Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አሊ-ዒምራን (የዒምራን ቤተሰብ ምዕራፍ)

3:1
አ.ለ.መ.*** (አሊፍ ላም ሚም)
(*** በዚህና በመሰሉ ትርጉምብዙዎቹ ሊቃውንት ፍችውን ከአላህ በቀር የሚያውቀው የለም ይላሉ፤ እኔ አላህ ነኝ ዐውቃለሁ ማለት ነው የሚሉም አልሉ፤ ከዚህም ሌላ ነብዩ ሙሐመድ ቁር አኑን ሲያነቡ ዐረቦች እየተሰበሰቡ ድግምት ነው ይስባችኋል አታዳምጡት እያሉ ይጮኹ ስለ ነበር በነሱ ዘንድ ያልታወቀ አነጋገር ምህጻረ ቃላት አውርዶ ዝም ለማሰኘት ነው የሚሉም ብዙዎች ናቸው።)


Alif, Lam, Meem.

3:2
አላህ ከሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም (እሱ) ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነዉ።

Allah - there is no deity except Him, the Ever-Living, the Sustainer of existence.

3:3
ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን መጽሐፉን (ቁርአንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በዉነት አወረደ። ተዉራትንና ኢንጅልንም *** አውርዷል።
*** ኦሪትንና ወንጌልን


He has sent down upon you, [O Muhammad], the Book in truth, confirming what was before it. And He revealed the Torah and the Gospel.

3:4
(ከቁርአን) በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ (አወረዳቸዉ)፤ ፉርቃንንም አወረደ እነዚያ በአላህ ታዓምራቶች የካዱ ለነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸዉ፤ አላህም አሸናፊ የመበቀል ባለቤት ነዉ::

Before, as guidance for the people. And He revealed the Qur'an. Indeed, those who disbelieve in the verses of Allah will have a severe punishment, and Allah is exalted in Might, the Owner of Retribution

3:5
አላህ በምድርም በሰማይም ምንም ነገር በርሱ ላይ አይሰወርም።

Indeed, from Allah nothing is hidden in the earth nor in the heaven.

3:6
እርሱ ያ በማሕፀኖች ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነዉ። ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አሸናፊዉ ጥበበኛዉ ነዉ።

It is He who forms you in the wombs however He wills. There is no deity except Him, the Exalted in Might, the Wise.

3:7
እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነዉ፤ ከርሱ (ከመጽሐፉ) ግልጽ የሆኑ አንቀጾች አሉ፤ እነሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸዉ፤ ሌሎቹም ተመሳሳዮች አሉ፤ እነዚያማ በልቦቻቸዉ ዉሰጥ ጥመት ያለባቸዉ ሰዎች፣ ማሳሳትን ለመፈለግና ትችቱን ለመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለዉን ይከታተላሉ። (ትክክለኛ) ትችቱንም አላህ ብቻ እንጅ ሌላ አያወቀውም በዕውቀትም የጠለቁት በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነዉ ይላሉ። የአእምሮ ባለበቶችም እንጂ (ሌላዉ) አይገሠጽም።

It is He who has sent down to you, [O Muhammad], the Book; in it are verses [that are] precise - they are the foundation of the Book - and others unspecific. As for those in whose hearts is deviation [from truth], they will follow that of it which is unspecific, seeking discord and seeking an interpretation [suitable to them]. And no one knows its [true] interpretation except Allah . But those firm in knowledge say, "We believe in it. All [of it] is from our Lord." And no one will be reminded except those of understanding.

3:8
(እነሱም ይላሉ) ፦ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን፤ ከአንተ ዘንድ የሆነን ችሮታም ለኛ ስጠን፤ አንተ በጣም ለጋስ ነህና።

[Who say], "Our Lord, let not our hearts deviate after You have guided us and grant us from Yourself mercy. Indeed, You are the Bestower.

3:9
ጌታችን ሆይ! አንተ (ለመምጣቱ) በርሱ ጥርጥር የሌለበት በሆነ ቀን ሰዉን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ ምንጊዜም አላህ ቀጠሮን አያፈርስምና።

Our Lord, surely You will gather the people for a Day about which there is no doubt. Indeed, Allah does not fail in His promise."

3:10
እነዚያ የካዱትን ሰዎች ገንዘቦቻቸዉንና ልጆቻቸዉ ከአላህ (ቅጣት) ምንም አያስጥሉዋቸዉም፤ እነዚያም እነርሱ የእሳት ማገዶዎች ናቸዉ

Indeed, those who disbelieve - never will their wealth or their children avail them against Allah at all. And it is they who are fuel for the Fire.

3:11
(ልማዳቸዉ ሁሉ)፣ እንደ ፈርዖን ቤተሰብና እንደነዚያ ከበፊታቸዉ እንደነበሩት ሕዝቦች ልማድ ነዉ፤ በአንቀጾቻችን አስተባበሉ፤ አላህም በኃጢአቶቻቸዉ ያዛቸዉ አላህም ቅጣተ ብርቱ ነዉ።

[Theirs is] like the custom of the people of Pharaoh and those before them. They denied Our signs, so Allah seized them for their sins. And Allah is severe in penalty.

3:12
ለነዚያ ለካዱት ሰዎች በላቸዉ፦ በቅርብ ጊዜ ትሸነፋላችሁ፤ ወደ ገሀነምም ትሰበሰባላችሁ፤ ምንጣፊቱም ምን ትከፋ!

Say to those who disbelieve, "You will be overcome and gathered together to Hell, and wretched is the resting place."

3:13
(የበድር ቀን) በተጋጠሙት ሁለት ጭፍሮች ለናንተ በእርግጥ ተአምር አለ፤ አንደኛዋ ጭፍራ በአላህ መንገድ ትጋደላለች፤ ሌላይቱም ከሐዲ ናት ከሓዲዎቹ (አማኞቹን) በዓይን አስተያየት እጥፋቸዉን ሆነው ያዩዋቸዋል፤ አላህም በርዳታዉ የሚሻዉን ሰዉ ያበረታል፤ በዚህ ውስጥ ለማስተዋል ባለቤቶች በእርግጥ መገሠጫ አለበት::

Already there has been for you a sign in the two armies which met - one fighting in the cause of Allah and another of disbelievers. They saw them [to be] twice their [own] number by [their] eyesight. But Allah supports with His victory whom He wills. Indeed in that is a lesson for those of vision.

3:14
ከሴቶች, ከወንዶች ልጆችም ከወርቅና ከብር ከተከማቹ ገንዘቦችም, ከተሰማሩ ፈረሶችም, ከግመል ከከብትና ከፍየልም, ከአዝመራም የሆኑ ፍላጐቶችን መዉደድ ለሰዎች ተሸለመ፤ ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነዉ፤ አላህም አርሱ ዘንድ መልካም መመለሻ (ገነት) አለ::

Beautified for people is the love of that which they desire - of women and sons, heaped-up sums of gold and silver, fine branded horses, and cattle and tilled land. That is the enjoyment of worldly life, but Allah has with Him the best return.

3:15
ከዚኻቺሁ የሚበልጥን ልንገራችሁን? በላቸዉ- (እርሱም) ለነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸዉ ዘንድ በሥራቸዉ ወንዞች የሚፈሱባቸዉ ገነቶች በዉስጧ ሁል ጊዜ ነዋሪዎች ሲሆኑ፣ ንጹሕ የተደረጉ ሚስቶችም ከአላህም የሆነ ዉዴታ አላቸዉ፤ አላህም ባሮችን ተመልካች ነዉ::

Say, "Shall I inform you of [something] better than that? For those who fear Allah will be gardens in the presence of their Lord beneath which rivers flow, wherein they abide eternally, and purified spouses and approval from Allah . And Allah is Seeing of [His] servants -

3:16
(እነርሱም) እነዚያ- ጌታችን ሆይ! እኛ አመንን፤ ኀጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን። የሚሉ ናቸዉ።

Those who say, "Our Lord, indeed we have believed, so forgive us our sins and protect us from the punishment of the Fire,"

3:17
ታጋሾች፣ እውነተኞችም፣ ታዛዦችም፣ ለጋሶችና በሌሊት መጨረሻዎች ምሕረትን ለማኞች ናቸዉ።

The patient, the true, the obedient, those who spend [in the way of Allah ], and those who seek forgiveness before dawn.

3:18
አላህ, በማስተካከል የቆመ (አሰተናባሪ) ሲሆን፣ ከእርሱ በሰተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መሆኑን መሰከረ፤ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ) ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም:: አሸናፊዉ ጥበበኛ ነዉ::

Allah witnesses that there is no deity except Him, and [so do] the angels and those of knowledge - [that He is] maintaining [creation] in justice. There is no deity except Him, the Exalted in Might, the Wise.

3:19
አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነዉ፣ እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች በመካከላቸዉ ላለዉ ምቀኝነት እዉቀቱ ከመጣላቸዉ በኋላ እንጅ አልተለያዩም፤ በአላህም አንቀጾች የሚክድ አላህ ምርመራዉ ፈጣን ነዉ::

Indeed, the religion in the sight of Allah is Islam. And those who were given the Scripture did not differ except after knowledge had come to them - out of jealous animosity between themselves. And whoever disbelieves in the verses of Allah , then indeed, Allah is swift in [taking] account.

3:20
ቢከራከሩህም :- ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች (እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ) በላቸዉ፤ ለእነዚያም መጽሐፍን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሀይሞቹ፦ሰለችማሁን? በላቸዉ፤ ቢሰልሙም በእርገጥ ተመሩ እምቢ ቢሉም በአንተ ላይ ያለበህ ማድረስ ብቻ ነዉ:: አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው::

So if they argue with you, say, "I have submitted myself to Allah [in Islam], and [so have] those who follow me." And say to those who were given the Scripture and [to] the unlearned, "Have you submitted yourselves?" And if they submit [in Islam], they are rightly guided; but if they turn away - then upon you is only the [duty of] notification. And Allah is Seeing of [His] servants.

3:21
እነዚያ በአላህ አንቀጾች የሚክዱ፣ ነቢያትንም ያለ አግባብ የሚገድሉ፣ ከሰዎችም ዉስጥ እነዚያን በትክክለኛነት የሚያዙትን የሚገድሉ፣ በአሰማሚ ቅጣት አብስራቸዉ

Those who disbelieve in the signs of Allah and kill the prophets without right and kill those who order justice from among the people - give them tidings of a painful punishment.

3:22
እነዚያ፣ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ሥራዎቻቸዉ የተበላሹ ናቸዉ፤ ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም።

They are the ones whose deeds have become worthless in this world and the Hereafter, and for them there will be no helpers.

3:23
ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ (ትምህርት) ዕድልን ወደ ተሰጡት ሰዎች አላየህምን? ወደ አላህ መጽሐፍ በመካከላቸዉ ይፈርዱ ዘንድ ይጠራሉ፤ ከዚያም ከነሱ ገሚሶቹ እነርሱ (እውነቱን) የተው ሆነዉ ይሸሻሉ።

Do you not consider, [O Muhammad], those who were given a portion of the Scripture? They are invited to the Scripture of Allah that it should arbitrate between them; then a party of them turns away, and they are refusing.

3:24
ይኽ እነርሱ እሳት የተቆጠሩ ቀኖችን እንጅ አትነካንም በማለታቸዉ ነዉ። በሃይማኖታቸዉም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር አታለላቸዉ።

That is because they say, "Never will the Fire touch us except for [a few] numbered days," and [because] they were deluded in their religion by what they were inventing.

3:25
በርሱ (መምጣት) ጥርጥር የሌለበት በሆነዉ ቀን በሰበሰብናቸዉና ነፍስ ሁሉ የሠራችዉን ሥራ በተሞላች ጊዜ እንዴት ይሆናሉ? እነርሱም አይበደሉም።

So how will it be when We assemble them for a Day about which there is no doubt? And each soul will be compensated [in full for] what it earned, and they will not be wronged.

3:26
(ሙሐመድ ሆይ!) በል- የንግሥና ባለቤት የሆንክ አላህ ሆይ! ለምትሻዉ ሰዉ ንግሥናን ትሰጣለህ፤ ከምትሻዉም ሰዉ ንግስናን ትገፍፋለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታልቃለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታዋርዳለህ። መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና።

Say, "O Allah , Owner of Sovereignty, You give sovereignty to whom You will and You take sovereignty away from whom You will. You honor whom You will and You humble whom You will. In Your hand is [all] good. Indeed, You are over all things competent.

3:27
ለሊቱን በቀን ዉስጥ ታስገባለህ፤ ቀኑንም በሌሊቱ ዉስጥ ታስገባለህ፤ ሕያዉንም ከሙት ዉስጥ ታወጣለህ፤ ሙትንም ከሕያዉ ዉስጥ ታወጣለህ፣ ለምትሻዉም ሰዉ ያለግምት ትሰጣለህ።

You cause the night to enter the day, and You cause the day to enter the night; and You bring the living out of the dead, and You bring the dead out of the living. And You give provision to whom You will without account."

3:28
ምእምናን ከሐዲዎችን ከምእምናን ሌላ ረዳቶች አድርገዉ አይያዙ፤ ይኽንንም የሚሠራ ሰዉ ከአላህ (ሃይማኖት) በምንም ዉስጥ አይደለም፤ ከነርሱ መጠበቅን ብትጠብቁ እንጂ፤ አላህም ነፍሱን (ቁጣዉን) ያሰጠነቅቃችኋል። መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነዉ።

Let not believers take disbelievers as allies rather than believers. And whoever [of you] does that has nothing with Allah , except when taking precaution against them in prudence. And Allah warns you of Himself, and to Allah is the [final] destination.

3:29
በደረቶቻችሁ ዉሰጥ ያለዉን ነገር ብትደብቁ ወይም ብትገልጹት አላህ ያውቀዋል፤ በሰማያት ያለዉንና በምድርም ያለዉን ሁሉ ያዉቃል። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነዉ (በል)።

Say, "Whether you conceal what is in your breasts or reveal it, Allah knows it. And He knows that which is in the heavens and that which is on the earth. And Allah is over all things competent.

3:30
ነፍስ ሁሉ ከመልካም ነገር የሠራችዉን የቀረበ ሆኖ የምታገኝበትን ቀን (አስታውስ) ከመጥፎም የሠራችዉ በርስዋና በርሱ (በኀጢአትዋ) መካከል በጣም የሰፋ ርቀት ቢኖር ትመኛለች፤ አላህ ነፍሱን ያስጠነቅቃችኋል። አላህም ለባሮቹ ሩኅሩህ ነዉ።

The Day every soul will find what it has done of good present [before it] and what it has done of evil, it will wish that between itself and that [evil] was a great distance. And Allah warns you of Himself, and Allah is Kind to [His] servants."

3:31
በላቸዉ- አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ፣ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኅጢአቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነዉ።

Say, [O Muhammad], "If you should love Allah , then follow me, [so] Allah will love you and forgive you your sins. And Allah is Forgiving and Merciful."

3:32
አላህንና መልክተኛዉን ታዘዙ ብትሸሹም አላህ ከሐዲዎችን አይወድም በላቸዉ።

Say, "Obey Allah and the Messenger." But if they turn away - then indeed, Allah does not like the disbelievers.

3:33
አላህ አደምን፣ ኑሕንም፣ የኢብራሂምንም ቤተሰብ የኢምራንንም ቤተሰብ፣ በዓለማት ላይ መረጠ።

Indeed, Allah chose Adam and Noah and the family of Abraham and the family of 'Imran over the worlds -

3:34
ከፊልዋ ከከፊሉ የሆነች ዝርያ አድርጐ፣ (መረጣት)፤ አላህም ሰሚ ዓዋቂ ነዉ።

Descendants, some of them from others. And Allah is Hearing and Knowing.

3:35
የዒምራን ባለቤት (ሐና)- ጌታዬ ሆይ! እኔ በሆዴ ዉስጥ ያለዉን (ፅንስ ከሥራ) ነጻ የተደረገ ሲሆን ለአንተ ተሳልኩ፤ ከኔም ተቀበል፤ አንተ ሰሚዉ አዋቂዉ ነህና ባለች ጊዜ (አስታውስ)

[Mention, O Muhammad], when the wife of 'Imran said, "My Lord, indeed I have pledged to You what is in my womb, consecrated [for Your service], so accept this from me. Indeed, You are the Hearing, the Knowing."

3:36
በወለደቻትም ጊዜ- ጌታዬ ሆይ እኔ ሴት ሆና ወለድኋት፤ አላህም የወለደችዉን ዐዋቂ ነዉ፤ ወንድም እንደ ሴት አይደለም፤ እኔም መርየም ብዬ ስም አወጣሁላት፣ እኔም እስዋንም ዘርያዋንምን ከተረገመዉ ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ አለች።

But when she delivered her, she said, "My Lord, I have delivered a female." And Allah was most knowing of what she delivered, "And the male is not like the female. And I have named her Mary, and I seek refuge for her in You and [for] her descendants from Satan, the expelled [from the mercy of Allah ]."

3:37
ጌታዋም በደህና አቀባበል ተቀበላት፤ በመልካም አስተዳደግም አፋፋት፤ ዘከሪያም ** አሳደጋት ዘከሪያ በርሷ ላይ በምኲራቧ *** በገባ ቊጥር እርስዋ ዘንድ ሲሳይን አገኘ፤ -- መርየም ሆይ ይህ ለአንቺ ከየት ነዉ? አላት፤ --እርሱ ከአላህ ዘንድ ነዉ፤ አላህ ለሚሻዉ ሰዉ ሲሳዩን ያለድካም ይሰጣል አላችዉ።
**ዘካሪያስ *** በመፀለያ ስፍራዋ


So her Lord accepted her with good acceptance and caused her to grow in a good manner and put her in the care of Zechariah. Every time Zechariah entered upon her in the prayer chamber, he found with her provision. He said, "O Mary, from where is this [coming] to you?" She said, "It is from Allah . Indeed, Allah provides for whom He wills without account."

3:38
እዚያ ዘንድ ዘከርያ ጌታዉን ለመነ- ጌታዬ ሆይ ከአንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለኔ ስጠኝ፤ አንተ ጸሎትን ሰሚ ነህና አለ።

At that, Zechariah called upon his Lord, saying, "My Lord, grant me from Yourself a good offspring. Indeed, You are the Hearer of supplication."

3:39
እርሱም በጸሎት ማድረሻዉ ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት ጠራችዉ።** አላህ በየሕያ*** ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም፣ ከደጋጐቹ ነቢይም ሲሆን ያበስርሃል፤ በማለት፥ (መላእክት ጠራችዉ)
** ጂብሪል ጠራው *** በዮሐንስ (መጥምቁ)


So the angels called him while he was standing in prayer in the chamber, "Indeed, Allah gives you good tidings of John, confirming a word from Allah and [who will be] honorable, abstaining [from women], and a prophet from among the righteous."

3:40
- ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና በእርግጥ የደረሰብኝ ስትሆን ባልተቤቴም መካን ስትሆን፥ ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለ (መልአኩም) እንደዚሁ አላህ የሚሻዉን ነገር ይሠራል አለዉ፤

He said, "My Lord, how will I have a boy when I have reached old age and my wife is barren?" The angel said, "Such is Allah ; He does what He wills."

3:41
፡-ጌታዬ ሆይ! ለኔ ምልክትን አድርግልኝ አለ፤ ምልክትሕ ሦስት ቀን በጥቅሻ ቢሆን እንጅ ሰዎችን አለማናገርህ ነዉ፤ ጌታህንም በብዙ አዉሳ፤ በማታና በጧትም አወድሰዉ፥ አለዉ።

He said, "My Lord, make for me a sign." He Said, "Your sign is that you will not [be able to] speak to the people for three days except by gesture. And remember your Lord much and exalt [Him with praise] in the evening and the morning."

3:42
መላእክትም ያሉትን (አስታዉስ) - መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሽ፣ አነጻሽም፣ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ።

And [mention] when the angels said, "O Mary, indeed Allah has chosen you and purified you and chosen you above the women of the worlds.

3:43
መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ፤ ስገጂም፤ ከአጐንባሾቹም ጋር አጐንብሺ።

O Mary, be devoutly obedient to your Lord and prostrate and bow with those who bow [in prayer]."

3:44
ይኽ ወደ አንተ የምናወርደዉ የሆነ ከሩቅ ወሬዎች ነዉ፤ መርየምንም ማን እንደሚያሳድግ ብርዖቻቸዉን (ለዕጣ) በጣሉ ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም፤ በሚከራከሩም ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም።

That is from the news of the unseen which We reveal to you, [O Muhammad]. And you were not with them when they cast their pens as to which of them should be responsible for Mary. Nor were you with them when they disputed.

3:45
መላእክት ያሉትን (አስታዉስ) ፡- መርየም ሆይ አላህ ከርሱ በሆነዉ ቃል፣ ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ (ልጅ) ያበስረሻል፤

[And mention] when the angels said, "O Mary, indeed Allah gives you good tidings of a word from Him, whose name will be the Messiah, Jesus, the son of Mary - distinguished in this world and the Hereafter and among those brought near [to Allah ].

3:46
በህጻንነቱና በከፈኒሳነቱ*** ሰዎችን ያነጋግራል ከመልካሞቹም ነዉ (አላት)
*** የበሰለ ሰው ዕድሜው ከ30-40 የኾነ


He will speak to the people in the cradle and in maturity and will be of the righteous."

3:47
ጌታዬ ሆይ! ሰዉ ያልነካኝ ስሆን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፤ ነገሩ እንደዚህሽ ነዉ፤ አላህ የሚሻዉን የፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ሁን ይለዋል ወድያዉኑም ይሆናል፥ አላት።

She said, "My Lord, how will I have a child when no man has touched me?" [The angel] said, "Such is Allah ; He creates what He wills. When He decrees a matter, He only says to it, 'Be,' and it is.

3:48
ጹሕፈትንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል።

And He will teach him writing and wisdom and the Torah and the Gospel

3:49
ወደ እሥራኤልም ልጆች መልክተኛ የደርገዋል፤ (ይላልም) ፡-እኔ ከጌታዬ ዘንድ በታምር መጣኋችሁ። እኔ ለናንተ ከጭቃ አንደ ወፍ ቅርጽ እፈጥራለሁ፤ በርሱም እተነፍስበታለሁ፤ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይሆናል። በአላህም ፈቃድ ዕዉር ሆኖ የተወለደን፥ ለምጸኛንም፥ አድናለሁ፤ ሙታንንም አስነሳለሁ። የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ የምታምኑ እንደሆናችሁ ለእናንተ በዚህ ዉስጥ በእርግጥ ታምር አለበት።

And [make him] a messenger to the Children of Israel, [who will say], 'Indeed I have come to you with a sign from your Lord in that I design for you from clay [that which is] like the form of a bird, then I breathe into it and it becomes a bird by permission of Allah . And I cure the blind and the leper, and I give life to the dead - by permission of Allah . And I inform you of what you eat and what you store in your houses. Indeed in that is a sign for you, if you are believers.

3:50
ከተዉራትም ከኔ በፊት ያልለዉን ያረጋገጥሁ ስሆን የዚያንም በናንተ ላይ እርም የተደረገዉን ከፊል ለናንተ እፈቅድ ዘንድ፥ (መጣኋችሁ) ከጌታችሁም በሆነ ታምር መጣሁዋችሁ አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም።

And [I have come] confirming what was before me of the Torah and to make lawful for you some of what was forbidden to you. And I have come to you with a sign from your Lord, so fear Allah and obey me.

3:51
አላህ ጌታየና ጌታችሁ ነዉ፤ ስለዚህ ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነዉ (አላቸዉ)።

Indeed, Allah is my Lord and your Lord, so worship Him. That is the straight path."

3:52
ዒሳ ከነርሱ ክሕደት በተሰማዉም ጊዜ ፡-ወደ አላህ (ተጨምረዉ) ረዳቶቼ እነማን ናቸዉ? አለ፤ ሐዋሪያት ፡ -እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህም አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መሆናችንን፥ መስክር፥ አሉ።

But when Jesus felt [persistence in] disbelief from them, he said, "Who are my supporters for [the cause of] Allah ?" The disciples said," We are supporters for Allah . We have believed in Allah and testify that we are Muslims [submitting to Him].

3:53
ጌታችን ሆይ! ባወረድኽዉ አመንን፤ መልክተኛዉንም ተከተልን፤ ከመስካሪዎችም ጋር መዝግበን (አሉ)

Our Lord, we have believed in what You revealed and have followed the messenger Jesus, so register us among the witnesses [to truth]."

3:54
(አይሁዶችም) አደሙ፤ አላህም አድማቸዉን መለሰባቸዉ፤ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነዉ።

And the disbelievers planned, but Allah planned. And Allah is the best of planners.

3:55
አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ፣ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፤ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ፤*** እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ፥ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፤ ከዚያም መመለሻችሁ ወደኔ ነዉ፤ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ።
*** ከጉርብትናቸው አራቂህ ነኝ


[Mention] when Allah said, "O Jesus, indeed I will take you and raise you to Myself and purify you from those who disbelieve and make those who follow you [in submission to Allah alone] superior to those who disbelieve until the Day of Resurrection. Then to Me is your return, and I will judge between you concerning that in which you used to differ.

3:56
እነዚያማ የካዱት ሰዎች በቅርቢቱ ዓለምና በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱን ቅጣት እቀጣቸዋለሁ፤ ለነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም።

And as for those who disbelieved, I will punish them with a severe punishment in this world and the Hereafter, and they will have no helpers."

3:57
እነዚያማ ያመኑትማ፥ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት፣ ምንዳዎቻቸዉን ይሞላላቸዋል፤ አላህም በዳዮችን አይወድም።

But as for those who believed and did righteous deeds, He will give them in full their rewards, and Allah does not like the wrongdoers.

3:58
ይህ ከታምራቶችና ጥበብን ከያዘዉ ተግሣጥ ሲሆን በአንተ ላይ እናነበዋለን።

This is what We recite to you, [O Muhammad], of [Our] verses and the precise [and wise] message.

3:59
አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ፥ እንደ አዳም ብጤ ነዉ፤ ከዐፈር ፈጠረዉ፤ ከዚያም ለርሱ (ሰዉ) ሁን አለዉ፥ ሆነም።

Indeed, the example of Jesus to Allah is like that of Adam. He created Him from dust; then He said to him, "Be," and he was.

3:60
ይህ ከጌታህ ዘንድ የሆነ እዉነት ነዉ፤ ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን።

The truth is from your Lord, so do not be among the doubters

3:61
ዕውቀቱም ከመጣልህ በኋላ በርሱ (በዒሳ) የተከራከሩህን ሰዎች ፡- ኑ፤ ልጆቻችንንና ልጆቻችሁንም፤ ሴቶቻችንንና ሴቶቻችሁንም፤ ነፍሶቻችንንና ነፍሶቻችንን እንጥራ፤ ከዚያም አጥብቀን አላህን እንለምን፤ የአላህንም ቁጣ በዉሸታሞቹ ላይ እናድርግ በላቸዉ።

Then whoever argues with you about it after [this] knowledge has come to you - say, "Come, let us call our sons and your sons, our women and your women, ourselves and yourselves, then supplicate earnestly [together] and invoke the curse of Allah upon the liars [among us]."

3:62
ይህ እርሱ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነዉ፤ አምላክም ከአላህ በስተቀር ምንም የለም። አላህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊዉ ጥበበኛዉ ነዉ።

Indeed, this is the true narration. And there is no deity except Allah . And indeed, Allah is the Exalted in Might, the Wise.

3:63
(ከማመን) እንቢ ቢሉም አላህ አጥፊዎቹን በእርግጥ ዐዋቂ ነዉ።

But if they turn away, then indeed - Allah is Knowing of the corrupters.

3:64
የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በኛና በናንተ መካከል ትክክል ወደሆነች ቃል ኑ፤ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጐ ላይይዝ ነዉ፤ በላቸዉ። እምቢ ቢሉም ፡- እኛ ሙስሊሞች መሆናችንን መስክሩ በሏቸው

Say, "O People of the Scripture, come to a word that is equitable between us and you - that we will not worship except Allah and not associate anything with Him and not take one another as lords instead of Allah ." But if they turn away, then say, "Bear witness that we are Muslims [submitting to Him]."

3:65
እላንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በኢብራሂም ለምን ትከራከራላቹሁ? ተዉራትና ኢንጂልም ከርሱ በኋላ እንጅ አልተወረዱም፤ ልብ አታደርጉምን? በላቸዉ።

O People of the Scripture, why do you argue about Abraham while the Torah and the Gospel were not revealed until after him? Then will you not reason?

3:66
ንቁ፤ እናንተ እነዚያ ለናንተ በርሱ ዕዉቀት ባላችሁ ነገር የተከራከራቹሁ ናቸዉ፤ ታዲያ ለናንተ በርሱ ዕዉቀት በሌላችሁ ነገር ለምን ትከራከራላችሁ? አላህም ያውቃል። እናንተ ግን አታዉቁም።

Here you are - those who have argued about that of which you have [some] knowledge, but why do you argue about that of which you have no knowledge? And Allah knows, while you know not.

3:67
ኢብራሒም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም ግን ወደ ቀጥተኛዉ ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፤ ከአጋሪዋችም አልነበረም።

Abraham was neither a Jew nor a Christian, but he was one inclining toward truth, a Muslim [submitting to Allah ]. And he was not of the polytheists.

3:68
ከሰዉ ሁሉ በኢብራሒም ተገቢዎች እነዚያ የተከተሉትን ይህ ነቢይ እነዚያም ያመኑት ናቸዉ፤ አላህም የምእምናን ረዳት ነዉ።

Indeed, the most worthy of Abraham among the people are those who followed him [in submission to Allah ] and this prophet, and those who believe [in his message]. And Allah is the ally of the believers.

3:69
ከመጽሐፉ ባለቤቶች የሆኑ ጭፍሮች ነፍሶቻቸዉን እንጂ የማያሳስቱ ሲሆኑ ሊያሳስቱዋችሁ ተመኙ ግን አያውቁም

A faction of the people of the Scripture wish they could mislead you. But they do not mislead except themselves, and they perceive [it] not.

3:70
የመጽሐፉ ባለቤቶቹ ሆይ! እናንተ የምታዉቁ ስትሆን በአላህ አንቀጾች ለምን ትክዳላችሁ?

O People of the Scripture, why do you disbelieve in the verses of Allah while you witness [to their truth]?

3:71
የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! እዉነቱን በዉሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ? እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?

O People of the Scripture, why do you confuse the truth with falsehood and conceal the truth while you know [it]?

3:72
ከመጽሐፉ ባለቤቶቹ የሆኑ ጭፍሮችም አሉ ፡- በነዚያ በአመኑት ላይ በተወረደዉ (ቁርአን) በቀኑ መጀመሪያ ላይ እመኑበት በመጨረሻዉም ካዱት፤ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና

And a faction of the People of the Scripture say [to each other], "Believe in that which was revealed to the believers at the beginning of the day and reject it at its end that perhaps they will abandon their religion,

3:73
እናንተ የተሰጣችሁትን ብጤ አንድም ሰዉ መሰጠቱን ወይም እጌታችሁ ዘንድ የሚከራከሩዋችሁ መሆንን ሃይማኖታችሁን ለተከተለ ሰዉ ቢሆን እንጂ አትመኑ፣ (አትግለጹ፥አሉ)፤ መምሪያዉ የአላህ መምሪያ ብቻ ነዉ በላቸዉ፤ ችሮታ በአላህ እጅ ነዉ፣ ለሚሻዉ ይሰጠዋል፤ አላህም ችሮታዉ ሰፊ ዐዋቂ ነዉ በላቸዉ።

And do not trust except those who follow your religion." Say, "Indeed, the [true] guidance is the guidance of Allah . [Do you fear] lest someone be given [knowledge] like you were given or that they would [thereby] argue with you before your Lord?" Say, "Indeed, [all] bounty is in the hand of Allah - He grants it to whom He wills. And Allah is all-Encompassing and Wise."

3:74
በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻዉን ይመርጣል አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።

He selects for His mercy whom He wills. And Allah is the possessor of great bounty.

3:75
ከመጽሐፉ ሰዎችም በብዙ ገንዘብ ብታምነዉ ወዳንተ የሚመልስ ሰዉ አልለ። ከነሱዉም በአንድ ዲናር እንኳ ብታምነዉ፤ ሁል ጊዜ በርሱ ላይ የምትጠባበቅ ካልሆንክ በስተቀር የማይመልስ ሰዉ አለ። ይኽ በመሃይምናን (በምናደርገዉ) በኛ ላይ ምንም መንገድ የለብንም ስለሚሉ ነዉ፤ እነርሱ እያወቁም በአላህ ላይ ዉሸትን ይናገራሉ።

And among the People of the Scripture is he who, if you entrust him with a great amount [of wealth], he will return it to you. And among them is he who, if you entrust him with a [single] silver coin, he will not return it to you unless you are constantly standing over him [demanding it]. That is because they say, "There is no blame upon us concerning the unlearned." And they speak untruth about Allah while they know [it].

3:76
አይደለም (አለባቸዉ እንጁ)፤ በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀ ሰዉ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል።

But yes, whoever fulfills his commitment and fears Allah - then indeed, Allah loves those who fear Him.

3:77
እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሐላዎቻቸዉ ጥቂቱን ዋጋ የሚለዉጡ እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ዕድል የላቸዉም፤ በትንሣኤ ቀንም አላህ አያነጋግራቸዉም፤ ወደ ነርሱም አይመለከትም፣ አያነጻቸዉምም፤ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸዉ።

Indeed, those who exchange the covenant of Allah and their [own] oaths for a small price will have no share in the Hereafter, and Allah will not speak to them or look at them on the Day of Resurrection, nor will He purify them; and they will have a painful punishment.

3:78
ከነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲሆን ከመጸሐፉ መሆኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸዉን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ። እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልሆነ ሲሆን እርሱ ከአላህ ዘንድ ነዉም ያላሉ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑም በአላህ ላይ ዉሸትን ይናገራሉ።

And indeed, there is among them a party who alter the Scripture with their tongues so you may think it is from the Scripture, but it is not from the Scripture. And they say, "This is from Allah ," but it is not from Allah . And they speak untruth about Allah while they know.

3:79
ለማንም ሰዉ አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠዉና ከዚያም ለሰዎች ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሆኑ ሊል አይገባዉም፤ ግን መጽሐፍን የምታስተምሩ በነበራችሁትና የምታጠኑም በነበራችሁት በዕዉቀታችሁ ሠሪዎች ሁኑ (ይላቸዋል)።

It is not for a human [prophet] that Allah should give him the Scripture and authority and prophethood and then he would say to the people, "Be servants to me rather than Allah ," but [instead, he would say], "Be pious scholars of the Lord because of what you have taught of the Scripture and because of what you have studied."

3:80
መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ ሊያዛችሁ (አይገባዉም)፤ እናንተ ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክሕደት ያዛችኋልን?

Nor could he order you to take the angels and prophets as lords. Would he order you to disbelief after you had been Muslims?

3:81
አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን፣ ከመጽሐፍና ከጥበብ ሰጥቻችሁ ከዚያም ከእናንተ ጋር ላለዉ (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ መልክተኛ ቢመጣላቸዉ፣ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም እንድትረዱት ሲል በያዘ ጊዜ (አስታዉስ)፤ አረጋገጣችሁን? በይሃችሁ ላይ ኪዳኔን ያዛችሁምን? አላቸዉ፤ አረጋገጥን አሉ እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ አላቸዉ።

And [recall, O People of the Scripture], when Allah took the covenant of the prophets, [saying], "Whatever I give you of the Scripture and wisdom and then there comes to you a messenger confirming what is with you, you [must] believe in him and support him." [ Allah ] said, "Have you acknowledged and taken upon that My commitment?" They said, "We have acknowledged it." He said, "Then bear witness, and I am with you among the witnesses."

3:82
ከዚህም በኋላ የሸሹ ሰዎች እነዚያ እነሱ አመጠኞች ናቸዉ።

And whoever turned away after that - they were the defiantly disobedient.

3:83
በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ፤ በዉድም በግድም ለርሱ የታዘዙ ወደርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ (ከሐዲዎች) ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?

So is it other than the religion of Allah they desire, while to Him have submitted [all] those within the heavens and earth, willingly or by compulsion, and to Him they will be returned?

3:84
በአላህ አመንን፤ በኛ ላይ በተወረደዉም፥ (በቁርአን) በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሐቅም በያዕቆብም፣ በነገዶችም ላይ በተወረደዉ፤ ለሙሳና ለዒሳም፣ ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸዉ በተሰጠዉ (አመንን)፤ ከነርሱ መካከል አንዱንም አንለይም፤ እኛ ለርሱ ታዛዦች ነን፣ በል።

Say, "We have believed in Allah and in what was revealed to us and what was revealed to Abraham, Ishmael, Isaac, Jacob, and the Descendants, and in what was given to Moses and Jesus and to the prophets from their Lord. We make no distinction between any of them, and we are Muslims [submitting] to Him."

3:85
ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰዉ፣ ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለዉም፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎች ነዉ።

And whoever desires other than Islam as religion - never will it be accepted from him, and he, in the Hereafter, will be among the losers.

3:86
ከእምነታቸዉና መልክተኛዉም እዉነት መሆኑን ከመሰከሩ፣ የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸዉ በኋላ የካዱን ሕዝቦች፥ አላህ አንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም።

How shall Allah guide a people who disbelieved after their belief and had witnessed that the Messenger is true and clear signs had come to them? And Allah does not guide the wrongdoing people.

3:87
እነዚያ ቅጣታቸዉ የአላህና የመላእክት፥ የሰዎችም ሁሉ ርግማን በነሱ ላይ መሆን ነዉ።

Those - their recompense will be that upon them is the curse of Allah and the angels and the people, all together,

3:88
በውስጧ ዘዉታሪዎች ሲሆኑ፤ ቅጣቱም፤ በነሱ ላይ አይቃለልላቸዉም፤ እነሱም ቀን አይሰጡም።

Abiding eternally therein. The punishment will not be lightened for them, nor will they be reprieved.

3:89
እነዚያ ከዚህ በኋላ ንሰሐ የገቡና (ሥራቸዉን) ያሳመሩ ሲቀሩ፥ (እነዚህንስ ይምራቸዋል)፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነዉና።

Except for those who repent after that and correct themselves. For indeed, Allah is Forgiving and Merciful.

3:90
እነዚያ ከእምነታቸዉ በኋላ የካዱ፣ ከዚያም ክህደትን የጨመሩ፣ ጸጸታቸዉ ፈጽሞ ተቀባይ የላትም፥ እነዚያም የተሳሳቱ እነርሱ ናቸዉ።

Indeed, those who reject the message after their belief and then increase in disbelief - never will their [claimed] repentance be accepted, and they are the ones astray.

3:91
እነዚያ የካዱና ከእነርሱም በክሕደታቸዉ ላይ እንዳሉ የሞቱ፥ ከነሱ ከአንዳቸዉ በምድር ሙሉ የሆነ ወርቅ፣ (ቢኖረውና) በርሱ ቢበዥበትም እንኳ ፈጽሞ ተቀባይን አያገኝም፤ እነዚያ ለነርሱ የሚያሰቃይ ቅጣት አላቸዉ፤ ለነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም።

Indeed, those who disbelieve and die while they are disbelievers - never would the [whole] capacity of the earth in gold be accepted from one of them if he would [seek to] ransom himself with it. For those there will be a painful punishment, and they will have no helpers.

3:92
የምትወዱትን አስከምትለግሱ ድረስ በጐን ሥራ (ዋጋውን ) አታገኙም፤ ከምንም ነገር ብትለግሱ፥ አላህ ያዉቀዋል።

Never will you attain the good [reward] until you spend [in the way of Allah ] from that which you love. And whatever you spend - indeed, Allah is Knowing of it.

3:93
ተዉራት ከመወረድዋ በፊት እስራኤል በራሱ ላይ እርም ካደረገዉ ነገር በስተቀር ምግብ ሁሉ ለእስራኤል ልጆች የተፈቀደ ነበር፤ እዉነተኞችም አንደሆናችሁ ተዉራትን አምጡ አንብቡዋትም በላቸው።

All food was lawful to the Children of Israel except what Israel had made unlawful to himself before the Torah was revealed. Say, [O Muhammad], "So bring the Torah and recite it, if you should be truthful."

3:94
ከዚህም በኋላ በአላህ ላይ ዉሸትን የቀጣጠፉ ሰዎች፣ እነዚያ እነርሱ በደለኞች ናቸዉ።

And whoever invents about Allah untruth after that - then those are [truly] the wrongdoers.

3:95
አላህ እዉነትን ተናገረ፤ የኢብራሄምንም መንገድ ወደ እዉነት ያዘነበለ ሲሆን ተከተሉ ከአጋሪዎችም አልነበረም በላቸዉ።

Say, " Allah has told the truth. So follow the religion of Abraham, inclining toward truth; and he was not of the polytheists."

3:96
ለሰዎች (መጸለያ) መጀመሪያ የተኖረዉ ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መምርያ ሲሆን ያ በበካህ (በመካ) ያለዉ ነዉ።

Indeed, the first House [of worship] established for mankind was that at Makkah - blessed and a guidance for the worlds.

3:97
በዉስጡ ግልጽ የሆኑ ታምራቶች፥ የኢብራሂም መቆሚያ አለ የገባዉም ሰዉ ጸጥተኛ ይሆናል፤*** ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጐብኘት ግዴታ አለባቸዉ፤ የካደም ሰዉ አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነዉ።
*** ሰላምን ያገኛል


In it are clear signs [such as] the standing place of Abraham. And whoever enters it shall be safe. And [due] to Allah from the people is a pilgrimage to the House - for whoever is able to find thereto a way. But whoever disbelieves - then indeed, Allah is free from need of the worlds.

3:98
የመጽሃፉ ባለቤቶች ሆይ! አላህ በምትሠሩት ሁሉ ላይ ዐዋቂ ሲሆን፥ በአላህ ታምራት ለምን ትክዳላችሁ? በላቸዉ።

Say, "O People of the Scripture, why do you disbelieve in the verses of Allah while Allah is Witness over what you do?"

3:99
የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እናንተ መስካሪዎች ሆናችሁ፣ ከአላህ መንገድ መጥመሟን የምትፈልጓት ስትሆኑ፣ ያመነን ሰዉ ለምን ትከለክላላችሁ? አላህም ከምትሰሩት ነገር ሁሉ ዘንጊ አይደለም በላቸዉ

Say, "O People of the Scripture, why do you avert from the way of Allah those who believe, seeking to make it [seem] deviant, while you are witnesses [to the truth]? And Allah is not unaware of what you do."

3:100
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ መጽሐፉን ከተሰጡት ሰዎች ከፊሉን ብትታዘዙ ከእምነታችሁ በኋላ ከሐዲዎች አድርገዉ ይመልሱዋችኋል።

O you who have believed, if you obey a party of those who were given the Scripture, they would turn you back, after your belief, [to being] unbelievers.

3:101
የአላህም አንቀጾች በናንት ላይ የሚነበቡ ሲሆን መልክተኛዉም በዉስጣቸሁ ያለ ሲሆን፥ መልክተኛዉም በዉስጣቸሁ ያለ ሲሆን፥ አናንተ እንዴት ትክዳላችሁ? በአላህም የሚጠበቅ ሰዉ ወደ ቀጥተኛዉ መንገድ በእርግጥ ተመራ።

And how could you disbelieve while to you are being recited the verses of Allah and among you is His Messenger? And whoever holds firmly to Allah has [indeed] been guided to a straight path.

3:102
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢዉን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፤ እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጅ አትሙቱ።

O you who have believed, fear Allah as He should be feared and do not die except as Muslims [in submission to Him].

3:103
የአላህንም (የማመን) ገመድ ሁሉችሁም ያዙ፤ አትለያዩም፤ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በናንተ ላይ (የዋለዉን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፤ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፤ በጸጋዉም ወንድማማቾች ሆናችሁ፤ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፤ ከእርስዋም አዳናችሁ፤ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለናንተ አንቀጾች ያብራራል።

And hold firmly to the rope of Allah all together and do not become divided. And remember the favor of Allah upon you - when you were enemies and He brought your hearts together and you became, by His favor, brothers. And you were on the edge of a pit of the Fire, and He saved you from it. Thus does Allah make clear to you His verses that you may be guided.

3:104
ከናንተም ወደ በጐ ነገር የሚጠሩ፣ በመልካም ሥራም የሚያዙ፣ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ፣ ህዝቦች ይኑሩ። እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸዉ።

And let there be [arising] from you a nation inviting to [all that is] good, enjoining what is right and forbidding what is wrong, and those will be the successful.

3:105
እንደነዚያም ግልጽ ታምራት ከመጣላቸዉ በኋላ እንደተለያዩትና እንደ ተጨቃጨቁት አትሁኑ፤ እነዚያም ለነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸዉ።

And do not be like the ones who became divided and differed after the clear proofs had come to them. And those will have a great punishment.

3:106
ፊቶች የሚያበሩበትን ፊቶችም የሚጠቁሩበትን ቀን (አሰታዉስ)፤ እነዚያ ፊቶቻቸዉ የጠቆሩትማ ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን? ትክዱት በነበራችሁት ነገር ቅጣቱን ቅመሱ። (ይባላሉ)።

On the Day [some] faces will turn white and [some] faces will turn black. As for those whose faces turn black, [to them it will be said], "Did you disbelieve after your belief? Then taste the punishment for what you used to reject."

3:107
እነዚያም ፊቶቻቸዉ ያበሩትማ በአላህ ችሮታ (ገነት) ዉስጥ ናቸው፤ እነርሱ በዉስጧ ዘዉታሪዎች ናቸዉ።

But as for those whose faces will turn white, [they will be] within the mercy of Allah . They will abide therein eternally.

3:108
ይህች በአንተ ላይ በዉነት የምናነባት ስትሆን የአላህ ታምራት ናት፤ አላህም ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም።

These are the verses of Allah . We recite them to you, [O Muhammad], in truth; and Allah wants no injustice to the worlds.

3:109
በሰማያት ያለዉና በምድር ያለዉም ሁሉ የአላህ ነዉ፤ ነገሮችም ሁሉ ወደ አላህ በቻ ይመለሳሉ።

To Allah belongs whatever is in the heavens and whatever is on the earth. And to Allah will [all] matters be returned.

3:110
ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ሆናችሁ፤ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ፤ የመጽሐፉም ሰዎች ባመኑ ኖሮ ለነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር፤ ከነርሱ አማኞች አሉ፤ አብዛኞቻቸዉ ግን አመጸኞች ናቸው።

You are the best nation produced [as an example] for mankind. You enjoin what is right and forbid what is wrong and believe in Allah . If only the People of the Scripture had believed, it would have been better for them. Among them are believers, but most of them are defiantly disobedient.

3:111
ማስከፋትን እንጅ ፈጽሞ አይጐዱዋችሁም፤ ቢዋጉዋችሁም ጀርባዎችን ያዙሩላችኋል፤ (ይሸሻሉ)፤ ከዚያም አይረዱም።

They will not harm you except for [some] annoyance. And if they fight you, they will show you their backs; then they will not be aided.

3:112
የትም በተገኙበት ስፍራ ከአላህ በሆነ ቃል ኪዳን ከሰዎችም በሆነ ቃል ኪዳን (የተጠበቁ) ካልሆኑ በስተቀር በነርሱ ላይ ዉርደት ተመታችባቸዉ፤ ከአላህም በሆነ ቁጣ ተመለሱ፤ በነርሱም ላይ ድኽነት ተመታችባችችዉ፤ ይኸ እነርሱ በአላህ ታምራት ይክዱ ስለ ነበሩና ነቢያትንም ያለ ህግ ይገድሉ ስለ ነበሩ ነዉ፤ ይህ፥ በማመጣቸዉና ወሰንን የተላለፉ ሰለ ነበሩ ነዉ።

They have been put under humiliation [by Allah ] wherever they are overtaken, except for a covenant from Allah and a rope from the Muslims. And they have drawn upon themselves anger from Allah and have been put under destitution. That is because they disbelieved in the verses of Allah and killed the prophets without right. That is because they disobeyed and [habitually] transgressed.

3:113
(የመጽሐፉ ሰዎች ሁሉ) እኩል አይደሉም፤ ከመጽሐፉ ሰዎች ቀጥ ያሉ በሌሊት ሰዓቶች እነርሱ የሚሰግዱ ሆነዉ የአላህን አንቀጾች የሚያነቡ፣ ሕዝቦች አሉ።

They are not [all] the same; among the People of the Scripture is a community standing [in obedience], reciting the verses of Allah during periods of the night and prostrating [in prayer].

3:114
በአላህና በመጨረሻዉ ቀን ያምናሉ፤ በጽድቅ ነገርም ያዛሉ፣ ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ፤ በበጐ ሥራዎችም፥ ይጣደፋሉ። እነዚያም ከመልካሞች ናቸዉ

They believe in Allah and the Last Day, and they enjoin what is right and forbid what is wrong and hasten to good deeds. And those are among the righteous.

3:115
ከበጐ ሥራ ማንኛውንም ቢሠሩ፣ አይካዱትም*** አላህም ጥንቁቆቹን ዐዋቂ ነዉ።
*** ኢስላምን ተቀብለው በበግ ምግባራቸው እስከቀጠሉ ድረስ ምንዳቸውን አያጡም።


And whatever good they do - never will it be removed from them. And Allah is Knowing of the righteous.

3:116
እነዚያ የካዱት ሰዎች ገንዘቦቻቸዉና ልጆቻቸዉ ከአላህ (ቅጣት) እነርሱን ምንንም አያድኑዋቸዉም፤ እነዚያም የእሳት ጓዶች ናቸዉ፤ እነርሱ በእርስዋ ዉስጥ ዘዉታሪዎች ናቸዉ።

Indeed, those who disbelieve - never will their wealth or their children avail them against Allah at all, and those are the companions of the Fire; they will abide therein eternally.

3:117
የዚያ በዚች በቅርቢቱ ሕይወት የሚለግሱት ነገር ምሳሌ፣ በዉስጧ ዉርጭ ያለባት ነፋስ፣ ነፍሶቻቸዉን የበደሉን ሕዝቦች አዝመራ እንደ ነካችና፣ እንዳጠፋችዉ ብጤ ነዉ፤ አላህም አልበደላቸዉም ግን ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ።

The example of what they spend in this worldly life is like that of a wind containing frost which strikes the harvest of a people who have wronged themselves and destroys it. And Allah has not wronged them, but they wrong themselves.

3:118
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፤ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፤ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፥ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸዉ በእርግጥ ተገለጸች። ልቦቻቸዉም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነዉ። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለናንተ ማብራራያዎችን በእርግጥ ገለጽን።

O you who have believed, do not take as intimates those other than yourselves, for they will not spare you [any] ruin. They wish you would have hardship. Hatred has already appeared from their mouths, and what their breasts conceal is greater. We have certainly made clear to you the signs, if you will use reason.

3:119
እነሆ እናንተ እነዚያ የምትወዱዋቸዉ ናቸሁ፤ (እነሱ) ግን አይወዳችሁም በመጸሐፉም በሁሉም ታምናላችሁ፤ ባገኙዋችሁም ጊዜ አምነናል ይላሉ፤ ባገለሉም ጊዜ ከቁጭታቸዉ የተነሳ በናንተ ላይ ዐጥቆቻቸዉን ይነክሳሉ፤ በቁጭታችሁ ሙቱ፤ አላህ ልቦች የቋጠሩትን ዐዋቂ ነዉና በላቸዉ።

Here you are loving them but they are not loving you, while you believe in the Scripture - all of it. And when they meet you, they say, "We believe." But when they are alone, they bite their fingertips at you in rage. Say, "Die in your rage. Indeed, Allah is Knowing of that within the breasts."

3:120
ደግ ነገር ብትነካችሁ ታስከፋቸዋለች መጥፎም ነገር ብታገኛችሁ በርሷ ይደሰታሉ፤ ብትታገሡና ብትጠነቀቁም ተንኮላቸዉ ምንም አይጐዳችሁም። አላህ በሚሠሩት ሁሉ (በዕዉቀቱ) ከባቢ ነዉና።

If good touches you, it distresses them; but if harm strikes you, they rejoice at it. And if you are patient and fear Allah , their plot will not harm you at all. Indeed, Allah is encompassing of what they do.

3:121
ለምእምኖቹም ለዉጊያ ስፍራዎችን የምታዘጋጁ ሆነህ ከቤተሰብህ በማለድክ ጊዜ (አስታዉስ) አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነዉ።

And [remember] when you, [O Muhammad], left your family in the morning to post the believers at their stations for the battle [of Uhud] - and Allah is Hearing and Knowing -

3:122
ከናንተ ሁለት ጭፍሮች አላህ ረዳታቸዉ ሲሆን ለመፍራት ባሰቡ ጊዜ (አስታዉስ)፤ በአላህም ላይ ብቻ ምእምናኖች ይመኩ።

When two parties among you were about to lose courage, but Allah was their ally; and upon Allah the believers should rely.

3:123
በበድርም፣ እናንተ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ፤ አላህንም ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት።

And already had Allah given you victory at [the battle of] Badr while you were few in number. Then fear Allah ; perhaps you will be grateful.

3:124
ለምእመናን ጌታችሁ በሦስት ሺሕ መላእክት የተወረዱ ሲሆን ቢረዳችሁ አይበቃችሁንም? በምትል ጊዜ (አስታዉስ)።

[Remember] when you said to the believers, "Is it not sufficient for you that your Lord should reinforce you with three thousand angels sent down?

3:125
አዎን፣ ብትታገሡና ብትጠነቀቁ ከዚህም ፍጥነታቸዉ (ጠላቶቻችሁ) ቢመጡባችሁ፣ ጌታችሁ ምልክት ባላቸዉ፣ አምስት ሺሕ መላእክትን ይረዳችኋል።

Yes, if you remain patient and conscious of Allah and the enemy come upon you [attacking] in rage, your Lord will reinforce you with five thousand angels having marks [of distinction]

3:126
አላህም (እረዳታዉን) ለናንተ ብስራትና ልቦቻችሁ በርሱ እንዲረኩ እንጂ አላደረገዉም፤ ድልም መንሳት አሸናፊ ጥበበኛ በሆነዉ አላህ ዘንድ እንጅ ከሌላ አይደለም

And Allah made it not except as [a sign of] good tidings for you and to reassure your hearts thereby. And victory is not except from Allah , the Exalted in Might, the Wise -

3:127
(ድልን ያጐናጸፋችሁ) ከነዚያ ከካዱት ከፊልን ሊቆርጥ (ሊያጠፋ)፣ ወይም ሊያዋርዳቸዉን ያፈሩ ሆነዉ እንዲመለሱ ነዉ

That He might cut down a section of the disbelievers or suppress them so that they turn back disappointed.

3:128
(አላህ) በነርሱ ላይ ይቅርታ እስኪያደርግ ወይም እነርሱ በዳዮች ናቸዉና እስኪቀጣቸዉ ድረስ፣ ላንተ ከነገሩ ምንም የለህም።

Not for you, [O Muhammad, but for Allah ], is the decision whether He should [cut them down] or forgive them or punish them, for indeed, they are wrongdoers.

3:129
በሰማያት ያለዉ፣ በምድርም ያለዉ፣ ሁሉ፣ የአላህ ነዉ፤ ለሚሻዉ ሰዉ ይምራል፤ የሚሻዉንም ሰዉ ይቀጣል፤ አላህም ማሐሪ አዛኝ ነዉ።

And to Allah belongs whatever is in the heavens and whatever is on the earth. He forgives whom He wills and punishes whom He wills. And Allah is Forgiving and Merciful.

3:130
እናንተ ያመናችሁ ሆይ አራጣን የተነባበሩ እጥፎች ሲሆኑ፥ አትበሉ፤ ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ።

O you who have believed, do not consume usury, doubled and multiplied, but fear Allah that you may be successful.

3:131
ያችንም ለከሐዲዎች የተደገሰችዉን እሳት ተጠንቀቁ።

And fear the Fire, which has been prepared for the disbelievers.

3:132
ይታዘንላችሁም ዘንድ፥ አላህንና መልክተኛዉን ታዘዙ።

And obey Allah and the Messenger that you may obtain mercy.

3:133
ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ሆነች ገነት፥ አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትሆን ተቻኮሉ።

And hasten to forgiveness from your Lord and a garden as wide as the heavens and earth, prepared for the righteous

3:134
ለነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፥ ቁጭትንም ገቺዎች፥ ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት (ተደግሳለች)፤ አላህም በጐ ሠሪዎችን ይወዳል።

Who spend [in the cause of Allah ] during ease and hardship and who restrain anger and who pardon the people - and Allah loves the doers of good;

3:135
ለነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ፥ ወይም ነፍሶቻቸዉን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታዉሱና ለኀጢአቶቻቸዉ ምሕረትን የሚለምኑ ለሆኑት፣ ከአላህም ሌላ ኅጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፤ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያዉቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት (ተደግሳለች)።

And those who, when they commit an immorality or wrong themselves [by transgression], remember Allah and seek forgiveness for their sins - and who can forgive sins except Allah ? - and [who] do not persist in what they have done while they know.

3:136
እነዚያ ምንዳቸዉ ከጌታቸዉ ምሕረትና በዉስጣቸዉ ዘዉታሪዎች ሲሆኑ በሥሮቻቸዉ ወንዞች የሚፈሱባቸዉ ገነቶችም ናቸዉ። የሠሪዎችም ምንዳ (ገነት) ምንኛ አማረች?

Those - their reward is forgiveness from their Lord and gardens beneath which rivers flow [in Paradise], wherein they will abide eternally; and excellent is the reward of the [righteous] workers.

3:137
ከናንተ በፊት ድርጊቶች በእርግጥ አልፈዋል። በምድርም ላይ ኺዱ፣ የአስተባባዮችም ፍጻሜ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ።

Similar situations [as yours] have passed on before you, so proceed throughout the earth and observe how was the end of those who denied.

3:138
ይህ ለሰዎች ገላጭ፤ ለጥንቁቆች መሪና ገሣጭ ነዉ።

This [Qur'an] is a clear statement to [all] the people and a guidance and instruction for those conscious of Allah .

3:139
እናንተም የበላዮች ስትሆኑ፥ ምእምናን እንደሆናችሁ አትሥነፉ፤ አትዘኑም።

So do not weaken and do not grieve, and you will be superior if you are [true] believers.

3:140
ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፤ ይኽችንም ቀናት በሰዎች መካከል እናዘዋዉራታለን፤ (እንድትገሠጹና) አላህም እነዚያን ያመኑትን እንዲያዉቅ (እንዲለይ)፣ ከናንተም ሰማዕታትን እንዲይዝ ነዉ፤*** አላህም በዳዮችን አይወድም።
*** በሰማዕታት የሚገደሉን እንዲያደርግ


If a wound should touch you - there has already touched the [opposing] people a wound similar to it. And these days [of varying conditions] We alternate among the people so that Allah may make evident those who believe and [may] take to Himself from among you martyrs - and Allah does not like the wrongdoers -

3:141
አላህም እነዚያን ያመኑትን (ከኅጢአት) ሊያነጻና ከሐዲዎችንም ሊያጠፋ ነዉ።

3 And that Allah may purify the believers [through trials] and destroy the disbelievers.

3:142
በዉነቱ አላህ ከናንተ እነዚያን የታገሉትን ሳያዉቅ (ሳይለይ) ታጋሾቹንም ሳያዉቅ ገነትን ልትገቡ አሰባችሁን?

Or do you think that you will enter Paradise while Allah has not yet made evident those of you who fight in His cause and made evident those who are steadfast?

3:143
(በጦርነት ላይ) መሞትንም ሳታገኙት በፊት በርግጥ የምትመኙት ነበራችሁ፥ እናንተም የምትመለከቱ ስትሆን በርግጥ አያችሁት፤ (ታዲያ ለምን ሸሻችሁ?)

And you had certainly wished for martyrdom before you encountered it, and you have [now] seen it [before you] while you were looking on.

3:144
ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፤ ታድያ ቢሞት፥ ወይም ቢገደል ወደኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? (1) ወደኋላዉ የሚገለበጥም ሰዉ አላህን ምንም አይጐዳም። አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል።
*** ወደ ክህደት ተመለሳችሁ።


Muhammad is not but a messenger. [Other] messengers have passed on before him. So if he was to die or be killed, would you turn back on your heels [to unbelief]? And he who turns back on his heels will never harm Allah at all; but Allah will reward the grateful.

3:145
ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ፍርድ ቢሆን እንጅ ልትሞት አይገባትም፤ (ጊዜዉም) ተወስኖ ተጽፏል፤ የቅርቢቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰዉ፥ከእርስዋ እንሰጠዋለን። የመጨረሻይቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰዉ፥ ከእርስዋ እንሰጠዋለን፤ አመስጋኞችንም በእርግጥ እንመነዳለን።

And it is not [possible] for one to die except by permission of Allah at a decree determined. And whoever desires the reward of this world - We will give him thereof; and whoever desires the reward of the Hereafter - We will give him thereof. And we will reward the grateful.

3:146
ከነቢይም ብዙ ሊቃዉንት ከርሱ ጋር ሆነዉ የተዋጉ ብዙ ናቸዉ፤ በአላህም መንገድ ለሚደርስባቸዉ ነገር አልፈሩም፤ አልደከሙምም፤ (ለጠላት) አልተዋረደምም አላህም ትዕግሥተኞችን ይወዳል።

And how many a prophet [fought and] with him fought many religious scholars. But they never lost assurance due to what afflicted them in the cause of Allah , nor did they weaken or submit. And Allah loves the steadfast.

3:147
ንግግራቸዉም፡- ጌታችን ሆይ ኃጢአቶቻችንንና በነገራችን ሁሉ ወሰን ማለፋችንን ለኛ ማር፤ ይዞታችንንም አደላድል፤ (1) በከሐዲዎችም ሕዝቦች ላይ እርዳን፤ ማለታቸዉ እንጅ ሌላ አልነበረም።

And their words were not but that they said, "Our Lord, forgive us our sins and the excess [committed] in our affairs and plant firmly our feet and give us victory over the disbelieving people."

3:148
አላህም የቅርቢቱን ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸዉ። አላህም በጐ አድራጊዎችን ይወዳል።

So Allah gave them the reward of this world and the good reward of the Hereafter. And Allah loves the doers of good.

3:149
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን የካዱትን ሰዎች ብትታዘዙ፥ ወደ ኋላችሁ ይመልሱዋችኋል፤ ከሳሪዎች ሆናችሁም ትገለበጣላችሁ።

O you who have believed, if you obey those who disbelieve, they will turn you back on your heels, and you will [then] become losers.

3:150
(አይረዷችሁም)፤ ይልቁን አላህ ብቻ ረዳታችሁ ነዉ። እርሱም ከረዳቶች ሁሉ በላጭ ነዉ።

But Allah is your protector, and He is the best of helpers.

3:150
አላህ ቢረዳችሁ ለናንተ አሸናፊ የለም፤ ቢያዋርዳችሁም ያ ከርሱ (ማዋረድ) በኋላ የሚረዳችሁ ማነዉ? በአላህም ላይ ብቻ ምእምናን ይመኩ።

If Allah should aid you, no one can overcome you; but if He should forsake you, who is there that can aid you after Him? And upon Allah let the believers rely.

3:151
በነዚያ በካዱት ሰዎች ልቦች ዉስጥ፤ አላህ በርሱ አስረጅ ያላወረደበትን ነገር በአላህ በማጋራታቸዉ ምክንያት ፍርሃትን እንጥላለን መኖሪያቸዉም እሳት ናት፤ የበዳዮችም መኖርያ ምን ትከፋ!

We will cast terror into the hearts of those who disbelieve for what they have associated with Allah of which He had not sent down [any] authority. And their refuge will be the Fire, and wretched is the residence of the wrongdoers.

3:152
አላህም በፈቃዱ በምትጨፈጭፏቸው ጊዜ ኪዳኑን በእርግጥ አረጋገጠላችሁ። የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ፥ በትእዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባምመጣችሁ ጊዜ፥ (እርዳታዉን ከለከላችሁ)፤ ከናንተ ዉስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ፤ ከናንተም የመጨረሻይቱን ዓለም የሚሻ አልለ፤ ከዚያም ሊሞክራችሁ ከነርሱ አዞራችሁ፤ በእርግጥም ከናንተ ይቅርታ አደረገላችሁ አላህም በምእምናን ላይ የችሮታ ባለቤት ነዉ፡

And Allah had certainly fulfilled His promise to you when you were killing the enemy by His permission until [the time] when you lost courage and fell to disputing about the order [given by the Prophet] and disobeyed after He had shown you that which you love. Among you are some who desire this world, and among you are some who desire the Hereafter. Then he turned you back from them [defeated] that He might test you. And He has already forgiven you, and Allah is the possessor of bounty for the believers.

3:153
መልክተኛዉ ከኋላችሁ የሚጠራችሁ ሲሆን፥ ርቃችሁ በምትሸሹና በአንድም ላይ የማትዞሩ በሆናችሁ ጊዜ፥ (አስታዉሱ)፤ ባመለጣችሁና በደረሰባችሁም ነገር እንድታዝኑ በሐሳብ ላይ ሐሳብን መነዳችሁ፤ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ዉስጠ ዐዋቂ ነዉ።

[Remember] when you [fled and] climbed [the mountain] without looking aside at anyone while the Messenger was calling you from behind. So Allah repaid you with distress upon distress so you would not grieve for that which had escaped you [of victory and spoils of war] or [for] that which had befallen you [of injury and death]. And Allah is [fully] Acquainted with what you do.

3:154
ከዚያም ከጭንቅ በኋላ ጸጥታን ከናንተ ከፊሎችን የሚሸፍንን እንቅልፍ፥ በናንተ ላይ አወረደ፤ ከፊሎቹም ነፍሶቻቸዉ በእርግጥ አሳሰቧቸዉ። እዉነት ያልሆነዉን የመሃይምነትን መጠራጠር በአላህ ይጠራጠራሉ፤ ከነገሩ ለኛ ምንም የለንም ይላሉ፤ ነገሩ ሁሉም ለአላህ ነዉ፣ በላቸዉ። ለአንተ የማይገለጹትን በነፍሶቻቸዉ ዉስጥ ይደብቃሉ፤ ከነገሩ ለኛ አንዳች በነበርን ኖሮ፥ እዚህ ባልተገደልን ነበር፥ ይላሉ። በቤታችሁ ዉስጥ በሆናችሁም ኖሮ እነዚያ በነርሱ ላይ መገደል የተጻፈባቸዉ ወደ መዉደቂያቸዉ በወጡ ነበር በላቸዉ፤ አላህ (ፍርዱን ሊፈጽምና) በደረቶቻችሁም ዉስጥ ያለዉን ሊፈትን በልቦቻችሁም ዉስጥ ያለዉን ነገር ሊገልጹ (ይህን ሠራ)፤ አላህም በደረቶች ዉስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነዉ።

Then after distress, He sent down upon you security [in the form of] drowsiness, overcoming a faction of you, while another faction worried about themselves, thinking of Allah other than the truth - the thought of ignorance, saying, "Is there anything for us [to have done] in this matter?" Say, "Indeed, the matter belongs completely to Allah ." They conceal within themselves what they will not reveal to you. They say, "If there was anything we could have done in the matter, some of us would not have been killed right here." Say, "Even if you had been inside your houses, those decreed to be killed would have come out to their death beds." [It was] so that Allah might test what is in your breasts and purify what is in your hearts. And Allah is Knowing of that within the breasts.

3:155
እነዚያ ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙ ቀን ከእናነተ የሸሹት ሰዎች፥ በዚያ በሠሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸዉ ሰይጣን ነዉ፤ አላህም ከነሱ በእርግጥ ይቅር አለ፤ አላህ መሐሪ በቅጣት የማይቸኩል ነዉና

Indeed, those of you who turned back on the day the two armies met, it was Satan who caused them to slip because of some [blame] they had earned. But Allah has already forgiven them. Indeed, Allah is Forgiving and Forbearing.

3:156
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደነዚያ እንደ ካዱትና ስለ ወንድሞቻቸዉ በምድር ላይ በተጓዙ ወይም ዘማቾች በሆኑ ጊዜ፣ እኛ ዘንድ በነበሩ ኖሮ ባልሞቱም ባልተገደሉም ነበር እንደሚሉት አትሁኑ፤ አላህ ይኽንን በልቦቻቸዉ ዉስጥ ጸጸት ያደርግባቸዉ ዘንድ (ይህንን አሉ)። አላህም ሕያዉ ያደርጋል፤ ይገድላልም፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነዉ።

O you who have believed, do not be like those who disbelieved and said about their brothers when they traveled through the land or went out to fight, "If they had been with us, they would not have died or have been killed," so Allah makes that [misconception] a regret within their hearts. And it is Allah who gives life and causes death, and Allah is Seeing of what you do.

3:157
በአላህም መንገድ ብትገደሉ ወይም፤ በትሞቱ፥ ከአላህ የሆነዉ ምሕረትና እዝነት (ከእነርሱ) ከሚሰበስቡት ሀብት በእርግጥ በላጭ ነው።

And if you are killed in the cause of Allah or die - then forgiveness from Allah and mercy are better than whatever they accumulate [in this world].

3:158
ብትሞቱም፥ ወይም ብትገደሉ፣ በእርግጥ ወደ አላህ ብቻ ትሰበሰባላችሁ።

And whether you die or are killed, unto Allah you will be gathered.

3:159
ከአላህም በሆናችሁ ችሮታ ለዘብክላቸዉ። ዐመለ መጥፎ ልበ ደረቅም በሆንክ ኖሮ ከዙርያህ በተበተኑ ነበር። ከነርሱም ይቅር በል። ለነርሱም ምሕረት ለምንላቸዉ። በነገሩም ሁሉ አማክራቸዉ። ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ። አላህ በራሱ ላይ ተመኪዮችን ይወዳልና

So by mercy from Allah , [O Muhammad], you were lenient with them. And if you had been rude [in speech] and harsh in heart, they would have disbanded from about you. So pardon them and ask forgiveness for them and consult them in the matter. And when you have decided, then rely upon Allah . Indeed, Allah loves those who rely [upon Him].

3:161
ለነቢይም ሰለባን መደበቅ አይገባዉም ሰላባንም የሚደብቅ ሰዉ በትንሣኤ ቀን በደበቀዉ ነገር (ተሸክሞ) ይመጣል። ከዚያም ነፍስ ሁሉ የሥራዉን ዋጋ ትሞላለች እነርሱም አይበደሉም።

It is not [attributable] to any prophet that he would act unfaithfully [in regard to war booty]. And whoever betrays, [taking unlawfully], will come with what he took on the Day of Resurrection. Then will every soul be [fully] compensated for what it earned, and they will not be wronged.

3:162
የአላህን ዉዴታ የተከተለ ሰዉ፣ ከአላህ በሆነ ቁጣ እንደ ተመለሰና መኖሪያዉ ገሀነም እንደ ሆነ ሰዉ ነውን? መመለሻዉ ምን ይከፋ!

So is one who pursues the pleasure of Allah like one who brings upon himself the anger of Allah and whose refuge is Hell? And wretched is the destination.

3:163
እነርሱ አላህ ዘንድ ባለ ደረጃዎች ናቸዉ፤ አላህም የሚሠሩትን ነገር ተመልካች ነዉ።

They are [varying] degrees in the sight of Allah , and Allah is Seeing of whatever they do.

3:164
አላህ በምእምናን ላይ ከጐሳቸዉ የሆነን፤ በነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ፥ የሚጠራቸዉ፥ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸዉም የሆነን መልክተኛ በዉስጣቸዉ በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሰላቸዉ፤ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልጽ ስሕተት ዉስጥ ነበሩ።

Certainly did Allah confer [great] favor upon the believers when He sent among them a Messenger from themselves, reciting to them His verses and purifying them and teaching them the Book and wisdom, although they had been before in manifest error.

3:165
ሁለት ብጤዎችዋን በእርግጥ ያገኛችሁ የሆነች መከራ (መጠቃት) ባገኘቻችሁ ጊዜ ይህ ከየት ነዉ አላቸሁን? እርሱ ከነፍሶቻችሁ ዘንድ ነዉ። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነዉና በላቸዉ።

Why [is it that] when a [single] disaster struck you [on the day of Uhud], although you had struck [the enemy in the battle of Badr] with one twice as great, you said, "From where is this?" Say, "It is from yourselves." Indeed, Allah is over all things competent.

3:166
ሁለቱ ጭፍሮችም በተጋጠሙ ቀን የደረሰባችሁ በአላህ ፈቃድ ነዉ፤ ምእምናንንም (ሊፈትንና) ሊገልጽ ነዉ

And what struck you on the day the two armies met was by permission of Allah that He might make evident the [true] believers.

3:167
እነዚያንም የነፈቁትንና ለነርሱ ኑ፤ በአላህ መንገድ ተጋደሉ፤ ወይም ተከላከሉ፤ የተባሉትን ሊገልጽ ነዉ መዋጋትን (መኖሩን) ብናዉቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር አሉ፤ እነርሱ ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክሕደት የቀረቡ ናቸዉ፤ በልቦቻቸዉ የሌለዉን በአፎቻቸዉ ይናገራሉ አላህም የሚደብቁትን አዋቂ ነዉ።

And that He might make evident those who are hypocrites. For it was said to them, "Come, fight in the way of Allah or [at least] defend." They said, "If we had known [there would be] fighting, we would have followed you." They were nearer to disbelief that day than to faith, saying with their mouths what was not in their hearts. And Allah is most Knowing of what they conceal -

3:168
እነዚያ (ከትግል) የቀሩ ሲሆን ለወንድሞቻቸዉ- በታዘዙን ኖሮ ባልተገደሉ ነበር ያሉ ናቸዉ፥ እዉነተኞች እንደሆናችሁ ከነፍሶቻችሁ ላይ ሞትን ገፍትሩ በላቸዉ።

Those who said about their brothers while sitting [at home], "If they had obeyed us, they would not have been killed." Say, "Then prevent death from yourselves, if you should be truthful." them, nor will they grieve.

3:169
እነዚያን በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሙታን አድርገህ አትገምታቸዉ። በእርግጥ እነርሱ እጌታቸዉ ዘንድ ሕያዋን ናቸዉ፤ ይመገባሉ።

And never think of those who have been killed in the cause of Allah as dead. Rather, they are alive with their Lord, receiving provision,

3:170
አላህ ከችሮታዉ በሰጣቸዉ ነገር ተደሳቾች ሲኾ (ይመገባሉ)፤ በነዚያም ከኋላቸዉ ገና በነርሱ ባልተከተሉት*** በነርሱ ላይ ፍርሃት ባለመኖሩና እነርሱም የማያዝኑ በመሆናቸዉ ይደሰታሉ።
*** ባልሞቱት ወንድሞቻቸው


Rejoicing in what Allah has bestowed upon them of His bounty, and they receive good tidings about those [to be martyred] after them who have not yet joined them - that there will be no fear concerning

3:171
ከአላህ በሆነ ጸጋና ልግስና አላህም የምእምናንን ምንዳ የማያጠፋ በመሆኑ ይደሰታሉ።

They receive good tidings of favor from Allah and bounty and [of the fact] that Allah does not allow the reward of believers to be lost -

3:172
እነዚያ መቁሰል ካገኛቸዉ በኋላ ለአላህና ለመልክተኛዉ የታዘዙትን ከነሱ ለነዚያ በጐ ለሠሩትና ለተጠነቀቁት ታላቅ ምንዳ አላቸዉ።

Those [believers] who responded to Allah and the Messenger after injury had struck them. For those who did good among them and feared Allah is a great reward -

3:173
እነዚያ ሰዎች ለነርሱ ፡- ሰዎች ለናንተ (ጦርን) አከማችተዋልና ፍሩዋቸዉ ያሉዋቸዉና (ይህም) እምነትን የጨመረላቸዉ በቂያችንም አላህ ነዉ፥ ምን ያምርም መጠጊያ! ያሉ ናቸዉ።

Those to whom hypocrites said, "Indeed, the people have gathered against you, so fear them." But it [merely] increased them in faith, and they said, "Sufficient for us is Allah , and [He is] the best Disposer of affairs."

3:174
ከአላህም በሆነ ጸጋና ችሮታ ክፉ ነገር ያልነካቸዉ ሆነዉ ተመለሱ፤ የአላህንም ዉዴታ ተከትተሉ፤ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነዉ

So they returned with favor from Allah and bounty, no harm having touched them. And they pursued the pleasure of Allah , and Allah is the possessor of great bounty.

3:175
ይሃቸዉ፣ ሰይጣን ብቻ ነዉ፣ ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል፤ አትፍሩዋቸውም፤ ምእምናንም እንደሆናችሁ ፍሩኝ።

That is only Satan who frightens [you] of his supporters. So fear them not, but fear Me, if you are [indeed] believers.

3:176
እነዚያም በክሕደት የሚቻኮሉት አያሳዝኑህ። እነርሱ ፈጽሞ አላህን በምንም አይጐዱምና፤ አላህ በመጨረሻይቱ ዓለም ለነሱ ዕድልን ላያደርግ ይሻል፤ ለነርሱም ታላቅ ቅጣት አላቸዉ።

And do not be grieved, [O Muhammad], by those who hasten into disbelief. Indeed, they will never harm Allah at all. Allah intends that He should give them no share in the Hereafter, and for them is a great punishment.

3:177
እነዚያ ክህደት በእምነት የለወጡ፥ አላህን በምንም ነገር ፈጽሞ አይጐዱትም፤ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸዉ።

Indeed, those who purchase disbelief [in exchange] for faith - never will they harm Allah at all, and for them is a painful punishment.

3:178
እነዚያ የካዱት ሰዎች እነርሱን ማዘግየታችንን ለነፍሶቻቸዉ ደግ ነገር ነዉ ብለዉ አያስቡ፣ እነርሱን የምናዘገያቸዉ ኃጢአትን እንዲጨምሩ ብቻ ነዉ፤ ለነሱም አዋራጅ ስቃይ አላቸዉ።

And let not those who disbelieve ever think that [because] We extend their time [of enjoyment] it is better for them. We only extend it for them so that they may increase in sin, and for them is a humiliating punishment.

3:179
አላህ መጥፎዉን ከመልካሙ እስከሚለይ ድረስ ምእምናንን እናንተ በርሱ ላይ ባላችሁበት (ሁኔታ) ላይ የሚተዉ አይደለም፤ አላህም ሩቁን ነገር የሚያሳውቃችሁ አይደለም፤ ግን አላህ ከመልክተኞቹ የሚሻዉን ይመርጣል፤ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ። ብታምኑና ብትጠነቀቁም ለናንተ ታላቅ ምንዳ አላችሁ።

Allah would not leave the believers in that [state] you are in [presently] until He separates the evil from the good. Nor would Allah reveal to you the unseen. But [instead], Allah chooses of His messengers whom He wills, so believe in Allah and His messengers. And if you believe and fear Him, then for you is a great reward.

3:180
እነዚያ አላህ ከችሮታዉ በሰጣቸዉ ገንዘብ የሚነፍጉ እርሱ ለነሱ ደግ አይምሰላቸዉ፤ ይልቁንም፤ እርሱ ለነሱ መጥፎ ነዉ፤ ያንን በርሱ የነፈጉበትን በትንሣኤ ቀን (እባብ ኾኖ) ይጠለቃሉ። የሰማያትና የምድርም ዉርስ ለአላህ ብቻ ነዉ፤ አላህም በሚሠሩት ሁሉ ዉስጥ ዐዋቂ ነዉ።

And let not those who [greedily] withhold what Allah has given them of His bounty ever think that it is better for them. Rather, it is worse for them. Their necks will be encircled by what they withheld on the Day of Resurrection. And to Allah belongs the heritage of the heavens and the earth. And Allah , with what you do, is [fully] Acquainted

3:181
የእነዚያን አላህ ድኻ ነዉ፥ እኛ ግን ከበርቴዎች ነን ያሉትን ሰዎች ቃል አላህ በእርግጥ ሰማ፤ ያንን ያሉትንና ነቢያትን ያለ ሕግ መግደላቸዉን በእርግጥ እንጽፋለን፤ የእሳትንም ስቃይ ቅመሱ እንላቸዋለን።

Allah has certainly heard the statement of those [Jews] who said, "Indeed, Allah is poor, while we are rich." We will record what they said and their killing of the prophets without right and will say, "Taste the punishment of the Burning Fire.

3:182
ያ (ስቃይ) እጆቻችሁ ባሳለፉት ሥራ ነዉ። አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነዉ።

That is for what your hands have put forth and because Allah is not ever unjust to [His] servants."

3:183
እነዚያ ለማንኛዉም መልክተኛ እሳት የምትበላዉ የሆነን ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ ላናምን አላህ ወደኛ አዟል ያሉ ናቸዉ፤ መልክተኞች ከኔ በፊት በታምራትና በዚያም ባላችሁት (ቁርባን) በእርግጥ መጥተዉላችኋል፣ እዉነተኞች ከሆናችሁ ታድያ ለምን ገደላችኋቸዉ? በላቸዉ።

[They are] those who said, "Indeed, Allah has taken our promise not to believe any messenger until he brings us an offering which fire [from heaven] will consume." Say, "There have already come to you messengers before me with clear proofs and [even] that of which you speak. So why did you kill them, if you should be truthful?"

3:184
ቢያስተባብሉህም ከአንተ በፊት በግልጽ ታምራትና በጹሁፎች በብሩህ መጽሐፍም፥ የመጡት መልክተኞች በእርግጥ ተስተባብለዋል።

Then if they deny you, [O Muhammad] - so were messengers denied before you, who brought clear proofs and written ordinances and the enlightening Scripture.

3:185
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት** በትንሣኤ ቀን ብቻ ነዉ። ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ*** ሰዉ፣ በእርግጥ ምኞቱን አገኘ ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሣሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም።
** የምትሰጡት *** እንዲገባ የተደረገ


Every soul will taste death, and you will only be given your [full] compensation on the Day of Resurrection. So he who is drawn away from the Fire and admitted to Paradise has attained [his desire]. And what is the life of this world except the enjoyment of delusion.

3:186
በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ በእርግጥ ትፈተናላችሁ፤ ከነዚያም ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትና ከነዚያም ከአጋሩት፥ ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፤ ብትታገሱና ብትጠነቀቁ፥ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነዉ።

3 You will surely be tested in your possessions and in yourselves. And you will surely hear from those who were given the Scripture before you and from those who associate others with Allah much abuse. But if you are patient and fear Allah - indeed, that is of the matters [worthy] of determination.

3:187
አላህ የነዚያን መጽሐፉን የተሰጡትን ቃል ኪዳን ለሰዎች በእርግጥ ታብራሩታላችሁ፥ አትደብቁትምም፥ በማለት የያዘባቸዉን (አስታዉሱ)፤ በጀርባዎቻቸዉም ኋላ ጣሉት፤ በርሱም ጥቂቱን ዋጋ ገዙ፤ የሚገዙትም ነገር ከፋ!

And [mention, O Muhammad], when Allah took a covenant from those who were given the Scripture, [saying], "You must make it clear to the people and not conceal it." But they threw it away behind their backs and exchanged it for a small price. And wretched is that which they purchased.

3:188
እነዚያን በሠሩት ነገር የሚደሰቱትንና ባልሠሩትም መመስገንን የሚወዱትን አትሰብ፤ ከቅጣት በመዳን ላይ ናቸዉ ብለህ አትሰባቸው፤ ለነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸዉ።

And never think that those who rejoice in what they have perpetrated and like to be praised for what they did not do - never think them [to be] in safety from the punishment, and for them is a painful punishment.

3:189
የሰማያትና የምድር ንግስና ለአላህ ብቻ ነዉ፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነዉ።

And to Allah belongs the dominion of the heavens and the earth, and Allah is over all things competent.

3:190
ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር፣ ሌሊትና ቀንም በመተካካት፥ ለባለ አእምሮዎች በእርግጥ ምልክቶች አሉ።

Indeed, in the creation of the heavens and the earth and the alternation of the night and the day are signs for those of understanding.

3:191
(እነርሱም) እነዚያ ቆመዉ ተቀምጠዉም፥ በጐኖቻቸዉ ተጋድመዉም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚይስተነትኑ ፡- ጌታችን ሆይ! ይህን በከንቱ አልፈጠርከዉም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን የሚሉ ናቸዉ።

Who remember Allah while standing or sitting or [lying] on their sides and give thought to the creation of the heavens and the earth, [saying], "Our Lord, You did not create this aimlessly; exalted are You [above such a thing]; then protect us from the punishment of the Fire.

3:192
ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታገባውን ሰው በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበደለኞችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም።

Our Lord, indeed whoever You admit to the Fire - You have disgraced him, and for the wrongdoers there are no helpers.

3:193
ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፤ አመንንም፤ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፤ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፤ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤

Our Lord, indeed we have heard a caller calling to faith, [saying], 'Believe in your Lord,' and we have believed. Our Lord, so forgive us our sins and remove from us our misdeeds and cause us to die with the righteous.

3:194
ጌታችን ሆይ! በመልክተኞችህም ላይ ተስፋ ቃል ያደረግክልንን ስጠን፤ በትንሣኤ ቀንም አታዋርደን፤ አንተ ቀጠሮን አታፈርስምና፤ (የሚሉ ናቸዉ)።

Our Lord, and grant us what You promised us through Your messengers and do not disgrace us on the Day of Resurrection. Indeed, You do not fail in [Your] promise."

3:195
ጌታቸዉም እኔ ከናንተ ከወንድ ወይም ከሴት፥ የሠሪን ሥራ አላጠፋም፤ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነዉ፤ በማለት ለነርሱ ልመናቸዉን ተቀበለ እነዚያም የተሰደዱ፥ ከአገሮቻቸዉም የተባረሩ፣ በመንገዴም የተጠቁ፣ የተጋደሉም፣ የተገደሉም፥ ክፉ ሥራዎቻቸዉን ከነርሱ በእርግጥ አብሳለሁ፤ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸዉን ገነቶች በእርግጥ አገባቸዋለሁ፤ ከአላህ ዘንድ የሆነን ምንዳ (ይመነዳሉ)፤ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አለ።
*** ከመካ ወደ ሐበሻ ወይንም ወደ መዲና


And their Lord responded to them, "Never will I allow to be lost the work of [any] worker among you, whether male or female; you are of one another. So those who emigrated or were evicted from their homes or were harmed in My cause or fought or were killed - I will surely remove from them their misdeeds, and I will surely admit them to gardens beneath which rivers flow as reward from Allah , and Allah has with Him the best reward."

3:196
የነዚያ የካዱት ሰዎች በአገሮች መንፈላሰስ አያታልህ።

Be not deceived by the [uninhibited] movement of the disbelievers throughout the land.

3:197
አነስተኛ ጥቅም ነዉ፤ ከዚያም መኖሪያቸዉ ገሀነም ናት፤ ምን ትከፋም ምንጣፍ

[It is but] a small enjoyment; then their [final] refuge is Hell, and wretched is the resting place.

3:198
ግን እነዚያ ጌታቸዉን የፈሩ ለነሱ ከስሮቻቸዉ ወንዞች የሚፈሱባቸዉ ገነቶች በዉስጧ ዘዉታሪዎች ሲሆን ከአላህ ዘንድ (የተሰጡ) መስተንግዶዎች አሏቸዉ፤ አላህም ዘንድ ያለዉ (ምንዳ) ለበጐ ሠሪዎች በላጭ ነዉ

But those who feared their Lord will have gardens beneath which rivers flow, abiding eternally therein, as accommodation from Allah . And that which is with Allah is best for the righteous.

3:199
ከመጽሐፉም ባለቤቶች*** ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለዉጡ ሲኾኑ፣ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደዉ፣ በዚያም ወደነርሱ በተወረደዉ የሚያምኑ ሰዎች አሉ፤ እነዚያ ለነርሱ በጌታቸዉ ዘንድ ምንዳቸዉ አላቸዉ፤ አላህ ምርመራዉ ፈጣን ነዉ።
*** እንደ አብደላህን ሰላምና እንደሐበሻ ንጉሥ


And indeed, among the People of the Scripture are those who believe in Allah and what was revealed to you and what was revealed to them, [being] humbly submissive to Allah . They do not exchange the verses of Allah for a small price. Those will have their reward with their Lord. Indeed, Allah is swift in account.

3:200
እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ታገሡ፤ ተበራቱም (በጦር ኬላ ላይ) ተሰለፉም ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ።

O you who have believed, persevere and endure and remain stationed and fear Allah that you may be successful.

Copyright 2013, AmharicQuran.com