Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ኢስራእ (የሌሊት ጉዞ ምዕራፍ)፣

17:1
ያ ባሪያውን (1) ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፤ ከታምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፤ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው።

Exalted is He who took His Servant by night from al-Masjid al-Haram to al-Masjid al- Aqsa, whose surroundings We have blessed, to show him of Our signs. Indeed, He is the Hearing, the Seeing.

17:2
ሙሳንም መጽሐፉን ሰጠነው፤ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው፤ ከኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ፤ (አልናቸውም)።

And We gave Moses the Scripture and made it a guidance for the Children of Israel that you not take other than Me as Disposer of affairs,

17:3
እላንተ ከኑሕ ጋር (በመርከቢቱ) የጫናቸው ዘሮች ሆይ! (አላህን ተገዙ)፣ እርሱ በብዙ አመስጋኝ ባሪያ ነበረና።

O descendants of those We carried [in the ship] with Noah. Indeed, he was a grateful servant.

17:4
ወደ እስራኤል ልጆች በመጽሐፉ ውስጥ (እንዲህ በማለት) አወረድን፤ በምድር ላይ በእርግጥ ሁለት ጊዜ ታጠፋላችሁ፤ ትልቅንም ኩራት ትኮራላችሁ፤

And We conveyed to the Children of Israel in the Scripture that, "You will surely cause corruption on the earth twice, and you will surely reach [a degree of] great haughtiness

17:5
ከሁለቱ (ጊዜያቶች) የመጀመሪያይቱ ቀጠሮ በመጣም ጊዜ ለኛ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የሆኑትን በናንተ ላይ እንልካለን፤ በቤቶችም መካከል ይመላለሳሉ፤ (ይበረብሩታል፤ ይህ) ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር።

So when the [time of] promise came for the first of them, We sent against you servants of Ours - those of great military might, and they probed [even] into the homes, and it was a promise fulfilled.

17:6
ከዚያም (በኋላ) ለናንተ በነሱ ላይ ድልን መለስንላችሁ፣ በገንዘቦችና በወንዶች ልጆችም ጨመርንላችሁ፤ በወገንም የበዛችሁ አደረግናችሁ።

Then We gave back to you a return victory over them. And We reinforced you with wealth and sons and made you more numerous in manpower

17:7
መልካም ብትሠሩ (በነፍሶቻችሁ) ላይ ነው፤ (አልን)፤ የኋለኛይቱም (ጊዜ) ቀጠሮ በመጣ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደ እንደገቡት ሊገቡ ያሸነፉትንም ሁሉ (ፈጽመው) ማጥፋትን እንዲያጠፉ፣ (እንልካቸዋለን)።

[And said], "If you do good, you do good for yourselves; and if you do evil, [you do it] to yourselves." Then when the final promise came, [We sent your enemies] to sadden your faces and to enter the temple in Jerusalem, as they entered it the first time, and to destroy what they had taken over with [total] destruction.

17:8
(በመጽሐፉም አልን ብትጸጸቱ)፦ጌታችሁ ሊያዝንላችሁ ይከጀላል፤ (ወደ ማጥፋት) ብትመለሱም እንመለሳለን፤ ገሀነምንም ለከሐዲዎች ማሰሪያ አድርገናል።

[Then Allah said], "It is expected, [if you repent], that your Lord will have mercy upon you. But if you return [to sin], We will return [to punishment]. And We have made Hell, for the disbelievers, a prison-bed."

17:9
ይህ ቁርአን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል፤ እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መሆኑን ያበስራል።

Indeed, this Qur'an guides to that which is most suitable and gives good tidings to the believers who do righteous deeds that they will have a great reward.

17:10
እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት አሳማሚ ቅጣት አዘጋጅተንላቸዋል፤

And that those who do not believe in the Hereafter - We have prepared for them a painful punishment.

17:11
ሰው መልካምን ነገር እንደሚለምን ሁሉ፤ መጥፎ ነገርንም ይለምናል፤ ሰውም ቸኳላ ነው።

And man supplicates for evil as he supplicates for good, and man is ever hasty.

17:12
ሌሊትንና ቀንንም (ለችሎታችን) ምልክቶች አደረግን፤ የሌሊትን ምልክትም አበስን፤ የቀንን ምልክትም የምታሳይ አደረግን፤ (ይህም የሆነበት) ከጌታችሁ ትርፍን ልትፈልጉ የዓመታትንም ቁጥርና ሒሳብንም ታውቁ ዘንድ ነው፤ ነገሩንም ሁሉ ተለያይተን ዘረዘርነው።

And We have made the night and day two signs, and We erased the sign of the night and made the sign of the day visible that you may seek bounty from your Lord and may know the number of years and the account [of time]. And everything We have set out in detail.

17:13
ሰውንም ሁሉ በራሪውን (ሥራውን) በአንገቱ አስያዝነው፤ ለርሱም በትንሳኤ ቀን፣ የተዘረጋ ሆኖ የሚያገኘው የሆነን መጽሐፍ እናወጣለታለን።

And [for] every person We have imposed his fate upon his neck, and We will produce for him on the Day of Resurrection a record which he will encounter spread open.

17:14
መጽሐፍህን አንብብ፤ ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ በቃ (ይባላል)።

[It will be said], "Read your record. Sufficient is yourself against you this Day as accountant."

17:15
የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፤ የተሳሳተም ሰው፣ የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በርሷ ላይ ነው፤ ተሸካሚም (ነፍስ፣) የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም፤ መልክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም።

Whoever is guided is only guided for [the benefit of] his soul. And whoever errs only errs against it. And no bearer of burdens will bear the burden of another. And never would We punish until We sent a messenger.

17:16
ከተማንም ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ፣ ባለጸጋዎችዋን እናዛለን፤ በውስጧም ያምጣሉ፤ በርሷም ላይ ቃሉ (ቅጣቱ) ይፈጸምባታል፤ ማጥፋትንም እናጠፋታለን።

And when We intend to destroy a city, We command its affluent but they defiantly disobey therein; so the word comes into effect upon it, and We destroy it with [complete] destruction.

17:17
ከኑሕም በኋላ ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ያጠፋናቸው ብዙዎች ናቸው፤ የባሮቹንም ኃጢአቶች ውስጠ ዐዋቂ ተመልካች መሆን በጌታህ በቃ።

And how many have We destroyed from the generations after Noah. And sufficient is your Lord, concerning the sins of His servants, as Acquainted and Seeing.

17:18
ቸኳይቱን ዓለም (በሥራው) የሚፈልግ ሰው ለሱ በርሷ ውስጥ የሻነውን (ጸጋ) ለምንሻው ሰው እናስቸኩልለታለን፤ ከዚያም ለርሱ ገሀነምን (መኖሪያ) አድርገንለታል፤ ተወቃሽ ብራሪ ኾኖ ይገባታል።

Whoever should desire the immediate - We hasten for him from it what We will to whom We intend. Then We have made for him Hell, which he will [enter to] burn, censured and banished.

17:19
መጨረሻይቱንም ዓለም የፈለገ ሰው፣ እርሱ አማኝ ሆኖ ለርሷ (ተገቢ) ሥራዋን የሠራም ሰው እነዚህ ሥራቸው የተመሰገነ ይሆናል።

But whoever desires the Hereafter and exerts the effort due to it while he is a believer - it is those whose effort is ever appreciated [by Allah ].

17:20
ሁሉንም እነዚህንና እነዚያን ከጌታህ ስጦታ (በዚህ ዓለም) እንጨምርላቸዋለን፤ የጌታህም ስጦታ (በዚህ ዓለም) ክልክል አይደለም።

To each [category] We extend - to these and to those - from the gift of your Lord. And never has the gift of your Lord been restricted.

17:21
ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ እንዴት እንዳበለጥን ተመልከት፤ የመጨረሻይቱም አገር በማዕረጎች በጣም የከበረችና በመብለጥም የተለቀች ናት።

Look how We have favored [in provision] some of them over others. But the Hereafter is greater in degrees [of difference] and greater in distinction.

17:22
ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ፤ የተወቀስክ ረዳት የሌለህ ትሆናለህና፤

Do not make [as equal] with Allah another deity and [thereby] become censured and forsaken.

17:23
ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፦ እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤ በአንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፤ አትገላምጣቸውም፤ ለነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው።

And your Lord has decreed that you not worship except Him, and to parents, good treatment. Whether one or both of them reach old age [while] with you, say not to them [so much as], "uff," and do not repel them but speak to them a noble word.

17:24
ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፤ ጌታዬ ሆይ በሕጻንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ፣ እዘንላቸውም በል።

And lower to them the wing of humility out of mercy and say, "My Lord, have mercy upon them as they brought me up [when I was] small."

17:25
ጌታችሁ፣ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው። ታዛዦችም ብትሆኑ፣ (በመሳሳትም ብታጠፉ) እርሱ ለተመላሾች መሐሪ ነው።

Your Lord is most knowing of what is within yourselves. If you should be righteous [in intention] - then indeed He is ever, to the often returning [to Him], Forgiving.

17:26
ለዝምድና ባለቤትም መብቱን ስጥ፤ ለምስኪንና ለመንገደኛም (ስጥ)፤ ማባከንንም አታባክን።

And give the relative his right, and [also] the poor and the traveler, and do not spend wastefully.

17:27
አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና፤ ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሐዲ ነው።

Indeed, the wasteful are brothers of the devils, and ever has Satan been to his Lord ungrateful.

17:28
ከጌታህም የምትከጅላትን ጸጋ ለማጣት፣ ከነርሱ ብትዞር፣ ለነሱ ልዝብን ቃል ተናገራቸው።

And if you [must] turn away from the needy awaiting mercy from your Lord which you expect, then speak to them a gentle word.

17:29
እጅህንም ወደ አንገትህ የታሠረች አታድርግ፣ መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት፤ የተወቀስክ፣ የተቆጨህ፣ ትሆናለህና።

And do not make your hand [as] chained to your neck or extend it completely and [thereby] become blamed and insolvent.

17:30
ጌታህ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ያሰፋል፤ ያጠባልም፤ እርሱ በባሮቹ ሁኔታ ውስጠ ዐዋቂ ተመልካች ነውና።

Indeed, your Lord extends provision for whom He wills and restricts [it]. Indeed He is ever, concerning His servants, Acquainted and Seeing.

17:31
ልጆቻችሁንም ድኽነትን በመፍራት አትግደሉ፤ እኛ እንመግባቸዋለን፣ (እናንተንም እንመግባለን)፤ እነሱን መግደል ኃጢአት ነውና።

And do not kill your children for fear of poverty. We provide for them and for you. Indeed, their killing is ever a great sin.

17:32
ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!

And do not approach unlawful sexual intercourse. Indeed, it is ever an immorality and is evil as a way.

17:33
ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፤ የተበደለም ሆኖ የተገደለ ሰው፣ ለዘመዱ (በገዳዩ ላይ) በእርግጥ ስልጣንን አድርገናል፤ በመግደልም ወሰንን አይለፍ፤ እርሱ የተረዳ ነውና።

And do not kill the soul which Allah has forbidden, except by right. And whoever is killed unjustly - We have given his heir authority, but let him not exceed limits in [the matter of] taking life. Indeed, he has been supported [by the law].

17:34
የየቲምንም ገንዘብ፣ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በሆነች ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ፤ በኪዳናችሁም ምሉ፤ ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና።

And do not approach the property of an orphan, except in the way that is best, until he reaches maturity. And fulfill [every] commitment. Indeed, the commitment is ever [that about which one will be] questioned.

17:35
በሰፈራችሁም ጊዜ ስፍርን ሙሉ፤ በትክክለኛው ሚዛንም መዝኑ፤ ይህ መልካም ነገር ነው፤ መጨረሻውም ያማረ ነው።

And give full measure when you measure, and weigh with an even balance. That is the best [way] and best in result.

17:36
ለአንተም በርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፤ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም፣ እነዚህ ሁሉ (ባለቤታቸው) ከነሱ ተጠያቂ ነውና።

And do not pursue that of which you have no knowledge. Indeed, the hearing, the sight and the heart - about all those [one] will be questioned.

17:37
በምድርም ላይ የተንበጣረርክ ሆነህ አትኺድ፤ አንተ ፈጽሞ ምድርን አትሰረጉድምና፣ በርዝመትም ፈጽሞ ጋራዎችን አትደርስምና።

And do not walk upon the earth exultantly. Indeed, you will never tear the earth [apart], and you will never reach the mountains in height.

17:38
ይህ ሁሉ (1) መጥፎው (2) እጌታህ ዘንድ የተጠላ ነው።
1 ከሃያ አምስቱ ጠባዮች ውስጥ 2 አሥራ ሁለቱ ክልክሎች


All that - its evil is ever, in the sight of your Lord, detested.

17:39
ይህ ጌታህ ከጥበቡ ወደ አንተ ካወረደው ነገር ነው፤ ከአላህም ጋር ሌላ አምላክን አታድርግ፤ የተወቀስክ የተባረርክ ሆነህ በገሀነም ውስጥ ትጣላለህና።

That is from what your Lord has revealed to you, [O Muhammad], of wisdom. And, [O mankind], do not make [as equal] with Allah another deity, lest you be thrown into Hell, blamed and banished.

17:40
ጌታችሁ በወንዶች ልጆች መረጣችሁና ከመላእክት ሴቶችን (ልጆች) ያዝን? እናንተ ከባድን ቃል በእርግጥ ትናገራላችሁ።

Then, has your Lord chosen you for [having] sons and taken from among the angels daughters? Indeed, you say a grave saying.

17:41
ይገሠጹም ዘንድ በዚህ ቁርአን ውስጥ ደጋግመን በእርግጥ ገለጽን መበርገግንም እንጂ ሌላ አይጨምርላቸውም።

And We have certainly diversified [the contents] in this Qur'an that mankind may be reminded, but it does not increase the disbelievers except in aversion.

17:42
(ሙሐመድ ሆይ) በአላቸው፦ እንደምትሉት ከርሱ ጋር አማልክት በነበሩ ኖሮ ያን ጊዜ ወደ ዐርሹ (1) ባለቤት መንገድን በፈለጉ ነበር።
ወደ ዙፋኑ


Say, [O Muhammad], "If there had been with Him [other] gods, as they say, then they [each] would have sought to the Owner of the Throne a way."

17:43
ጥራት ይግባው ከሚሉትም ነገር ሁሉ ከፍ ያለን ልቅና ላቀ።

Exalted is He and high above what they say by great sublimity.

17:44
ሰባቱ ሰማያትና ምድርም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ለርሱ ያጠራሉ፣ ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው (1) እንጂ አንድም የለም፤ ግን ማጥራታቸውን አታውቁትም፤ እርሱ ታጋሽ መሐሪ ነው።
የሚያወድሰው


The seven heavens and the earth and whatever is in them exalt Him. And there is not a thing except that it exalts [ Allah ] by His praise, but you do not understand their [way of] exalting. Indeed, He is ever Forbearing and Forgiving.

17:45
ቁርአንንም ባነበብክ ጊዜ ባንተና በነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም በማያምኑት ሰዎች መካከል የሚሸሽግን ግርዶሽ አድርገናል።

And when you recite the Qur'an, We put between you and those who do not believe in the Hereafter a concealed partition.

17:46
እንዳያውቁትም በልቦቻቸውም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን፤ ጌታህንም ብቻውን ሆኖ በቁርአን ባወሳኸው ጊዜ የሚሸሹሆነው በጀርቦቻቸው ላይ ይዞራሉ።

And We have placed over their hearts coverings, lest they understand it, and in their ears deafness. And when you mention your Lord alone in the Qur'an, they turn back in aversion.

17:47
እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ ጊዜ እነሱም የሚንሾካሾኩ ጊዜ በዳዮች (እርስ በርሳቸው) የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም በሚሉ ጊዜ በርሱ የሚያዳምጡበትን ምክንያት ዐዋቂ ነን።

We are most knowing of how they listen to it when they listen to you and [of] when they are in private conversation, when the wrongdoers say, "You follow not but a man affected by magic."

17:48
ምሳሌዎችን ለአንተ እንዴት እንዳደረጉልህና (1) እንደተሳሳቱ ተመልከት፤ (ወደ እውነቱ ለመድረስ) መንገድንም አይችሉም።
1.የተደገመበት ነው፤ ገጣሚ ነው በማለት


Look how they strike for you comparisons; but they have strayed, so they cannot [find] a way.

17:49
አሉም፦ እንዴት አጥንቶችና ብስብሶች በሆን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት ሆነን በእርግጥ ተንቀሳቃሾች ነን?

And they say, "When we are bones and crumbled particles, will we [truly] be resurrected as a new creation?"

17:50
በላቸው፦ደንጊያዎችን ወይም ብረትን ሁኑ፤

Say, "Be you stones or iron

17:51
ወይም በልቦቻችሁ ውስጥ የሚተልቅን ፍጥረት (ሁኑ መቀስቀሳችሁ አይቀርም) የሚመልሰንም ማነው? ይላሉ፤ ያ በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ ነው በላቸው፤ ወደ አንተም ራሶቻቸውን ይነቀንቃሉ እርሱም መቼ ነው ይላሉ፤ (እርሱ) ቅርብ ሊሆነን ይቻላል በላቸው።

Or [any] creation of that which is great within your breasts." And they will say, "Who will restore us?" Say, "He who brought you forth the first time." Then they will nod their heads toward you and say, "When is that?" Say, "Perhaps it will be soon -

17:52
(እርሱም) የሚጠራችሁና (አላህን) አመስጋኞቹ ሆናችሁ ጥሪውን የምትቀበሉበት ጥቂትንም (ቀኖች) እንጂ ያልቆያችሁ መሆናችሁን የምትጠራጠሩበት ቀን ነው (በላቸው)።

On the Day He will call you and you will respond with praise of Him and think that you had not remained [in the world] except for a little."

17:53
ለባሮቼም በላቸው፦ ያችን እርሷ መልካም የሆነችውን (ቃል) ይናገሩ፤ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፤ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና።

And tell My servants to say that which is best. Indeed, Satan induces [dissension] among them. Indeed Satan is ever, to mankind, a clear enemy.

17:54
ጌታችሁ በናንተ (ሁኔታ) ዐዋቂ ነው፤ ቢሻ ያዝንላችኋል፤ ወይም ቢሻ ይቀጣችኋል፤ በነሱም ላይ ኃላፊ ሆነህ አላክንህም።(አታስገድዳቸውም)።

Your Lord is most knowing of you. If He wills, He will have mercy upon you; or if He wills, He will punish you. And We have not sent you, [O Muhammad], over them as a manager.

17:55
ጌታህም በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፤ ከፊሉንም ነቢያት በከፊሉ ላይ በእርግጥ አብልጠናል፤ ዳውድንም ዘቡርን ሰጥተነዋል።

And your Lord is most knowing of whoever is in the heavens and the earth. And We have made some of the prophets exceed others [in various ways], and to David We gave the book [of Psalms].

17:56
እነዚያን ከርሱ ሌላ (አማልክት) የምትሏቸውን ጥሩ፤ ከናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን (ወደ ሌላ) ማዞርንም አይችሉም በላቸው።

Say, "Invoke those you have claimed [as gods] besides Him, for they do not possess the [ability for] removal of adversity from you or [for its] transfer [to someone else]."

17:57
እነዚያ እነርሱ የሚግገዟቸው ማንኛቸውንም (ወደ አላህ) በጣም ቀራቢያቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን (ሥራ) ይፈልጋሉ፤ እዝነቱንም ይከጂላሉ፤ ቅጣቱንም ይፈራሉ የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና።

Those whom they invoke seek means of access to their Lord, [striving as to] which of them would be nearest, and they hope for His mercy and fear His punishment. Indeed, the punishment of your Lord is ever feared.

17:58
አንዲትም ከተማ የለችም እኛ ከትንሣኤ ቀን በፊት አጥፊዎችዋ ወይንም ብርቱን ቅጣት ቀጭዎችዋ ብንሆን እንጂ ይህ በመጽሐፉ የተጻፈ ነው።

And there is no city but that We will destroy it before the Day of Resurrection or punish it with a severe punishment. That has ever been in the Register inscribed.

17:59
ታምራቶችንም ከመላክ የቀድሞዎቹ ሰዎች በርሷ ማስተባበልና (መጥፋት) እንጂ ሌላ አልከለከልንም፤ ለሠሙድም ግመልን ግልጽ ታምር ሆና ሰጠናቸው፤ በርሷም በደሉ፤ታምራቶችንንም ለማስፈራራት እንጂ አንልክም።

And nothing has prevented Us from sending signs except that the former peoples denied them. And We gave Thamud the she-camel as a visible sign, but they wronged her. And We send not the signs except as a warning.

17:60
ላንተም ጌታህ (ዕውቀቱ) በሰዎቹ ከበበ ባልንህ ጊዜ (አስታውስ)። ያችንም (በሌሊቱ ጉዞ በ ዓይንህ) ያሳየንህን ትር ዕይት ለሰዎች ፈተና እንጂ አላደረግንም) እናስፈራራቸዋለንም፤ ታላቅንም ጥመት እንጂ አይጨምርላቸውም።

And [remember, O Muhammad], when We told you, "Indeed, your Lord has encompassed the people." And We did not make the sight which We showed you except as a trial for the people, as was the accursed tree [mentioned] in the Qur'an. And We threaten them, but it increases them not except in great transgression.

17:61
ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ «ከጭቃ ለፈጠርከው ሰው እሰግዳለሁን» አለ፡፡

And [mention] when We said to the angles, "Prostrate to Adam," and they prostrated, except for Iblees. He said, "Should I prostrate to one You created from clay?"

17:62
ንገረኝ ይህ ያ በኔ ላይ ያበለጥከው ነውን? እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ብታቆየኝ ዘሮቹን ጥቂቶች ሲቀሩ ወደ ስሕተት በእርግጥ እስባቸዋለሁ አለ።

[Iblees] said, "Do You see this one whom You have honored above me? If You delay me until the Day of Resurrection, I will surely destroy his descendants, except for a few."

17:63
(አላህም) አለው፦ ኺድ ከነሱም የተከተለህ ገሀነም የተሟላች ስትሆን ፍዳችሁ ናት።

[ Allah ] said, "Go, for whoever of them follows you, indeed Hell will be the recompense of you - an ample recompense.

17:64
ከነሱ የቻልከውን በድምጽህ አታል፤ በነሱም ላይ በፈረሰኞችህ በ እግረኞችህም ላይ ሆነህ ለልብ፤ በገንዘቦቻቸውም በልጆቻቸውም ተጋራቸው፤ ተስፋ ቃልም ግባላቸው፤ ሰይጣንም ማታለልን እንጂ ተስፋ ቃልን አይገባላቸውም።

And incite [to senselessness] whoever you can among them with your voice and assault them with your horses and foot soldiers and become a partner in their wealth and their children and promise them." But Satan does not promise them except delusion.

17:65
ባሮቼ በነሱ ላይ ፈጽሞ ስልጣን የለህን፤ መጠጊያም በጌታህ በቃ።

Indeed, over My [believing] servants there is for you no authority. And sufficient is your Lord as Disposer of affairs.

17:66
ጌታችሁ ያ ከችሮታው ትፈልጉ ዘንድ መርከቦችን በባህር ለናንተ የሚነዳላችሁ ነው፤ እነሆ እርሱ ለናንተ አዛኝ ነውና።

It is your Lord who drives the ship for you through the sea that you may seek of His bounty. Indeed, He is ever, to you, Merciful.

17:67
በባሕሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛችሁ ጊዜ የምትጠሩዋቸው (አማልክት) ሁሉ ከርሱ (ከአላህ) በቀር ይጠፋሉ፣ ወደ የብስም በማድረስ ባዳናችሁ ጊዜ (እምነትን) ትተዋላችሁ፤ ሰውም በጣም ከሐዲ ነው።

And when adversity touches you at sea, lost are [all] those you invoke except for Him. But when He delivers you to the land, you turn away [from Him]. And ever is man ungrateful.

17:68
የየብሱን በኩል (ምድርን) በናንተ መገልበጡን ወይም ጠጠርን የያዘ ነፋስን በናንተ ላይ መላኩን ከዚያም ለናንተ ጠባቂ አለማግኘታቸውን አትፈሩምን?

Then do you feel secure that [instead] He will not cause a part of the land to swallow you or send against you a storm of stones? Then you would not find for yourselves an advocate.

17:69
ወይስ ሌላ ጊዜ ወደ እርሱ (ወደ ባሕር) የሚመልሳችሁ ወዲያውም በናንተ ላት ብርቱን ነፋስ የሚልክ በክሕደታችሁም ምክንያት የሚያሰጥማችሁ መሆኑን ከዚያም በኛ ላይ በርሱ ተከታይን (ረዳትን) ለናንተ የማታገኙ መሆናችሁን አትፈሩምን?

Or do you feel secure that He will not send you back into the sea another time and send upon you a hurricane of wind and drown you for what you denied? Then you would not find for yourselves against Us an avenger.

17:70
የአደምንም ልጆች በእርግጥ (ከሌላው ፍጡር) አከበርናቸው በየብስን በባሕርም አስሳፈርናቸው፤ ከመልካሞችም (ሲሳዮች) ሰጠናቸው፤ ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው።

And We have certainly honored the children of Adam and carried them on the land and sea and provided for them of the good things and preferred them over much of what We have created, with [definite] preference.

17:71
ሰዎችንም ሁሉ በመሪያቸው የምንጠራበትን ቀን (አስታውስ)፤ መጽሐፉንም በቀኙ የተሰጠ ሰው እነዚያ መጽሐቸውን ያነባሉ፤ በተምር ፍሬ ስንጥቅ ላይ ያለውን ክር ያክል አይበደሉም።

[Mention, O Muhammad], the Day We will call forth every people with their record [of deeds]. Then whoever is given his record in his right hand - those will read their records, and injustice will not be done to them, [even] as much as a thread [inside the date seed].

17:72
በዚህችም ዓለም (ልበ) ዕውር የሆነ ሰው እርሱ በመጨረሻይቱም (ዓለም) ይበልጥ ዕውር ነው፤ መንገድንም በጣም የተሳሳተ ነው።

And whoever is blind in this [life] will be blind in the Hereafter and more astray in way.

17:73
እነሆ ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፤ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር።

And indeed, they were about to tempt you away from that which We revealed to you in order to [make] you invent about Us something else; and then they would have taken you as a friend.

17:74
ባላረጋንህም ኖሮ ወደነሱ ጥቂትን (ዝንባሌ) ልትዘነብል በእርግጥ በተቃረብክ ነበር።

And if We had not strengthened you, you would have almost inclined to them a little.

17:75
ያን ጊዜ የሕይወትን ድርብ (ቅጣት) የሞትንም ድርብ (ቅጣት) ባቀመስንህ ነበር፤ ከዚያም ላንተ በኛ ላይ ረዳትን አታገኝም ነበር።

Then [if you had], We would have made you taste double [punishment in] life and double [after] death. Then you would not find for yourself against Us a helper.

17:76
ከምድሪቱም (ከ ዓረብ ምድር) ከርሷ ያወጡህ ዘንድ ሊያሸብሩህ፣ በእርግጥ ተቃረቡ፤ ይአን ጊዜም ከአንተ በኋላ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር።

And indeed, they were about to drive you from the land to evict you therefrom. And then [when they do], they will not remain [there] after you, except for a little.

17:77
ከመልክተኞቻችን ካንተ በፊት በእርግጥ እንደላክናቸው ሰዎች ልማድ ብጤ (ይጠፉ ነበር)፤ ለልማዳችንም መለወጥን አታገኝም።

[That is Our] established way for those We had sent before you of Our messengers; and you will not find in Our way any alteration.

17:78
ሶላትን ከፀሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፤ የጎህ ሶላት (መላ እክት) የሚጣዱት ነውና።

Establish prayer at the decline of the sun [from its meridian] until the darkness of the night and [also] the Qur'an of dawn. Indeed, the recitation of dawn is ever witnessed.

17:79
ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት፣ በርሱ (በቁርአን) ስገድ፤ ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል።

And from [part of] the night, pray with it as additional [worship] for you; it is expected that your Lord will resurrect you to a praised station.

17:80
በልም፦ ጌታዬ ሆይ! የተወደደን ማግባት አግባኝ የተወደደንም ማውጣት አውጣኝ፤ ለኔም ከአንተ ዘንድ የተረዳን ስልጣን አድርግልኝ።

And say, "My Lord, cause me to enter a sound entrance and to exit a sound exit and grant me from Yourself a supporting authority."

17:81
በልም፦እውነት መጣ፣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፣

And say, "Truth has come, and falsehood has departed. Indeed is falsehood, [by nature], ever bound to depart."

17:82
ከቁርአንም ለምእመናን መድኀኒትና እዝነት የሆነን እናወርዳለን፤በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸውም።

And We send down of the Qur'an that which is healing and mercy for the believers, but it does not increase the wrongdoers except in loss.

17:83
በሰውም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ (ከምስጋና) ይዞራል፤ጎኑንም (ከውነት) ያርቃል፤ ችግርም በነካው ጊዜ ተስፋ ቆራጭ ይሆናል።

And when We bestow favor upon the disbeliever, he turns away and distances himself; and when evil touches him, he is ever despairing.

17:84
ሁሉም በሚመስለው መንገዱ ላይ ይሠራል ጌታችሁም እርሱ መንገዱ ቀጥተኛ የሆነውን ሰው ዐዋቂ ነው በላቸው።

Say, "Each works according to his manner, but your Lord is most knowing of who is best guided in way."

17:85
ከሩሕም(1) ይጠይቁሃል፤ ሩሕ ከጌታዬ ነገር (2) ነው ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም፤ በላቸው።
1. አካል ሕያው የሚኾንባት ነፍስ 2. በዕውቀቱ የተለየበት ነገር ነው።


And they ask you, [O Muhammad], about the soul. Say, "The soul is of the affair of my Lord. And mankind have not been given of knowledge except a little."

17:86
ብንሻም ያንን ወዳንተ ያወረድነውን በእርግጥ እናስወግዳለን፤ ከዚያም ላንተ በኛ ላይ በርሱ (ለማስመለስ) ተያዢን አታገኝም።

And if We willed, We could surely do away with that which We revealed to you. Then you would not find for yourself concerning it an advocate against Us.

17:87
ግን ከጌታህ በሆነው እዝነት (ጠበቅነው)፤ ችሮታው ባንተ ላይ ታላቅ ነውና።

Except [We have left it with you] as a mercy from your Lord. Indeed, His favor upon you has ever been great.

17:88
፦ ሰዎችም ጋኔኖችም የዚህን ቁርአን ብጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆንም እንኳ፣ ብጤውን አያመጡም በላቸው።

Say, "If mankind and the jinn gathered in order to produce the like of this Qur'an, they could not produce the like of it, even if they were to each other assistants."

17:89
በዚህም ቁርአን ውስጥ ከምሳሌው ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ መላለስን፤ አብዛኛዎቹም ሰዎች ክሕደትን እንጂ ሌላን እምቢ አሉ።

And We have certainly diversified for the people in this Qur'an from every [kind] of example, but most of the people refused [anything] except disbelief.

17:90
አሉም፦ለኛ ከምድር ምንጭን እስከምታፈነዳልን ለአንተ አናምንም፤

And they say, "We will not believe you until you break open for us from the ground a spring.

17:91
ወይም ከዘንባባዎችና ከወይን የሆነች አትክልት ለአንተ እስከምትኖርህና በመካከልዋም ጅረቶችን በብዛት እስከምታንቧቧ፤

Or [until] you have a garden of palm tress and grapes and make rivers gush forth within them in force [and abundance]

17:92
ወይም እንደምትለው ከሰማይ ቁራጮችን በኛ ላይ እስከምታወድቅ፤ ወይም አላህንና መላ እክትን በግልጽ እስከምታመጣ፤

Or you make the heaven fall upon us in fragments as you have claimed or you bring Allah and the angels before [us]

17:93
ወይም ከወርቅ የሆነ ቤት ላንተ እስከሚኖርህ፤ ወይም በሰማይ እስከምትወጣ፤ ለመውጣትህም በኛ ላይ የምናነበው የኮነን መጽሐፍ እስከምታወርድልን ድረስ ፈጽሞ አናምንልህም፤ (አሉ)። ጌታዬ ጥራት ይገባው፤ እኔ ሰው መልክተኛ እንጂ ሌላ አይደለሁም፤ በላቸው።

Or you have a house of gold or you ascend into the sky. And [even then], we will not believe in your ascension until you bring down to us a book we may read." Say, "Exalted is my Lord! Was I ever but a human messenger?"

17:94
ሰዎችንም መሪ (ቁርአን) በመጣላቸው ጊዜ ከማመን አላህ ሰውን መልክተኛ አድርጎ ላከን? ማለታቸው እንጂ ሌላ አልከለከላቸውም።

And what prevented the people from believing when guidance came to them except that they said, "Has Allah sent a human messenger?"

17:95
፦ በምድር ላይ ረግተው የሚኼዱ መላእክት በነበሩ ኖሮ በነሱ ላይ (ከጎሳቸው) የመል አክን መልክተኛ ባወረድን ነበር በላቸው።

Say, "If there were upon the earth angels walking securely, We would have sent down to them from the heaven an angel [as a] messenger."

17:96
፦ በኔና በናንተ መስካሪ በአላህ በቃ፤ እርሱ በባሮቹ (ነገር) ውስጥ ዐዋቂ ተመልካች ነውና፤ በላቸው።

Say, "Sufficient is Allah as Witness between me and you. Indeed he is ever, concerning His servants, Acquainted and Seeing."

17:97
አላህም ያቀናው ሰው ቅኑ እርሱ ብቻ ነው፤ ያጠመማቸውም ሰዎች ከርሱ ሌላ ለነርሱ ፈጽሞ ረዳት አታገኝላቸውም፤ በትንሣኤ ቀንም ዕውሮች፣ ዲዳዎች፣ ደንቆሮዎችም ሆነው በፊቶቻቸው ላይ (እየተጎተቱ) እንሰበስባቸዋለን፤ መኖሪያቸው ገሀነም ናት፤ (ነዲድዋ) በደከመች ቁጥር፣ መንቀልቀልን እንጨምርባቸዋለን።

And whoever Allah guides - he is the [rightly] guided; and whoever He sends astray - you will never find for them protectors besides Him, and We will gather them on the Day of Resurrection [fallen] on their faces - blind, dumb and deaf. Their refuge is Hell; every time it subsides We increase them in blazing fire.

17:98
ይህ(ቅጣት)፤ እነርሱ በአንቀጾቻችን ስለካዱና አጥንቶችና ብስብሶች በሆን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት ሆነን ተንቀሳቃሾች ነን? ስላሉም ፍዳቸው ነው።

That is their recompense because they disbelieved in Our verses and said, "When we are bones and crumbled particles, will we [truly] be resurrected [in] a new creation?"

17:99
ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ አላህ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ መሆኑን በርሱ ጥርጣሬ የሌለበትንም ጊዜ (ለሞትም ለትንሣኤም) ለርሱ የተወሰነ መሆኑን አላወቁምን? በደለኞችም ከክሕደት በቀር እምቢ አሉ።

Do they not see that Allah , who created the heavens and earth, is [the one] Able to create the likes of them? And He has appointed for them a term, about which there is no doubt. But the wrongdoers refuse [anything] except disbelief.

17:100
እናንተ የጌታዬን የችሮታ መካዚኖች ብትይዙ ኖሮ ያን ጊዜ በማውጣታችሁ ማለቋን በመፍራት በጨበጣችሁ ነበር፤ ሰውም በጣም ቆጣቢ ነው።

Say [to them], "If you possessed the depositories of the mercy of my Lord, then you would withhold out of fear of spending." And ever has man been stingy.

17:101
ለሙሳም ግልጽ የሆኑን ዘጠኝ ታምራቶች በእርግጥ ሰጠነው፤ በመጣቸውም ጊዜ የእስራኤልን ልጆች (ከፈርዖን እንዲለቀቁ) ጠይቅ (አልነው)፤ ፈርዖንም፦ ሙሳ ሆይ! እኔ የተደገመብህ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ አለው።

And We had certainly given Moses nine evident signs, so ask the Children of Israel [about] when he came to them and Pharaoh said to him, "Indeed I think, O Moses, that you are affected by magic."

17:102
(ሙሳም)፦ እነዚህን ታምራቶች) መገሰጫዎች ሲሆኑ የሰማያትና የምድር ጌታ እንጂ ሌላ እንዳላወረዳቸው በእርግጥ አውቀሀል፤ እኔም ፈርዖን ሆይ! የምትጠፋ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ አለው።

[Moses] said, "You have already known that none has sent down these [signs] except the Lord of the heavens and the earth as evidence, and indeed I think, O Pharaoh, that you are destroyed."

17:103
ከምድርም ሊቀሰቅሳቸው አሰበ፤ እርሱንና ከርሱጋ የነበሩትንም ሰዎች ሁሉንም አሰጠምናቸው።

So he intended to drive them from the land, but We drowned him and those with him all together.

17:104
ከርሱም በኋላ ለእስራኤል ልጆች፦ ምድሪቱን ተቀመጡባት የኋለኛይቱም (ሰዓት) ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትሆኑ እናመጣችኋላን አልናቸው።

And We said after Pharaoh to the Children of Israel, "Dwell in the land, and when there comes the promise of the Hereafter, We will bring you forth in [one] gathering."

17:105
(ቁርአንን) በውነትም አወረድነው፤ በውነትም ወረደ፤ አንተንም አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን እንጂ አልላክህንም።

And with the truth We have sent the Qur'an down, and with the truth it has descended. And We have not sent you, [O Muhammad], except as a bringer of good tidings and a warner.

17:106
ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው።

And [it is] a Qur'an which We have separated [by intervals] that you might recite it to the people over a prolonged period. And We have sent it down progressively.

17:107
፦ በርሱ እመኑ፣ ወይም አትመኑ በላቸው፤(1) እነዚያ ከርሱ በፊት ዕውቀትን የተሰጡት በነሱ ላይ በተነበበ ጊዜ ሰጋጆች ሆነው በሸንጎበቶቻቸው (2) ይወድቃሉ፤
1. ዛቻ ነው፤ ውጤቱን ታገኙታላችህ ማለት ነው። 2. *በአገጮቻቸው


Say, "Believe in it or do not believe. Indeed, those who were given knowledge before it - when it is recited to them, they fall upon their faces in prostration,

17:108
ይላሉም፦ጌታችን ጥራት ይገባው! እነሆ የጌታችን ተስፋ ተፈጻሚ ነው።

And they say, "Exalted is our Lord! Indeed, the promise of our Lord has been fulfilled."

17:109
እያለቀሱም በሸንጎበቶቻቸው ላይ ይወድቃሉ፤(አላህን) መፍራትንም ይጨመርላቸዋል።

And they fall upon their faces weeping, and the Qur'an increases them in humble submission.

17:110
፦አላህን ጥሩ፤ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤(ከሁለቱ) ማንኛውንም ብትጠሩ፣(መልካም ነው)፤ ለርሱ መልካም ስሞች አሉትና በላቸው፤ በስግደትህም (ስታነብ) አትጩህ፤ በርሷም ድምጽህን ዝቅ አታድርግ፤ በዚህም መካከል መንገድን ፈልግ።

Say, "Call upon Allah or call upon the Most Merciful. Whichever [name] you call - to Him belong the best names." And do not recite [too] loudly in your prayer or [too] quietly but seek between that an [intermediate] way.

17:111
፦ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዝነው ለርሱም በንግሥናው ተጋሪ ለሌለው ለርሱም ከውርደት ረዳት ለሌለው ይግባው፣ በልም ማክበርን አክብረው።

And say, "Praise to Allah , who has not taken a son and has had no partner in [His] dominion and has no [need of a] protector out of weakness; and glorify Him with [great] glorification."

Copyright 2013, AmharicQuran.com