Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል-ነሕል፥ (የንብ ምዕራፍ)

16:1
የአላህ ትእዛዝ መጣ፤ ስለዚህ አታስቸኩሉት፤ ከማይገባው ሁሉ ጠራ፤ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ፤

The command of Allah is coming, so be not impatient for it. Exalted is He and high above what they associate with Him.

16:2
ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል፤ (ከሐዲዎችን በቅጣት) አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም ፍሩኝም ማለትን (አሳታውቁ በማለት ያወርዳል)።

He sends down the angels, with the inspiration of His command, upon whom He wills of His servants, [telling them], "Warn that there is no deity except Me; so fear Me."

16:3
ሰማያትንና ምድርን በውነት ፈጠረ፤ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።

He created the heavens and earth in truth. High is He above what they associate with Him.

16:4
ሰውን ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይሆናል።

He created man from a sperm-drop; then at once, he is a clear adversary.

16:5
ግመልን ከብትን ፍየልንም በርሷ (ብርድ መከላከያ) ሙቀት ጥቅሞችም ያሉባት ስትሆን ለናንተ ፈጠረላችሁ ከሷም ትበላላችሁ።

And the grazing livestock He has created for you; in them is warmth and [numerous] benefits, and from them you eat.

16:6
ለናንተም በርሷ ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜ በምታሰማሩዋትም ጊዜ ውበት አላች ሁ።

And for you in them is [the enjoyment of] beauty when you bring them in [for the evening] and when you send them out [to pasture].

16:7
ጉዋዞቻችሁም በነፍሶች ችግር እንጂ ወደማትደርሱበት አገር ትሸከማለች፤ ጌታችሁ በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነውና።

And they carry your loads to a land you could not have reached except with difficulty to yourselves. Indeed, your Lord is Kind and Merciful.

16:8
ፈረሶችንም፣ በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸውና ልታጌጡባቸው (ፈጠረላችሁ)፤ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል።

And [He created] the horses, mules and donkeys for you to ride and [as] adornment. And He creates that which you do not know.

16:9
በአላህም ላይ (በችሮታው) ቀጥተኛውን መንገድ መግለጽ አለበት፤ ከርሷም (ከመንገድ) ጠማማ አልለ፤ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም በእርግጥ ባቀናችሁ ነበር።

And upon Allah is the direction of the [right] way, and among the various paths are those deviating. And if He willed, He could have guided you all.

16:10
እርሱ ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው፤ ከርሱ ለናንተ መጠጥ አላችሁ፤ ከርሱም (እንሰሳዎችን) በርሱ የምታሰማሩበት ዛፍ (ይበቅልበታል)።

It is He who sends down rain from the sky; from it is drink and from it is foliage in which you pasture [animals].

16:11
በርሱ ለእናንተ አዝመራን፣ (የዘይት) ወይራንም ዘምባባዎችንም (ተምርን) ወይኖችንም፣ ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አልለ።

He causes to grow for you thereby the crops, olives, palm trees, grapevines, and from all the fruits. Indeed in that is a sign for a people who give thought.

16:12
ለናንተም ሌሊትንና ቀንን ፀሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ፤ ክዋክብትም በፈቃዱ የተገሩ ናቸው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ።

And He has subjected for you the night and day and the sun and moon, and the stars are subjected by His command. Indeed in that are signs for a people who reason.

16:13
በምድርም ላይ መልኮቹ የተለያዩ ኾኖ ለናንተ የፈጠረላችሁን ሁሉ (ገራላችሁ)፤ በዚህ ውስጥ ለሚገሠጡ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አለ።

And [He has subjected] whatever He multiplied for you on the earth of varying colors. Indeed in that is a sign for a people who remember.

16:14
እርሱም ያ ባሕርን ከርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ የገራ ነው፤ መርከቦችንም በውስጡ (ውሃውን) ቀዳጆች ሆነው (ሲንሻለሉ) ታያለህ፤ ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም (ገራላችሁ)።

And it is He who subjected the sea for you to eat from it tender meat and to extract from it ornaments which you wear. And you see the ships plowing through it, and [He subjected it] that you may seek of His bounty; and perhaps you will be grateful.

16:15
በምድርም ውስጥ በናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት፤ ጂረቶችንም፣ መንገዶችንም ትመሩ ዘንድ (አደረገ)።

And He has cast into the earth firmly set mountains, lest it shift with you, and [made] rivers and roads, that you may be guided,

16:16
ምልክቶችንም (አደረገ)፤ በከዋክብትም እነሱ ይመራሉ።

And landmarks. And by the stars they are [also] guided.

16:17
የሚፈጥር፣ እንደማይፈጥር ነውን? አትገሡጹምን ?

Then is He who creates like one who does not create? So will you not be reminded?

16:18
የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፤ አላህ በእርግጥም መሐሪ አዛኝ ነውና።

And if you should count the favors of Allah , you could not enumerate them. Indeed, Allah is Forgiving and Merciful.

16:19
አላህም የምትደብቁትንና የምትገልጹትን ሁሉ ያውቃል።

And Allah knows what you conceal and what you declare.

16:20
እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው ምንንም አይፈጥሩም፤ እነርሱም ይፈጠራሉ፤

And those they invoke other than Allah create nothing, and they [themselves] are created

16:21
ሕያው ያልሆኑ ሙታን ናቸው፤ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም።

They are, [in fact], dead, not alive, and they do not perceive when they will be resurrected.

16:22
አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት፣ ልቦቻቸው ከሐዲዎች ናቸው፤ እነሱም የኮሩ ናቸው፤ (አያምኑም)።

Your god is one God. But those who do not believe in the Hereafter - their hearts are disapproving, and they are arrogant.

16:23
አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመሆኑ ጥርጣሬ የለበትም፤ እርሱ ኩሩዎችን አይወድም።

Assuredly, Allah knows what they conceal and what they declare. Indeed, He does not like the arrogant.

16:24
ለነርሱም ጌታቸሁ (በሙሐመድ ላይ) ምንን አወረደ? በተባሉ ጊዜ (እርሱ) የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶች ነው ይላሉ።

And when it is said to them, "What has your Lord sent down?" They say, "Legends of the former peoples,"

16:25
(ይህንንም የሚሉት) በትንሣኤ ቀን ኃጢአቶቻቸውን በሙሉ ከነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኃጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው፤ ንቁ የሚሸከሙት ኀጢአት ምንኛ ከፋ!

That they may bear their own burdens in full on the Day of Resurrection and some of the burdens of those whom they misguide without knowledge. Unquestionably, evil is that which they bear.

16:26
እነዚያ ከነሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት በእርግጥ መከሩ፤ አላህም ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ፤ ጣሪያውም በነሱ ላይ ከበላያቸው ወደቀባቸው፤ ቅጣቱም ከማያውቁት ስፍራ መጣባቸው።

Those before them had already plotted, but Allah came at their building from the foundations, so the roof fell upon them from above them, and the punishment came to them from where they did not perceive.

16:27
ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል፤ እነዚያም በነሱ (ጉዳይ) ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው? ይላቸዋል፤ እነዚያ ዕውቀትን የተሰጡት፣ ፦ ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በእርግጥ በከሐዲዎች ላይ ነው ይላሉ።

Then on the Day of Resurrection He will disgrace them and say, "Where are My 'partners' for whom you used to oppose [the believers]?" Those who were given knowledge will say, "Indeed disgrace, this Day, and evil are upon the disbelievers" -

16:28
(እነርሱ) እነዚያ ነፍሶቻቸውን በዳይ ሆነው መላእክት የሚገድሏቸው ናቸው፤ ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርን (ሲሉ) ታዝዥነታቸውን ይገልጻሉ፤ በውነት አላህ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር ዐዋቂ ነው (ይባላሉ)።

The ones whom the angels take in death [while] wronging themselves, and [who] then offer submission, [saying], "We were not doing any evil." But, yes! Indeed, Allah is Knowing of what you used to do.

16:29
የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ (ይባላሉ)። የኩሩዎችም መኖሪያ (ገሀነም) በእርግጥ ከፋች!

So enter the gates of Hell to abide eternally therein, and how wretched is the residence of the arrogant.

16:30
ለነዚያም ለተጠነቀቁት ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ? ተባሉ፤ መልካምን ነገር አሉ፤ ለነዚያ ደግ ለሠሩት በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አላቸው፤ የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት፤ የጥንቁቆቹም አገር ምን ታምር!

And it will be said to those who feared Allah , "What did your Lord send down?" They will say, "[That which is] good." For those who do good in this world is good; and the home of the Hereafter is better. And how excellent is the home of the righteous -

16:31
(እርሷም) የሚገቡዋትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትሆን የመኖሪያ አትክልቶች ናት፤ ለነሱም በውስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፤ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል።

Gardens of perpetual residence, which they will enter, beneath which rivers flow. They will have therein whatever they wish. Thus does Allah reward the righteous -

16:32
እነዚያ በመልካም ሁኔታ ላይ ሆነው መላእክት ሰላም በናንተ ላይ እያሉ፣ የሚገድሏቸው ናቸው፤ ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ፣ (ይባላሉ)።

The ones whom the angels take in death, [being] good and pure; [the angels] will say, "Peace be upon you. Enter Paradise for what you used to do."

16:33
(ከሐዲዎች) መላእክት ወደነሱ መምጣትን ወይም የጌታህ ትእዛዝ መምጣቱን እንጂ አይጠባበቁም፤ ከነሱ በፊት የነበሩት እንደዚህ ሠርተዋል፤ አላህም አልበደላቸውም፤ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ።

Do the disbelievers await [anything] except that the angels should come to them or there comes the command of your Lord? Thus did those do before them. And Allah wronged them not, but they had been wronging themselves.

16:34
የሠሩዋቸውም ኀጢአቶች (ቅጣት) አገኛቸው፤ በርሱም ይሳለቁበት የነበሩት ሁሉ በነሱ ላይ ወረደባቸው።

So they were struck by the evil consequences of what they did and were enveloped by what they used to ridicule.

16:35
እነዚያም (ጣዖታትን) ያጋሩት፣ አላህ በሻ ኖሮ ከርሱ ሌላ እኛም አባቶቻችንም ምንንም ባልተገዛን ነበር፤ ያለርሱም (ትእዛዝ) ምንንም እርም ባላደረግን ነበር አሉ፤ እነዚያም ከነሱ በፊት የነበሩት፣ እንደዚሁ ሠሩ፤ በመልክተኞቹም ላይ ግልጽ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸውም።

And those who associate others with Allah say, "If Allah had willed, we would not have worshipped anything other than Him, neither we nor our fathers, nor would we have forbidden anything through other than Him." Thus did those do before them. So is there upon the messengers except [the duty of] clear notification?

16:36
በየሕዝቡም ሁሉ አውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤ ከነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ፤ ከነሱም ውስጥ አላህ በርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አለ፤ በምድርም ላይ ኺዱ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ።

And We certainly sent into every nation a messenger, [saying], "Worship Allah and avoid Taghut." And among them were those whom Allah guided, and among them were those upon whom error was [deservedly] decreed. So proceed through the earth and observe how was the end of the deniers.

16:37
በመቅናታቸው ላይ ብትጓጓ (ምንም ልታደርግ አትችልም)፤ አላህ የሚጠመውን ሰው (1) አያቀናውምና፤ ለነሱም ከረዳቶች ምንም የላቸውም።

[Even] if you should strive for their guidance, [O Muhammad], indeed, Allah does not guide those He sends astray, and they will have no helpers.

(1) እንዲጠም የሻውን ሰው

16:38
ጥብቅ መሐሎቻቸውንም አላህ የሚሞትን አያነሳም ሲሉ በአላህ ስም ማሉ፤ ሐሰት ነው (ያነሳቸዋል)፤ በርሱ ላይ ቃል ኪዳን ገብቷል፤ አረጋግጧል፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።

And they swear by Allah their strongest oaths [that] Allah will not resurrect one who dies. But yes - [it is] a true promise [binding] upon Him, but most of the people do not know.

16:39
(የሚቀሰቅሳቸውም) ለነሱ ያንን በርሱ የሚልለያዩበትን ሊገልጽላቸው፤ እነዚያ የካዱትም እነሱ ውሸታሞች የነበሩ መሆናቸውን እንዲያውቁ ነው።

[It is] so He will make clear to them [the truth of] that wherein they differ and so those who have disbelieved may know that they were liars.

16:40
ለማንኛውም ነገር (መሆኑን) በሻነው ጊዜ ቃላችን ለርሱ ሁን ማለት ብቻ ነው፤ ወዲያውም ይሆናል።

Indeed, Our word to a thing when We intend it is but that We say to it, "Be," and it is.

16:41
እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ (መንገድ ላይ) የተሰደዱት፣ በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፤ የመጨረሻይቱ ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው፤ (ከሐዲዎች) ቢያውቁ ኖሮ (በተከሏቸው ነበር)።

And those who emigrated for [the cause of] Allah after they had been wronged - We will surely settle them in this world in a good place; but the reward of the Hereafter is greater, if only they could know.

16:42
(እነርሱ) እነዚያ የታገሡት በጌታቸውም ላይ የሚጠጉት ናቸው።

[They are] those who endured patiently and upon their Lord relied.

16:43
ከአንተም በፊት ወደነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ፣ ሌላን አልላክንም፤ የማታውቁም ብትሆኑ የዕውቀትን በለቤቶች ጠይቁ።

And We sent not before you except men to whom We revealed [Our message]. So ask the people of the message if you do not know.

16:44
በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት (ላክናቸው)፤ ወደ አንተም፣ ለሰዎች ወደነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርአንን አወረድን።

[We sent them] with clear proofs and written ordinances. And We revealed to you the message that you may make clear to the people what was sent down to them and that they might give thought.

16:45
እነዚያ መጥፎዎችን የዶለቱ፥ አላህ በነሱ ምድርን የሚገለብጥባቸው ወይም ከማያውቁት ስፍራ ቅጣት የሚመጣባቸው መሆኑን አይፈሩምን?

Then, do those who have planned evil deeds feel secure that Allah will not cause the earth to swallow them or that the punishment will not come upon them from where they do not perceive?

16:47
ወይም (ካገር ወደ አገር) በሚዛወሩበት ጊዜ፣ የሚይዛቸው መሆኑን (አይፈሩምን?) እነሱም አሸናፊዎች አይደሉም።

Or that He would not seize them during their [usual] activity, and they could not cause failure?

16:47
ወይም ቀስ በቀስ በማጉደል ላይ የሚያዛቸው መሆኑን (አይፈሩምን?) ጌታች፣ሁም በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነው።

Or that He would not seize them gradually [in a state of dread]? But indeed, your Lord is Kind and Merciful.

16:48
ወደዚያ ከማንኛውም ነገር አላህ ወደ ፈጠረው ጥላዎቹ እነርሱ የተዋረዱ ሲሆኑ ለአላህ ሰጋጆች ሆነው ከቀኝና ከግራዎች ወደሚዛወሩት አላዩምን?

Have they not considered what things Allah has created? Their shadows incline to the right and to the left, prostrating to Allah , while they are humble.

16:49
ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሻም በምድር ያለው ሁሉ መላክትም ይሰግዳሉ፤ እነርሱም አይኮሩም።

And to Allah prostrates whatever is in the heavens and whatever is on the earth of creatures, and the angels [as well], and they are not arrogant.

16:50
ጌታቸውን ከበላያቸው ሲሆን ይፈሩታል፤ የታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ።

They fear their Lord above them, and they do what they are commanded.

16:51
አላህ አለ፦ ሁለት አማልክትን አትያዙ፤ እርሱ አምላክ ብቻ ነው፤ እኔንም ብቻ ፍሩ።

And Allah has said, "Do not take for yourselves two deities. He is but one God, so fear only Me."

16:52
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፤ መገዛትም ዘወትር ሲሆን ለርሱ ብቻ ነው፤ ከአላህም ሌላ ያለን ትፈራላችሁን?

And to Him belongs whatever is in the heavens and the earth, and to Him is [due] worship constantly. Then is it other than Allah that you fear?

16:53
ማንኛውም በናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ነው፤ ከዚያም ችግር በደረሰባቸሁ ጊዜ፣ ወደርሱ ብቻ ትጮሃላችሁ።

And whatever you have of favor - it is from Allah . Then when adversity touches you, to Him you cry for help.

16:54
ከዚያም ከናንተ ላይ ችግርን ባነሳላችሁ ጊዜ፣ ከናንተው የሆኑ ጭፍሮች ወዲያውኑ በጌታቸው (ጣዖትን) ያጋራሉ።

Then when He removes the adversity from you, at once a party of you associates others with their Lord

16:55
(የሚያጋሩትም) በሰጠናቸው ሊክዱ ነው፤ ተጠቀሙም ወደፊትም (የሚደርስባችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ።

So they will deny what We have given them. Then enjoy yourselves, for you are going to know.

16:56
ለማያውቁትም (ጣዖታት)፤ ከሰጠናቸው ሲሳይ ፈንታን ያደርጋሉ፤ በአላህ እምላለሁ፤ ትቀጣጥፉት ከነበራሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ።

And they assign to what they do not know a portion of that which We have provided them. By Allah , you will surely be questioned about what you used to invent.

16:57
ለአላህም (ከመላእክት) ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ፤ ጥራት ተገባው፤ ለነርሱም የሚፈልጉትን (ወንዶች ልጆችን) ያደርጋሉ።

And they attribute to Allah daughters - exalted is He - and for them is what they desire.

16:58
አንዳቸውም በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ኾኖ፣ ፊቱ ጠቊሮ ይውላል።

And when one of them is informed of [the birth of] a female, his face becomes dark, and he suppresses grief.

16:59
በርሱ ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት፣ በውርደት ላይ ኾኖ ይያዘውን? ወይስ በዐፈር ውስጥ ይደብቀውን? (በማለት እያምታታ) ከሰዎች ይደበቃል፤ ንቁ፣ የሚፈርዱት (ፍርድ) ምንኛ ከፋ!

He hides himself from the people because of the ill of which he has been informed. Should he keep it in humiliation or bury it in the ground? Unquestionably, evil is what they decide.

16:60
ለነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ለማያምኑት መጥፎ ጠባይ አላቸው፤ ለአላህም ታላቅ ባሕርይ አለው፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።

For those who do not believe in the Hereafter is the description of evil; and for Allah is the highest attribute. And He is Exalted in Might, the Wise.

16:61
አላህም ሰዎችን በበደላቸው በያዛቸው ኖሮ፣ በርሷ (በምድር) ላይ ከተንቀሳቃሽ ምንንም ባልተወ ነበር፤ ግን እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል፤ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም።

And if Allah were to impose blame on the people for their wrongdoing, He would not have left upon the earth any creature, but He defers them for a specified term. And when their term has come, they will not remain behind an hour, nor will they precede [it].

16:62
ለአላህም፣ የሚጠሉትን ነገር ያደርጋሉ (1) ለነሱም መልካሚቱ (አገር) አለቻቸው፣ በማለት ምላሶቻቸው ውሸትን ይናገራሉ፤ ለነሱ እሳት ያለቻቸው መሆናቸውና እነሱም (ወደርሷ) በቅድሚያ የሚነዱ መሆናቸው ጥርጥር የለበትም።
(1) ሴት ልጅ ተጋሪዎች አለው ይላሉ።


And they attribute to Allah that which they dislike, and their tongues assert the lie that they will have the best [from Him]. Assuredly, they will have the Fire, and they will be [therein] neglected.

16:63
በአላህ እንምላለ፣ን ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ (መልክተኞችን) ልከናል፤ ሰይጣንም ለነርሱ ሥራዎቻቸውን ሸለመላቸው፤ እርሱም ዛሬ ረዳታቸው ነው፤ ለነሱም (ኋላ) አሳማሚ ቅጣት አላቸው።

By Allah , We did certainly send [messengers] to nations before you, but Satan made their deeds attractive to them. And he is the disbelievers' ally today [as well], and they will have a painful punishment.

16:64
ባንተም ላይ መጽሐፉን አላወረድንም፤ ያንን በርሱ የተለያዩበትን ለነርሱ ልታብራራላችውና፥ ለሚያምኑትም ሕዝቦች መሪና እዝነት ሊሆን እንጂ።

And We have not revealed to you the Book, [O Muhammad], except for you to make clear to them that wherein they have differed and as guidance and mercy for a people who believe.

16:65
አላህም ከሰማይ ውሃን አወረደ፤ በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው አደረገ፤ በዚህ፣ ውስጥ፣ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አልለ።

And Allah has sent down rain from the sky and given life thereby to the earth after its lifelessness. Indeed in that is a sign for a people who listen.

16:66
ለናንተም በግመል፣ በከብት፣ በፍየል፣ በእርግጥ መገምገሚያ አልላችሁ፤ በሆዶቹ ውስጥ ካለው ከፈርስና ከደም መካክል ጥሩ ወተትን ለጠጪዎች ተዋጭ ሲሆን እናጠጣችኋለን።

And indeed, for you in grazing livestock is a lesson. We give you drink from what is in their bellies - between excretion and blood - pure milk, palatable to drinkers.

16:67
ከዘምባባዎችና ከወይኖችም ፍሬዎች፣ (እንመግባችኋለን)፤ ከርሱ ጠጅንና መልካም ምግብንም ትሠራላችሁ። በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አልለ።

And from the fruits of the palm trees and grapevines you take intoxicant and good provision. Indeed in that is a sign for a people who reason.

16:68
ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አሳወቀ፥ ከተራራዎች፥ ከዛፍም (ሰዎች) ከሚሠሩትም (ቀፎ) ቤቶችን ያዢ።

And your Lord inspired to the bee, "Take for yourself among the mountains, houses, and among the trees and [in] that which they construct.

16:69
ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፤ የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲሆኑ ግቢ፤ ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለየያዩ መጠጥ ይወጣል፤ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኀኒት አለበት፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አለበት።

Then eat from all the fruits and follow the ways of your Lord laid down [for you]." There emerges from their bellies a drink, varying in colors, in which there is healing for people. Indeed in that is a sign for a people who give thought.

16:70
አላህም ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ይገድላችኋል፤ ከናንተም ከዕውቀት በኋላ ምንንም ነገር እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፤ አላህ ዐዋቂ ቻይ ነው።

And Allah created you; then He will take you in death. And among you is he who is reversed to the most decrepit [old] age so that he will not know, after [having had] knowledge, a thing. Indeed, Allah is Knowing and Competent.

16:71
አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በሲሳይ አበለጠ፤ እነዚያም በላጭ የተደረጉት ሲሳያቸውን እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሮች) ላይ፣ እነሱ በርሱ ይተካከሉ ዘንድ መላሾች አይደሉም፤ (1) ታዲያ በአላህ ጸጋ (ለርሱ ተጋሪ በማድረግ) ይክዳሉን?
(1) በሲሳያቸው አገልጋያቸውን እያጋሩዋቸውም


And Allah has favored some of you over others in provision. But those who were favored would not hand over their provision to those whom their right hands possess so they would be equal to them therein. Then is it the favor of Allah they reject?

16:72
አላህ ከነፍሶቻሁ (ከጐሶቻችሁ) ለናንተ ሚስቶችን አደረገ፤ ለናንተም ከሚስቶቻሁ ወንዶች ልጆችን የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ፤ ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ፤ ታዲያ በውሸት (በጣዖት) ያምናሉን? በአላህም ጸጋ እነሱ ይክዳሉን?

And Allah has made for you from yourselves mates and has made for you from your mates sons and grandchildren and has provided for you from the good things. Then in falsehood do they believe and in the favor of Allah they disbelieve?

16:74
ከአላህም ሌላ ከሰማያትም ከምድርም ምንንም ሲሳይ የማይሰጧቸውን፣ (ምንንም) የማይችሉትንም ይግገዛሉ።

And they worship besides Allah that which does not possess for them [the power of] provision from the heavens and the earth at all, and [in fact], they are unable.

16:75
ለአላህም አምሳያዎችን አታድርጉ፤ አላህ (መሳይ እንደሌለው) ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም።

So do not assert similarities to Allah . Indeed, Allah knows and you do not know.

16:75
በምንም ላይ የማይችለውን፣ በይዞታ ያለውን ባሪያና ከኛ መልካም ሲሳይን የሰጠነውን እርሱም ከርሱ (ከሰጠነው) በምስጢርና በግልጽ የሚለግሰውን ( ነጻ) ሰው አላህ፣ (ለጣዖትና ለርሱ) ምሳሌ አደረገ፤ (ሁለቱ) ይተካከላሉን? ምስጋና ለአላህ ይሁን፤ በውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም።

Allah presents an example: a slave [who is] owned and unable to do a thing and he to whom We have provided from Us good provision, so he spends from it secretly and publicly. Can they be equal? Praise to Allah ! But most of them do not know.

16:76
አላህም ሁለትን ወንዶች (ለከሐዲና ለምእመናን) ምሳሌ አደረገ፤ አንደኛቸው፣ በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው፤ እነሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው፤ ወደ የትም ቢያዞረው በደግ ነገር አይመጣም፤ እርሱና ያ እርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሆኖ በማስተካከል የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን?

And Allah presents an example of two men, one of them dumb and unable to do a thing, while he is a burden to his guardian. Wherever he directs him, he brings no good. Is he equal to one who commands justice, while he is on a straight path?

16:77
በሰማያትና በምድርም ያለው ሩቅ ምስጢር የአላህ ነው፤ የሰዓቲቱም ነገር (መምጣቷ) እንደ ዓይን ቅጽበት እንጂ አይደለም፤ ወይም እርሱ ይበልጥ የቀረበ ነው፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

And to Allah belongs the unseen [aspects] of the heavens and the earth. And the command for the Hour is not but as a glance of the eye or even nearer. Indeed, Allah is over all things competent.

16:78
አላህም ከናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አውጣችሁ፤ ታመስግኑም ዘንድ ለናንተ መስሚያን፣ ማያዎችንም፣ ልቦችንም አደረገላችሁ።

And Allah has extracted you from the wombs of your mothers not knowing a thing, and He made for you hearing and vision and intellect that perhaps you would be grateful.

16:79
ወደ በራሪዎች፣ በሰማይ አየር ውስጥ (ለመብረር) የተገሩ ሲሆኑ (ከመውደቅ) አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው ኾነው አይመለከቱምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ።

Do they not see the birds controlled in the atmosphere of the sky? None holds them up except Allah . Indeed in that are signs for a people who believe.

16:80
አላህም ከቤቶቻችሁ፣ ለናንተ መርጊያ አደረገላችሁ፤ ከእንሰሳዎችም ቆዳዎች፤ በጉዟችሁ ቀን በመቀመጫችሁም ቀን የምታቀልሏቸውን (፩) ቤቶች ለናንተ አደረገላችሁ፤ ከበግዋ ሱፎች፣ ከግመልዋም ጠጉሮች፣ ከፍየልዋም፣ ጠጉሮች የቤት ዕቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን (አደረገላችሁ)።
(1) ቀላል ሆነው የምታገኙዋቸውን ድንኳኖች


And Allah has made for you from your homes a place of rest and made for you from the hides of the animals tents which you find light on your day of travel and your day of encampment; and from their wool, fur and hair is furnishing and enjoyment for a time.

16:81
አላህም ከፈጠረው ነገር ለናንተ ጥላዎችን አደረገላችሁ፤ ከጋራዎችም ለናንተ መክከሊያዎችን አደረገላችሁ፤ ሐሩርንም (ብርድንም) የሚጠብቋችሁን ልብሶች፣ የጦራችሁንም አደጋ የሚጠብቋችሁን፤ ጥሩሮች ለናንተ አደረገላችሁ፤ እንደዚሁ ትሰልሙ ዘንድ ጸጋውን በናንተ ላይ ይሞላል።

And Allah has made for you, from that which He has created, shadows and has made for you from the mountains, shelters and has made for you garments which protect you from the heat and garments which protect you from your [enemy in] battle. Thus does He complete His favor upon you that you might submit [to Him].

16:82
(ከኢስላም) ቢሸሹም ባንተ ላይ ያለብህ ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው።

But if they turn away, [O Muhammad] - then only upon you is [responsibility for] clear notification.

16:83
የአላህ ጸጋ ያውቃሉ፤ ከዚያም ይክዷታል፤ አብዛኞቻቸውም ከሐዲዎቹ ናቸው።

They recognize the favor of Allah ; then they deny it. And most of them are disbelievers.

16:84
ከየሕዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን (አስታውስ)፤ ከዚያም ለነዚያ ለካዱት (ንግግር) አይፈቀድላቸውም፤ እነሱም በወቀሳ አይታለፉም።

And [mention] the Day when We will resurrect from every nation a witness. Then it will not be permitted to the disbelievers [to apologize or make excuses], nor will they be asked to appease [ Allah ].

16:85
እነዚያም የበደሉት ቅጣቱን ባዩ ጊዜ፣ ከነሱ (ቅጣቱ) አይቀለልላቸውም፤ እነሱም ጊዜ አይሰጡም።

And when those who wronged see the punishment, it will not be lightened for them, nor will they be reprieved.

16:86
እነዚያም ያጋሩት የሚያጋሩዋቸውን ባዩ ጊዜ፣ ጌታችን ሆይ እነዚህ ከአንተ ሌላ እንግ ገዛቸው የነበርነው ተጋሪዎቻችን ናቸው ይላሉ፤ (አማልክቶቹ) እናንተ በእርግጥ ውሸታሞች ናችሁ፣ የማለትንም ቃል ወደነሱ ይጥላሉ።

And when those who associated others with Allah see their "partners," they will say," Our Lord, these are our partners [to You] whom we used to invoke besides You." But they will throw at them the statement, "Indeed, you are liars."

16:87
(አጋሪዎቹ) በዚያ ቀንም ታዛዥነታቸውን ወደ አላህ ያቀርባሉ፤ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ሁሉ ከነርሱ ይጠፋቸዋል።

And they will impart to Allah that Day [their] submission, and lost from them is what they used to invent.

16:88
እነዚያ የካዱ ከአላህም መንገድ የከለከሉ፥ ያጠፉ በነበሩት ምክንያት ቅጣትን በቅጣት ላይ ጨመርንባቸው።

Those who disbelieved and averted [others] from the way of Allah - We will increase them in punishment over [their] punishment for what corruption they were causing.

16:89
በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ፣ ከጐሳቸው በነሱ ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን፣ አንተንም በነዚህ (ሕዝቦች) ላይ መስካሪ አድርገን፣ የምናመጣህን ቀን (አስታውስ)፤ መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ፥ መሪም እዝነትም ለሙስሊሞችም አብሳሪ ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው።

And [mention] the Day when We will resurrect among every nation a witness over them from themselves. And We will bring you, [O Muhammad], as a witness over your nation. And We have sent down to you the Book as clarification for all things and as guidance and mercy and good tidings for the Muslims.

16:90
አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም ለዝምድና ባለ ቤት በመስጠትም ያዛል፤ ከአስከፊም፣ (ከማመንዘር)፤ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፤ ትገነዘቡ ዘንድ ይገሥጻችኋል።

Indeed, Allah orders justice and good conduct and giving to relatives and forbids immorality and bad conduct and oppression. He admonishes you that perhaps you will be reminded.

16:91
ቃል ኪዳንም በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ፤ መሐሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላ፣ አላህን በእናንተ ላይ በእርግጥ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትሆኑ አታፍርሱ፤ አላህ የምት ሠሩትን ሁሉ ያውቃልና።

And fulfill the covenant of Allah when you have taken it, [O believers], and do not break oaths after their confirmation while you have made Allah , over you, a witness. Indeed, Allah knows what you do.

16:92
(ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ አንዲቱ) ሕዝብ እርሷ ከ(ሌላይቱ) ሕዝብ የበዛች ለመሆንዋ በመካከላችሁ መሐሎቻችሁን (ለክዳት) መግቢያ፣ አድርጋችሁ የምትይዙ ስትሆኑ፣ እንደዚያች ፈትልዋን ከጠነከረ በኋላ ትርትሮች አድርጋ እንዳፈረሰችው፣ (ሴት) አትሁኑ። አላህ በርሱ (1) ይሞክራችኋል፤ በትንሣኤ ቀንም በርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር ለናንተ በእርግጥ ያብራራላችኋል።
(1) ቃል ኪዳንን በመሙላት በማዘዙ


And do not be like she who untwisted her spun thread after it was strong [by] taking your oaths as [means of] deceit between you because one community is more plentiful [in number or wealth] than another community. Allah only tries you thereby. And He will surely make clear to you on the Day of Resurrection that over which you used to differ.

16:93
አላህም በሻ ኖሮ አንዲት ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር፤ ግን የሚሻውን ሰው ያጠማል፤ የሚሻውንም ሰው ያቀናል፤ ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ።

And if Allah had willed, He could have made you [of] one religion, but He causes to stray whom He wills and guides whom He wills. And you will surely be questioned about what you used to do.

16:94
ጫማዎች ከተደላደሉ በኋላ እንዳይንዳለጡ፣ ከአላህም መንገድ በመከላከላችሁ ምክንያት ቅጣትን እንዳትቀምሱ መሐሎቻችሁን በመካከላችሁ ለክዳት መግቢያ አድርጋችሁ አትያዙ፤ ለናንተም (ያን ጊዜ) ታላቅ ቅጣት አላችሁ።

And do not take your oaths as [means of] deceit between you, lest a foot slip after it was [once] firm, and you would taste evil [in this world] for what [people] you diverted from the way of Allah , and you would have [in the Hereafter] a great punishment.

16:95
በአላህም ቃል ኪዳን ጥቂትን ዋጋ አትግዙ፤ የምታውቁ ብትሆኑ አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ እርሱ ለናንተ በላጭ ነውና።

And do not exchange the covenant of Allah for a small price. Indeed, what is with Allah is best for you, if only you could know.

16:96
እናንተ ዘንድ ያለው ሁሉ ያልቃል፤ አላህ ዘንድ ያለው ግን (ዘለዓለም) ቀሪ ነው፤ እነዚያንም የታገሡትን፣ ይሠሩ፤ በነበሩት በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።

Whatever you have will end, but what Allah has is lasting. And We will surely give those who were patient their reward according to the best of what they used to do.

16:97
ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፤ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።

Whoever does righteousness, whether male or female, while he is a believer - We will surely cause him to live a good life, and We will surely give them their reward [in the Hereafter] according to the best of what they used to do.

16:98
ቁርአንንም ባነበብህ ጊዜ፣ ርጉም ከሆነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ።

So when you recite the Qur'an, [first] seek refuge in Allah from Satan, the expelled [from His mercy].

16:99
እርሱ በነዚያ ባመኑትና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለርሱ ሥልጣን የለውምና።

Indeed, there is for him no authority over those who have believed and rely upon their Lord.

16:100
ሥልጣኑ በነዚያ በሚታዘዙት ላይና በነዚያም እነርሱ በርሱ (ምክንያት) አጋሪዎች በሆኑት ላይ ብቻ ነው።

His authority is only over those who take him as an ally and those who through him associate others with Allah .

16:101
በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለውጥን ጊዜ፣ አላህም የሚያወርደውን ነገር ዐዋቂ ነው፤ አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም ይላሉ፤ በውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም።

And when We substitute a verse in place of a verse - and Allah is most knowing of what He sends down - they say, "You, [O Muhammad], are but an inventor [of lies]." But most of them do not know.

16:102
እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር (ቁርአንን)፣ ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲሆን ከጌታህ አወረደው በላቸው።

Say, [O Muhammad], "The Pure Spirit has brought it down from your Lord in truth to make firm those who believe and as guidance and good tidings to the Muslims."

16:103
እነሱም እርሱን (ቁርአንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው፣ ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፤ የዚያ ወደርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐጀም ነው፤ (1) ይህ (ቁርአን) ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ ነው።
(1) ከአረብኛ ሌላ የኾነ ቋንቋ ነው።


And We certainly know that they say, "It is only a human being who teaches the Prophet." The tongue of the one they refer to is foreign, and this Qur'an is [in] a clear Arabic language.

16:104
እነዚያን በአላህ አንቀጾች የማያምኑትን አላህ አይመራቸውም፤ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው።

Indeed, those who do not believe in the verses of Allah - Allah will not guide them, and for them is a painful punishment.

16:105
ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነሱ ብቻ ናቸው።

They only invent falsehood who do not believe in the verses of Allah , and it is those who are the liars.

16:106
ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አለው)፤ ልቡ በእምነት የረጋ ሆኖ (በክሕደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር፤ ግን ልባቸውን በክህደት የከፈቱ ሰዎች፣ በነሱ ላይ ከአላህ ቁጣ አልለባቸው፤ ለነሱም ታላቅ ቅጣት አልላቸው።

Whoever disbelieves in Allah after his belief... except for one who is forced [to renounce his religion] while his heart is secure in faith. But those who [willingly] open their breasts to disbelief, upon them is wrath from Allah , and for them is a great punishment;

16:107
ይህ (ቅጣት) እነሱ ቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ በመምረጣቸው ምክንያትና አላህም ከሐዲዎችን ሕዝቦች የማያቀና በመሆኑ ነው።

That is because they preferred the worldly life over the Hereafter and that Allah does not guide the disbelieving people.

16:108
እነዚያ እነርሱ በልቦቻቸው፣ በዓይኖቻቸውም፤ በጆሮዎቻቸም፤ ላይ አላህ ያተማባቸው ናቸው፤ እነዚያም ዝንጉዎቹ እነሱ ናቸው።

Those are the ones over whose hearts and hearing and vision Allah has sealed, and it is those who are the heedless.

16:109
እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከሳሪዎቹ እነሱ ለመኾናቸው ጥርጥር የለም።

Assuredly, it is they, in the Hereafter, who will be the losers.

16:110
ከዚያም ጌታህ፣ ለነዚያ ከተፈተኑ በኋላ ለተሰደዱት፣ ከዚያም ለታገሉትና ለታገሡት፣ (መሐሪ አዛኝ ነው)፤ ጌታህ ከርሷ (ከፈተናዋ) በኋላ በእርግጥ መሐሪ አዛኝ ነውና።

Then, indeed your Lord, to those who emigrated after they had been compelled [to renounce their religion] and thereafter fought [for the cause of Allah ] and were patient - indeed, your Lord, after that, is Forgiving and Merciful

16:111
ነፍስ ሁሉ ከራሷ ላይ የምትከራከር ሆና የምትመጣበትን፣ ነፍስም ሁሉ የሠራችውን (ዋጋ) የምትቀልበትን ቀን (አስታውስ)፤ እነርሱም አይበደሉም።

On the Day when every soul will come disputing for itself, and every soul will be fully compensated for what it did, and they will not be wronged.

16:112
አላህ ጸጥተኛ፣ የረካች ሲሳይዋ ስፊ ሆኖ ከየሥፍራው ይመጣላት የነበረችውንና በአላህ ጸጋዎች የካደችውን፣ አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢአት የረኃብንና የፍርሃትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ (መካን) ምሳሌ አደረገ።

And Allah presents an example: a city which was safe and secure, its provision coming to it in abundance from every location, but it denied the favors of Allah . So Allah made it taste the envelopment of hunger and fear for what they had been doing.

16:113
ከነርሱ ውስጥ የኾነ መልክተኛም በእርግጥ መጣላቸው፤ አሰተባበሉትም፤ እነሱም በዳዮች ሆነው ቅጣቱ ያዛቸው።

And there had certainly come to them a Messenger from among themselves, but they denied him; so punishment overtook them while they were wrongdoers.

16:114
አላህም ከሰጣችሁ ሲሳይ፣ የተፈቀደ ንጹሕ ሲሆን ብሉ፤ የአላህንም ጸጋ እርሱን የምትግገዙት፣ ብትሆኑ አመስግኑ።

Then eat of what Allah has provided for you [which is] lawful and good. And be grateful for the favor of Allah , if it is [indeed] Him that you worship.

16:115
በናንተ ላይ እርም ያደረገው፣ በክትንና ደምን፣ የአሳማንም ሥጋ፣ ያንንም (በመታረድ ጊዜ) በርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፤ አመጠኛም ወሰን አላፊም ሳይሆን (ለመብላት) የተገደደ ሰው (ይፈቀድለታል)፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።

He has only forbidden to you dead animals, blood, the flesh of swine, and that which has been dedicated to other than Allah . But whoever is forced [by necessity], neither desiring [it] nor transgressing [its limit] - then indeed, Allah is Forgiving and Merciful.

16:116
በአላህም ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ፣ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት፥ ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህም እርም ነው፣ አትበሉ፤ እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ፣ አይድኑም።

And do not say about what your tongues assert of untruth, "This is lawful and this is unlawful," to invent falsehood about Allah . Indeed, those who invent falsehood about Allah will not succeed.

16:117
ጥቂት መጣቀም አላቸው፤ ለነሱም አላማሚ ቅጣት አላቸው።

[It is but] a brief enjoyment, and they will have a painful punishment.

16:118
በነዚያም ይሁዳውያን በሆኑት ላይ ከአሁን በፊት በአንተ ላይ የተረክነውን ነገር እርም አድርገንባቸዋል፤ እኛም አልበደልናቸውም፤ ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ።

And to those who are Jews We have prohibited that which We related to you before. And We did not wrong them [thereby], but they were wronging themselves.

16:119
ከዚያም ጌታህ ለነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ፤ ጌታህ ከርሷ በኋላ በእርግጥ መሐሪ አዛኝ ነው።

Then, indeed your Lord, to those who have done wrong out of ignorance and then repent after that and correct themselves - indeed, your Lord, thereafter, is Forgiving and Merciful.

16:120
ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ፣ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ሕዝብ ነበር፤ ከአጋሪዎቹም አልነበረም።

Indeed, Abraham was a [comprehensive] leader, devoutly obedient to Allah , inclining toward truth, and he was not of those who associate others with Allah .

16:121
ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር፤ መረጠው፤ ወደ ቀጥተኛውም መንገድ መራው።

[He was] grateful for His favors. Allah chose him and guided him to a straight path.

16:122
በቅርቢቱም ዓለም በጎን ነገር ሰጠነው፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም በእርግጥ ከመልካሞቹ ነው።

And We gave him good in this world, and indeed, in the Hereafter he will be among the righteous.

16:123
ከዚያም ወደ አንተ የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲሆን ተከተል፤ ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለትን አወረድን።

Then We revealed to you, [O Muhammad], to follow the religion of Abraham, inclining toward truth; and he was not of those who associate with Allah .

16:124
ሰንበት (ክልክል) የተደረገው፣ በነዚያ በርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው፤ ጌታህም በትንሣኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል።

The sabbath was only appointed for those who differed over it. And indeed, your Lord will judge between them on the Day of Resurrection concerning that over which they used to differ.

16:125
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሣጼ (በለዘብታ ቃል)፥ ጥራ፤ በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፤ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፤ እርሱም ቅን የሆኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው።

Invite to the way of your Lord with wisdom and good instruction, and argue with them in a way that is best. Indeed, your Lord is most knowing of who has strayed from His way, and He is most knowing of who is [rightly] guided.

16:126
ብትበቀሉም፣ በርሱ በተቀጣችሁበት ብጤ ተበቀሉ፤ ብትታገሡም፣ እርሱ ለታጋሾች በእርግጥ በላጭ ነው።

And if you punish [an enemy, O believers], punish with an equivalent of that with which you were harmed. But if you are patient - it is better for those who are patient.

16:127
ታገሥም፤ መታገሥህም፣ በአላህ (ማስቻል) እንጂ አይደለም፤ በነርሱም ላይ (ባያምኑ) እትተክዝ (ባንተ ላይ) ከሚመክሩትም ተንኮል በጭንቅት ውስጥ አትሁን።

And be patient, [O Muhammad], and your patience is not but through Allah . And do not grieve over them and do not be in distress over what they conspire.

16:128
አላህ ከነዚያ ከሚፈሩትና ከነዚያም እነሱ መልካም ሠሪዎች ከሆኑት ጋር ነውና።

Indeed, Allah is with those who fear Him and those who are doers of good.

Copyright 2013, AmharicQuran.com