመላሾች ኾነው ይጠሩታል፤ ከዚያም ከርሱ ችሮታን ባቀመሳቸው ጊዜ፥ ከነሱ ከፊሎቹ ወዲያውኑ በጌታቸው፥ (ጣዖትን) ያጋራሉ፤

And when adversity touches the people, they call upon their Lord, turning in repentance to Him. Then when He lets them taste mercy from Him, at once a party of them associate others with their Lord,

30:34
በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱ (ያጋራሉ)፤ ተጣቀሙም፤ በእርግጥም (መጨረሻችሁን)፥ ወደፊት ታውቃላችሁ።

So that they will deny what We have granted them. Then enjoy yourselves, for you are going to know.

30:35
በነሱ ላይ አስረጅን አወረድን? ታዲያ እርሱ በዚያ በርሱ ያጋሩ በነበሩት ነገር ይናገራልን? (የለም)።

Or have We sent down to them an authority, and it speaks of what they were associating with Him?

30:36
ሰዎችንም ችሮታን ባቀመስናቸው ጊዜ፣ በርሷ ይደሰታሉ፤ እጆቻቸውም ባሳለፉት ምክንያት መከራ ብታገኛቸው፥ ወዲያውኑ እነርሱ ተስፋ ይቆርጣሉ።

And when We let the people taste mercy, they rejoice therein, but if evil afflicts them for what their hands have put forth, immediately they despair.

30:37
አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን የሚያሰፋ፥ የሚያጠብም መሆኑን አያዩምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስደናቂ ምልክቶች አሉበት።

Do they not see that Allah extends provision for whom He wills and restricts [it]? Indeed, in that are signs for a people who believe.

30:38
የዝምድናን ባለቤት ተገቢውን ስጠው፤ ለድኻም፣ ለመንገደኛም፥ (እርዳ)፤ ይህ፣ ለነዚያ የአላህን ፊት፣ (ውዴታውን) ለሚሹ መልካም ነው፤ እነዚያም እነሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው።

So give the relative his right, as well as the needy and the traveler. That is best for those who desire the countenance of Allah , and it is they who will be the successful

30:39
ከበረከትም በሰዎች ገንዘቦች ውስጥ ይጨመር ዘንድ (1) የምትሰጡት አላህ ዘንድ አይጨምርም፤ ከምጽዋትም የአላህን ፊት የምትሹ ሆናችሁ የምትሰጡት፥ እነዚያ (ሰጪዎች) አበርካቾች እነሱ ናቸው።

And whatever you give for interest to increase within the wealth of people will not increase with Allah . But what you give in zakah, desiring the countenance of Allah - those are the multipliers.

30:40
አላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም የሚያሞታችሁ፥ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ነው፤ ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ውስጥ ከዚኻችሁ አንዳችን የሚሠራ አልለን? ለአላህ ጥራት ይገባው፤ (በርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ።

Allah is the one who created you, then provided for you, then will cause you to die, and then will give you life. Are there any of your "partners" who does anything of that? Exalted is He and high above what they associate with Him.

30:41
የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢአት ምክንያት፣ የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀመሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ)፤ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና።

Corruption has appeared throughout the land and sea by [reason of] what the hands of people have earned so He may let them taste part of [the consequence of] what they have done that perhaps they will return [to righteousness].

30:42
፦ በምድር ላይ ኺዱ፣ የነዚያንም በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ በላቸው፤ አብዛኞቻቸው አጋሪዎች ነበሩ።

Say, [O Muhammad], "Travel through the land and observe how was the end of those before. Most of them were associators [of others with Allah ].

30:43
ለርሱ መመለስ የሌለው ቀን (የትንሣኤ ቀን)፥ ከአላህ ሳይመጣ በፊት፣ ፊትህን ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፤ በዚያ ቀን (ወደ ገነትና ወደ እሳት) ይለያያሉ፤

So direct your face toward the correct religion before a Day comes from Allah of which there is no repelling. That Day, they will be divided.

30:44
የካደ ሰው ክሕደቱ (ጠንቁ) በርሱው ላይ ነው፤ መልካምም የሠሩ ለነፍሶቻቸው (ማረፊያዎችን) ያዘጋጃሉ።

Whoever disbelieves - upon him is [the consequence of] his disbelief. And whoever does righteousness - they are for themselves preparing,

30:45
እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ከችሮታው ይመነዳ ዘንድ፤ (ይለያያሉ)፤ እርሱ ከሐዲዎችን አይወድምና።

That He may reward those who have believed and done righteous deeds out of His bounty. Indeed, He does not like the disbelievers.

30:46
እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ከችሮታው ይመነዳ ዘንድ፤ (ይለያያሉ)፤ እርሱ ከሐዲዎችን አይወድምና።

That He may reward those who have believed and done righteous deeds out of His bounty. Indeed, He does not like the disbelievers.

30:47
ከአንተ በፊትም መልክተኞችን ወደየ ሕዝቦቻቸው በእርግጥም ላክን፤ በግልጽ ማስረጃዎችም መጡባቸው፤ ከነዚያ ካምመጡትም ተበቀልን፤ ምእምኖቹንም መርዳት በኛ ላይ ተገቢ ኾነ።

And We have already sent messengers before you to their peoples, and they came to them with clear evidences; then We took retribution from those who committed crimes, and incumbent upon Us was support of the believers.

30:48
አላህ ያ ነፋሶችን የሚልክ ነው፤ ደመናንም ይቀሰቅሳሉ፤ በሰማይ ላይም እንደሚሻ ይዘረጋዋል፤ ቁርጥራጮችም ያደርገዋል፤ ዝናሙንም ከደመናው መካካል ሲወጣ ታያለህ፤ በርሱም ከባሮቹ የሚሻውን በለየ ጊዜ ወዲያውኑ እነሱ ይደሰታሉ።

It is Allah who sends the winds, and they stir the clouds and spread them in the sky however He wills, and He makes them fragments so you see the rain emerge from within them. And when He causes it to fall upon whom He wills of His servants, immediately they rejoice

30:49
በነሱ ላይ ከመውረዱ በፊት ከርሱ በፊት በእርግጥ ተስፋ ቆራጮች ነበሩ።

Although they were, before it was sent down upon them - before that, in despair.

30:50
ምድርንም ከሞተች በኋላ እንዴት ሕያው እንደሚያደርጋት ወደ አላህ ፈለጎች ተመልከት፤ ይህ (አድራጊ) ሙታንንም በእርግጥ ሕያው አድራጊ ነው፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

So observe the effects of the mercy of Allah - how He gives life to the earth after its lifelessness. Indeed, that [same one] will give life to the dead, and He is over all things competent

30:51
ነፋስንም (በአዝመራዎች ላይ) ብንልክና ገርጥቶ ቢያዩት ከርሱ በኋላ በርግጥ (ችሮታውን) የሚክዱ ይኾናሉ።

But if We should send a [bad] wind and they saw [their crops] turned yellow, they would remain thereafter disbelievers.

30:52
አንተም ሙታንን አታሰማም፤ ደንቆሮዎችንም ዟሪዎች ሆነው በሸሹ ጊዜ ጥርሪን አታሰማም።

So indeed, you will not make the dead hear, nor will you make the deaf hear the call when they turn their backs, retreating.

30:53
አንተ ዕውሮችንም ከጥመታቸው የሚታቀና አይደለህም፤ በአንቀጾቻችን የሚያምኑትን ሰዎች እንጂ ሌላን አታሰማም፤ እነሱም ታዛዦች ናቸው።

And you cannot guide the blind away from their error. You will only make hear those who believe in Our verses so they are Muslims [in submission to Allah ].

30:54
አላህ ያ ከደካማ (ፍትወት ጠብታ) የፈጠራችሁ ነው፤ ከዚያም ከደካማነት በኋላ ኅይልን አደረገ፤ ከዚያም ከብርቱነት በኋላ ደካማነትንና ሺበትን አደረገ፤ የሚሻውን ይፈጥራል፤ እርሱም ዐዋቂው ቻዩ ነው።

Allah is the one who created you from weakness, then made after weakness strength, then made after strength weakness and white hair. He creates what He wills, and He is the Knowing, the Competent.

30:55
ሰዓቲቱም በምትሆንበት ቀን፣ ከሐዲዎች ከአንዲት ሰዓት በስተቀር (በመቃብር) አልቆየንም ብለው ይምላሉ፤ እንደዚሁ (ከውነት) ይመለሱ ነበሩ።

And the Day the Hour appears the criminals will swear they had remained but an hour. Thus they were deluded.

30:56
እነዚያም ዕውቀትንና እምነትን የተሰጡት፥ በአላህ መጽሐፍ (ፍርድ) እስከ ትንሣኤ ቀን በእርግጥ ቆያችሁ፤ ይህም (የካዳችሁት)፣ የትንሣኤ ቀን ነው፤ ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ ይሏቸዋል።

But those who were given knowledge and faith will say, "You remained the extent of Allah 's decree until the Day of Resurrection, and this is the Day of Resurrection, but you did not used to know."

30:57
በዚያም ቀን፣ እነዚያን የበደሉትን ማመካኘታቸው አይጠቅማቸውም። እነሱም በወቀሳ አይታለፉም፤

So that Day, their excuse will not benefit those who wronged, nor will they be asked to appease [ Allah ].

30:58
በዚህም ቁርአን ውስጥ ከምሳሌ ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ ገለጽን፤ በታምርም ብትመጣባቸው እነዚያ የካዱት ሰዎች እናንተ አበላሺዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም ይላሉ፤

And We have certainly presented to the people in this Qur'an from every [kind of] example. But, [O Muhammad], if you should bring them a sign, the disbelievers will surely say, "You [believers] are but falsifiers."

30:59
እንደዚሁ፣ አላህ በነዚያ በማያውቁት ሰዎች ልቦች ላይ ያትማል።

Thus does Allah seal the hearts of those who do not know.

30:60
ስለዚህ ታገሥ፤ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፤ እነዚያም በትንሣኤ የማያረጋግጡ አያቅልሉህ። (1)

So be patient. Indeed, the promise of Allah is truth. And let them not disquiet you who are not certain [in faith].

Copyright 2013, AmharicQuran.com