Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱርቱ መርየም፣ (የማርያም ምዕራፍ)

19:1
ከ፡ሀ፡የ፡ዐ፡ጸ (ካፍ፡ ሃ፡ ያ፡ ዓይን፡ሷድ )፡ (1)
1. ለባሮቼ በቂ፣ መሪ፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ዐዋቂ እውነተኛ ነኝ።


Kaf, Ha, Ya, 'Ayn, Sad.

19:2
(ይህ) ጌታህ ባሪያውን ዘከሪያን (2) በችሮታዉ ያወሳበት ነው።
2.ዘካርያስን


[This is] a mention of the mercy of your Lord to His servant Zechariah

19:3
ጌታውን የምስጢር ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)

When he called to his Lord a private supplication.

19:4
፦ አለ ጌታዬ ሆይ እኔ አጥንቴ ደከመ ፤ ራሴም በሺበት ተንቀለቀለ ፤ አንተንም በመለመኔ ጌታዬ ሆይ! (ምንግዜም) ዕደለ ቢስ አልኾንኩም ።

He said, "My Lord, indeed my bones have weakened, and my head has filled with white, and never have I been in my supplication to You, my Lord, unhappy.

19:5
እኔም ከበኃላዬ ዘመዶቼን (3)በእርግጥ ፈራሁ፤ ሚስቴም መካን ነበረች፣ ስለዚህ ከአንተ ዘንድ ለኔ ልጅን ስጠኝ፤
(3). ሃይማኖትህን ይበድላሉ ብዬ


And indeed, I fear the successors after me, and my wife has been barren, so give me from Yourself an heir

19:6
የሚወርሰኝ ከያዕቆብ ቤተሰቦችም የሚወርስ የኾነን፣ (ልጅ)፤ ጌታዬ ሆይ! ተወዳጅም አድርገው።

Who will inherit me and inherit from the family of Jacob. And make him, my Lord, pleasing [to You]."

19:7
ዘከሪያ ሆይ! እኛ በወንድ ልጅ፣ ስሙ የሕያ (4) በኾነ፣ ከዚህ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት እናበስርሃለን ፤ (አለው)።
(4). ዮሐንስ


[He was told], "O Zechariah, indeed We give you good tidings of a boy whose name will be John. We have not assigned to any before [this] name."

19:8
፦ ጌታዬ ሆይ! ሚስቴ መካን የነበረች ስትኾን፣ እኔም ከእርጅና ድርቀትን በእርግጥ የደረስኩ ስኾን፣ እንዴት ልጅ ይኖርኛል! አለ።

He said, "My Lord, how will I have a boy when my wife has been barren and I have reached extreme old age?"

19:9
(ጅብሪል) አለ (ነገሩ)እንድዚሁ ነው ጌታህ ከአሁን በፊት ምንም ያልነበርከውን የፈጠርኩህ ስኾን፣ እርሱ በኔ ላይ ቀላል ነው፤ አለ።

[An angel] said, "Thus [it will be]; your Lord says, 'It is easy for Me, for I created you before, while you were nothing.' "

19:10
ጌታዬ ሆይ! (እንግዲያስ) ለኔ ምልክትን አድርግልኝ አለ፤ ምልክትህ ጤናማ ሆነህ ሳለህ ሦስት ሌሊትን (ከነቀናቸዉ) ሰዎችን ለማነጋገር አለመቻልህ ነዉ ፤ አለው።

[Zechariah] said, "My Lord, make for me a sign." He said, "Your sign is that you will not speak to the people for three nights, [being] sound."

19:11
ከምኲራቡም በሕዝቦቹ ላይ ወጣ፤ በጧትና በማታ (ጌታችሁን) አወድሱ በማለትም፣ ወደነሱ ጠቀሰ።

So he came out to his people from the prayer chamber and signaled to them to exalt [ Allah ] in the morning and afternoon.

19:12
የሕያ ሆይ! መጽሐፉን በጥብቅ ያዝ፣ (አልነዉ)፤ ጥበብንም በሕጻንነቱ ሰጠነዉ።

[ Allah ] said, "O John, take the Scripture with determination." And We gave him judgement [while yet] a boy

19:13
ከኛም የኾነን ርኅራኄ፣ ንጽሕናንም (ሰጠነው)፤ ጥንቁቅም ነበር።

And affection from Us and purity, and he was fearing of Allah

19:14
ለወላጆቹም በጎ ሠሪ ነበር፤ ትዕቢተኛ አመጠኛም አልነበረም።

And dutiful to his parents, and he was not a disobedient tyrant.

19:15
በተወለደበት ቀንና በሚሞትበትም ቀን፣ ሕያዉ ኾኖ በሚነሳበትም ቀን፣ ሰላም በሱ ላይ ይኹን።

And peace be upon him the day he was born and the day he dies and the day he is raised alive.

19:16
በመጽሐፉ ዉስጥ መርየምንም ከቤተ ሰቧ ወደ ምሥራቃዊ ስፍራ በተለየች ጊዜ (የኾነዉን ታሪኳን) አዉሳ።

And mention, [O Muhammad], in the Book [the story of] Mary, when she withdrew from her family to a place toward the east

19:17
ከነሱም መጋረጃን አደረገች፣ መንፈሳችንንም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፤ ለርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት።

And she took, in seclusion from them, a screen. Then We sent to her Our Angel, and he represented himself to her as a well-proportioned man.

19:18
፦ እኔ ከአንተ በአልረሕማን እጠበቃለሁ፤ ጌታህን ፈሪ እንደ ኾንክ፣ (አትቅረበኝ) አለች።

She said, "Indeed, I seek refuge in the Most Merciful from you, [so leave me], if you should be fearing of Allah ."

19:19
፦ እኔ ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ፣ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ አላት።

He said, "I am only the messenger of your Lord to give you [news of] a pure boy."

19:20
(በጋብቻ) ሰዉ ያልነካኝ ኾኜ፣ አመንዝራም ሳልኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል! አለች።

She said, "How can I have a boy while no man has touched me and I have not been unchaste?"

19:21
፦ አላት (ነገሩ) እንደዚህሽ ነው ፤ ጌታሽ ፦ እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፤ ለሰዎችም ታምር፣ ከኛም ችሮታ ልናደርገው (ይህንን ሠራን) የተፈረደም ነገር ነዉ አለ፤ (ነፋባትም)።

He said, "Thus [it will be]; your Lord says, 'It is easy for Me, and We will make him a sign to the people and a mercy from Us. And it is a matter [already] decreed.' "

19:22
ወዲያዉኑም አረገዘችዉ፤ በርሱም (በሆድዋ ይዛዉ) ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች።

So she conceived him, and she withdrew with him to a remote place.

19:23
ምጡም ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት፣ ዋ ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፣ ተረስቼም የቀረሁ በኾንኩ፤ አለች።

And the pains of childbirth drove her to the trunk of a palm tree. She said, "Oh, I wish I had died before this and was in oblivion, forgotten."

19:24
ከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት ፦ አትዘኝ፤ ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል።

But he called her from below her, "Do not grieve; your Lord has provided beneath you a stream.

19:25
የዘምባባይቱንም ግንድ ወዳንቺ ወዝዉዧት፤ ባንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና።

And shake toward you the trunk of the palm tree; it will drop upon you ripe, fresh dates.

19:26
ብይም፣ ጠጭም፤ ተደሰችም፤ ከሰዎችም አንድን ብታይ ፦ እኔ ለአልረሕማን ዝምታን ተስያለሁ፤ ዛሬም ሰዉን በፍጹም አላነጋግርም በይ።

So eat and drink and be contented. And if you see from among humanity anyone, say, 'Indeed, I have vowed to the Most Merciful abstention, so I will not speak today to [any] man.' "

19:27
በርሱም የተሸከመቺዉ ኾና ወደ ዘመዶችዋ መጣች ፦ መርየም ሆይ ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ አሏት።

Then she brought him to her people, carrying him. They said, "O Mary, you have certainly done a thing unprecedented.

19:28
የሃሩን (1) እኅት ሆይ አባትሽ መጥፎ ሰዉ አልነበረም፤ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም አሉዋት።
(1) የአባትዋ ልጅ ነው የሙሳ ወንድም ሀሩን አይደለም።


O sister of Aaron, your father was not a man of evil, nor was your mother unchaste."

19:29
ወደርሱም ጠቀሰች ፤ በአንቀልባ ያለን ሕፃን እንዴት እናናግራለን! አሉ።

So she pointed to him. They said, "How can we speak to one who is in the cradle a child?"

19:30
(ሕፃኑም) አለ እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ መጽሐፍም ሰጥቶኛል ነቢይም አድረጎኛል።

[Jesus] said, "Indeed, I am the servant of Allah . He has given me the Scripture and made me a prophet.

19:31
በየትም ስፍራ ብኾን ብሩክ አድርጎኛል፤ በሕይወትም እስከ አለዉ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል።

And He has made me blessed wherever I am and has enjoined upon me prayer and zakah as long as I remain alive

19:32
ለእናቴም ታዛዥ (አድርጎኛል)፤ ትዕቢተኛ እምቢተኛም አላደረገኝም።

And [made me] dutiful to my mother, and He has not made me a wretched tyrant.

19:33
ሰላምም በኔ ላይ ነው፣ በተወለድሁ ቀን፣ በምሞተበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን፤

And peace is on me the day I was born and the day I will die and the day I am raised alive."

19:34
ይህ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው፤ ያ በርሱ የሚጠራጠሩበት እዉነተኛ ቃል ነዉ።

That is Jesus, the son of Mary - the word of truth about which they are in dispute.

19:35
ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባዉም፤ (ከጉድለት ሁሉ) ጠራ፤ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለዉ ኹን ነዉ ውዲያዉም ይኾናል።

It is not [befitting] for Allah to take a son; exalted is He! When He decrees an affair, He only says to it, "Be," and it is.

19:36
(ዒሳ አለ) ፦ አላህም ጌታዬ ጌታችሁም ነዉና ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው።

[Jesus said], "And indeed, Allah is my Lord and your Lord, so worship Him. That is a straight path."

19:37
ከመካከላቸዉም አሕዛቦቹ በርሱ ነገር ተለያዩ ለነዚያም ለካዱት ሰዎች፣ ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ወዮላቸዉ።

Then the factions differed [concerning Jesus] from among them, so woe to those who disbelieved - from the scene of a tremendous Day.

19:38
በሚመጡን ቀን፣ ምን ሰሚ ምንስ ተመልካች አደረጋቸዉ! ግን አመጠኞች ዛሬ (በዚህ ዓለም ) በግልጽ ስሕተተ ዉስጥ ናቸዉ።

How [clearly] they will hear and see the Day they come to Us, but the wrongdoers today are in clear error.

19:39
እነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ኾነው ሳሉ እነሱም የማያምኑ ሲኾኑ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁልጭቱን ቀን አስፈራራቸው።

And warn them, [O Muhammad], of the Day of Regret, when the matter will be concluded; and [yet], they are in [a state of] heedlessness, and they do not believe.

19:40
እኛ ምድርን፣ በርሷም ላይ ያለውን ሁሉ እኛ እንወርሳለን፤ ወደኛም ይመለሳሉ።

Indeed, it is We who will inherit the earth and whoever is on it, and to Us they will be returned.

19:41
በመጽሐፉ ውስጥ ኢብራሂምንም አዉሳ፤ እርሱ በጣም እውነተኛ ነቢይ ነበርና።

And mention in the Book [the story of] Abraham. Indeed, he was a man of truth and a prophet.

19:42
ላባቱ ባለ ጊዜ (አስታዉስ) ፦ አባቴ ሆይ የማይሰማንና የማያይን፣ ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን (ጣዖት)ለምን ትግገዛለህ?

[Mention] when he said to his father, "O my father, why do you worship that which does not hear and does not see and will not benefit you at all?

19:43
አባቴ ሆይ! እኔ ከዕዉቀት ያልመጣልህ ነገር በእርግጥ መጥቶልኛልና ተከተለኝ ቀጥተኛዉን መንገድ እመራሃለሁና።

O my father, indeed there has come to me of knowledge that which has not come to you, so follow me; I will guide you to an even path.

19:44
አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትግገዛ፤ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጠኛ ነዉና።

O my father, do not worship Satan. Indeed Satan has ever been, to the Most Merciful, disobedient.

19:45
አባቴ ሆይ! ከአልረሕማን ቅጣት ሊያገኝህ ለሰይጣንም ጎደኛ ልትኾን እፈራለሁ።

O my father, indeed I fear that there will touch you a punishment from the Most Merciful so you would be to Satan a companion [in Hellfire]."

19:46
(አባቱም) ኢብራሂም ሆይ አንተ ከአምላኮቼ ትተህ የምትዞር ነህን ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ ፤ረዢም ጊዜንም ተዎኝ አለ።

[His father] said, "Have you no desire for my gods, O Abraham? If you do not desist, I will surely stone you, so avoid me a prolonged time."

19:47
ደህና ኹን ወደፊት ከጌታየ ምሕረትን እለምንልሃለሁ እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩህ ነዉና አለ፤

[Abraham] said, "Peace will be upon you. I will ask forgiveness for you of my Lord. Indeed, He is ever gracious to me.

19:48
እናንተንም ከአላህ ሌላ የምትግዙትንም እርቃለሁ፤ ጌታየንም እግዛለሁ፤ ጌታየን በመገዛት የማፍር አለመኾኔን እከጅላለሁ።

And I will leave you and those you invoke other than Allah and will invoke my Lord. I expect that I will not be in invocation to my Lord unhappy."

19:49
እነሱንም ከአላህ ሌላ የሚግገዙትንም በራቀ ጊዜ ለርሱ ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው፤ ሁሉንም ነቢይ አደረግንም።

So when he had left them and those they worshipped other than Allah , We gave him Isaac and Jacob, and each [of them] We made a prophet.

19:50
ለነሱም ከችሮታችን ሰጠናቸዉ፤ ለነሱም ከፍ ያለ ምስጉን ዝናን አደረግንላቸዉ።

And We gave them of Our mercy, and we made for them a reputation of high honor.

19:51
በመጽሐፉ ዉስጥ ሙሳንም አዉሳ፤ እርሱ ምርጥ ነበርና መልክተኛ ነቢይም ነበር።

And mention in the Book, Moses. Indeed, he was chosen, and he was a messenger and a prophet.

19:52
ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው ያነጋገርነዉም ሲኾን አቀረብነው።

And We called him from the side of the mount at [his] right and brought him near, confiding [to him].

19:53
ከችሮታችንም ወንድሙን ሃሩንን ነቢይ አድርገን ሰጠነዉ።

And We gave him out of Our mercy his brother Aaron as a prophet.

19:54
በመጽሐፉ ኢስማዔልንም አዉሳ፤ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፤ መልክተኛ ነቢይም ነበር።

And mention in the Book, Ishmael. Indeed, he was true to his promise, and he was a messenger and a prophet.

19:55
ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር፤ እጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር።

And he used to enjoin on his people prayer and zakah and was to his Lord pleasing.

19:56
በመጽሐፉ ኢድሪስንም (ሄኖክን) አዉሳ እርሱ እዉነተኛ ነቢይ ነበርና።

And mention in the Book, Idrees. Indeed, he was a man of truth and a prophet.

19:57
ወደ ከፍተኛም ስፍራ አነሳነዉ።

And We raised him to a high station.

19:58
እነዚህ (ዐሥሩ) እነዚያ አላህ በነሱ ላይ የለገሰላቸው ከነቢያት፣ ከአዳም ዘር፣ ከኑሕ ጋር (በመርከቢቱ ላይ)ከጫናቸዉም (ዘሮች)፣ ከኢብራሂምና ከእስራኤልም ዘሮች፣ ከመራናቸውም የኾኑት፣ የአልረሕማን አንቀጾች በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ፣ ሰጋጆችና አልቃሾች ኾነዉ ይወድቃሉ።

Those were the ones upon whom Allah bestowed favor from among the prophets of the descendants of Adam and of those We carried [in the ship] with Noah, and of the descendants of Abraham and Israel, and of those whom We guided and chose. When the verses of the Most Merciful were recited to them, they fell in prostration and weeping.

19:59
ከነሱም በኋላ ሶላትን ያጎደሉ፣ (የተዉ)፣ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ።

But there came after them successors who neglected prayer and pursued desires; so they are going to meet evil -

19:60
ግን የተጸጸተና ያመነም በጎንም ሥራ የሠራ ሰዉ እነዚህ ገነትን ይገባሉ፤ አንዳችንም አይበደሉም።

Except those who repent, believe and do righteousness; for those will enter Paradise and will not be wronged at all.

19:61
የመኖሪያን ገነቶች፣ ያችን አልረሕማን ለባሮቹ በሩቅ ኾነዉ ሳሉ ተስፋ ቃል የገባላቸዉን፣ (ይገባሉ)እርሱ ተስፋዉ ተፈጻሚ ነዉና፤

[Therein are] gardens of perpetual residence which the Most Merciful has promised His servants in the unseen. Indeed, His promise has ever been coming.

19:62
በርሷ ሰላምን እንጂ ዉድ ቅን ነገር አይሰሙም፤ ለነሱም በርሷ ዉስጥ፣ ጧትም ማታም ሲሳያቸዉ አላቸዉ።

They will not hear therein any ill speech - only [greetings of] peace - and they will have their provision therein, morning and afternoon.

19:63
ይህች ያቺ ከባሮቻቸን ጥንቁቆች ለኾኑት፣ የምናወርሳት ገነት ናት።

That is Paradise, which We give as inheritance to those of Our servants who were fearing of Allah .

19:64
(ጂብሪል፤ አለ) በጌታህም ትእዛዝ እንጂ አንወርድም፤ በፊታችን ያለው በኋላችንም ያለዉ፣ በዚህም መካከል ያለዉ ሁሉ የርሱ ነው፤ ጌታህም ረሺ አይደለም።

[Gabriel said], "And we [angels] descend not except by the order of your Lord. To Him belongs that before us and that behind us and what is in between. And never is your Lord forgetful -

19:65
(እርሱ) የሰማያትና የምድር፣ በሁለቱም መካካል ላለዉ ሁሉ ጌታ ነዉና ተገዛዉ፤ እርሱን በመግገዛትም ላይ ታገሥ፤ ለርሱ ሞክሼን ታዉቃለህን ?

Lord of the heavens and the earth and whatever is between them - so worship Him and have patience for His worship. Do you know of any similarity to Him?"

19:66
ሰውም፣ በሞትኩ ጊዜ ወደፊት ሕያዉ ኾኜ (ከመቃብር) እወጥጣለሁን? ይላል።

And the disbeliever says, "When I have died, am I going to be brought forth alive?"

19:67
ሰዉ፣ ከአሁን በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲኾን፣ እኛ የፈጠርነዉ መኾኑን አያስታዉስምን ?

Does man not remember that We created him before, while he was nothing?

19:68
በጌታህ እንምላለን፣ ሰይጣናት ጋር በእርግጥ እንሰበስባቸዋለን፤ ከዚያም በገሀነም ዙሪያ የተንበረከኩ ኾነዉ፤ በእርግጥ እናቀርባቸዋለን።

So by your Lord, We will surely gather them and the devils; then We will bring them to be present around Hell upon their knees.

19:69
ከዚያም ከየጭፍሮቹ ሁሉ ከነርሱ ያንን (እርሱ) በአልረሕማን ላይ በድፍረት በጣም ብርቱ የኾነዉን እናወጣለን፤

Then We will surely extract from every sect those of them who were worst against the Most Merciful in insolence.

19:70
ከዚያም እኛ እነዚያን እነሱ በርሷ ለመግባት ተገቢ የኾኑትን እናዉቃለን።

Then, surely it is We who are most knowing of those most worthy of burning therein.

19:71
ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፤ (መዉረዱም) ጌታህ የፈረደዉ ግዴታ ነዉ።

And there is none of you except he will come to it. This is upon your Lord an inevitability decreed.

19:72
ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፤ አመጠኞቹንም የተንበረከኩ ኾነዉ በዉስጧ እንተዋቸዋለን።

Then We will save those who feared Allah and leave the wrongdoers within it, on their knees.

19:73
በነሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጽ ማስረጃዎቸ ኾነው በተነበቡ ጊዜ፣ እነዚያ የካዱት ለነዚያ ላመኑት ከሁለቱ ክፍሎች መኖሪያዉ የሚበልጠዉና ቨንጎዉም ይበልጥ የሚያምረዉ ማንኛው ነዉ ይላሉ ።

And when Our verses are recited to them as clear evidences, those who disbelieve say to those who believe, "Which of [our] two parties is best in position and best in association?"

19:74
ከነሱም በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች እነሱ በቁሳቁስና በትርኢትም በጣም ያማሩትን ብዙዎችን አጥፍተናል።

And how many a generation have We destroyed before them who were better in possessions and [outward] appearance?

19:75
፦ በስሕተት ዉስጥ የኾነ ሰዉ አልረሕማን ለርሱ ማዘግየትን ያዘገየዋል፣ (1) የሚዛትባቸዉንም ወይም ቅጣቱን ወይም ሰዓቲቱን ባዩ ጊዜ፣ እርሱ ስፍራዉ መጥፎና ሰራዊቱ ደካማ የኾነዉ ሰዉ ማን እንደኾነ በእርግጥ ያዉቃሉ፤ በላቸዉ።
(1) አዝናንቶ ለመያዝ ጊዜ ይሰጠዋል ሁለቱንም ያፋፋለታል።


Say, "Whoever is in error - let the Most Merciful extend for him an extension [in wealth and time] until, when they see that which they were promised - either punishment [in this world] or the Hour [of resurrection] - they will come to know who is worst in position and weaker in soldiers."

19:76
እነዚያንም የቀኑትን ሰዎች አላህ ቅንነትን ይጨምርላቸዋል፤ መልካሞቹ ቀሪዎች (ሥራዎች) እጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸዉ፤ በመመለሻም የተሻሉ ናቸው ።

And Allah increases those who were guided, in guidance, and the enduring good deeds are better to your Lord for reward and better for recourse.

19:77
ያንንም በአንቀጾቻችን የካደዉን (በትንሣኤ ቀን) ገንዘብም ልጅም በእርግጥ እስሰጣለሁ ያለዉንም አየህን?

Then, have you seen he who disbelieved in Our verses and said, "I will surely be given wealth and children [in the next life]?"

19:78
ሩቁን ምስጢር ዐወቀን? ወይስ አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ ?

Has he looked into the unseen, or has he taken from the Most Merciful a promise?

19:79
ይከልከል (አይሰጠውም) የሚለዉን ሁሉ በእርግጥ እንጽፋለን ለርሱም ከቅጣት ጪማሬን እንጨምርለታለን።

No! We will record what he says and extend for him from the punishment extensively.

19:80
(አልለኝ) የሚለዉንም ሁሉ እንወርሰዋለን፤ ብቻዉንም ኾኖ ይመጣል።

And We will inherit him [in] what he mentions, and he will come to Us alone.

19:81
ከአላህም ሌላ አማልክትን ለነሱ መከበሪያ (አማላጅ) እንዲኾኑዋቸዉ ያዙ፤

And they have taken besides Allah [false] deities that they would be for them [a source of] honor.

19:82
ይከልከሉ መገዛታቸዉን በእርግጥ ይክዷቸዋል ፤ በነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል።

No! Those "gods" will deny their worship of them and will be against them opponents [on the Day of Judgement].

19:83
እኛ ሰይጣናትን በከሓዲዎች ላይ (በመጥፎ ሥራ) ማወባራትን የሚያወባሩዋቸዉ ሲኾኑ የላክን መኾናችንን አላየህምን ?

Do you not see that We have sent the devils upon the disbelievers, inciting them to [evil] with [constant] incitement?

19:84
በነሱም (መቀጣት) ላይ አትቻኮል፤ ለነሱ (ቀንን) መቁጠርን እንቆጥርላቸዋለንና።

So be not impatient over them. We only count out to them a [limited] number.

19:85
ምእምናንን የተከበሩ ጭፍሮች ኾነዉ፣ ወደ አልረሕማን የምንሰበሰብበትን ቀን (አስታዉስ)።

On the Day We will gather the righteous to the Most Merciful as a delegation

19:86
ከሐዲዎችንም የተጠሙ ኾነው፣ ወደ ገሀነም የምንነዳበትን (ቀን አስታውስ)።

And will drive the criminals to Hell in thirst

19:87
አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰዉ ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም።

None will have [power of] intercession except he who had taken from the Most Merciful a covenant.

19:88
፦ አልረሕማንም ልጂን ያዘ (ወለደ) አሉ፤

And they say, "The Most Merciful has taken [for Himself] a son."

19:89
ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፤

You have done an atrocious thing.

19:90
ከርሱ (ከንግግራቸዉ) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡

The heavens almost rupture therefrom and the earth splits open and the mountains collapse in devastation

19:91
ለአልረሕማን ልጅ አለዉ ስለ አሉ።

That they attribute to the Most Merciful a son.

19:92
ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም።

And it is not appropriate for the Most Merciful that He should take a son.

19:93
በሰማያትና በምድር ያለዉ ሁሉ (በትንሣኤ ቀን)፣ ለአልረሕማን ባሪያ ኾነዉ የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም።

There is no one in the heavens and earth but that he comes to the Most Merciful as a servant.

19:94
በእርግጥ (በዕዉቀቱ) ከቧቸዋል፤ መቁጠርንም ቆጥሯቸዋል።

He has enumerated them and counted them a [full] counting.

19:95
ሁሉም፤ በትንሣኤ ቀን ለየብቻ ኾነዉ ወደርሱ መጪዎች ናቸዉ።

And all of them are coming to Him on the Day of Resurrection alone.

19:96
እነዚያ ያመኑና በጎ ሥራዎችን የሠሩ አልረህማን ለነሱ ዉዴታን ይሰጣቸዋል።

Indeed, those who have believed and done righteous deeds - the Most Merciful will appoint for them affection.

19:97
በምላሥህም (ቁርአንን) ያገራነው፣ በርሱ ጥንቁቆቹን ልታበስርበት በርሱም ተከራካሪዎችን ሕዝቦች ልታስፈራራበት ነው።

So, [O Muhammad], We have only made Qur'an easy in the Arabic language that you may give good tidings thereby to the righteous and warn thereby a hostile people.

19:98
ከነሱም በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን አጥፍተናል፤ ከነሱ አንድን እንኳ ታያለህን? ወይስ ለነሱ ሹክሹክታን ትሰማለህን?

And how many have We destroyed before them of generations? Do you perceive of them anyone or hear from them a sound?

Copyright 2013, AmharicQuran.com