Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ አል- ረዕድ፥ (የነጎድጓድ ምዕራፍ)

13:1
አ. ለ. መ. ረ (አሊፍ ላም ሚም ራ)(1) ይህች (አናቅጽ) ከመጽሐፉ አንቀጾች ናት፤ ያም ከጌታህ ወዳንተ የተወረደው እውነት ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም።
(1) እኔ አላህ ነኝ ዐውቃለሁ አያለሁም


Alif, Lam, Meem, Ra. These are the verses of the Book; and what has been revealed to you from your Lord is the truth, but most of the people do not believe.

13:2
አላህ ያ ሰማያትን የምታዩዋት አዕማድ ሳትኖር ያነሳት፥ ከዚያም በዐርሹ (ዙፋኑ) ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ፥ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ነው፤ ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ፤ ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል፤ በጌታችሁ መገናኘት ታረጋግጡ ዘንድ ታምራቶችን ይዘረዝራል።

It is Allah who erected the heavens without pillars that you [can] see; then He established Himself above the Throne and made subject the sun and the moon, each running [its course] for a specified term. He arranges [each] matter; He details the signs that you may, of the meeting with your Lord, be certain.

13:3
እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ፥ በሷም ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ፥ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው፤ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፤ በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ።

And it is He who spread the earth and placed therein firmly set mountains and rivers; and from all of the fruits He made therein two mates; He causes the night to cover the day. Indeed in that are signs for a people who give thought.

13:4
በምድርም የተጐራበቱ ቁርጥራጮች አሉ፤ ከወይኖችም አትክልቶች፥ አዝርዕቶችም፥ መንታዎችና መንታዎች ያልሆኑ ዘንባባዎችም አሉ፥ በአንድ ውሃ ይጥጠጣሉ፤ (በጣዕምም ይሊያያሉ)፤ ከፊሉዋንም በከፊሉ ላይ በሚበላው ሰብል እናበልጣለን፤ በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ታምራት አለበት።

And within the land are neighboring plots and gardens of grapevines and crops and palm trees, [growing] several from a root or otherwise, watered with one water; but We make some of them exceed others in [quality of] fruit. Indeed in that are signs for a people who reason.

13:5
ብትደነቅም፥ ዐፈር በኾንን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት እንሆናለን? ማለታቸው (ታላቅ) ድንቅ ነው፤ እነዚህ፥ እነዚያ በጌታቸው የካዱት ናቸው፥ እነዚህም እንዛዝላዎች በአንገቶቻቸው ላይ ያሉባቸው ናቸው፤ እነዚህም የእሳት ጓዶች ናቸው፤ እነሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው።

And if you are astonished, [O Muhammad] - then astonishing is their saying, "When we are dust, will we indeed be [brought] into a new creation?" Those are the ones who have disbelieved in their Lord, and those will have shackles upon their necks, and those are the companions of the Fire; they will abide therein eternally.

13:6
ከነሱ በፊት የመሰሎቻቸው ቅጣቶች በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመልካሙ በፊት በመጥፎው ያስቸኩሉሃል፤ ጌታህም ለሰዎች ከመበደላቸው ጋር በእርግጥ የምሕረት ባለቤት ነው፤ ጌታህም በእርግጥ ቅጣተ ብርቱ ነው።

They impatiently urge you to bring about evil before good, while there has already occurred before them similar punishments [to what they demand]. And indeed, your Lord is full of forgiveness for the people despite their wrongdoing, and indeed, your Lord is severe in penalty.

13:7
እነዚያም የካዱት፥ በርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም ይላሉ፤ አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው።

And those who disbelieved say, "Why has a sign not been sent down to him from his Lord?" You are only a warner, and for every people is a guide.

13:8
አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ያውቃል፤ ማሕፀኖችም የሚያጐድሉትን የሚጨምሩትንም፥ (ያውቃል)፤ ነገሩም ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው።

Allah knows what every female carries and what the wombs lose [prematurely] or exceed. And everything with Him is by due measure.

13:9
ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ታላቅ የላቀ ነው።

[He is] Knower of the unseen and the witnessed, the Grand, the Exalted.

13:10
ከናንተ ውስጥ ቃሉን ዝቅ ያደረገ ሰው፥ በርሱ የጮኸም ሰው፥ እርሱ በሌሊት ተደባቂም፥ በቀን (ተገልጾ) ኺያጅም የሆነ ሰው፥ (እርሱ ዘንድ) እኩል ነው።

It is the same [to Him] concerning you whether one conceals [his] speech or one publicizes it and whether one is hidden by night or conspicuous [among others] by day.

13:11
ለርሱ (ለሰው)፥ ከስተፊቱም ከኋላውም፥ በአላህ ትእዛዝ (ከክፉ) የሚጠብቁት ተተካኪዎች (መላእክት) አልሉት፤ አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ፥ በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚልውጡ ድረስ አይለውጥም፤ አላህምበሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለርሱ መመለስ የለውም፤ ለነርሱም ከርሱ ሌላ : ምንም ተከላካይ የላቸውም።

For each one are successive [angels] before and behind him who protect him by the decree of Allah . Indeed, Allah will not change the condition of a people until they change what is in themselves. And when Allah intends for a people ill, there is no repelling it. And there is not for them besides Him any patron.

13:12
እርሱ ያ፥ የምትፈሩና የምትከጅሉም ስትሆኑ፥ ብልጭታን የሚያሳያችሁ ከባዶች ደመናዎችንም የሚያስገኝ ነው።

It is He who shows you lightening, [causing] fear and aspiration, and generates the heavy clouds.

13:13
ነጐድጓድም አላህን በማመስገን ያጠራል፣ መላእክትም እርሱን ለመፍራት (ያጠሩታል)፤ መብረቆችንም ይልካል፤ እነርሱም (ከሐዲዎች) በአላህ የሚከራከሩ ሲሆኑ በርሷ የሚሻውን ሰው ይመታል እርሱም ኀይለ ብርቱ ነው።

And the thunder exalts [ Allah ] with praise of Him - and the angels [as well] from fear of Him - and He sends thunderbolts and strikes therewith whom He wills while they dispute about Allah ; and He is severe in assault.

13:14
ለርሱ (ለአላህ) የውነት መጥሪያ አለው፤ እነዚያም ከርሱ ሌላ የሚግገዙዋቸው (ጣዖታት) ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ ወደ ውሃ መዳፎቹን (በሩቅ ሆኖ) እንደሚዘረጋ (ሰው መልስ) እንጂ ለነርሱ በምንም አይመልሱላቸውም፤(1) እርሱም ወደ አፉ ደራሽ አይደለም፤ የከሐዲዎችም ጥሪ በከንቱ እንጂ አይደለም።
(1) ውኃው በእጁ ቢጠቅሰው ወደ አፉ እንደማይመጣ ጣዖታቶቹም ፀሎታቸውን አይሰሟቸውም።


To Him [alone] is the supplication of truth. And those they call upon besides Him do not respond to them with a thing, except as one who stretches his hands toward water [from afar, calling it] to reach his mouth, but it will not reach it [thus]. And the supplication of the disbelievers is not but in error [i.e. futility].

13:15
በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ፤ ጥላዎቻቸውም በጧቶችና በሠርኮች (1) (ይሰግዳሉ)።
(1) ሠርክ ከአሥራ አንድ እስከ ዐሥራ ሁለት ያለው ጊዜ ነው።


And to Allah prostrates whoever is within the heavens and the earth, willingly or by compulsion, and their shadows [as well] in the mornings and the afternoons.

13:16
የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው? በላቸው፤ አላህ ነው በል፤ ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከርሱ ሌላ ያዛችሁን? በላቸው፤ ዕውርና የሚያይ ይተካከላሉን? ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይተካከላሉን? ወይስ ለአላህ እንደርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አደረጉለትና ፍጥረቱ በነሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን? በል፤ አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው በል።

Say, "Who is Lord of the heavens and earth?" Say, " Allah ." Say, "Have you then taken besides Him allies not possessing [even] for themselves any benefit or any harm?" Say, "Is the blind equivalent to the seeing? Or is darkness equivalent to light? Or have they attributed to Allah partners who created like His creation so that the creation [of each] seemed similar to them?" Say, " Allah is the Creator of all things, and He is the One, the Prevailing."

13:17
ከሰማይ ውሃን አወረደ፤ ሸለቆዎቹም በመጠናቸው ፈሰሱ፤ ጎርፉም አሰፋፊውን ኮረፋት ተሸከመ፤ ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጐት በርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም (ማዕድን)፥ ብጤው የሆነ ኮረፋት አለው፤ እንደዚሁ አላህ ለውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል፤ ኮረፋቱማ፥ ግብስብስ ሆኖ ይጠፋል፤ ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል፤ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልጻል።

He sends down from the sky, rain, and valleys flow according to their capacity, and the torrent carries a rising foam. And from that [ore] which they heat in the fire, desiring adornments and utensils, is a foam like it. Thus Allah presents [the example of] truth and falsehood. As for the foam, it vanishes, [being] cast off; but as for that which benefits the people, it remains on the earth. Thus does Allah present examples.

13:18
ለነዚያ ለጌታቸው ለታዘዙት መልካም ነገር (ገነት) አላቸው፤ እነዚያም ለርሱ ያልታዘዙት፥ ለነሱ በምድር ያለው ሁሉ ከርሱም ጋር ብጤው ቢኖራቸው ኖሮ፥ በርሱ በተበዡበት ነበር፤ እነዚያ ለነሱ ክፉ ምርመራ አለባቸው፤ መኖሪያቸውም ገሀነም ናት፤ ፍራሻቸውም ከፋች!

For those who have responded to their Lord is the best [reward], but those who did not respond to Him - if they had all that is in the earth entirely and the like of it with it, they would [attempt to] ransom themselves thereby. Those will have the worst account, and their refuge is Hell, and wretched is the resting place.

13:19
ከጌታህ ወዳንተ የተወረደው እውነት መሆኑን የሚያውቅ ሰው፥ እንደዚያ እርሱ ዕውር እንደ ሆነው ሰው ነውን? የሚገሠጹት የአእምሮ ባለ ቤቶች ብቻ ናቸው።

Then is he who knows that what has been revealed to you from your Lord is the truth like one who is blind? They will only be reminded who are people of understanding -

13:20
እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳን የሚሞሉ፥ የጠበቀውንም ኪዳን የማያፈርሱ ናቸው።

Those who fulfill the covenant of Allah and do not break the contract,

13:21
እነዚያም አላህ እንዲቀጠል በርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ፥ ጌታቸውንም የሚያከብሩ፥ መጥፎንም ቁጥጥር የሚፈሩ ናቸው።

And those who join that which Allah has ordered to be joined and fear their Lord and are afraid of the evil of [their] account,

13:22
እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሡ፥ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ሆነ በግልጽ የመጸወቱ፥ ክፉውንም ነገር በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው፤ እነዚያ ለነሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው።

And those who are patient, seeking the countenance of their Lord, and establish prayer and spend from what We have provided for them secretly and publicly and prevent evil with good - those will have the good consequence of [this] home -

13:23
(እርሷም) የመኖሪያ ገነቶች ናት፤ ይገቡባታል፤ ከአባቶቻቸውም ከሚስቶቻቸውም ከዝርያቸውም መልካም የሠራ ሰው (ይገባታል)፤ መላእክትም በነሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ።

Gardens of perpetual residence; they will enter them with whoever were righteous among their fathers, their spouses and their descendants. And the angels will enter upon them from every gate, [saying],

13:24
ሰላም ለናንተ ይሁን (ይህ ምንዳ) በመታገሣችሁ ነው የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር (ይሏቸዋል)።

"Peace be upon you for what you patiently endured. And excellent is the final home."

13:25
እነዚያም የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኋላ የሚያፈርሱ አላህም እንዲቀጠል በርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ፥ በምድርም ላይ የሚያበላሹ፥ እነዚያ ለነሱ ርግማን አለባቸው፤ ለነሱም መጥፎ አገር (ገሀነም) አላቸው።

But those who break the covenant of Allah after contracting it and sever that which Allah has ordered to be joined and spread corruption on earth - for them is the curse, and they will have the worst home.

13:26
አላህ፥ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል፤ ያጠባልም፤ (ከሐዲዎች) በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ፤ የቅርቢቱም ሕይወት፥ በመጨረሻይቱ አንጻር፥ (ትንሽ መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም።

Allah extends provision for whom He wills and restricts [it]. And they rejoice in the worldly life, while the worldly life is not, compared to the Hereafter, except [brief] enjoyment.

13:27
እነዚያም የካዱት፥ በርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደም ይላሉ፤ አላህ የሚሻውን ያጠማል፤ የተመለሰውንም ሰው ወደርሱ ይመራል፥ በላቸው።

And those who disbelieved say, "Why has a sign not been sent down to him from his Lord?" Say, [O Muhammad], "Indeed, Allah leaves astray whom He wills and guides to Himself whoever turns back [to Him] -

13:28
(እነሱም) እነዚያ ያመኑ፥ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፤ ንቁ፥ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ።

Those who have believed and whose hearts are assured by the remembrance of Allah . Unquestionably, by the remembrance of Allah hearts are assured."

13:29
እነዚያ ያመኑትና መልካም ሥራዎችን የሠሩት ለነሱ ደግ ኑሮ መልካም መመለሻም አላቸው።

Those who have believed and done righteous deeds - a good state is theirs and a good return.

13:30
እንደዚሁ ከበፊትዋ ብዙ ሕዝቦች በእርግጥ ያለፉ ወደ ሆነችው ሕዝብ፥ እነርሱ በአልረሕማን (1) የሚክዱ ሲሆኑ፥ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርአን በነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ፤ እርሱ (አልረሕማን) ጌታዬ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ በርሱ ላይ ተጠጋሁ፤ መመለሻየም ወደርሱ ብቻ ነው በላቸው።
(1) አልረሕማን የአላህ ልዩ ስም ነው።


Thus have We sent you to a community before which [other] communities have passed on so you might recite to them that which We revealed to you, while they disbelieve in the Most Merciful. Say, "He is my Lord; there is no deity except Him. Upon Him I rely, and to Him is my return."

13:31
ቁርአንም በርሱ ተራራዎች በተነዱበት፥ ወይም በርሱ ምድር በተቆራረጠችበት፥ ወይም በርሱ ሙታን እንዲናገሩ በተደረጉበት ኖሮ፥ (የመካ ከሐዲዎች ባላመኑ ነበር)፤ በውነቱ ነገሩ ሁሉ የአላህ ነው፤ እነዚያ ያመኑት ሰዎች፥ እነሆ አላህ በሻ ኖሮ ሰዎችን በመላ በእርግጥ ይመራቸው እንደ ነበረ አያውቁምን? እነዚያም የካዱት፥ በሥራቸው ምክንያት (አጥፊ) ዐደጋ የምታገኛቸው ከመሆን፥ ወይም የአላህ ቀጠሮ እስኪመጣ በአገራቸው አቅራቢያ (አንተ) የምትሰፍርባቸው ከመሆን አይወገዱም፤ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና።

And if there was any qur'an by which the mountains would be removed or the earth would be broken apart or the dead would be made to speak, [it would be this Qur'an], but to Allah belongs the affair entirely. Then have those who believed not accepted that had Allah willed, He would have guided the people, all of them? And those who disbelieve do not cease to be struck, for what they have done, by calamity - or it will descend near their home - until there comes the promise of Allah . Indeed, Allah does not fail in [His] promise.

13:32
ከአንተ በፊት በነበሩትም መልክተኞች፥ በእርግጥ ተላግጦባቸዋል፤ ለነዚያም ለካዱት፥ ጊዜን ሰጠኋቸው፤ ከዚያም (በቅጣት) ያዝኩዋቸው፤ ቅጣቴም እንዴት ነበር!

And already were [other] messengers ridiculed before you, and I extended the time of those who disbelieved; then I seized them, and how [terrible] was My penalty.

13:33
እርሱ በነፍስ ሁሉ ላይ በሠራችው ሥራ ተጠባባቂ የሆነው፥ (አላህ፥ እንደዚህ እንዳልሆነው ጣዖት ብጤ ነውን?) ለአላህም ተጋሪዎችን አደረጉ፤ ጥሯቸው (1) አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ኖሮ ትነግሩታላችሁን? ወይስ ከቃል በግልጽ (ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎች በማለት ትጠሩዋቸዋላችሁን?) በላቸው፤ በውነቱ ለነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው፤ ከውነቱ መንገድም ታገዱ፤ አላህም ያጠመመው ሰው፥ ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም።
(1) የአምላክነት ባሕርይ እንዳላቸው መጥኑዋቸው።


Then is He who is a maintainer of every soul, [knowing] what it has earned, [like any other]? But to Allah they have attributed partners. Say, "Name them. Or do you inform Him of that which He knows not upon the earth or of what is apparent of speech?" Rather, their [own] plan has been made attractive to those who disbelieve, and they have been averted from the way. And whomever Allah leaves astray - there will be for him no guide.

13:34
ለነሱ በቅርቢቱ ሕይወት ቅጣት አላቸው፤ የመጨረሻይቱም (ዓለም) ቅጣት በጣም የበረታ ነው፤ ለነሱም ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ የላቸውም።

For them will be punishment in the life of [this] world, and the punishment of the Hereafter is more severe. And they will not have from Allah any protector.

13:35
ያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰትጧ ገነት ምጣኔዋ፥ (እንደሚነገራችሁ ነው)፤ ከሥርዋ ወንዞች ይፈሳሉ፤ ምግቧ (ሁልጊዜ) የማይቋረጥ፤ ነው፤ ጥላዋም (እንደዚሁ)፥ ይህች የነዚያ የተጠነቀቁት መጨረሻ ናት፤ የከሐዲዎችም መጨረሻ እሳት ናት።

The example of Paradise, which the righteous have been promised, is [that] beneath it rivers flow. Its fruit is lasting, and its shade. That is the consequence for the righteous, and the consequence for the disbelievers is the Fire.

13:36
እነዚያም መጽሐፉን የሰጠናቸው፥ ወዳንተ በተወረደው ይደሰታሉ፤ ከአሕዛብም ከፊሉን የሚክዱ ሰዎች አሉ፤ እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድግገዛ፥ በርሱም እንዳላጋራ ነው፤ ወደርሱ እጠራለሁ፤ መመለሻየም ወደርሱ ነው በላቸው።

And [the believers among] those to whom We have given the [previous] Scripture rejoice at what has been revealed to you, [O Muhammad], but among the [opposing] factions are those who deny part of it. Say, "I have only been commanded to worship Allah and not associate [anything] with Him. To Him I invite, and to Him is my return."

13:37
እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲሆን አወረድነው፤ ዕውቀቱ ከመጣልህም በኋላ፥ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል፥ ከአላህ ቅጣት ምንም ረዳትም ጠባቂም የለህም።

And thus We have revealed it as an Arabic legislation. And if you should follow their inclinations after what has come to you of knowledge, you would not have against Allah any ally or any protector.

13:38
ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፤ ለነሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል፤ ለማንኛውም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ፥ ታምር ሊያመጣ አይገባውም፤ ለጊዜው ሁሉ ጽሁፍ አለው።

And We have already sent messengers before you and assigned to them wives and descendants. And it was not for a messenger to come with a sign except by permission of Allah . For every term is a decree.

13:39
አላህ የሚሻውን ያብሳል፤ ያጸድቃልም፤ የመጽሐፉ መሠረትም እርሱ ዘንድ ነው።

Allah eliminates what He wills or confirms, and with Him is the Mother of the Book

13:40
የዚያንም ያስፈራራናቸውን ከፊሉን ብናሳይህ፥ (መልካም ነው)፤ ወይም ብንገድልህ (ወቀሳ የለብህም)፤ በአንተ ላይ ያለብህ፥ ማድረስ ብቻ ነው፤ ምርመራውም በኛ ላይ ነው።

And whether We show you part of what We promise them or take you in death, upon you is only the [duty of] notification, and upon Us is the account.

13:41
እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ሆነን የምንመጣባት መሆናችንን፥ አላዩምን? አላህም ይፈርዳል፤ ለፍርዱም ገልባጭ የለውም፤ እርሱም ምርመራው ፈጣን ነው።

Have they not seen that We set upon the land, reducing it from its borders? And Allah decides; there is no adjuster of His decision. And He is swift in account.

13:42
እነዚያም ከነሱ በፊት የነበሩት በእርግጥ መከሩ፤ አዘንግቶም የመያዙ ዘዴ በሙሉ የአላህ ነው፤ ነፍስ ሁሉ የምትሠራውን ያውቃል፤ ከሐዲዎችም የመጨረሻይቱ አገር ለማን እንደምትሆን ወደፊት ያውቃሉ።

And those before them had plotted, but to Allah belongs the plan entirely. He knows what every soul earns, and the disbelievers will know for whom is the final home.

13:43
እነዚያም የካዱት ሰዎች፥ መልክተኛ አይደለህም ይላሉ፤ በኔና በናንተ መካከል መስካሪ በአላህና እርሱ ዘንድ የመጽሐፉ ዕውቀት ባለው ሰው በቃ፥ በላቸው።

And those who have disbelieved say, "You are not a messenger." Say, [O Muhammad], "Sufficient is Allah as Witness between me and you, and [the witness of] whoever has knowledge of the Scripture."

Copyright 2013, AmharicQuran.com