Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ዐንከቡት (የሸረሪት ምዕራፍ)

29:1
አ.ለ.መ. (አሊፍ ላም ሚም)

Alif, Lam, Meem

29:2
ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚትተዉ መሆናቸውን ጠረጠሩን?

Do the people think that they will be left to say, "We believe" and they will not be tried?

29:3
እነዚያንም ከነሱ በፊት የነበሩትን በእርግጥ ፈትነናል፤ እነዚያንም እውነት የተናገሩትን አላህ በእርግጥ ያውቃል፤ ውሸታሞችንም ያውቃል።

But We have certainly tried those before them, and Allah will surely make evident those who are truthful, and He will surely make evident the liars.

29:4
ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሊያመልጡን ይጥረጥራሉን? ያ የሚፈርዱት (ፍርድ) ከፋ።

Or do those who do evil deeds think they can outrun Us? Evil is what they judge.

29:5
የአላህን መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው፣ (ይዘጋጅ)፤ የአላህ ቀጠሮ በርግጥ መጪ ነውና፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው።

Whoever should hope for the meeting with Allah - indeed, the term decreed by Allah is coming. And He is the Hearing, the Knowing.

29:6
የታገለ ሰውም የሚታገለው ለነፍሱ ነው፤ አላህ ከዓለማት በእርግጥ ተብቃቂ ነውና።

And whoever strives only strives for [the benefit of] himself. Indeed, Allah is free from need of the worlds.

29:7
እነዚያም ያመኑ፤ መልካሞችንም የሠሩ መጥፎዎቹም ሥራዎቻቸውን ከነሱ ላይ እናብላቸዋለን፤ በዚያም ይሠሩት በነበሩት መልካም ሥራ በእርግጥ እንመነዳቸዋለን።

And those who believe and do righteous deeds - We will surely remove from them their misdeeds and will surely reward them according to the best of what they used to do.

29:8
ሰውንም በወላጆቹ መልካም አድራጎትን አዘዝነው፤ ላንተም በርሱ ዕውቀት የሌለህን (ጣዖት) በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው፤ መመለሻችሁ ወደኔ ነው፤ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ።

And We have enjoined upon man goodness to parents. But if they endeavor to make you associate with Me that of which you have no knowledge, do not obey them. To Me is your return, and I will inform you about what you used to do.

29:9
እነዚያም ያመኑ፤ መልካም ሥራዎችን የሠሩ በደጋጎቹ ውስጥ በእርግጥ እናገባቸዋለን።

And those who believe and do righteous deeds - We will surely admit them among the righteous [into Paradise].

29:10
ከሠዎችም በአላህ አመንን የሚል ሰው አለ፤ በአላህም (በማመኑ) በተሰቃዬ ጊዜ የሰዎችን ማሰቃየት እንደ አላህ ቅጣት ያደርጋል፤ ከጌታህም እርዳታ ቢመጣ፣ እኛ በእርግጥ ከናንተ ጋር ነበርን ይላሉ፤ አላህ በዓለማት ሕዝብ ልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ አይደለምን?

And of the people are some who say, "We believe in Allah ," but when one [of them] is harmed for [the cause of] Allah , they consider the trial of the people as [if it were] the punishment of Allah . But if victory comes from your Lord, they say, "Indeed, We were with you." Is not Allah most knowing of what is within the breasts of all creatures?

29:11
አላህም እነዚያን ያመኑትን በእርግጥ ያውቃል፤ መናፍቆቹንም ያውቃል።

And Allah will surely make evident those who believe, and He will surely make evident the hypocrites.

29:12
እነዚያም የካዱት ሰዎች ለነዚያ ላመኑት መንገዳችንን ተከተሉ፤ ኃጢያቶቻችሁንም እንሸከማለን አሉ፤ እነሱም ከኀጢአቶቻቸው ምንንም ተሸካሚዎች አይደሉም፤ እነርሱ በርግጥ ውሸታሞች ናቸው።

And those who disbelieve say to those who believe, "Follow our way, and we will carry your sins." But they will not carry anything of their sins. Indeed, they are liars.

29:13
ሸክሞቻቸውንና ከሸክሞቻቸው ጋር (ሌሎች) ሸክሞችንም በእርግጥ ይሸከማሉ፤ በትንሣኤም ቀን ይቀጥፉት ከነበሩት በእርግጥ ይጠየቃሉ።

But they will surely carry their [own] burdens and [other] burdens along with their burdens, and they will surely be questioned on the Day of Resurrection about what they used to invent.

29:14
ኑሕንም ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፤ በውስጣቸውም ሺሕ ዓመት አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ፤ እነርሱ በዳዮች ሆነውም የውሃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው።

And We certainly sent Noah to his people, and he remained among them a thousand years minus fifty years, and the flood seized them while they were wrongdoers.

29:15
ኑሕንና የመርከቢቱንም ጓዶች አዳናቸው፤ እርስውንም ለዓለማት ታምር አደረግናት።

But We saved him and the companions of the ship, and We made it a sign for the worlds.

29:16
ኢብራሂምንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፦ አላህን ተገዙ፤ ፍሩትም፤ ይሃችሁ የታውቁ ብትሆኑ ለናንተ በላጭ ነው።

And [We sent] Abraham, when he said to his people, "Worship Allah and fear Him. That is best for you, if you should know.

29:17
ከአላህ ሌላ የምትግገዙት ጣዖታትን ብቻ ነው፤ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዙዋችው ለናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፤ ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ፤ ተገዙትም፤ ለርሱም አመስግኑ፤ ወደርሱ ትመለሳላችሁ።

You only worship, besides Allah , idols, and you produce a falsehood. Indeed, those you worship besides Allah do not possess for you [the power of] provision. So seek from Allah provision and worship Him and be grateful to Him. To Him you will be returned."

29:18
ብታስተባብሉም ከፊታችሁ የነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ አስተባብለዋል፤ በመልክተኛውም ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም።

And if you [people] deny [the message] - already nations before you have denied. And there is not upon the Messenger except [the duty of] clear notification.

29:19
አላህ መፍጠርን እንዴት እንደሚጀምር ከዚያም እንዴት እንደሚመልሰው አይመለከቱምን? ይህ በአላህ ላይ ቀላል ነው።

Have they not considered how Allah begins creation and then repeats it? Indeed that, for Allah , is easy.

29:20
፦ በምድር ላይ ኺዱ፤ መፍጠርን እንዴት እንደ ጀመረ ተመልከቱ፤ ከዚያም፤ አላህ የመጨረሻይቱን መነሳት ያስነሳል፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና በላቸው።

Say, [O Muhammad], "Travel through the land and observe how He began creation. Then Allah will produce the final creation. Indeed Allah , over all things, is competent."

29:21
የሚሻውን ሰው ይቀጣል፤ የሚሻውንም ሰው ያዝንለታል፤ ወደርሱም ትመለሳላችሁ፤

He punishes whom He wills and has mercy upon whom He wills, and to Him you will be returned.

29:22
እናንተም በምድርም ሆነ በሰማይ የምታቅቱ አይደላችሁም፤ ከአላህም ሌላ ረዳትም ተከላካይም የላችሁም።

And you will not cause failure [to Allah ] upon the earth or in the heaven. And you have not other than Allah any protector or any helper.

29:23
እነዚያም በአላህ አንቀጾችና በመገናኘቱ የካዱ እነዚያ ከእዝነቴ ተስፋን ቆረጡ፤ እነዚያም ለነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው።

And the ones who disbelieve in the signs of Allah and the meeting with Him - those have despaired of My mercy, and they will have a painful punishment.

29:24
የሕዝቦቹም (1) መልስ ፦ ግደሉት፤ ወይም አቃጥሉት ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፤ ከእሳቲቱም አላህ አዳነው፤ በዚህ ውስጥ ለምምይምን ሕዝቦች ታማቶች አሉበት።

And the answer of Abraham's people was not but that they said, "Kill him or burn him," but Allah saved him from the fire. Indeed in that are signs for a people who believe.

29:25
(ኢብራሂም) አለም፦ ከአላህ ሌላ ጣዖታትን (አማልክት) የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው፤ ከዚያም በትንሣኤ ቀን ከፊላችሁ በከፊሉ ይክዳል፤ ከፊላችሁም ከፊሉን ይረግማል፤ መኖሪያችሁም እሳት ናት፤ ለናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም።

And [Abraham] said, "You have only taken, other than Allah , idols as [a bond of] affection among you in worldly life. Then on the Day of Resurrection you will deny one another and curse one another, and your refuge will be the Fire, and you will not have any helpers."

29:26
ሎጥም ለርሱ አመነ (ኢብራሂም) ፦ እኔ ወደ ጌታዬ ተሰዳጅ ነኝ፤ እነሆ እርሱ አሸናፊው ጥበበኛው ነውና አለም።

And Lot believed him. [Abraham] said, "Indeed, I will emigrate to [the service of] my Lord. Indeed, He is the Exalted in Might, the Wise."

29:27
ለርሱም ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው፤ በዘሩም ውስጥ ነቢይነትንና መጽሐፍን አደረግን፤ ምንዳውንም በቅርቢቱ ዓለም ሰጠነው፤(2) እሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከደጋጎቹ ነው።

And We gave to Him Isaac and Jacob and placed in his descendants prophethood and scripture. And We gave him his reward in this world, and indeed, he is in the Hereafter among the righteous.

29:28
ሎጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፦ እናንተ ጠያፍን ሥራ ትሠራላችሁን? በርሷ ከዓለማት አድም አልቀደማችሁም፤

And [mention] Lot, when he said to his people, "Indeed, you commit such immorality as no one has preceded you with from among the worlds.

29:29
እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን? መንገድን ትቆርጣላችሁን? በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን? (አላቸው)፤ የሕዝቦቹም መልስ ከውነተኞቹ እንደ ኾንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።

Indeed, you approach men and obstruct the road and commit in your meetings [every] evil." And the answer of his people was not but they said, "Bring us the punishment of Allah , if you should be of the truthful."

29:30
፦ጌታዬ ሆይ በአመጠኞች ሕዝቦች ላይ እርዳኝ አለ።

He said, "My Lord, support me against the corrupting people."

29:31
መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ እኛ የዚችን ከተማ አጥፊዎች ነን፤ ሰውዎችዋ በዳዮች ነበሩና አሉት።

And when Our messengers came to Abraham with the good tidings, they said, "Indeed, we will destroy the people of that Lot's city. Indeed, its people have been wrongdoers."

29:32
በርሷ ውስጥ ሎጥ አልለ እኮ አላቸው፤ እኛ በውስጧ ያለውን ይበልጥ ዐዋቂ ነን (እርሱን) በእርግጥ እናድነዋለን፤ ቤተሰቦቹንም ጭምር ሚስቱ ብቻ ስትቀር፤ እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከሚቀሩት ናት አሉት።

[Abraham] said, "Indeed, within it is Lot." They said, "We are more knowing of who is within it. We will surely save him and his family, except his wife. She is to be of those who remain behind."

29:33
መልክተኞቻችንም ሎጥን በመጡት ጊዜ በነሱ ምክንያት አዘነ፤ በነርሱም ልቡ ተጨነቀ፤ አትፍራ አትዘንም፤ እኛ አዳኞችህ ነን፤ ቤተሰቦችህንም፤ ሚስትህ ብቻ ስትቀር፤ እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎች ናት አሉትም።

And when Our messengers came to Lot, he was distressed for them and felt for them great discomfort. They said, "Fear not, nor grieve. Indeed, we will save you and your family, except your wife; she is to be of those who remain behind.

29:34
እኛ በይህች ከተማ ሰዎች ላይ ያምጡ በነበሩት ምክንያት ከሰማይ ቅጣትን አውራጆች ነን።

Indeed, we will bring down on the people of this city punishment from the sky because they have been defiantly disobedient."

29:35
በእርግጥ ለሚያስቡ ሰዎች ከርሷ ግልጽ ምልክትን ተውን (አስቀረን)።

And We have certainly left of it a sign as clear evidence for a people who use reason.

29:36
ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹብዐይብን (ላክን)፤ ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ የመጨረሻውንም ቀን ፍሩ፤ በምድርም ውስጥ የምታጠፉ ሆናችሁ አታበላሹ አላቸውም።

And to Madyan [We sent] their brother Shu'ayb, and he said, "O my people, worship Allah and expect the Last Day and do not commit abuse on the earth, spreading corruption."

29:37
አስተባበሉትም፤ የምድር መንቀጥቀጥም ያዘቻቸው፤ ባገራቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አነጉ።

But they denied him, so the earthquake seized them, and they became within their home [corpses] fallen prone.

29:38
ዓድንና ሰሙድንም (አጠፋን)፤ ከመኖሪያዎቻቸው (ፍርራሾች በኩል መጥፋታቸው) ለናንተ በውነት ተገለጠላችሁ፤ ሰይጣንም ስራዎቻቸውን ለነርሱ ሸለመላቸው፤ ከመንገድም አገዳቸው፤ የማስተዋልም ባለቤቶች ነበሩ፤ (ግን አላስተዋሉም)።

And [We destroyed] 'Aad and Thamud, and it has become clear to you from their [ruined] dwellings. And Satan had made pleasing to them their deeds and averted them from the path, and they were endowed with perception.

29:39
ቃሩንንም፣ ፈርዖንንም፣ ሃማንንም (አጠፋን)፤ ሙሳም በታምራቶች በእርግጥ መጣባቸው፤ በምድርም ኮሩ፤ አምላጪዎችም አልነበሩም።

And [We destroyed] Qarun and Pharaoh and Haman. And Moses had already come to them with clear evidences, and they were arrogant in the land, but they were not outrunners [of Our punishment].

29:40
ሁሉንም በሐጢአቱ ያዝነው፤ከነሱ ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፋስን የላክንበት አለ ከነሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አለ፤ ከነሱም ውስጥ በርሱ ምድርን ይደረባንበት አለ፤ ከነሱም ውስጥ ያሰጠምነው አለ፤ አላህ የሚበድላቸው አልነበረም፤ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ።

So each We seized for his sin; and among them were those upon whom We sent a storm of stones, and among them were those who were seized by the blast [from the sky], and among them were those whom We caused the earth to swallow, and among them were those whom We drowned. And Allah would not have wronged them, but it was they who were wronging themselves.

29:41
የነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ቢጤ ነው ከቤቶችም ሁሉ ደካማው ይሽረሪት ቤት ነው፤ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይይዟቸውም ነበር)።

The example of those who take allies other than Allah is like that of the spider who takes a home. And indeed, the weakest of homes is the home of the spider, if they only knew.

29:42
አላህ ያንን ከርሱ ሌላ የሚግገዙትን ማንኛውንም ያውቃል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።

Indeed, Allah knows whatever thing they call upon other than Him. And He is the Exalted in Might, the Wise.

29:43
እነዚህንም ምሳሌዎች ለሰዎች እንገልጻቸዋለን፤ ከሊቃውንቶቹም በስተቀር ሌሎቹ አያውቋትም።

And these examples We present to the people, but none will understand them except those of knowledge.

29:44
አላህ ሰማያትንና ምድርን እውነተኛ ሆኖ ፈጠረ፤ በዚህ ውስጥ ለምዕመናን ታምር አለበት።

Allah created the heavens and the earth in truth. Indeed in that is a sign for the believers.

29:45
ከመጽሐፉ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ ሶላትንም ድንቡን ጠብቀህ ስገድ፤ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፤ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል።

Recite, [O Muhammad], what has been revealed to you of the Book and establish prayer. Indeed, prayer prohibits immorality and wrongdoing, and the remembrance of Allah is greater. And Allah knows that which you do.

29:46
የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፤ ከነሱ ነዚያን የበደሉትን ሲቀር በሉም ፦ በዚያ ወደኛ በተወረደው፣ ወደናንተም በተወረደው አመንን፤ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፤ እኛም ለርሱ ታዛዦች ነን።

And do not argue with the People of the Scripture except in a way that is best, except for those who commit injustice among them, and say, "We believe in that which has been revealed to us and revealed to you. And our God and your God is one; and we are Muslims [in submission] to Him."

29:47
እንደዚሁም ወዳንተ መጽሐፍን አወረድን፤ እነዚያም መጽሐፍን የሰጠናቸው፤ በርሱ ያምናሉ፤ ከነዚህም (ከመካ ሰዎች) በርሱ የሚያምኑ አሉ፤ በታምራቶቻችንም ከሐዲዎቹ እንጂ ማንም አይክድም።

And thus We have sent down to you the Qur'an. And those to whom We [previously] gave the Scripture believe in it. And among these [people of Makkah] are those who believe in it. And none reject Our verses except the disbelievers.

29:48
ከርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም፤ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራሩ ነበር።

And you did not recite before it any scripture, nor did you inscribe one with your right hand. Otherwise the falsifiers would have had [cause for] doubt

29:49
አይደለም እርሱ (ቁርአን) በነዚያ ዕውቀትን በተሰጡት ሰዎች ልቦች ውስጥ (የጠለቀ) ግልጾች አንቀጾች ነው፤ በአንቀጾቻችንም በዳዮች እንጂ ሌላው አይክድም።

Rather, the Qur'an is distinct verses [preserved] within the breasts of those who have been given knowledge. And none reject Our verses except the wrongdoers.

29:50
በርሱ ላይም ከጌታው ዘንድ ታምራቶች፣ ለምን አልተወረዱም አሉ፤ ታምራቶች አላህ ዘንድ ብቻ ናቸው፤ እኔም ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ በላቸው።

But they say, "Why are not signs sent down to him from his Lord?" Say, "The signs are only with Allah , and I am only a clear warner."

29:51
እኛ መጽሐፉን በነሱ ላይ የሚነበብ ሆኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ችሮታና ግሣጼ አለበት።

Sahih International And is it not sufficient for them that We revealed to you the Book which is recited to them? Indeed in that is a mercy and reminder for a people who believe.

29:52
በኔና በናንተ መካክል መስካሪ በአላህ በቃ፤ በሰማያትና በምድርም ያለውን ሁሉ ያውቃል በላቸው፤ እነዚያም በብላሽ ነገር ያመኑ፣ በአላህም የካዱ፣ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎች ናቸው።

Say, "Sufficient is Allah between me and you as Witness. He knows what is in the heavens and earth. And they who have believed in falsehood and disbelieved in Allah

29:53
በቅጣትም ያስቸኩሉሃል፤ የተወሰነም ጊዜ ባልነበረ ኖሮ፣ ቅጣቱ በመጣባቸው ነበር፤ እነሱ የማያውቁ ሲሆኑም በድንገት በእርግጥ ይመጣባቸዋል።

And they urge you to hasten the punishment. And if not for [the decree of] a specified term, punishment would have reached them. But it will surely come to them suddenly while they perceive not.

29:54
በቅጣትም ያስቸኩሉሃል፤ ገሀነምም በከሐዲዎች በእርግጥ ከባቢ ናት።

They urge you to hasten the punishment. And indeed, Hell will be encompassing of the disbelievers

29:55
ቅጣቱ ከበላያቸው፣ ከእግሮቻቸውም ሥር በሚሸፍናቸው ቀን በሚሸፍናቸው ቀን ትሠሩት የነበራችሁትን ቅመሱ በሚላቸው (ቀን ትከባቸዋለች)።

On the Day the punishment will cover them from above them and from below their feet and it is said, "Taste [the result of] what you used to do."

29:56
እላንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፤ እኔንም ብቻ ተገዙኝ።

O My servants who have believed, indeed My earth is spacious, so worship only Me.

29:57
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ ከዚያም ወደኛ ትመለሳለችሁ።

Every soul will taste death. Then to Us will you be returned.

29:58
እነዚያም ያመኑና መልካም ስራዎችን የሠሩ ከገነት በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ሰገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፤ የሰራተኞች ምንዳ ምንኛ አማረ!

And those who have believed and done righteous deeds - We will surely assign to them of Paradise [elevated] chambers beneath which rivers flow, wherein they abide eternally. Excellent is the reward of the [righteous] workers

29:59
(እነሱ) እነዚያ የታገሡ በጌታቸውም ላይ የሚመኩ ናቸው።

Who have been patient and upon their Lord rely.

29:60
ከተንቀሳቃሺም ምግቧን ለመሸከም የማትችለው ብዙ ናት፣ አላህ ይመግባታል፤ እናንተንም፣ (ይመግባል)፤ እርሱ ሰሚው አዋቂው ነውና።

And how many a creature carries not its [own] provision. Allah provides for it and for you. And He is the Hearing, the Knowing.

29:61
ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ምን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፤ ታዲያ እንዴት ይመለሳሉ።

If you asked them, "Who created the heavens and earth and subjected the sun and the moon?" they would surely say, " Allah ." Then how are they deluded?

29:62
አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሲሳይን ያሰፋል፤ ለርሱም ያጠባል፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና።

Allah extends provision for whom He wills of His servants and restricts for him. Indeed Allah is, of all things, Knowing.

29:63
ከሰማይም ውሃን ያወረደና በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደርጋት ማን እንደ ሆነ ብትጠይቃቸው አላህ ነው፣ በላቸው፤ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።

And if you asked them, "Who sends down rain from the sky and gives life thereby to the earth after its lifelessness?" they would surely say " Allah ." Say, "Praise to Allah "; but most of them do not reason.

29:64
ይህችም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለች፤ የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ሕይወት አገር ናት፤ የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ፤ (ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር)።

And this worldly life is not but diversion and amusement. And indeed, the home of the Hereafter - that is the [eternal] life, if only they knew.

29:65
በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም፣ አላህን መግገዛትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፣ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ውዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ።

And when they board a ship, they supplicate Allah , sincere to Him in religion. But when He delivers them to the land, at once they associate others with Him

29:66
በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱና ሊጠቃቀሙ (ያጋራሉ)፤ ወደ ፊትም (የሚጠብቃቸውን) ያውቃሉ።

So that they will deny what We have granted them, and they will enjoy themselves. But they are going to know.

29:67
ሰዎቹ ከዙሪያቸው ሲነጠቁ እኛ (አገራቸውን) ጸጥተኛ ክልል ማድረጋችንን አያዩምን? በውድቅ ነገር ያምናሉን? በአላህም ጸጋ ይክዳሉን?

Have they not seen that We made [Makkah] a safe sanctuary, while people are being taken away all around them? Then in falsehood do they believe, and in the favor of Allah they disbelieve?

29:68
በአላህ ላይም ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነቱ በመጣለት ጊዜ ከአስዋሽ ይበልጥ በዳይ ማነው? በገሀነም ውስጥ ለከሐዲዎች መኖሪያ የለምን?

And who is more unjust than one who invents a lie about Allah or denies the truth when it has come to him? Is there not in Hell a [sufficient] residence for the disbelievers?

29:69
እነዚያም በኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፤ አላህም በእርግጥ ክበጎ ሠሪዎች ጋር ነው።

And those who strive for Us - We will surely guide them to Our ways. And indeed, Allah is with the doers of good.

Copyright 2013, AmharicQuran.com