Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ሐጅ (የሐጅ ምዕራፍ)

22:1
እላንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፣ የሰዓቲቱ (1) እንቅጥቃጤ በጣም ከባድ ነገር ነዉና።
የትንሣኤ ቀን


O mankind, fear your Lord. Indeed, the convulsion of the [final] Hour is a terrible thing.

22:2
በምታዩዋት ቀን፣ አጥቢ ሁሉ ከአጠባችዉ ልጅ ትፈዝዛለች፤ የእርግዝና ባለቤት የሆነችም ሁሉ፣ እርጉዝዋን ትጨነግፋለች፤ ሰዎቹንም (በድንጋጤ ብርታት)፣ የሰከሩ ሆነው ታያለህ፤ እነሱም (ከመጠጥ) የሰከሩ አይደሉም፤ ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ነው።

On the Day you see it every nursing mother will be distracted from that [child] she was nursing, and every pregnant woman will abort her pregnancy, and you will see the people [appearing] intoxicated while they are not intoxicated; but the punishment of Allah is severe.

22:3
ከሰዎቹም ያለ ዕውቀት በአላህ ነገር የሚከራከር ሞገደኛ ሰይጣንንም ሁሉ የሚከተል ሰው አለ።

And of the people is he who disputes about Allah without knowledge and follows every rebellious devil.

22:4
እነሆ! የተከተለዉን ሰው እርሱ ያጠመዋል፤ ወደ ነዳጅ እሳት ስቃይም ይመረዋል፣ ማለት በርሱ ላይ ተጽፏል።

It has been decreed for every devil that whoever turns to him - he will misguide him and will lead him to the punishment of the Blaze.

22:5
እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ)፤ እኛም ከዐፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ ከዚያም ከቁራጭ፣ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤ የምንሻውንም፣ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ፣ በማህጸን ዉስጥ እናረጋዋለን ከዚያም ሕጻን ሆናችሁ እናወጣችኋለን። ከዚያም ሙሉ ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፣ (እናሳድጋችኋለን)፤ ከናንተም የሚሞት ሰው አለ፤ ከናንተም ከዕውቀት በኋላ፣ ምንንም እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፤ ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ፤ በስዋም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ፣ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም፤ ውበት ካለው ቦታ ሁሉ ታበቅላለችም።

O People, if you should be in doubt about the Resurrection, then [consider that] indeed, We created you from dust, then from a sperm-drop, then from a clinging clot, and then from a lump of flesh, formed and unformed - that We may show you. And We settle in the wombs whom We will for a specified term, then We bring you out as a child, and then [We develop you] that you may reach your [time of] maturity. And among you is he who is taken in [early] death, and among you is he who is returned to the most decrepit [old] age so that he knows, after [once having] knowledge, nothing. And you see the earth barren, but when We send down upon it rain, it quivers and swells and grows [something] of every beautiful kind.

22:6
ይህ፣ አላህ እርሱ መኖሩ የተረጋገጠ፤ እርሱም ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው።

That is because Allah is the Truth and because He gives life to the dead and because He is over all things competent

22:7
ሰዓቲቱም መጪ በርሷ ፈጽሞ ጥርጣሬ የሌለባት በመሆኗ፣ አላህም በመቃብሮች ዉስጥ ያለን ሁሉ፣ የሚቀሰቅስ በመሆኑ ነው።

And [that they may know] that the Hour is coming - no doubt about it - and that Allah will resurrect those in the graves.

22:8
ከሰዎችም ዉስጥ፣ ያለ ዕዉቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም፣ በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አልለ።

And of the people is he who disputes about Allah without knowledge or guidance or an enlightening book [from Him],

22:9
ጐኑን ያጠፈ ኾኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስት፣ (ይከራከራል)፤ በቅርቢቱ አለም፣ ለርሱ ዉርደት አለው፤ በትንሣኤ ቀንም፣ አቃጣይን ቅጣት አናቀምሰዋለን።

Twisting his neck [in arrogance] to mislead [people] from the way of Allah . For him in the world is disgrace, and We will make him taste on the Day of Resurrection the punishment of the Burning Fire [while it is said],

22:10
ይህ፣ እጆችህ ባስቀደሙት ኃጢያት፣ አላህም ለባሮቹ ፌፅሞ በዳይ ባለመኾኑ ነው፣ (ይባላል)።

"That is for what your hands have put forth and because Allah is not ever unjust to [His] servants."

22:11
ከሰዎችም (ከሀይማኖት) በጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚግገዛ ሰው አለ፤ ታዲያ መልካም ነገር ቢያገኘው በርሱ ይረጋል፤ መከራም ብታገኘው በፊቱ ላይ ይገለበጣል የቅርቢቱን ዓለምም የመጨረሻይቱንም ከሰረ፣ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው።

And of the people is he who worships Allah on an edge. If he is touched by good, he is reassured by it; but if he is struck by trial, he turns on his face [to the other direction]. He has lost [this] world and the Hereafter. That is what is the manifest loss.

22:12
ከአላህ ሌላ የማይጎዳውንና የማይጠቅመውን ይግገዛል፤ ይህ እርሱ (ከእውነት) የራቀ ስሕተት ነው።

He invokes instead of Allah that which neither harms him nor benefits him. That is what is the extreme error

22:13
ያንን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚቀርብን ይግገዛል፤ ረዳቱ ምንኛን ከፋ! ወዳጁም ምንኛ ከፋ!

He invokes one whose harm is closer than his benefit - how wretched the protector and how wretched the associate.

22:14
አላህ፣ እነዚያን ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን፣ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያገባቸዋል፤ አላህ የሚሻውን ነገር በእርግጥ ይሠራል።

Indeed, Allah will admit those who believe and do righteous deeds to gardens beneath which rivers flow. Indeed, Allah does what He intends.

22:15
አላህ፣ (መልክተኛውን) በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም፣ አይረዳውም ብሎ የሚያስብ ሰው ገመድን ወደ ሰማይ ይዘርጋ፤ ከዚያም (ትንፋሹ እስኪቆረጥ) ይታነቅ፤ ተንኮሉ የሚያስቆጨውን ነገር ያስወግድለት እንደሆነም ይመልከት።

Whoever should think that Allah will not support [Prophet Muhammad] in this world and the Hereafter - let him extend a rope to the ceiling, then cut off [his breath], and let him see: will his effort remove that which enrages [him]?

22:16
እንደዚሁም (ቁርአንን) የተብራሩ አንቀጾች አድርገን አወረድነው፤ አላህም የሚሻውን ሰው ይመራል።

And thus have We sent the Qur'an down as verses of clear evidence and because Allah guides whom He intends.

22:17
እነዚያ ያመኑ፣ እነዚያም ይሁዳውያን የሆኑ፣ ሳቢያኖችም፣ ክርስቲያኖችም፣ መጁሶችም (1) እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ. አላህ በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና።
(1) በፀሐይና በጨረቃ በእሳት የሚያመልኩ


Indeed, those who have believed and those who were Jews and the Sabeans and the Christians and the Magians and those who associated with Allah - Allah will judge between them on the Day of Resurrection. Indeed Allah is, over all things, Witness.

22:18
አላህ፣ በሰማያት ያለው ሁሉ፣ በምድርም ያለው ሁሉ ፀሐይና ጨረቃም፣ ክዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾችም፣ ከሰዎች ብዙዎችም ለርሱ የሚሰግዱለት መኾኑን አታውቁምን? ብዙውን በርሱ ላይ ቅጣት ተረጋገጠበት፤ አላህ የሚያዋርደው ሰው ለርሱ ምንም አክባሪ የለውም፤ አላህ የሻውን ይሠራልና።

Do you not see that to Allah prostrates whoever is in the heavens and whoever is on the earth and the sun, the moon, the stars, the mountains, the trees, the moving creatures and many of the people? But upon many the punishment has been justified. And he whom Allah humiliates - for him there is no bestower of honor. Indeed, Allah does what He wills.

22:19
እነዚህ (1) በጌታቸው የተከራከሩ ሁለት ባላጋራዎች ናቸው፤ እነዚያም የካዱት ለነርሱ የእሳት ልብሶች ተለክተውላቸዋል፤ ከራሶቻቸው በላይ የፈላ ውሃ ይምቧቧባቸዋል።
(1) ያመኑትና አምስቱ ክፍሎች እሐዲያኖች


These are two adversaries who have disputed over their Lord. But those who disbelieved will have cut out for them garments of fire. Poured upon their heads will be scalding water

22:20
በሆዶቻቸው ውስጥ ያለው፣ ቆዳዎቻቸውም በርሱ ይቀለጣሉ።

By which is melted that within their bellies and [their] skins.

22:21
ለነሱም (መቅጫ) ከብረት የሆኑ መዶሻዎች አሉ።

And for [striking] them are maces of iron.

22:22
ከጭንቀት ብርታት የተነሣ፣ ከርሷ ለመውታት በፈለጉ ቁጥር በርሷ ውስጥ እንዲመለሱ ይደረጋሉ፤ በጣም የሚያቃጥልን ቅጣት፣ ቅመሱ (ይባላሉ)።

Every time they want to get out of Hellfire from anguish, they will be returned to it, and [it will be said], "Taste the punishment of the Burning Fire!"

22:23
አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን ሰዎች፣ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈስ ሱባቸውን ገነቶች ያገባቸዋል፤ በርሷ ውስጥ ከወርቅ የሆኑን አንባሮችና ሉልን ይሸለማሉ፤ በርሷ ውስጥ ልብሶቻቸውም ሐር ናቸው።

Indeed, Allah will admit those who believe and do righteous deeds to gardens beneath which rivers flow. They will be adorned therein with bracelets of gold and pearl, and their garments therein will be silk.

22:24
ከንግግርም ወደ መልካሙ ተመሩ፤ ወደ ምስጉኑም መንገድ ተመሩ።

And they had been guided [in worldly life] to good speech, and they were guided to the path of the Praiseworthy.

22:25
እነዚያ የካዱ ከአላህም መንገድና ከዚያም ለሰዎች በውስጡ ነዋሪ ለሆኑትም ከሩቅ ለሚመጡትም እኩል ካደረግነው ከተከበረው፣ መስኪድ (ሰዎችን) የሚከለክሉ፣ (አሳማሚን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን)። በርሱም ውስጥ (ከትክክለኛ መንገድ)፣ በመዘንበል በዳይ ኾኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚፈልግ ሰው፣ ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።

Indeed, those who have disbelieved and avert [people] from the way of Allah and [from] al-Masjid al-Haram, which We made for the people - equal are the resident therein and one from outside; and [also] whoever intends [a deed] therein of deviation [in religion] or wrongdoing - We will make him taste of a painful punishment.

22:26
ለኢብራሂምም የቤቱን (የከዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ (ባልነው ጊዜ አስታውስ)።

And [mention, O Muhammad], when We designated for Abraham the site of the House, [saying], "Do not associate anything with Me and purify My House for those who perform Tawaf and those who stand [in prayer] and those who bow and prostrate.

22:27
(አልነውም) ፦ በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፤ እግረኞች፣ ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና።

And proclaim to the people the Hajj [pilgrimage]; they will come to you on foot and on every lean camel; they will come from every distant pass -

22:28
ለነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ፣ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)፤ ከርሷም ብሉ፤ ችግረኛ ድኻንም አብሉ።

That they may witness benefits for themselves and mention the name of Allah on known days over what He has provided for them of [sacrificial] animals. So eat of them and feed the miserable and poor

22:29
ከዚያም (እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን) ትርፍ አካላችቸንንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ በጥንታዊው ቤት ይዙሩ።

Then let them end their untidiness and fulfill their vows and perform Tawaf around the ancient House."

22:30
(ነገሩ) ይህ ነው፤ የአላህንም ሕግጋት የሚያከብር ሰው፣ እርሱ እጌታው ዘንድ ለርሱ በጣም የተሻለ ነው፤ የቤት እንሰሳትም (1) በናንተ ላይ (እርም መሆኑ) ከሚነበብላችሁ በስተቀር ለናንተ ተፈቅዳላችኋለች። ከጣዖታት ርክሰት ተጠንቀቁ፤ ሀሰትንም ቃል ራቁ።
(1) ግመል ከብት በግና ፍየል


That [has been commanded], and whoever honors the sacred ordinances of Allah - it is best for him in the sight of his Lord. And permitted to you are the grazing livestock, except what is recited to you. So avoid the uncleanliness of idols and avoid false statement,

22:31
ለአላህ ታዛዦች በርሱ የማታጋሩ ሆናችሁ (ከሐሰት ራቁ)፤ በአላህም የሚያጋራ ሰው ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው፣ ወይም ነፍሰ እርሱን በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው።

Inclining [only] to Allah , not associating [anything] with Him. And he who associates with Allah - it is as though he had fallen from the sky and was snatched by the birds or the wind carried him down into a remote place.

22:32
(ነገሩ) ይህ ነው የአላህንም የሃይማኖት ምልክቶች (1) የሚያከብር ሰው እርሷ ከልቦች የሆነች ጥንቃቄ ናት፥፥
(1) ወደ መካ የሚነዱትን መሥዋዕት


That [is so]. And whoever honors the symbols of Allah - indeed, it is from the piety of hearts.

22:33
ለናንተ በርሷ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ጥቅሞች አሏችሁ፤ ከዚያም (የማረጃ) ስፍራዋ እጥንታዊው ቤት አጠገብ ነው፥፥

For you the animals marked for sacrifice are benefits for a specified term; then their place of sacrifice is at the ancient House.

22:34
ለሕዝብም ሁሉ (ወደ አላህ) መሥዎዕት ማቅርብን ደነገግን፣ ከቤት እንሰሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላሀን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ፣ (አዘዝናቸው)፤ አምላካችሁም አንድ አምላህ ብቻ ነው፤ ለርሱም ብቻ ታዘዙ፤ ለአላህ ተዋራጆቸንም አብስራቸው።

And for all religion We have appointed a rite [of sacrifice] that they may mention the name of Allah over what He has provided for them of [sacrificial] animals. For your god is one God, so to Him submit. And, [O Muhammad], give good tidings to the humble [before their Lord]

22:35
እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ፣ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን፣ በደረሰባቸውም (መከራ) ላይ ታጋሾችን፣ ሶላትንም አሰተካክለው ሰጋጆችን ከሰጥናቸውም ሲሳይ የሚለግሱትን (አብስር)።

Who, when Allah is mentioned, their hearts are fearful, and [to] the patient over what has afflicted them, and the establishers of prayer and those who spend from what We have provided them.

22:36
ግመሎችንም ለናንተ ከአላህ ሃይማኖት ምልክቶች አደረግናቸው፤ በርሷ ለናንተ መልካም ጥቅም አላችሁ በርሷም ላይ (ሰታርዷት) በሶስት እግሮችዋ ቆማ የተሰለፈች ሆና የአላህን ሰም አውሱ፤ ጎኖቻቸውም በወደቁ ጊዜ ከርሷ ብሉ፤ ለማኝንም፣ ለለመና የሚያገዳድምንም አብሉ፤ እንደዚሁ ታመስግኑ ዘንድ ለናንተ ገራናት፥፥

And the camels and cattle We have appointed for you as among the symbols of Allah ; for you therein is good. So mention the name of Allah upon them when lined up [for sacrifice]; and when they are [lifeless] on their sides, then eat from them and feed the needy and the beggar. Thus have We subjected them to you that you may be grateful.

22:37
አላህን ሰጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አየደርስውም፤ ግን ከናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርስዋል፤ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለናንተ ገራት በጎ ሠሪዎችንም አብስር።

Their meat will not reach Allah , nor will their blood, but what reaches Him is piety from you. Thus have We subjected them to you that you may glorify Allah for that [to] which He has guided you; and give good tidings to the doers of good.

22:38
አላህ ከነዚያ ካመኑት ላይ ይከላከልላቸዋል፤ አላህ ከዳተኛን፣ ውለታቢስን ሁሉ አይወድም።

Indeed, Allah defends those who have believed. Indeed, Allah does not like everyone treacherous and ungrateful.

22:39
ለነዚያ ለሚገደሉት (ምእመናን) እነርሱ የተበደሉ በመሆናቸው፣ (መጋደል) ተፈቀደላቸው፤ አላህም፣ እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው።

Permission [to fight] has been given to those who are being fought, because they were wronged. And indeed, Allah is competent to give them victory.

22:40
ለነዚያ ጌታችን አላህ ነው፥ ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት፣ (ተፈቀደ)፤ አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተ ክርስቲያኖችም፣ ምዅራቦችም (1) በውስጣቸው የአላህ ሰም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም፤ በተፈረሱ ነበር፤ አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው፣ በእርግጥ ይረዳዋል፤ አላህ ብርቱ አሽናፊ ነውና።
(1) የይሁዶች ቤተ ፀሎት


[They are] those who have been evicted from their homes without right - only because they say, "Our Lord is Allah ." And were it not that Allah checks the people, some by means of others, there would have been demolished monasteries, churches, synagogues, and mosques in which the name of Allah is much mentioned. And Allah will surely support those who support Him. Indeed, Allah is Powerful and Exalted in Might

22:41
(አነርሱም) እነዚያ በምድር ላይ ብናስመቻችው፣ ሶላትን እንደሚገባ የሚያስተካክሉ፣ ዘካንም የሚስጡ፣ በደግ ነገርም የሚያዝዙ፣ ከመጥፎ ነገርም የሚከለክሉ ናቸው፤ የነገሮቹም ሁሉ መጨረሻ፣ ወደ አላህ ነው።

[And they are] those who, if We give them authority in the land, establish prayer and give zakah and enjoin what is right and forbid what is wrong. And to Allah belongs the outcome of [all] matters.

22:42
ቢያሰተባብሉህም፣ ከነሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች፣ ዓድና ሠሙድም፣ በእርግጥ አሰተባብለዋል።

And if they deny you, [O Muhammad] - so, before them, did the people of Noah and 'Aad and Thamud deny [their prophets],

22:43
የኢብራሂምም ሕዝቦች፣ የሉጥም ሕዝቦች፣ (አሰተባብለዋል)፤

And the people of Abraham and the people of Lot

22:44
የመድየንም ሰዎች፣ (አሰተባብለዋል)፤ ሙሳም ተስተባብሏል፤ ለከሐዲዎቹም ጊዜ ሰጠኋቸው፤ ከዚያም ያዝኩዋቸው፤ ጥላቻየም እንዴት ነበር!

And the inhabitants of Madyan. And Moses was denied, so I prolonged enjoyment for the disbelievers; then I seized them, and how [terrible] was My reproach.

22:45
ከክተማም እርሷ በደለኛ ሆና ያጠፋናትና፣ እርሷ በጣሪያዎችዋ ላይ ወዳቂ የሆነችው ብዙ ናት፣ ከተራቆተችም የውሃ ጉድጏድ፣ ከተገነባም ሕንጻ (ያጠፋነው ብዙ ነው)።

And how many a city did We destroy while it was committing wrong - so it is [now] fallen into ruin - and [how many] an abandoned well and [how many] a lofty palace.

22:46
ለነርሱም፣ በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች፣ ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች፣ ይኖሩዋቸው ዘንድ፣ በምድር ላይ አይኼዱምን? እነሆ ዓይኖች አይታወሩም ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ።

So have they not traveled through the earth and have hearts by which to reason and ears by which to hear? For indeed, it is not eyes that are blinded, but blinded are the hearts which are within the breasts.

22:47
አላህ ቀጠሮውን በፍጹም የማይጥስ ሲሆን በቅጣት ያቻኩሉሃል፤ እጌታህም ዘንድ አንዱ ቀን፣ ከምትቆጥሩት (ቀን) እንደ ሺሕ ዓመት ነው።

And they urge you to hasten the punishment. But Allah will never fail in His promise. And indeed, a day with your Lord is like a thousand years of those which you count.

22:48
ከከተማ እርሷ በዳይ ሆና ለርሷ ጊዜ የሰጠኋትና ከዚያም የያዝኳት ብዙ ናት፤ መመለሻም ወደኔ ብቻ ነው።

And for how many a city did I prolong enjoyment while it was committing wrong. Then I seized it, and to Me is the [final] destination.

22:49
፦ እላንተ ስዎች ሆይ እኔ ለናንተ ግልጽ አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ፣ በላቸው።

Say, "O people, I am only to you a clear warner."

22:50
እነዚያም ያመኑ፣ መልካም ሥራዎችንም የሰሩ፣ ለነርሱ ምሕረትና ያማር ሲሳይ አላቸው።

And those who have believed and done righteous deeds - for them is forgiveness and noble provision.

22:51
እነዚያም የሚያመልጡ መስሏቸው ታምራቶቻችንን በመንቀፍ የተጉ፣ እነሱ የእሳት ጓዶች ናቸው።

But the ones who strove against Our verses, [seeking] to cause failure - those are the companions of Hellfire.

22:52
ከመልክተኛና ከነቢያም ከአንተ በፊት አንድንም አልላክንም፣ ባነበበ (ና ዝም ባለ) ጊዜ፣ ሰይጣን በንባቡ ላይ (ማጥመሚያን ቃል) የሚጥል ቢሆን እንጂ፤ ወዲያውም አላህ ስይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፤ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።

And We did not send before you any messenger or prophet except that when he spoke [or recited], Satan threw into it [some misunderstanding]. But Allah abolishes that which Satan throws in; then Allah makes precise His verses. And Allah is Knowing and Wise.

22:53
ሰይጣን የሚጥለውን ነገር፤ ለነዚያ በልቦችቸው ውስጥ በሺታ ላለባቸው፣ ልቦቻቸውም ደረቆች ለሆኑት፣ ፈተና ሊያደርግ (ይጥላል)፤ በዳዩችም፣ ከውነት በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ ናቸው።

[That is] so He may make what Satan throws in a trial for those within whose hearts is disease and those hard of heart. And indeed, the wrongdoers are in extreme dissension.

22:54
እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት፣ እርሱ (ቁርአን) ከጌታህ የሆነ እውነት መሆኑን እንዲያውቁና በነሱ እንዲያምኑ ልቦቻቸውም ለርሱ እንዲያምኑ ልቦቻቸውም ለርሱ እንዲረኩ (ያጠነክራል) አላህም እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው፥፥

And so those who were given knowledge may know that it is the truth from your Lord and [therefore] believe in it, and their hearts humbly submit to it. And indeed is Allah the Guide of those who have believed to a straight path

22:55
እነዚያም የካዱት ሰዎች፣ ስዓቲቱ በድንገት እስከምትመጣባቸው፣ ወይም (ከደግ ነገር) መካን የሆነው ቀን ቅጣት እሰከሚመጣቸው ድረስ ከርሱ (ከቁርአን) በመጠራጠር ውስጥ ከመሆን አይወገዱም።

But those who disbelieve will not cease to be in doubt of it until the Hour comes upon them unexpectedly or there comes to them the punishment of a barren Day.

22:56
በዚያ ቀን፣ ንግሥናው የአላህ ብቻ ነው፣ በመካከላቸው ይፈርዳል፤ እነዚያም ያመኑት፣ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት፣ በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ናቸው።

[All] sovereignty that Day is for Allah ; He will judge between them. So they who believed and did righteous deeds will be in the Gardens of Pleasure.

22:57
እነዚያም የካዱት በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉት፣ እነዚያ ለነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፥፥

And they who disbelieved and denied Our signs - for those there will be a humiliating punishment.

22:58
እነዚያም በአላህ ሃይማኖት የተሰደዱ፣ ከዚያም የተገደሉ፣ ወይም የሞቱ፣ አላህ መልካምን ሲሳይ በእርግጥ ይስጣቸዋል፣ አላህም እርሱ ከስጪዎች ሁሉ በላጭ ነው።

And those who emigrated for the cause of Allah and then were killed or died - Allah will surely provide for them a good provision. And indeed, it is Allah who is the best of providers.

22:59
የሚወዱትን መግቢያ፣ (ገነትን)፣ በእርግጥ ያገባቸዋል አላህም በእርግጥ ዐዋቂ፣ ታጋሽ ነው።

He will surely cause them to enter an entrance with which they will be pleased, and indeed, Allah is Knowing and Forbearing.

22:60
(ነገሩ) ይህ ነው፤ በሱ በተበደለበትም ብጤ የተበቀለ ሰው ከዚይም በርሱ ላይ ግፍ የተዋለበት አላህ በእርግጥ ይረዳዋል፤ አላህ በእርግጥ ይረዳዋል አላህ ይቅርባይ መሐሪ ነውና፤

That [is so]. And whoever responds [to injustice] with the equivalent of that with which he was harmed and then is tyrannized - Allah will surely aid him. Indeed, Allah is Pardoning and Forgiving.

22:61
ይህ፣ አላህ ሌሊትን በቀን ውሰጥ የሚያስገባ፣ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ፣ (ቻይ)፣ አላህም ሰሚ ተመልካች በመሆኑ ነው።

That is because Allah causes the night to enter the day and causes the day to enter the night and because Allah is Hearing and Seeing.

22:62
ይህ አላህ እርሱ እውነት በመሆኑ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር እርሱ ፍጹም ውሽት በመሆኑ አላህም እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ በመሆኑ ነው።

That is because Allah is the Truth, and that which they call upon other than Him is falsehood, and because Allah is the Most High, the Grand

22:63
አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱንና ምድር የምትለመልም መሆኗን አታይምን? አላህ ርኅሩኅ ውስጥ ዕዋቂ ነው።

Do you not see that Allah has sent down rain from the sky and the earth becomes green? Indeed, Allah is Subtle and Acquainted.

22:64
በሰማያት ውስጥ ያለውና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፤ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው።

To Him belongs what is in the heavens and what is on the earth. And indeed, Allah is the Free of need, the Praiseworthy.

22:65
አላሀ በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ ለናንተ የገራላችሁ መርከቦችንም በበሕር ውስጥ በፈቃዱ የሚንሻለሉ ሲሆኑ፣ (የገራላችሁ) መሆኑን፣ ስማይንም በፈቃዱ ካልሆነ በምድር ላይ እንዳትውድቅ የሚይዛት መሆኑን፣ አላየህምን? አላህ ለሰዎች በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነው።

Do you not see that Allah has subjected to you whatever is on the earth and the ships which run through the sea by His command? And He restrains the sky from falling upon the earth, unless by His permission. Indeed Allah , to the people, is Kind and Merciful.

22:66
እርሱም ያ ሕያው ያደርጋችሁ ነው፣ ከዚያም ይገድላችኃል፣ ከዚያም ሕያው ያደርጋችኃል፤ ሰው በእርግጥ በጣም ከሃዲ ነው።

And He is the one who gave you life; then He causes you to die and then will [again] give you life. Indeed, mankind is ungrateful

22:67
ለየሕዝቡ ሁሉ እነሱ የሚሠሩበት የሆነን ሥርዓተ ሃይማኖት አድርገናል፤ ሰለዚህ በነገሩ አይከራከሩህ፤ ወደ ጌታህ መንገድም ጥራ፤ አንተ በእርግጥ በቅኑ መንገድ ላይ ነህና።

For every religion We have appointed rites which they perform. So, [O Muhammad], let the disbelievers not contend with you over the matter but invite them to your Lord. Indeed, you are upon straight guidance.

22:68
ቢከራከሩህም አላህ የምሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፣ በላቸው።

And if they dispute with you, then say, " Allah is most knowing of what you do.

22:69
አላህ በትንሣኤ ቀን፣ በዚያ በርሱ ትለያዩበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል።

Allah will judge between you on the Day of Resurrection concerning that over which you used to differ."

22:70
አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ (የተመዘገበ) ነው፤ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው።

Do you not know that Allah knows what is in the heaven and earth? Indeed, that is in a Record. Indeed that, for Allah , is easy.

22:71
ከአላህ ሌላም በርሱ ማስረጃን ያላወረደበትን፣ ለነርሱም በርሱ ዕውቀት የሌላቸውን ነገር ይግገዛሉ፤ ለበዳዮችም ምንም ረዳት የላቸውም።

And they worship besides Allah that for which He has not sent down authority and that of which they have no knowledge. And there will not be for the wrongdoers any helper.

22:72
አንቀጾቻችንም የተብራሩ ሆነው፣ በነሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ፣ በነዚያ በካዱት ሰዎች ፊቶች ላይ ጥላቻን ታውቃለህ፤ በነዚያ በነሱ ላይ አንቀጾቻችንን በሚያነቡት ላይ በኅይል ሊዘልሉባቸው ይቃረባሉ፤ ከዚሃችሁ ይልቅ የከፋን ነገር ልንገራችሁን? በላቸው፤ (እርሱም) እሳት ናት፤ አላህ ለነዚያ ለካዱት ስዎች ቀጥሯታል፤ ምን ትከፋም መመለሻ!

And when Our verses are recited to them as clear evidences, you recognize in the faces of those who disbelieve disapproval. They are almost on the verge of assaulting those who recite to them Our verses. Say, "Then shall I inform you of [what is] worse than that? [It is] the Fire which Allah has promised those who disbelieve, and wretched is the destination."

22:73
እላንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምስሌ ተገለጸላችሁ ለእርሱም አድምጡት፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት) ዝምብን ፈጽሞ አይፈጥሩም፤ ለርሱ (ለመፍጠር) ቢሰበስቡም እንኳ (አይችሉም) አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከርሱ አያስጥሉትም ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ። (1)
(1) ገዢውም ተገዢውም ደካሞች ናቸው።


O people, an example is presented, so listen to it. Indeed, those you invoke besides Allah will never create [as much as] a fly, even if they gathered together for that purpose. And if the fly should steal away from them a [tiny] thing, they could not recover it from him. Weak are the pursuer and pursued.

22:74
አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፤ አላህ በጣም ኅያል አሸናፊ ነው።

They have not appraised Allah with true appraisal. Indeed, Allah is Powerful and Exalted in Might.

22:75
አላህ ከመላእክት ውስጥ መልክተኞችን ይመርጣል፤ ከስዎችም፣ (እንደዚሁ) አላህ ስሚ ተመልካች ነው።

Allah chooses from the angels messengers and from the people. Indeed, Allah is Hearing and Seeing.

22:76
በስተፊታቸው ያለን፣ በስተኃላቸውም ያለን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ አላህም ነገሮች ሁሉ ይመለሳሉ።

He knows what is [presently] before them and what will be after them. And to Allah will be returned [all] matters.

22:77
እላንተ ያመናችሁ ስዎች ሆይ (በስግደታችሁ) አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም ተገዙ፤ በጎንም ነገር ሥሩ፤ ልትድኑ ይከጃልላችኃልና።

O you who have believed, bow and prostrate and worship your Lord and do good - that you may succeed.

22:78
በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ; አርሱ መርጧችኃል በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፤ የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ፤ እርሱ ከዚህ በፊት ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል፤ በዚህም፣ (ቁርአን) መልክተኛው፣ በናንተ ላይ መስካሪ እንዲኾን፣ እናንተም በሰዎቹ ላይ መስካሪዎች እንድትኾኑ (ሙስሊሞች ብሎ ስይሟችኋል)፤ ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ በአላህም ተጠበቁ፤ እርሱ ረዳታችሁ ነው፤ (በእርሱ) ምን ያምር ጠባቂ! ምን ያምርም ረዳት!

And strive for Allah with the striving due to Him. He has chosen you and has not placed upon you in the religion any difficulty. [It is] the religion of your father, Abraham. Allah named you "Muslims" before [in former scriptures] and in this [revelation] that the Messenger may be a witness over you and you may be witnesses over the people. So establish prayer and give zakah and hold fast to Allah . He is your protector; and excellent is the protector, and excellent is the helper.

Copyright 2013, AmharicQuran.com