Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-አንቢያ (የነቢያት ምዕራፍ)

21:1
ለሰዎች እነሱ በዝንጋቴ ውስጥ (መሰናዳትን) የተው ኾነው ሳሉ ምርመራቸው ቀረበ

[The time of] their account has approached for the people, while they are in heedlessness turning away.

21:2
ከጌታቸው አዲስ የተወረደ ቁርአን አይመጣላቸውም እነሱ የሚያላግጡ ሆነው የሚያደምጡት ቢሆኑ እንጂ።

No mention comes to them anew from their Lord except that they listen to it while they are at play

21:3
ልቦቻቸው ዝንጉዎች ሆነው (የሚያዳምጡት ቢሆኑ እንጅ)፤ እነዚያም የበደሉት ሰዎች መንሾካሾክን ደበቁ፤ ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ ነውን? እናንተም የምታዩ ስትሆኑ ድግምትን ለመቀበል ትመጣላችሁን? (አሉ)።

With their hearts distracted. And those who do wrong conceal their private conversation, [saying], "Is this [Prophet] except a human being like you? So would you approach magic while you are aware [of it]?"

21:4
(ሙሐመድም) ጌታዬ ቃልን ሁሉ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለ ሲሆን ያውቃል፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፣ አለ።

The Prophet said, "My Lord knows whatever is said throughout the heaven and earth, and He is the Hearing, the Knowing."

21:5
፦ በውነቱ (ቁርአኑ) የሕልሞች ቅዠቶች ነው፤ ይልቁንም ቀጠፈው፤ እንዲያውም እርሱ ቅኔን ገጣሚ ነው፤ የቀድሞዎቹ እንደተላኩ (መልክተኛ ከሆነ) በታምር ይምጣብን አሉ።

But they say, "[The revelation is but] a mixture of false dreams; rather, he has invented it; rather, he is a poet. So let him bring us a sign just as the previous [messengers] were sent [with miracles]."

21:6
ከነሱ በፊት ያጠፋናት ከተማ አላመነችም፤ ታዲያ እነሱ ያምናሉን?

Not a [single] city which We destroyed believed before them, so will they believe?

21:7
ከአንተም በፊት ወደነሱ የምናወርድላቸው የኾኑ እንጂ ሌላን አልላክንም፤ የምታውቁም ብትኾኑም የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ።

And We sent not before you, [O Muhammad], except men to whom We revealed [the message], so ask the people of the message if you do not know.

21:8
ምግብን የማይበሉ አካልም አላደረግናቸውም ዘውታሪዎቹም አልነበሩም።

And We did not make the prophets forms not eating food, nor were they immortal [on earth].

21:9
ከዚያም ቀጠሮን ሞላንላቸው አዳናቸውም፤ የምንሻውንም ሰው (አዳን) ወሰን አላፊዎቹንም አጠፋን።

Then We fulfilled for them the promise, and We saved them and whom We willed and destroyed the transgressors.

21:10
ክብራችሁ በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደናንተ በእርግጥ አወረድን፤ አታውቁምን?

We have certainly sent down to you a Book in which is your mention. Then will you not reason?

21:11
በዳይም ከነበረች ከተማ ያጠፋናትና ከኋላዋም ሌሎችን ሕዝቦች ያስገኘነው ብዙ ናት።

And how many a city which was unjust have We shattered and produced after it another people.

21:12
ቅጣታችንም በተሰማቸው ጊዜ እነሱ ወዲያውኑ ከርሷ (ለመሸሽ) ይገሠግሣሉ።

And when its inhabitants perceived Our punishment, at once they fled from it.

21:13
አትገሥግሡ፤ ትልለምኑም ይኾናልና፣ በርሱ ወደ ተቀማጠላችሁበት ጸጋ ወደ መኖሪያዎቻችሁም ተመለሱ (ይባላሉ)። (1)
(1) ይህንን የሚባሉት ለቅጥጥብ ነው


[Some angels said], "Do not flee but return to where you were given luxury and to your homes - perhaps you will be questioned."

21:14
፡- ዋ ጥፋታችን! እኛ በእርግጥ በዳዮች ነበርን፣ ይላሉ።

They said, "O woe to us! Indeed, we were wrongdoers."

21:15
የታጨዱ ሬሳዎችም እስካደረግናቸው ድረስ ይህቺ ጥሪያቸው ከመሆን አልተወገደችም።

And that declaration of theirs did not cease until We made them [as] a harvest [mowed down], extinguished [like a fire].

21:16
ሰማይንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም።

And We did not create the heaven and earth and that between them in play

21:17
መጫወቻን (ሚስትን ልጅን) ልንይዝ በሻን ኖሮ ከኛ ዘንድ በያዝነው ነበር፣ (ግን) ሠሪዎች አይደለንም።

Had We intended to take a diversion, We could have taken it from [what is] with Us - if [indeed] We were to do so.

21:18
በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን፤ አንጎሉን ያፈርሰዋልም፤ ወዲያውም እርሱ ጠፊ ነው፤ ለእናንተም ከዚያ (ሚስትና ልጅ አለው በማለት) ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ፤ (ወዮላችሁ)።

Rather, We dash the truth upon falsehood, and it destroys it, and thereupon it departs. And for you is destruction from that which you describe.

21:19
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የርሱ ነው፤ እርሱ ዘንድ ያሉትም (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፤ አይሰለቹምም።

To Him belongs whoever is in the heavens and the earth. And those near Him are not prevented by arrogance from His worship, nor do they tire.

21:20
በሌሊትና በቀንም ያጠሩታል፤ አያርፉም።

They exalt [Him] night and day [and] do not slacken.

21:21
ይልቁንም ከምድር የሆኑን እነሱ ሙታንን የሚያስነሱን አማልክት ያዙን? (የለም)።

Or have men taken for themselves gods from the earth who resurrect [the dead]?

21:22
በሁለቱ (በሰማያትና በምድር) ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፤ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ።

Had there been within the heavens and earth gods besides Allah , they both would have been ruined. So exalted is Allah , Lord of the Throne, above what they describe.

21:23
ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም እነሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ።

He is not questioned about what He does, but they will be questioned.

21:24
ይልቁንም ከርሱ ሌላ አማልክት ያዙን? አስረጃችሁን አምጡ፤ ይህ (ቁርአን) እኔ ዘንድ ያለው ሕዝብ መገሠጫ፣ ከኔ በፊትም ከነበሩት ሕዝቦች መገሠጫ ነው በላቸው። በውነቱ አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም። ስለዚህ እነሱ እንቢተኞች ናቸው።

Or have they taken gods besides Him? Say, [O Muhammad], "Produce your proof. This [Qur'an] is the message for those with me and the message of those before me." But most of them do not know the truth, so they are turning away.

21:25
ከአንተ በፊትም፣ እነሆ ከኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።

And We sent not before you any messenger except that We revealed to him that, "There is no deity except Me, so worship Me."

21:26
አልረሕማንም (ከመላእክት) ልጅን ያዘ አሉ፤ ጥራት ተገባው፤ አይደለም (መላእክት) የተከበሩ ባሮች ናችው፤

And they say, "The Most Merciful has taken a son." Exalted is He! Rather, they are [but] honored servants.

21:27
በንግግር አይቀድሙትም፤ (ያላለውን አይሉም)፤ እነሱም በትእዛዙ ይሠራሉ።

They cannot precede Him in word, and they act by His command.

21:28
በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፤ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፤ እነሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው።

He knows what is [presently] before them and what will be after them, and they cannot intercede except on behalf of one whom He approves. And they, from fear of Him, are apprehensive.

21:29
ከነሱም እኔ ከርሱ ሌላ አምላክ ነኝ የሚል ያንን ገሀነምን እንመነዳዋለን፤ እንደዚሁ በዳዮችን እንመነዳለን።

And whoever of them should say, "Indeed, I am a god besides Him"- that one We would recompense with Hell. Thus do We recompense the wrongdoers.

21:30
እነዚያም የካዱት ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መሆናችንን አያውቁምን? ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን አያምኑምን?

Have those who disbelieved not considered that the heavens and the earth were a joined entity, and We separated them and made from water every living thing? Then will they not believe?

21:31
በምድርም ውስጥ በነሱ እንዳታረገርግ ጋራዎችን አደረግን፤ ይመሩም እንድ በርሷ ውስጥ ሰፋፊ መንገዶችን አደረግን።

And We placed within the earth firmly set mountains, lest it should shift with them, and We made therein [mountain] passes [as] roads that they might be guided.

21:32
ሰማይንም (ከመውደቅ) የተጠበቀ ጣራ አደረግን፤ እነሱም ከታምራቶቿ ዘንጊዎች ናቸው።

And We made the sky a protected ceiling, but they, from its signs, are turning away.

21:33
እርሱም ሌሊትና ቀንን ፀሐይንና ጨረቃንም፣ የፈጠረ ነው፤ ሁሉም በፈለካቸው (1) ውስጥ ይዋኛሉ።
(1) በመዞሪያቸው


And it is He who created the night and the day and the sun and the moon; all [heavenly bodies] in an orbit are swimming.

21:34
(ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘላለም መኖርን አላደረግንም፤ ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን?

And We did not grant to any man before you eternity [on earth]; so if you die - would they be eternal?

21:35
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፤ ወደኛም ትመለሳላችሁ።

Every soul will taste death. And We test you with evil and with good as trial; and to Us you will be returned.

21:36
እነዚያም የካዱት ሰዎች ባዩህ ኢዜ መሳለቂያ አድርገው እንጂ አይይዙህም፤ እነሱ በአልረሕማን መወሳት እነርሱ ከሐዲዎች ሲሆኑ ያ አማልክቶቻችሁን (በክፉ) የሚያነሳው ይህ ነውን? (ይላሉ)።

And when those who disbelieve see you, [O Muhammad], they take you not except in ridicule, [saying], "Is this the one who insults your gods?" And they are, at the mention of the Most Merciful, disbelievers.

21:37
ሰው ቸኳይ ሆኖ ተፈጠረ፤ ታምራቶቼን በእርግጥ አሳያችኋለሁና አታቻኩሉኝ።

Man was created of haste. I will show you My signs, so do not impatiently urge Me.

21:38
ይህ ቀጠሮም መቼ ነው? እውነተኞች ከሆናችሁ (አምጡት) ይላሉ።

And they say, "When is this promise, if you should be truthful?"

21:39
እነዚያ የካዱት ከፊቶቻቸውና ከጀርባዎቻቸው ላይ እሳትን የማይከለክሉበትን እነሱም የማይረዳዱበትን ጊዜ ቢያውቁ ኖሮ ይህንን አይሉም ነበር)።

If those who disbelieved but knew the time when they will not avert the Fire from their faces or from their backs and they will not be aided...

21:40
ይልቁንም (ሰዓቲቱ) በድንገት ትመጣቸዋለች፤ ታዋልላቸዋለችም፤ መመለሷንም አይችሉም፤ እነሱም አይቆዩም።

Rather, it will come to them unexpectedly and bewilder them, and they will not be able to repel it, nor will they be reprieved.

21:41
ከአንተ በፊትም የነበሩት መልክተኞች በእርግጥ ተቀለደባቸው፤ በነዚያም ከነሱ ይቀልዱ በነበሩት በርሱ ይሳለቁበት የነበሩት (ቅጣት) ሰፈረባቸው።

And already were messengers ridiculed before you, but those who mocked them were enveloped by what they used to ridicule.

21:42
ከአልረሕማን (ቅጣት) በሌሊትና በቀን የሚጠብቃችሁ ማነው? በላቸው፤ በውነቱ እነሱ ከጌታቸው ግሣጼ (ከቁርአን) ዘንጊዎች ናቸው።

Say, "Who can protect you at night or by day from the Most Merciful?" But they are, from the remembrance of their Lord, turning away.

21:43
ለነሱ ከኛ ሌላ የምትከላከልላቸው አማልክት አለቻቸውን? ነፍሶቻቸውን መርዳትን አይችሉም፤ እነሱም (ከሐዲዎቹ) ከኛ አይጠበቁም።

Or do they have gods to defend them other than Us? They are unable [even] to help themselves, nor can they be protected from Us.

21:44
በውነትም እነዚህንና አባቶቻቸውን፣ በነሱ ላይ ዕድሜ እስከረዘመባቸው ድረስ አጣቀምናቸው፤ (ተታለሉም)፣ እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ሆነን ስንመጣባት አያዩምን? እነሱ አሸናፊዎች ናቸውን?

But, [on the contrary], We have provided good things for these [disbelievers] and their fathers until life was prolonged for them. Then do they not see that We set upon the land, reducing it from its borders? So it is they who will overcome?

21:45
፦ የማስፈራራችሁ፣ በተወረደልኝ ብቻ ነው፣ ግን ደንቆሮዎች በሚስፈራሩበት ጊዜ ጥሪን አይሰሙም በላቸው።

Say, "I only warn you by revelation." But the deaf do not hear the call when they are warned.

21:46
ከጌታህ ቅጣትም ወላፈን ብትነካቸው፣ ዋ ጥፋታችን! እኛ በዳዮች ነበርን ላሉ።

And if [as much as] a whiff of the punishment of your Lord should touch them, they would surely say, "O woe to us! Indeed, we have been wrongdoers."

21:47
በትንሣኤም ቀን፣ ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን፣ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፤ (ሥራው) የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢሆንም እርሷን እናመጣታለን፤ ተቆጣጣሪዎችም በኛ በቃ።

And We place the scales of justice for the Day of Resurrection, so no soul will be treated unjustly at all. And if there is [even] the weight of a mustard seed, We will bring it forth. And sufficient are We as accountant.

21:48
ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን፣ ብርሃንንም፣ ለጥንቁቆችም መገሠጫን በእርግጥ ሰጠናቸው።

And We had already given Moses and Aaron the criterion and a light and a reminder for the righteous

21:49
ለነዚያ ጌታቸውን በሩቅ ለሚፈሩት፣ እነሱም ከሰዓቲቱ ተጨናቂዎች ለሆኑት (መገሠጫን ሰጠን)።

Who fear their Lord unseen, while they are of the Hour apprehensive.

21:50
ይህም (ቁርዓን) ያወረድነው የሆነ ብሩክ መገሠጫ ነው፤ ታዲያ እናንተ ለርሱ ከሐዲዎች ናችሁን?

And this [Qur'an] is a blessed message which We have sent down. Then are you with it unacquainted?

21:51
ለኢብራሂምም፣ ከዚያ በፊት ቅን መንገዱን በእርግጥ ሰጠነው፤ እኛም በርሱ (ተገቢነት) ዐዋቂዎች ነበርን።

And We had certainly given Abraham his sound judgement before, and We were of him well-Knowing

21:52
ለአባቱና ለሕዝቦቹ፦ ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ፣ ያቺ እናንተ ለርሷ ተገዢዎች የሆናችሁት ምንድን ናት? ባለ ጊዜ (መራነው)።

When he said to his father and his people, "What are these statues to which you are devoted?"

21:53
፡-አባቶቻችን ለሯ ተገዢዎች ሆነው አገኘን አሉ።

They said, "We found our fathers worshippers of them."

21:54
እናንተም አባቶቻችሁም፣ በእርግጥ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ነበራችሁ አላቸው።

He said, "You were certainly, you and your fathers, in manifest error."

21:55
በምሩ መጣልህን? ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ? አሉት።

They said, "Have you come to us with truth, or are you of those who jest?"

21:56
አይደለም፣ ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው፤ እኔም በይሃችሁ ላይ ከመስካሪዎቹ ነኝ፣ አለ።

He said, "[No], rather, your Lord is the Lord of the heavens and the earth who created them, and I, to that, am of those who testify.

21:57
በአላህም ስም እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከኼዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን ተንኮል እሰራባቸዋለሁ፣ (አለ)።

And [I swear] by Allah , I will surely plan against your idols after you have turned and gone away."

21:58
(ዘወር ሲሉ) ስብርብሮችም አደረጋቸው፤ ለነሱ የሆነ አንድ ታላቅ (ጣዖት) ብቻ ሲቀር ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ (እርሱን ተወው)።

So he made them into fragments, except a large one among them, that they might return to it [and question].

21:59
፦በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራ ማነው? እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው፣ አሉ።

They said, "Who has done this to our gods? Indeed, he is of the wrongdoers."

21:60
(ኢብራሂም) የሚባል ጎበዝ (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል ተባባሉ።

They said, "We heard a young man mention them who is called Abraham."

21:61
ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎች ዓይን (ፊት) ላይ አምጡት አሉ።

They said, "Then bring him before the eyes of the people that they may testify."

21:62
ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራህ አንተ ነህን? አሉት።

They said, "Have you done this to our gods, O Abraham?"

21:63
አይደለም፣ ይህ ትልቃቸው ሠራው፤ ይናገሩም እንደ ሆነ ጠይቋቸው፣ አለ።

He said, "Rather, this - the largest of them - did it, so ask them, if they should [be able to] speak."

21:64
ወደ ነፍሶቻቸውም ተመለሱ። እናንተ (በመጠየቃችሁ) በዳዮቹ እናንተው ናችሁም ተባባሉ።

So they returned to [blaming] themselves and said [to each other], "Indeed, you are the wrongdoers."

21:65
ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡ፤ (1) እነዚህ የሚናገሩ አለመሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀሃል፤ (አሉ)።
(1) ወደ መጥፎ ሁኔታቸው ተመለሱ


Then they reversed themselves, [saying], "You have already known that these do not speak!"

21:66
ታዲያ ለናንተ ምንም የማይጠቅማችሁንና የማይጎዳችሁን ነገር ከአላህ ሌላ ትግገዛላችሁን? አላቸው።

He said, "Then do you worship instead of Allah that which does not benefit you at all or harm you?

21:67
ፎህ! ለናንተ፣ ከአላህ ሌላ ለምትግገዙትም ነገር አታውቁምን? (አለ)።

Uff to you and to what you worship instead of Allah . Then will you not use reason?"

21:68
፦ሠሪዎች እንደ ሆናችሁ አቃጥሉት፣ አማልክቶቻችሁንም እርዱ አሉ። (በእሳት ላይ ጣሉትም)።

They said, "Burn him and support your gods - if you are to act."

21:69
፦እሳት ሆይ! ኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ አልን።

Allah said, "O fire, be coolness and safety upon Abraham."

21:70
በርሱም ተንኮልን አሰቡ፤በጣም ከሳሪዎችም አደረግናቸው።

And they intended for him harm, but We made them the greatest losers.

21:71
እርሱንና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (በመውሰድ) አዳን።

And We delivered him and Lot to the land which We had blessed for the worlds.

21:72
ለርሱም ኢስሐቅን፣ ያዕቆብንም ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው፤ ሁሉንም መልካሞች አደረግን።

And We gave him Isaac and Jacob in addition, and all [of them] We made righteous.

21:73
በትእዛዛችንም፣ ወደ በጎ ሥራ የሚመሩ፣ መሪዎች አደረግናቸው፤ ወደነሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትን መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን፣ አወረድን፤ ለኛ ተገዢዎችም ነበሩ።

And We made them leaders guiding by Our command. And We inspired to them the doing of good deeds, establishment of prayer, and giving of zakah; and they were worshippers of Us.

21:74
ሎጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው፤ ከዚያችም መጥፎ ሥራዎችን ትሠራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው፤ እነሱ ክፉ ሰዎች አመጠኞች ነበሩና።

And to Lot We gave judgement and knowledge, and We saved him from the city that was committing wicked deeds. Indeed, they were a people of evil, defiantly disobedient.

21:75
በችሮታችንም ውስጥ አገባነው፤ እርሱ ከመልካሞቹ ነውና።

And We admitted him into Our mercy. Indeed, he was of the righteous.

21:76
ኑሕንም ከዚያ በፊት (ጌታውን) በጠራ ጊዜ (አስታውስ)፤ ለርሱም (ጥሪውን) ተቀበልነው፤ እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን።

And [mention] Noah, when he called [to Allah ] before [that time], so We responded to him and saved him and his family from the great flood.

21:77
ከነዚያም በታምራቶቻችን ከአስተባበሉት ሕዝቦች (ተንኮል)ጠበቅነው፤ እነሱ ክፉ ሕዝቦች አመጠኞች ነበሩና፤ ሁሉንም አሰጠምናቸውም።

And We saved him from the people who denied Our signs. Indeed, they were a people of evil, so We drowned them, all together.

21:78
ዳውድንና ሱለይማንንም በአዝመራው ነገር በሚፈርዱ ጊዜ የሕዝቦቹ ፍየሎች ሌሊት በርሱ ውስጥ በተሠማሩ ጊዜ፣ (አስታውስ)፤ ፍርዳቸውንም ዐዋቂዎች ነበርን።

And [mention] David and Solomon, when they judged concerning the field - when the sheep of a people overran it [at night], and We were witness to their judgement.

21:79
ለሱለይማንም (ትክክለኛይቱን ፍርድ) አሳውቅናት፤ ለሁሉም ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠን፤ ተራራዎችንም ከዳውድ ጋር የሚያወድሱ ሲኾኑ ገራን፤ አእዋፍንም፣ (እንደዚሁ ገራን) ሠሪዎችም ነበርን።

And We gave understanding of the case to Solomon, and to each [of them] We gave judgement and knowledge. And We subjected the mountains to exalt [Us], along with David and [also] the birds. And We were doing [that].

21:80
የብረት ልብስንም ሥራ፣ ለናንተ ከጦራችሁ ትጠበቃችሁ ዘንድ፣ አስተማርነው፤ እናንተ አመስጋኞች ናችሁን?

And We taught him the fashioning of coats of armor to protect you from your [enemy in] battle. So will you then be grateful?

21:81
ለሱለይማም ነፋስን በኅይል የምትነፍስ በትእዛዙ ወደዚያች በርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንበት ምድር (ወደ ሻም) የምትፈስ ስትሆን (ገራንለት)፤ በነገር ሁሉም ዐዋቂዎች ነበርን።

And to Solomon [We subjected] the wind, blowing forcefully, proceeding by his command toward the land which We had blessed. And We are ever, of all things, Knowing.

21:82
ከሠይጣናትም ለርሱ (ሉልን ለማውጣት) የሚጠልሙንና ከዚያም ሌላ ያለን ሥራ የሚሠሩን (ገራንለት)፤ ለነሱም ተጠባባቂዎች ንበርን።

And of the devils were those who dived for him and did work other than that. And We were of them a guardian.

21:83
አዩብንም (እዮብን) ጌታውን ፦ እኔ መከራ አገኝኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ ዛኝ ነህ፣ ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)።

And [mention] Job, when he called to his Lord, "Indeed, adversity has touched me, and you are the Most Merciful of the merciful."

21:84
ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ ከጉዳትም በርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን፤ ቤተ ሰቦቹንም ከነሱም ጋር መሰላቸውን ከኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው።

So We responded to him and removed what afflicted him of adversity. And We gave him [back] his family and the like thereof with them as mercy from Us and a reminder for the worshippers [of Allah ].

21:85
ኢስማዒልንም፣ ኢድሪስንም፣ ዙልኪፍልንም (አስታውስ)፤ ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው።

And [mention] Ishmael and Idrees and Dhul-Kifl; all were of the patient.

21:86
በችሮታችንም ውስጥ አገባናቸው፤ እነሱ ከመልካሞቹ ናቸውና።

And We admitted them into Our mercy. Indeed, they were of the righteous.

21:87
የዐሣውንም ባለቤት (1) ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፤ እርሱም ላይ ፍጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ፤ (ዐሳም ዋጠው)፤ በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ ፦ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ጥራት ይገባህ፤ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ።
(1) ዮናስን


And [mention] the man of the fish, when he went off in anger and thought that We would not decree [anything] upon him. And he called out within the darknesses, "There is no deity except You; exalted are You. Indeed, I have been of the wrongdoers."

21:89
ዘከሪያንም፣ ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተዎኝ፤ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ ሲል፣ ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፤

And [mention] Zechariah, when he called to his Lord, "My Lord, do not leave me alone [with no heir], while you are the best of inheritors."

21:90
ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ ለርሱም የሕያን ሰጠነው፤ ለርሱም ሚስቱን አበጀንለት፤ (1) እነሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ፣ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑም ነበሩ፤ ለኛ ተዋራጆችም ነበሩ፤
(1) እንድትወልድለት አደረግንለት


So We responded to him, and We gave to him John, and amended for him his wife. Indeed, they used to hasten to good deeds and supplicate Us in hope and fear, and they were to Us humbly submissive.

21:91
ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን፣ በርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን እርስዋንም ልጅዋንም (እንደዚሁ)፣ ለዓለማት ታምር ያደረግናትን፣ (መርየምን፣ አታውስ)።

And [mention] the one who guarded her chastity, so We blew into her [garment] through Our angel [Gabriel], and We made her and her son a sign for the worlds.

21:92
ይህች (ሕግጋት) አንዲት መንገድ ስትኾን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ እኔም ጌታችሁ ነኝና ተገዙኝ።

Indeed this, your religion, is one religion, and I am your Lord, so worship Me.

21:93
በሃይማኖታቸውም ነገር በመካከላቸው ተለያዩ፤ ሁሉም ወደኛ ተመላሾች ናቸው።

And [yet] they divided their affair among themselves, [but] all to Us will return.

21:94
እርሱ ያመነ ሆኖ ከበጎ ሥራዎች ማንኛውንም የሚሠራም ሰው፤ ምንዳውን አይነፈግም፤ እኛም ለርሱ መዝጋቢዎች ነን።

So whoever does righteous deeds while he is a believer - no denial will there be for his effort, and indeed We, of it, are recorders.

21:95
ባጠፋናትም ከተማ ላይ እነሱ (ወደኛ) የማይመለሱ መሆናቸው እብለት ነው፤ (ይመለሳሉ)።

And there is prohibition upon [the people of] a city which We have destroyed that they will [ever] return

21:96
የእጁጅና መእጁጅም፣ እነርሱ ከየተረተሩ የሚንደረደሩ ሲሆኑ፣ (ግድባቸው) በተከፈተች ጊዜ፣

Until when [the dam of] Gog and Magog has been opened and they, from every elevation, descend

21:97
እውነተኛውም ቀጠሮ በቀረበ ጊዜ፣ ያን ጊዜ እነሆ የነዚያ የካዱት ሰዎች ዓይኖች ይፈጥጣሉ፤ ዋ ጥፋታችን! ከዚህ (ቀን) በእርግጥ በዝንጋቴ ላይ ነበርን፤ በውነትም በዳዮች ነበርን፤ (ይላሉ)።

And [when] the true promise has approached; then suddenly the eyes of those who disbelieved will be staring [in horror, while they say], "O woe to us; we had been unmindful of this; rather, we were wrongdoers."

21:98
እናንተ፣ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውም (ጣዖታት) የገሃነም ማገዶዎች ናችሁ፤ እናንተ ለርሷ ወራጆች ናችሁ።

Indeed, you [disbelievers] and what you worship other than Allah are the firewood of Hell. You will be coming to [enter] it.

21:99
እነዚህ (ጣዖታት)፣ አማልክት በነበሩ ኖሮ አይገቡዋትም ነበር፤ ግን ሁሉም በርስዋ ውስጥ ዘውታሪዎች ናችው።

Had these [false deities] been [actual] gods, they would not have come to it, but all are eternal therein.

21:100
ለነርሱ በርስዋ ውስጥ መንሰቅሰቅ አላቸው፤ እነርሱም በውስጧ (ምንንም) አይሰሙም።

For them therein is heavy sighing, and they therein will not hear.

21:101
እነዚያ ከኛ መልካምዋ ቃል ለነርሱ ያለፈችላቸው፣ እነዚያ ከርሷ የተራቁ ናቸው።

Indeed, those for whom the best [reward] has preceded from Us - they are from it far removed.

21:102
ድምጽዋን አይሰሙም፤ እነሱም ነፍሶቻቸው በሚሹት ነገር ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።

They will not hear its sound, while they are, in that which their souls desire, abiding eternally.

21:103
ታላቁ ድንጋጤ፣ አያስተክዛቸውም፤ መላእክትም፣ ይህ፣ ያ ትቀጠሩት የነበራችሁት ቀናችሁ ነው፤ እያሉ ይቀበሏቸዋል።

They will not be grieved by the greatest terror, and the angels will meet them, [saying], "This is your Day which you have been promised" -

21:104
ለመጽሐፎች የሆኑ ገጾች እንደሚጠቀለሉ ሰማይን የምንጠቀልልበትን ቀን (አስታውስ)፤ የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን፤ (መፈጸሙ) በኛ ላይ የሆነን ቀጠሮ ቀጠርን፤ እኛ (የቀጠርነውን) ሠሪዎች ነን።

The Day when We will fold the heaven like the folding of a [written] sheet for the records. As We began the first creation, We will repeat it. [That is] a promise binding upon Us. Indeed, We will do it.

21:105
ምድርንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል ማለትን ከመጽሐፉ (ከተጠበቀው ሰሌዳ) በኋላ፣ በመጽሐፎቹ በእርግጥ ጽፈናል።

And We have already written in the book [of Psalms] after the [previous] mention that the land [of Paradise] is inherited by My righteous servants.

21:106
በዚህ (ቁርአን) ውስጥ፣ ለተገዢዎች ሕዝቦች በቂነት አለ።

Indeed, in this [Qur'an] is notification for a worshipping people.

21:107
(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም።

And We have not sent you, [O Muhammad], except as a mercy to the worlds.

21:108
ያ ወደኔ የሚወረደው፣ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን? በላቸው።

Say, "It is only revealed to me that your god is but one God; so will you be Muslims [in submission to Him]?"

21:109
እምቢም ቢሉ (በማወቅ) በእኩልነት ላይ ሆነን (የታዘዝኩትን) አስታወቅኋችሁ፤ የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ፣ ወይም ሩቅ፣ መሆኑን አላውቅም፤ በላቸው።

But if they turn away, then say, "I have announced to [all of] you equally. And I know not whether near or far is that which you are promised.

21:110
እርሱ ከንግግር ጩኸትን ያውቃል፤ የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል።

Indeed, He knows what is declared of speech, and He knows what you conceal.

21:111
እርሱም (ቅጣትን ማቆየት) ምናልባት ለናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጣቀሚያ እንደኾነም አላውቅም፤ (በላቸው)።

And I know not; perhaps it is a trial for you and enjoyment for a time."

21:112
፦ ጌታዬ ሆይ በውነት ፍረድ፤ ጌታችንም እጅግ በጣም ርኅሩኅ፤ በምትሉት ነገር ላይ፤ መታገዣ ነው፤ አለ።

[The Prophet] has said, "My Lord, judge [between us] in truth. And our Lord is the Most Merciful, the one whose help is sought against that which you describe."

Copyright 2013, AmharicQuran.com