Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ነምል (የጉንዳን ምዕራፍ)

27:1
ጠ. ስ. (ጣ ሲን) ይህቺ ከቁር አኑና ከገላጩ መጽሐፍ አንቀጾች ናት።

Ta, Seen. These are the verses of the Qur'an and a clear Book

27:2
ለምእመናን መሪና ብስራት ናት።

As guidance and good tidings for the believers

27:3
ለነዚያ ሶላትን ለሚሰግዱት ዘካንም ለሚሰጡት እነሱም በመጨረሻይቱ ሕይወት እነሱ የሚያረጋግጡት ለሆኑት።

Who establish prayer and give zakah, and of the Hereafter they are certain [in faith].

27:4
እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለነሱ (ክፉ) ሥራዎቻቸውን ሸልመንላቸው (1) ስለዚህ እነርሱ ይዋልላሉ።

Indeed, for those who do not believe in the Hereafter, We have made pleasing to them their deeds, so they wander blindly.

27:5
እነርሱ እነዚያ ክፉ ቅጣት ለነርሱ ያላቸው ናቸው፤ እነሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ በጣም ከሳሪዎቹ ናቸው።

Those are the ones for whom there will be the worst of punishment, and in the Hereafter they are the greatest losers.

27:6
አንተም ቁርአንን ጥበበኛና ዐዋቂ ከሆነው (ጌታህ) ዘንድ በእርግጥ ትሠጣለህ።

And indeed, [O Muhammad], you receive the Qur'an from one Wise and Knowing.

27:7
ሙሳ ለቤተሰቦቹ ፦ እኔ እሳትን አየሁ ከርሷ ወሬን አመጣላችኋለሁ፤ ወይም ትሞቁ ዘንድ የተለኮሰ ችቦን አመጣላችኋለሁ ባለ ጊዜ (የሆነውን አውሳላቸው)።

[Mention] when Moses said to his family, "Indeed, I have perceived a fire. I will bring you from there information or will bring you a burning torch that you may warm yourselves."

27:8
በመጣትም ጊዜ እንዲህ በማለት ተጠራ፤ ፦ በ እሳቲቱ ያለው ሰውና በዙሪያዋ ያሉም ሁሉ ተባረኩ፤ የዓለማትም ጌታ አላህ ጥራት ይገባው፤

But when he came to it, he was called, "Blessed is whoever is at the fire and whoever is around it. And exalted is Allah , Lord of the worlds.

27:9
ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ነኝ።

O Moses, indeed it is I - Allah , the Exalted in Might, the Wise."

27:10
በትርህንም ጣል (ተባለ ጣለም)፤ እርሷ እንደ ትንሽ እባብ በፍጥነት ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ፊቱን ዞሮ ሸሸ፤ አልተመለሰምም፤ ሙሳ ሆይ! አትፍራ፤ እኔ መልክተኞቹ እኔ ዘንድ አይፈሩምና፤

And [he was told], "Throw down your staff." But when he saw it writhing as if it were a snake, he turned in flight and did not return. [ Allah said], "O Moses, fear not. Indeed, in My presence the messengers do not fear.

27:11
ግን የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሐሪ አዛኝ ነኝ፤

Otherwise, he who wrongs, then substitutes good after evil - indeed, I am Forgiving and Merciful.

27:12
እጅህንም በአንገትጌህ ውስጥ አግባ፤ ያለነውር (ያለ ለምጽ) ነጭ ሆና ትወጣለችና፤ በዘጠኝ ታምራት ወደ ፈርዖንና ወደ ሕዝቦቹ (ኺድ)፤ እነርሱ አመጠኞች ሕዝቦች ናቸውና።

And put your hand into the opening of your garment [at the breast]; it will come out white without disease. [These are] among the nine signs [you will take] to Pharaoh and his people. Indeed, they have been a people defiantly disobedient."

27:13
ታምራታችንም ግልጽ ሆና በመታቻቸው ጊዜ ግልጽ ድግምት ነው፤ አሉ።

But when there came to them Our visible signs, they said, "This is obvious magic."

27:14
ነፍሶቻቸው ያረጋገጧት ሲሆኑ ለበደልና ለኩራት በርሷ ካዱ፤ የአመጸኞችም ፈጻሜ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት።

And they rejected them, while their [inner] selves were convinced thereof, out of injustice and haughtiness. So see how was the end of the corrupters.

27:15
ለዳውድና ለሱሌይማንም ዕውቀትን በእርግጥ ሰጠናቸው፤ አሉም፦ ምስጋና ለአላህ ለዚያ ከምእመናን ባሮቹ በብዙዎች ላይ ላበለጠን ይገባው።

And We had certainly given to David and Solomon knowledge, and they said, "Praise [is due] to Allah , who has favored us over many of His believing servants."

27:16
ሱለይማንም ዳውድን ወረሰ፤ አለም፦ ሰዎች ሆይ! የበራሪን ንግግር (የወፍ ቋንቋ) ተስተማርን፤ ከነገሩም ሁሉ ተሰጠን፤ ይህ እርሱ በእርግጥ ግልጽ የሆነ ችሮታ ነው።

And Solomon inherited David. He said, "O people, we have been taught the language of birds, and we have been given from all things. Indeed, this is evident bounty."

27:17
ለሱለይማንም ሰራዊቶቹ ከጋኔን፣ ከሰውም ከበራሪም የሆኑት ተሰበሰቡ እነሱም ይከመከማሉ።

And gathered for Solomon were his soldiers of the jinn and men and birds, and they were [marching] in rows.

27:18
በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን፦ እላንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፤ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ አይሰባብሩዋችሁም አለች።

Until, when they came upon the valley of the ants, an ant said, "O ants, enter your dwellings that you not be crushed by Solomon and his soldiers while they perceive not."

27:19
ከንግግርዋም እየሳቀ ጥርሱን ፈገግ አደረገ፤ ጌታዬ ሆይ! ያቺን በኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውን በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፤ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ አለ።

So [Solomon] smiled, amused at her speech, and said, "My Lord, enable me to be grateful for Your favor which You have bestowed upon me and upon my parents and to do righteousness of which You approve. And admit me by Your mercy into [the ranks of] Your righteous servants."

27:20
በራሪዎቹንም ተመለከተ፤ አለም፦ ሁድሁድን (1) ለምን አላየውም! በውነቱ ከራቁት ነበርን?።

And he took attendance of the birds and said, "Why do I not see the hoopoe - or is he among the absent?

27:21
ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እቀጣዋለሁ፤ ወይም በእርግጥ ዐርደዋለሁ፤ ወይም ግልጽ በሆነ አስረጅ ይመጣልናል

I will surely punish him with a severe punishment or slaughter him unless he brings me clear authorization."

27:22
(ወፉ) ዕሩቅ ያልሆነንም ጊዜ ቆዬ፤ አለም፦ ያላወቅከውን ነገር አወቅኩ፤ ከሰበ እም እርግጠኛን ወሬ አመታህልህ፤

But the hoopoe stayed not long and said, "I have encompassed [in knowledge] that which you have not encompassed, and I have come to you from Sheba with certain news.

27:23
እኔ የምትገዛቸው የሆነችን ሰት፣ ከንገሩም ሁሉ የተሰተችን አገኘሁ፤ ለርሷም ታልቅ ዙፋን አላት፤

Indeed, I found [there] a woman ruling them, and she has been given of all things, and she has a great throne.

27:24
እርሱዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፤ ሰይጣንም ለነሱ ሥራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል፤ ከውነተኛው መንገድ አግዷቸዋል፤ ስለዚህ እነሱ (ወደ እውነት) አይመሩም

I found her and her people prostrating to the sun instead of Allah , and Satan has made their deeds pleasing to them and averted them from [His] way, so they are not guided,

27:25
ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፤ የምትሸሽጉትንና የምትገልጹትን ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል)።

[And] so they do not prostrate to Allah , who brings forth what is hidden within the heavens and the earth and knows what you conceal and what you declare -

27:26
አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ የታላቁ ዐርሽ (ዙፋን) ጌታ ነው።

Allah - there is no deity except Him, Lord of the Great Throne."

27:27
(ሱለይማንም) አለ፦ እውነት እንደተናገርክ ወም ከውሸታሞች እንደሆንክ ወደፊት እናያለን፤

[Solomon] said, "We will see whether you were truthful or were of the liars.

27:28
ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ኺድ፤ ወደነርሱም ጣለው፤ ከዚያም ከነሱ ዘወር በል፤ ምን እንደሚመልሱም ተመልከት።

Take this letter of mine and deliver it to them. Then leave them and see what [answer] they will return."

27:29
(እርሷም በደረሳት ጊዜ) አለች፦ እላንተ መማክርት ሆይ! እኔ ክብር ያለው ጽሁፍ ወደኔ ተጣለ፤

She said, "O eminent ones, indeed, to me has been delivered a noble letter.

27:30
እርሱ ከሱለይማን ነው፤ እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ፣ በጣም አዛኝ በሆነው፤

Indeed, it is from Solomon, and indeed, it reads: 'In the name of Allah , the Entirely Merciful, the Especially Merciful,

27:31
በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ታዛዦችም ኾናችሁ ወደኔ ኑ፤ (የሚል ነው)፡፡

Be not haughty with me but come to me in submission [as Muslims].' "

27:32
«እናንተ መማክርቶች ሆይ! በነገሬ (የሚበጀውን) ንገሩኝ፡፡ እስከምትገኙልኝ ድረስ አንድንም ነገር ቆራጭ አይደለሁምና» አለች፡፡

She said, "O eminent ones, advise me in my affair. I would not decide a matter until you witness [for] me."

27:33
«እኛ የኀይል ባለቤቶች የብርቱ ጦርም ባለቤቶች ነን፡፡ ግን ትዕዛዙ ወደ አንቺ ነው፡፡ ምን እንደምታዢም አስተውዪ፤» አሏት፡፡

They said, "We are men of strength and of great military might, but the command is yours, so see what you will command."

27:34
(እርሷም) አለች «ንጉሦች ከተማን (በኀይል) በገቡባት ጊዜ ያበላሹዋታል፡፡ የተከበሩ ሰዎችዋንም ወራዶች ያደርጋሉ፡፡ እንደዚሁም (እነዚህ) ይሠራሉ፡፡

She said, "Indeed kings - when they enter a city, they ruin it and render the honored of its people humbled. And thus do they do.

27:35
«እኔም ወደእነርሱ ገጸ በረከትን የምልክና መልክተኞቹ በምን እንደሚመለሱ የምጠባበቅ ነኝ፡፡»

But indeed, I will send to them a gift and see with what [reply] the messengers will return."

27:36
(መልክተኛው) ሱለይማንንም በመጣው ጊዜ አለ «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን አላህም የሰጠኝ ከሰጣችሁ የበለጠ ነው፡፡ ይልቁንም እናንተ በገጸ በረከታችሁ ትደሰታላችሁ፡፡»

So when they came to Solomon, he said, "Do you provide me with wealth? But what Allah has given me is better than what He has given you. Rather, it is you who rejoice in your gift.

27:37
«ወደእነሱ ተመለስ፡፡ ለእነርሱም በእርሷ ችሎታ በሌላቸው ሰራዊት እንመጣባቸዋለን፡፡ ከእርሷም እነርሱ የተዋረዱ ኾነው በእርግጥ እናወጣቸዋለን» (አለ)፡፡

Return to them, for we will surely come to them with soldiers that they will be powerless to encounter, and we will surely expel them therefrom in humiliation, and they will be debased."

27:38
«እናንተ መኳንንቶች ሆይ! ሙስሊሞች ኾነው ሳይመጡኝ በፊት ዙፋንዋን የሚያመጣልኝ ማንኛችሁ ነው» አለ፡፡

[Solomon] said, "O assembly [of jinn], which of you will bring me her throne before they come to me in submission?"

27:39
ከጋኔን ኀይለኛው «ከችሎትህ ከመነሳትህ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ፡፡ እኔም በእርሱ ላይ ብርቱ ታማኝ ነኝ» አለ፡፡

A powerful one from among the jinn said, "I will bring it to you before you rise from your place, and indeed, I am for this [task] strong and trustworthy."

27:40
ያ እርሱ ዘንድ ከመጽሐፉ ዕውቀት ያለው ሰው (የተገለጸው) «ዓይንህ ወደ አንተ ከመመለሱ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ» አለ፤ (እንደዚሁም አደረገ)፡፡ እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየውም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፡፡ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊሞክረኝ (ቸረልኝ)፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ነው፡፡ የካደም ሰው ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ ቸር ነው» አለ፡፡

Said one who had knowledge from the Scripture, "I will bring it to you before your glance returns to you." And when [Solomon] saw it placed before him, he said, "This is from the favor of my Lord to test me whether I will be grateful or ungrateful. And whoever is grateful - his gratitude is only for [the benefit of] himself. And whoever is ungrateful - then indeed, my Lord is Free of need and Generous."

27:41
«ዙፋንዋን ለእርሷ አሳስቱ፡፡ ታውቀው እንደኾነ ወይም ከእነዚያ ከማያወቁት ትኾን እንደሆነ፤ እናያለን፤» አላቸው፡፡

He said, "Disguise for her her throne; we will see whether she will be guided [to truth] or will be of those who is not guided."

27:42
በመጣች ጊዜ፡- «ዙፋንሽ እንደዚህ ነውን» ተባለች፡፡ «እርሱ ልክ እርሱ ነው መሰለኝ» አለች፡፡ (ሱለይማን) «ከእርሷ በፊትም ዕውቀትን ተሰጠን ሙስሊሞችም ነበርን፤» (አለ)፡፡

So when she arrived, it was said [to her], "Is your throne like this?" She said, "[It is] as though it was it." [Solomon said], "And we were given knowledge before her, and we have been Muslims [in submission to Allah ].

27:43
ከአላህ ሌላ ትግገዛው የነበረችውንም ከለከላት፡፡ እርሷ ከከሓዲዎች ሕዝቦች ነበረችና፡፡

And that which she was worshipping other than Allah had averted her [from submission to Him]. Indeed, she was from a disbelieving people."

27:44
ሕንጻውን ግቢ ተባለች፡፡ ባየቺውም ጊዜ ባሕር ነው ብላ ጠረጠረችው፡፡ ከባቶችዋም ገለጠች፡፡ «እርሱ ከመስተዋት የተለሰለሰ ሕንጻ ነው» አላት፡፡ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩ» አለች፡፡

She was told, "Enter the palace." But when she saw it, she thought it was a body of water and uncovered her shins [to wade through]. He said, "Indeed, it is a palace [whose floor is] made smooth with glass." She said, "My Lord, indeed I have wronged myself, and I submit with Solomon to Allah , Lord of the worlds."

27:45
ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊሕን አላህን ተገዙ በማለት በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም እነሱ የሚነታረኩ ሁለት ጭፍሮች ኾኑ፡፡

And We had certainly sent to Thamud their brother Salih, [saying], "Worship Allah ," and at once they were two parties conflicting.

27:46
«ሕዝቦቼ ሆይ! ከመልካሙ በፊት በክፉው (ቅጣትን አምጣብን በማለት) ለምን ታስቸኩላላችሀ ይታዘንላችሁ ዘንድ አላህን ምሕረትን አትለምኑምን» አላቸው፡፡

He said, "O my people, why are you impatient for evil instead of good? Why do you not seek forgiveness of Allah that you may receive mercy?"

27:47
«ባንተና ከአንተም ጋር ባሉት ሰዎች ምክንያት ገደቢሶች ኾን» አሉት፡፡ «ገደቢስነታችሁ አላህ ዘንድ ነው፤ ይልቁንም እናንተ የምትፈተኑ ሕዝቦች ናችሁ» አላቸው፡፡

They said, "We consider you a bad omen, you and those with you." He said, "Your omen is with Allah . Rather, you are a people being tested."

27:48
በከተማይቱም ውስጥ በምድር ውስጥ የሚያበላሹና የማያሳምሩ ዘጠኝ ሰዎች ነበሩ፡፡

And there were in the city nine family heads causing corruption in the land and not amending [its affairs].

27:49
«እርሱንና ቤተሰቦቹን ሌሊት ልንገድል ከዚያም ለዘመዱ የቤተሰቦቹን ጥፋት (መገደላቸውን) አላየንም፤ እኛም እውነተኞች ነን ልንል በአላህ ተማማሉ» አሉ፡፡

They said, "Take a mutual oath by Allah that we will kill him by night, he and his family. Then we will say to his executor, 'We did not witness the destruction of his family, and indeed, we are truthful.' "

27:50
ተንኮልንም መከሩ፡፡ እነርሱም የማያወቁ ሲኾኑ በተንኮላቸው አጠፋናቸው፡፡

And they planned a plan, and We planned a plan, while they perceived not.

27:51
የተንኮላቸውም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ እኛ እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም በሙሉ እንዴት እንዳጠፋናቸው ተመልከት፡፡

Then look how was the outcome of their plan - that We destroyed them and their people, all.

27:52
እኚህም በበደላቸው ምክንያት ባዶዎች ሲሆኑ ቤቶቻቸው ናቸው፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያወቁ ሕዝቦች አስደናቂ ተዓምር አለበት፡፡

So those are their houses, desolate because of the wrong they had done. Indeed in that is a sign for people who know.

27:53
እነዚያንም ያመኑትንና ከክሕደት ይጠነቀቁ የነበሩትን አዳን፡፡

And We saved those who believed and used to fear Allah .

27:54
ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ «እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ፀያፍን ነገር ትሠራላችሁን

And [mention] Lot, when he said to his people, "Do you commit immorality while you are seeing?

27:55
«እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናቸሁ፡፡»

Do you indeed approach men with desire instead of women? Rather, you are a people behaving ignorantly."

27:56
የሕዝቦቹም መልስ የሉጥን ቤተሰቦች «ከከተማችሁ አውጡ፡፡ እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡

But the answer of his people was not except that they said, "Expel the family of Lot from your city. Indeed, they are people who keep themselves pure."

27:57
እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳን፡፡ ሚስቱ፤ ብቻ ስትቀር፡፡ (በጥፋቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ አደረግናት፡፡

So We saved him and his family, except for his wife; We destined her to be of those who remained behind.

27:58
በእነርሱም ላይ (የድንጋይ) ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የተስፈራሪዎቹም ዝናብ ከፋ፡፡

And We rained upon them a rain [of stones], and evil was the rain of those who were warned.

27:59
(ሙሐመድ ሆይ) በል «ምስጋና ለአላህ ይግባው፡፡ በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሰላም ይውረድ፡፡ አላህ በላጭ ነውን ወይስ ያ የሚያጋሩት (ጣዖት)፡፡

Say, [O Muhammad], "Praise be to Allah , and peace upon His servants whom He has chosen. Is Allah better or what they associate with Him?"

27:60
ወይም ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት) በእርሱም ባለውበት የኾኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለናንተ ችሎታ ያልነበራችሁን አበቀልን፡፡ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን (የለም)፡፡ ግን እነርሱ (ከእውነት) የሚያዘነብሉ ሕዝቦች ናቸው፡፡

[More precisely], is He [not best] who created the heavens and the earth and sent down for you rain from the sky, causing to grow thereby gardens of joyful beauty which you could not [otherwise] have grown the trees thereof? Is there a deity with Allah ? [No], but they are a people who ascribe equals [to Him].

27:61
ወይም ያ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካከሏም ወንዞችን ያደረገ ለርሷም ጋራዎችን ያደረገና ብ በሁለቱምእመካከሏም ወንዞችን ያደረገ ለርሷም ጋራዎችን ያደረገ፣ በሁለቱ ባሕሮችም (በጣፋጩና በጨው ባሕር) መካከል ግርዶን ያደረገ (ይበልጣልን? ወስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።

Is He [not best] who made the earth a stable ground and placed within it rivers and made for it firmly set mountains and placed between the two seas a barrier? Is there a deity with Allah ? [No], but most of them do not know.

27:62
ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል መከራንም የሚያስወግድ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ፤ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም።

Is He [not best] who responds to the desperate one when he calls upon Him and removes evil and makes you inheritors of the earth? Is there a deity with Allah ? Little do you remember.

27:63
ወይም ያ በየብስና በባሕር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ነፋሶችንም ከዝናሙ በፊት አብሳሪ ሆነው የሚልክ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? አላህ (በርሱ) ከሚያጋሩዋቸው ሁሉ ላቀ።

Is He [not best] who guides you through the darknesses of the land and sea and who sends the winds as good tidings before His mercy? Is there a deity with Allah ? High is Allah above whatever they associate with Him.

27:64
ወይም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አምላክ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? እውነተኞች እንደሆናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ በላቸው።

Is He [not best] who begins creation and then repeats it and who provides for you from the heaven and earth? Is there a deity with Allah ? Say, "Produce your proof, if you should be truthful."

27:65
፦ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅ ምስጢር አያውቅም፤ ግን አላህ (ያውቀዋል)፤ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም በላቸው።

Say, "None in the heavens and earth knows the unseen except Allah , and they do not perceive when they will be resurrected."

27:66
በውነት የመጨረሻይቱን ዓለም (ሁኔታ) ማወቃቸው ተሟላን? አይደለም እነሱ ከርሷ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፤ በውነትም እነሱ ከርሷ ዕውሮች ናቸው።

Rather, their knowledge is arrested concerning the Hereafter. Rather, they are in doubt about it. Rather, they are, concerning it, blind.

27:67
እነዚያም የካዱት አሉ፦ እኛም አባቶቻችን ዐፈር በሆን ጊዜ እኛ (ከመቃብር) የምንወጣ ነ?

And those who disbelieve say, "When we have become dust as well as our forefathers, will we indeed be brought out [of the graves]?

27:68
ይህንንም እኛም ከፊት የነበሩት አባቶቻችንም በእርግጥ ተቀጥረንበታል፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም (አሉ)።

We have been promised this, we and our forefathers, before. This is not but legends of the former peoples."

27:69
፦ በምድር ላይ ኺዱ፤ የአመጠኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ በላቸው።

Say, [O Muhammad], "Travel through the land and observe how was the end of the criminals."

27:70
በነሱም ላይ አትዘን ከሚመሰክሩብህ ነገር ውስጥ ከጭንቀት ውስጥ አትሁን።

And grieve not over them or be in distress from what they conspire.

27:71
፦እውነተኞች እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው ይላሉ፤

And they say, "When is [the fulfillment of] this promise, if you should be truthful?"

27:72
፦ የዚያ የተቻኮሉበት ከፊሉ ለናንተ የቀረበ መሆኑ ተረጋግጧል በላቸው።

Say, "Perhaps it is close behind you - some of that for which you are impatient.

27:73
ጌታህም በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነው፤ ግን አብዛናዎቻቸው አያመሰግኑም።

And indeed, your Lord is full of bounty for the people, but most of them do not show gratitude."

27:74
ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ያውቃል።

And indeed, your Lord knows what their breasts conceal and what they declare.

27:75
በሰማይና በምድር ውስጥ ምንም የተደበቀ ነገር የለም ገላጭ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጅ።

And there is nothing concealed within the heaven and the earth except that it is in a clear Register.

27:76
ይህ ቁርአን በ እስራኤል ልጆች ላይ የዚያን እነሱ በርሱ የሚለያዩበትን አብዛኛውን ይነግራል።

Indeed, this Qur'an relates to the Children of Israel most of that over which they disagree.

27:77
እርሱም ለምእመናን መምሪያና እዝነት ነው።

And indeed, it is guidance and mercy for the believers.

27:78
ጌታህ በመካከላቸው በትክክል ፍርዱ ይፈርዳል፤ እርሱም አሸናፊው ዐዋቂው ነው።

Indeed, your Lord will judge between them by His [wise] judgement. And He is the Exalted in Might, the Knowing.

27:79
በአላህም ላይ ተጠጋ፤ አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና።

So rely upon Allah ; indeed, you are upon the clear truth.

27:80
አንተ ሙታንን አታሰማም፤ ደንቆሮችንም የሚተው ሆነው በዞሩ ጊዜ ጥሪን አታሰማም።

Indeed, you will not make the dead hear, nor will you make the deaf hear the call when they have turned their backs retreating.

27:81
አንተም (ልበ) ዕውሮችን ከጥመታቸው አቅኚ አይደለህም፤ በአንቀጾቻችን የሚያምኑትን በስተቀር አታሰማም፤ እነሱ ፍጹም ታዛዦች ናቸውና።

And you cannot guide the blind away from their error. You will only make hear those who believe in Our verses so they are Muslims [submitting to Allah ].

27:82
በነሱም ላይ (የቅጣት ቃሉ በተረጋገጠ ጊዜ ሰዎቹ በአንቀጾቻችን የማያረጋግጡ እንደነበሩ የምትነግራቸውን እንሰሳ ለነርሱ ከምድር እናወጣለን።

And when the word befalls them, We will bring forth for them a creature from the earth speaking to them, [saying] that the people were, of Our verses, not certain [in faith].

27:83
ህዝቦቹም ሁሉ በአንቀጾቻችን የሚያስተባብሉትን ጭፍሮች የምሰበስብበትን ቀን (አስታውስ)፤ እነሱም ይከመከማሉ።

And [warn of] the Day when We will gather from every nation a company of those who deny Our signs, and they will be [driven] in rows

27:84
በመጡም ጊዜ (አላህ) ይላቸዋል፦ በንቀጾቼ እርሷን በአወቅ ያላዳረሳችሁ ስትሆኑ አስተባበላችሁን? ወይስ ምንን ትሠሩ ነበራችሁ?

Until, when they arrive [at the place of Judgement], He will say, "Did you deny My signs while you encompassed them not in knowledge, or what [was it that] you were doing?"

27:85
በመደበላቸውም በነሱ ላይ ቃሉ ይፈጸምባቸዋል፤ እነርሱም አይናገሩም።

And the decree will befall them for the wrong they did, and they will not [be able to] speak.

27:86
እኛ ሌሊትን በርሱ ውስጥ እንዲያርፉበት ቀንንም የሚያሳይ እንዳደረግን አያዩምን?ለሚያምኑ ሰዎች በዚህ ውስጥ ታምራቶች አሉበት።

Do they not see that We made the night that they may rest therein and the day giving sight? Indeed in that are signs for a people who believe.

27:87
በቀንዱም በሚነፋ ቀን በሰማያት ውስጥ ያሉትና በምድርም ውስጥያሉት ሁሉ አላህ የሻው ነገር ብቻ ሲቀር በሚደነግጡበት ጊዜ (የሚሆነውን አስታውስ)፤ ሁሉም የተናነሱ ሆነውም ወደርሱ ይመጣሉ።

And [warn of] the Day the Horn will be blown, and whoever is in the heavens and whoever is on the earth will be terrified except whom Allah wills. And all will come to Him humbled.

27:88
ጋራዎችንም እርሷ እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትሆን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያታለህ፤ የዚያን ነገሩን ሁሉ የጠነከረውን የአላህን ጥበብ (ተመልከት)፤ እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው።

And you see the mountains, thinking them rigid, while they will pass as the passing of clouds. [It is] the work of Allah , who perfected all things. Indeed, He is Acquainted with that which you do.

27:89
በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለርሱ ከርስዋ የበለተ ምንዳ አለው፤ እርሱም በዚያ ቀን ከድንጋጤ ጸጥተኞች ናቸው።

Whoever comes [at Judgement] with a good deed will have better than it, and they, from the terror of that Day, will be safe.

27:90
በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ይነደፋሉ፤ ትሠሩት የነበራችሁትን እንጂ አትመነዱም (ይባላሉ)።

And whoever comes with an evil deed - their faces will be overturned into the Fire, [and it will be said], "Are you recompensed except for what you used to do?"

27:91
የታዘዝኩት የዚህችን አገር ጌታ ያንን ክልል ያደረጋትን እንድግገዛ ብቻ ነው፤ ነገሩም ሁሉ የርሱ ነው ከእስላሞችም እንድሆን ታዝዣለሁ (በላቸው)።

[Say, O Muhammad], "I have only been commanded to worship the Lord of this city, who made it sacred and to whom [belongs] all things. And I am commanded to be of the Muslims [those who submit to Allah ]

27:92
ቁርአንንም እንዳነብ (ታዝዣለሁ) የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፤ የተሳሳተም ሰው እኔ አስጠንቃቂዎች ነኝ እንጂ ሌላ አይደለሁም በለው።

And to recite the Qur'an." And whoever is guided is only guided for [the benefit of] himself; and whoever strays - say, "I am only [one] of the warners."

27:93
ምስጋና ለአላህ ነው፤ ታምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፤ ታውቋትም አላችሁ በላቸው፤ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም።

And say, "[All] praise is [due] to Allah . He will show you His signs, and you will recognize them. And your Lord is not unaware of what you do."

Copyright 2013, AmharicQuran.com