Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ ዩሱፍ (የዮሴፍ ምዕራፍ)

12:1
አ.ለ.ረ. (አሊፍ ላም ራ) እነዚህ የገላጩ መጽሐፍ አንቀጾች ናቸው።

Alif, Lam, Ra. These are the verses of the clear Book.

12:2
እኛ (ፍቹን) ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርአን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው።

Indeed, We have sent it down as an Arabic Qur'an that you might understand.

12:3
እኛ ይህንን ቁርአን ወደ አንተ በማውረዳችን በጣም መልካም ዜናዎችን በአንተ ላይ እንተርክልሃለን፤ እነሆ ከርሱ በፊት (ካለፉት ሕዝቦች ታሪክ) በእርግጥ ከዘንጊዎቹ ነበርክ።

We relate to you, [O Muhammad], the best of stories in what We have revealed to you of this Qur'an although you were, before it, among the unaware.

12:4
ዩሱፍ ለአባቱ፦ አባቴ ሆይ! እኔ ዐሥራ አንድ ክዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃን (በሕልሜ) አየሁ፤ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው ባለ ጊዜ (አስታውስ)።

[Of these stories mention] when Joseph said to his father, "O my father, indeed I have seen [in a dream] eleven stars and the sun and the moon; I saw them prostrating to me."

12:5
(አባቱም) አለ፦ ልጄ ሆይ! ሕልምህን ለወንድሞችህ አታውራ ላንተ ተንኮልን ይሠሩብሃልና፤ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና።

He said, "O my son, do not relate your vision to your brothers or they will contrive against you a plan. Indeed Satan, to man, is a manifest enemy.

12:6
እንደዚሁም (እንዳየኸው) ጌታህ ይመርጥሃል፤ ከንግግሮችም ፍች ያስተምርሃል፤ ጸጋውንም ከአሁን በፊት በሁለቱ አባቶችህ በኢብራሒምና በኢስሐቅ ላይ እንደአሟላት በአንተ ላይና በያቆብ ዘሮችም ላይ ይሞላታል፤ ጌታህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና።

And thus will your Lord choose you and teach you the interpretation of narratives and complete His favor upon you and upon the family of Jacob, as He completed it upon your fathers before, Abraham and Isaac. Indeed, your Lord is Knowing and Wise."

12:7
በየሱፍና በወንድሞቹ (ታሪኮች) ውስጥ ለጠያቂዎች ሁሉ በእርግጥ አስደናቂ ምልክቶች ነበሩ፤

Certainly were there in Joseph and his brothers signs for those who ask,

12:8
(ወንድሞቹ) ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፤- እኛ ጭፍሮች ስንሆን ዩሱፍና ወንድሙ (ብንያም) ወደ አባታችን ከኛ ይበልጥ የተወደዱ ናቸው አባታችን በግልጽ ስሕተት ውስጥ ነው፤

When they said, "Joseph and his brother are more beloved to our father than we, while we are a clan. Indeed, our father is in clear error.

12:9
ዩሱፍን ግደሉ ወይም በ(ሩቅ) ምድር ላይ ጣሉት፤ ያባታችሁ ፊት ለናንተ ግል ይሆናልና ከርሱም በኋላ መልካም ሕዝቦች ትሆናላቹና (ተባባሉ)።

Kill Joseph or cast him out to [another] land; the countenance of your father will [then] be only for you, and you will be after that a righteous people."

12:10
ከነሱ አንድ ተናጋሪ ዩሱፍን አትግደሉ ግን በጉድጓድ አዘቅት ጨለማ ውስጥ ጣሉት፤ ከተጓዢዎች አንዱ ያነሳዋልና፤ ሠሪዎች ብትሆኑ (በዚሁ ተብቃቁ) አላቸው።

Said a speaker among them, "Do not kill Joseph but throw him into the bottom of the well; some travelers will pick him up - if you would do [something]."

12:11
(እነሱም) አሉ ፦ አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ላይ ለምን አታምነንም? እኛም ለርሱ በእርግጥ አዛኞች ነን፤

They said, "O our father, why do you not entrust us with Joseph while indeed, we are to him sincere counselors?

12:12
ነገ ከእኛ ጋር ላከውና ይደሰት፤ ይጫወትም፤ እኛም ለርሱ ጠባቂዎች ነን።

Send him with us tomorrow that he may eat well and play. And indeed, we will be his guardians.

12:13
፦ እኔ እርሱን (ዩሱፍን) ይዛችሁ መኼዳችሁ በእርግጥ ያሳዝነኛል፤ እናንተም ከርሱ ዘንጊዎች ስትሆኑ ተኩላ ይበላዋል ብዬ እፈራለሁ አላቸው።

Jacob] said, "Indeed, it saddens me that you should take him, and I fear that a wolf would eat him while you are of him unaware."

12:14
፦እኛ ጭፍራዎች ሆነን ሳለን ተኩላ ቢበላውማ እኛ ያን ጊዜ በእርግጥ ከሳሪዎች ነን አሉት።

They said, " If a wolf should eat him while we are a [strong] clan, indeed, we would then be losers."

12:15
እርሱንም ይዘውት በኼዱና በጉድጓዱ ጨለማ አዘቅት ውስጥ እንዲያደርጉት በቆረጡ ጊዜ (ሐሳባቸውን ፈጸሙበት)፤ ወደርሱም እነሱ የማያውቁ ሲሆኑ ይህንን ሥራቸውን በእርግጥ ትነግራቸዋለህ ስንል ላክንበት።

So when they took him [out] and agreed to put him into the bottom of the well... But We inspired to him, "You will surely inform them [someday] about this affair of theirs while they do not perceive [your identity]."

12:16
አባታቸውንም በምሽት እያለቀሱ መጡት፤

And they came to their father at night, weeping

12:17
አባታችን ሆይ! እኛ (ለሩጫና ለውርወራ) ልንሽቀዳደም ኼድን፤ ዩሱፍንም ዕቃችን ዘንድ ተውነው ወዲያውም ተኩላ በላው፤ አንተም እውነተኛ ብንሆንም የምታምነን አይደለህም አሉ።

They said, "O our father, indeed we went racing each other and left Joseph with our possessions, and a wolf ate him. But you would not believe us, even if we were truthful."

12:18
በቀሚሱም ላይ የውሸትን ደም አመጡ፤ (አባታቸው) አይደለም፤ ነፍሶቻችሁ (ውሸት) ነገርን ለናንተ ሸለሙላችሁ፤ ስለዚህ መልካም ትእግሥት (ማድረግ አለብኝ) በምትሉትም ነገር ላይ መታገዣው አላህ ብቻ ነው አለ።

And they brought upon his shirt false blood. [Jacob] said, "Rather, your souls have enticed you to something, so patience is most fitting. And Allah is the one sought for help against that which you describe."

12:19
መንገዶኞችም መጡ፤ ውሃ ቀጂያቸውንም ላኩ፤ አኮሊውንም (ወደ ጉድጓዱ) ሰደደ፤(1) ፦ የምስራች! ይህ ወጣት ልጅ ነው አለ፤ ሸቀጥ አድርገውም ደበቁት፤ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው።
(1)ዩሱፍም አኮሌው ላይ ተንጠልጥሎ ወጣ


And there came a company of travelers; then they sent their water drawer, and he let down his bucket. He said, "Good news! Here is a boy." And they concealed him, [taking him] as merchandise; and Allah was knowing of what they did.

12:20
በርካሽ ዋጋም በሚቆጠሩ ዲርሃሞች ሸጡት፤ በርሱም ከቸልተኞቹ ነበሩ።

And they sold him for a reduced price - a few dirhams - and they were, concerning him, of those content with little.

12:21
ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ ፦ መኖሪያውን አክብሪ፤ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና፤ አላት፤ እንደዚሁም ለዩሱፍ (ገዥ ልናደርገውና) የሕልሞችንም ፍች፣ ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው፤ አላህም በነገሩ ላይ አሸናፊ ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።

And the one from Egypt who bought him said to his wife, "Make his residence comfortable. Perhaps he will benefit us, or we will adopt him as a son." And thus, We established Joseph in the land that We might teach him the interpretation of events. And Allah is predominant over His affair, but most of the people do not know.

12:22
ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው፤ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን።

And when Joseph reached maturity, We gave him judgment and knowledge. And thus We reward the doers of good

12:23
ያቺም እርሱ በቤትዋ የነበረባት ሴት፣ ከነፍሱ አባበለችው፤ ደጃፎችንም ዘጋች፤ ላንተ ተዘጋጅቼልሀለሁና ቶሎ ናም አለች፤ በአላህ እጠበቃለሁ እርሱ (የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና፤ (አልከዳውም)፤ እነሆ! በደለኞች አይድኑም፤ አላት።

And she, in whose house he was, sought to seduce him. She closed the doors and said, "Come, you." He said, "[I seek] the refuge of Allah . Indeed, he is my master, who has made good my residence. Indeed, wrongdoers will not succeed."

12:24
በእርሱም በእርግጥ አሰበች በርሷም አሰበ፤ የጌታውን ማስረጃ ባላዬ ኖሮ (የተፈጥሮ ፍላጎቱን ባረካ ነበር፤) እንደዚሁ መጥፎ ነገርንና ኃጢአትን ከርሱ ላይ ልንመልስለት፣ (አስረጃችንን አሳየነው)፤ እርሱ ከተመረጡት ባሮቻችን ነውና።

And she certainly determined [to seduce] him, and he would have inclined to her had he not seen the proof of his Lord. And thus [it was] that We should avert from him evil and immorality. Indeed, he was of Our chosen servants.

12:25
በሩንም ተሽቀዳደሙ (1) ቀሚሱንም ከስተኋላው ቀደደችው፤ ጌታዋንም (ባለቤትዋን) እበሩ አጠገብ አገኙት (ቀደም ብላ) በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጅ ሌላ አይደለም አለችው።
(1) እርሱ ለማምለጥ እርሷ ለመያዝ


And they both raced to the door, and she tore his shirt from the back, and they found her husband at the door. She said, "What is the recompense of one who intended evil for your wife but that he be imprisoned or a painful punishment?"

12:26
(ዩሱፍም) እርሷ ከነፍሴ አባበለችኝ አለ፤ ከቤተሰቦችዋም መስካሪ (እንዲህ ሲል) መሰከረ፤ ቀሚሱ ከስተፊት ተቀዶ እንደሆነ እውነት ተናገረች፤ እርሱም ከውሸታሞቹ ነው።

[Joseph] said, "It was she who sought to seduce me." And a witness from her family testified. "If his shirt is torn from the front, then she has told the truth, and he is of the liars.

12:27
ቀሚሱም ከኋላ ተቀዶ እንደሆነ ዋሸች፤ እርሱም ከእውነተኞቹ ነው።

But if his shirt is torn from the back, then she has lied, and he is of the truthful."

12:28
ቀሚሱንም ከኋላ ተቀዶ ባየ ጊዜ እርሱ (የተናገርሺው) ከተንኮላችሁ ነው፤ (ሴቶች) ተንኮላችሁ በእርግጥ ብርቱ ነውና አላት።

So when her husband saw his shirt torn from the back, he said, "Indeed, it is of the women's plan. Indeed, your plan is great.

12:29
፦ ዩሱፍ ሆይ! ከዚህ (ወሬ) ተከልከል፤ ለኃጢያትሽም ማርታን ለምኚ፤ አንቺ ከስሕተተኞቹ ሆነሻልና (አለ)።
(1) የማዕረግ ስሙ ነው፤ የተፀውዖ ስሙ ቂጥፊር ነው።


Joseph, ignore this. And, [my wife], ask forgiveness for your sin. Indeed, you were of the sinful."

12:30
በከተማው ያሉ ሴቶችም የዓዚዝ (1) ሚስት ብላቴናዋን ከነፍሱ ታባብለዋለች በውነቱ ፍቅሩ ልቧን መቷታል፤ እኛ እግልጽ ስሕተት ውስጥ ሆና በእርግጥ እናያታለን አሉ።

And women in the city said, "The wife of al-'Azeez is seeking to seduce her slave boy; he has impassioned her with love. Indeed, we see her [to be] in clear error."

12:31
ኀሜታቸውን በሰማች ጊዜ ወደነሱ ላከችባቸው፤ ምግብንም ለነርሱ አዘጋጀችላቸው ከነሱ ለያንዳንዳቸው ቢላዋን ሰጠች፤ በነሱም ላይ ውጣ አለችው፤ ባዩትም ጊዜ አደነቁት፤ እጆቻቸውንም ቆረጡ፤ አላህም ጥራት ይገባው ይህ ሰው አይደለም ይህ ያማረ መልአክ እንጅ ሌላ አይደለም አሉ።

So when she heard of their scheming, she sent for them and prepared for them a banquet and gave each one of them a knife and said [to Joseph], "Come out before them." And when they saw him, they greatly admired him and cut their hands and said, "Perfect is Allah ! This is not a man; this is none but a noble angel."

12:32
፦ ታዲያ ይኻችሁ ያ በርሱ (ፍቅር) የዘለፋችሁኝ ነው፤ በእርግጥም ከነፍሱ አባበልኩት፤ እንቢ አለም፤ የማዘውንም ነገር ባይሠራ በእርግጥ ይታሠራል፤ ከወራዶቹም ይሆናል አለች፤

She said, "That is the one about whom you blamed me. And I certainly sought to seduce him, but he firmly refused; and if he will not do what I order him, he will surely be imprisoned and will be of those debased."

12:33
፦ ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለኔ የተወደደ ነው፤ ተንኮላቸውንም ከኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ እዘነበላለሁ፤ ከስሕተተኞቹም እሆናለሁ አለ።

He said, "My Lord, prison is more to my liking than that to which they invite me. And if You do not avert from me their plan, I might incline toward them and [thus] be of the ignorant."

12:34
ጌታውም ጸሎቱን ተቀበለው ተንኮላቸውንም ከርሱ መለሰለት፤ እነሆ! እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና።

So his Lord responded to him and averted from him their plan. Indeed, He is the Hearing, the Knowing.

12:35
ከዚያም ማስረጃዎቹን ካዩ በኋላ እስከ ጊዜ ድረስ እንዲያስሩት ለነሱ ታያቸው።

Then it appeared to them after they had seen the signs that al-'Azeez should surely imprison him for a time.

12:36
ከርሱም ጋር ሁለት ጎበዞች እስር ቤቱ ገቡ አንደኛቸው እኔ ሕልሜ የወይን ጠጅን ስጠምቅ አየሁ አለ፤ ሌላውም ፦ እኔ በራሴ ላይ እንጀራን ተሸክሜ ከሱ በራሪ (አሞራ) ስትበላ አየሁ፤ ፍቹን ንገረን፤ እኛ ከአሳማሪዎች ሆነህ እናይሀለንና አሉት።

And there entered the prison with him two young men. One of them said, "Indeed, I have seen myself [in a dream] pressing wine." The other said, "Indeed, I have seen myself carrying upon my head [some] bread, from which the birds were eating. Inform us of its interpretation; indeed, we see you to be of those who do good."

12:37
(ዩሱፍም) አለ፦ ማንኛውንም የምትስሰጡት ምግብ ለናንተ ከመምጣቱ በፊት ፍቹን የምነግራችሁ ቢሆን እንጅ አይመጣላችሁም፤ ይሃችሁ፣ ጌታዬ ካሳወቀኝ ነገር ነው፤ እኔ በአላህ የማያምኑን እነርሱም መጨርሻይቱን ዓለም እነርሱ ከሐዲዎች የሆኑትን ሕዝቦች ኃይማኖት ትቻለሁ፤

He said, "You will not receive food that is provided to you except that I will inform you of its interpretation before it comes to you. That is from what my Lord has taught me. Indeed, I have left the religion of a people who do not believe in Allah , and they, in the Hereafter, are disbelievers.

12:38
የአባቶቼን የኢብራሂምንና፣ የኢስሐቅን፣ የያዕቆብንም ሃይማኖት ተከትያለሁ፤ ለኛ በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም፤ ያ (አለማጋራት) በኛ ላይና በሰዎቹ ላይ የአላህ ችሮታ ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም።

And I have followed the religion of my fathers, Abraham, Isaac and Jacob. And it was not for us to associate anything with Allah . That is from the favor of Allah upon us and upon the people, but most of the people are not grateful.

12:39
የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ (1) አምላኮች ይሻላሉን ወይንስ አሸናፊው አንዱ አላህ?
(1) ከብርና ከወርቅ ከእንጨት የተሠሩ


O [my] two companions of prison, are separate lords better or Allah , the One, the Prevailing?

12:40
ከርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸውን ስሞች እንጅ አትግገዙም፤ አላህ በርሷ ምንም አስረጅ አላወረደም ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም እርሱን እንጅ ሌላን እንዳትግገዙ አዟል፤ ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።

You worship not besides Him except [mere] names you have named them, you and your fathers, for which Allah has sent down no authority. Legislation is not but for Allah . He has commanded that you worship not except Him. That is the correct religion, but most of the people do not know.

12:41
የወህኒ ቤት ጓደኞቼ ሆይ! አንደኛችሁማ ጌታውን (ንጉሡን) ጠጅ ያጠጣል፤ ሌላውማ ይሰቀላል፤ ከራሱም በራሪ (አሞራ) ትበላለች፤ ያ ፍቹን የምትጠይቁት ነገር ተፈጸመ፤ (አላቸው)።

O two companions of prison, as for one of you, he will give drink to his master of wine; but as for the other, he will be crucified, and the birds will eat from his head. The matter has been decreed about which you both inquire."

12:42
ለዚያም ከሁለቱ እርሱ የሚድን መሆኑን ለተጠራጠረው፣ እጌታህ ዘንድ አስታውሰኝ አለው፤ ጌታውንም ከማስታወስ ሴጣን አስረሳው፤ ለጥቂት ዓመታትም በወህኒ ቤቱ ውስጥ ቆዬ።

And he said to the one whom he knew would go free, "Mention me before your master." But Satan made him forget the mention [to] his master, and Joseph remained in prison several years.

12:43
ንጉሡም እኔ ሰባትን የሰቡ ላሞች ሰባት ከሲታዎች ሲበሉዋቸው፣ ሰባትንም ለምለም ዘለላዎች ሌሎችንም ደረቆችን (ሲጠመጠሙባቸው በሕልሜ) አያለሁ፤ እናንተ ታላላቅ ሰዎች ሆይ! ሕልምን የምትፈቱ እንደሆናችሁ ሕልሜን ፍቱልኝ አላቸው።

And [subsequently] the king said, "Indeed, I have seen [in a dream] seven fat cows being eaten by seven [that were] lean, and seven green spikes [of grain] and others [that were] dry. O eminent ones, explain to me my vision, if you should interpret visions."

12:44
፦ የሕልሞች ቅዠቶች ናቸው፤ እኛም የሕልሞችን ፍች ዐዋቂዎች አይደለንም አሉት።

They said, "[It is but] a mixture of false dreams, and we are not learned in the interpretation of dreams."

12:45
ያም ከሁለቱ የዳነውና ከብዙ ጊዜ በኋላ (ዩሱፍን) ያስታወሰው ሰው እኔ ፍቹን እነግራችኋለሁና ላኩኝ አለ፤ (ወደ ዩሱፍ ኼደም)።

But the one who was freed and remembered after a time said, "I will inform you of its interpretation, so send me forth."

12:46
፦ አንተ እውነተኛው ዩሱፍ ሆይ! ሰባትን የሰቡ ላሞች፣ ሰባት ከሲታዎች ላሞች፣ ሲበሉዋቸው፣ ሰባትንም ለምለም ዘለላዎችም ሌሎችን ደረቆች (በነሱ ላይ ሲጠመጠሙባቸው ያየውን ሰው ሕልም ፍች) ተችልን፤ ያውቁ ዘንድ ወደ ሰዎቹ ልመለስ እከጅላለሁና (አለው)።

[He said], "Joseph, O man of truth, explain to us about seven fat cows eaten by seven [that were] lean, and seven green spikes [of grain] and others [that were] dry - that I may return to the people; perhaps they will know [about you]."

12:47
(እርሱም) አለ፦ ሰባትን የተከታተሉ ዓመታት ትዘራላችሁ፤ ያጨዳችሁትንም ሁሉ ከምትበሉት ጥቂት በስተቀር በዘለላው ውስጥ ተዉት።

[Joseph] said, "You will plant for seven years consecutively; and what you harvest leave in its spikes, except a little from which you will eat.

12:48
ከዚያም ከነዚያ በኋላ፣ ካደለባችሁት ጥቂት ሲቀር፣ ለነሱ ያደለባችሁትን ሁሉ የሚበሉ ሰባት የችግሮች ዓመታት ይመጣሉ።

Then will come after that seven difficult [years] which will consume what you saved for them, except a little from which you will store.

12:49
ከዚያም ከነዚያ በኋላ ሰዎቹ በርሱ የሚዘነቡበት፣ በርሱም (ወይንን) የሚጨምቁበት ዓመት ይመጣል።

Then will come after that a year in which the people will be given rain and in which they will press [olives and grapes]."

12:50
ንጉሡም ፦ እርሱን አምጡልኝ አለ፤ መልክተኛውም (ዩሱፍን) በመጣው ጊዜ፣ ወደ ጌታህ ተመለስ፤ የነዚያንም እጆቻቸውን የቆረጡትን ሴቶች ሁኔታ ጠይቀው፤ ጌታዬ ተንኮላቸውን አዋቂ ነውና አለው።

And the king said, "Bring him to me." But when the messenger came to him, [Joseph] said, "Return to your master and ask him what is the case of the women who cut their hands. Indeed, my Lord is Knowing of their plan."

12:51
(ንጉሡም)፦ ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ፣ ነገራችሁ ምንድነው? አላቸው፤ ለአላህ ጥራት ይገባው፤ በርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገር አላወቅንም አሉት፤ የዐዚዝ ሚስት፦ አሁን እውነቱ ተገለጸ፤ እኔ ከነፍሱ አባበልኩት፤ እርሱም ከውነተኞቹ ነው አለች።

Said [the king to the women], "What was your condition when you sought to seduce Joseph?" They said, "Perfect is Allah ! We know about him no evil." The wife of al-'Azeez said, "Now the truth has become evident. It was I who sought to seduce him, and indeed, he is of the truthful.

12:52
(ዩሱፍ) ይህ (1) (ጌታዬ) ሩቅ ሆኖ ሳለ ያልከዳሁት መኾኔን አላህም የከዳተኞችን ተንኮል የማያቃና መሆኑን እንዲያውቅ ነው፤ (አለ)።
(1)ጥራቴን መፈለጌ


That is so al-'Azeez will know that I did not betray him in [his] absence and that Allah does not guide the plan of betrayers.

12:53
ነፍሴንም (ከስሕተት) አላጠራም፤ ነፍስ ሁሉ፣ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፣ ጌታዬ በጣም መሐሪ አዛኝ ነው (አለ)።

And I do not acquit myself. Indeed, the soul is a persistent enjoiner of evil, except those upon which my Lord has mercy. Indeed, my Lord is Forgiving and Merciful."

12:54
ንጉሡም እርሱን አምጡልኝ፤ ለራሴ ግለኛ አደርገዋለሁና አለ፤ ባናገረውም ጊዜ አንተ ዛሬ እኛ ዘንድ ባለሟል ታማኝ ነህ አለው።

And the king said, "Bring him to me; I will appoint him exclusively for myself." And when he spoke to him, he said, "Indeed, you are today established [in position] and trusted."

12:55
በምድር ግምጃ ቤቶች ላይ (ሹም) አድርገኝ፤ እኔ ጠባቂ ዐዋቂ ነኝና አለ።

[Joseph] said, "Appoint me over the storehouses of the land. Indeed, I will be a knowing guardian."

12:56
እንደዚሁም ለዩሱፍ በምድር ላይ ከርሷ በፈለገው ስፍራ የሚሰፍር ሲሆን አስመቸነው፤ በችሮታችን የምንሻውን ሰው እንለያለን፤ የበጎ ሠሪዎችንም ዋጋ አናጠፋም።

And thus We established Joseph in the land to settle therein wherever he willed. We touch with Our mercy whom We will, and We do not allow to be lost the reward of those who do good.

12:57
የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው።

And the reward of the Hereafter is better for those who believed and were fearing Allah .

12:58
የዩሱፍ ወንድሞችም መጡ፤ በርሱም ላይ ገቡ፤ እነሱም እርሱን የሳቱት ሲሆኑ አወቃቸው።

And the brothers of Joseph came [seeking food], and they entered upon him; and he recognized them, but he was to them unknown.

12:59
(ጉዳያቸውን ፈጽሞ) ስንቃቸውንም ባዘጋጀላቸው ጊዜ አለ፦ ከአባታችሁ በኩል የሆነውን ወንድማችሁን አምጡልኝ እኔ ከአስተናጋጆች ሁሉ በላጭ ስሆን፤ ስፍርን የምሞላ መሆኔን አታዩምን?

And when he had furnished them with their supplies, he said, "Bring me a brother of yours from your father. Do not you see that I give full measure and that I am the best of accommodators?

12:60
እርሱንም ባታመጡልኝ፣ እኔ ዘንድ ለናንተ ስፍር የላችሁም፤ አትቀርቡኝምም።

But if you do not bring him to me, no measure will there be [hereafter] for you from me, nor will you approach me."

12:61
፦ ስለርሱ አባቱን በጥብቅ እንጠይቃለን፤ እኛም (ይህን) በእርግጥ ሠሪዎች ነን፣ አሉት።

They said, "We will attempt to dissuade his father from [keeping] him, and indeed, we will do [it]."

12:62
ለአሽከሮቹም ፦ ሸቀጣቸውን ወደ ቤተሰቦቻቸው በተመለሱ ጊዜ ያውቋት ዘንድ በየጓዞቻቸው ውስጥ አድርጉላቸው፤ ሊመለሱ ይከጀላልና አላቸው።

And [Joseph] said to his servants, "Put their merchandise into their saddlebags so they might recognize it when they have gone back to their people that perhaps they will [again] return."

12:63
ወደ አባታቸውም በተመለሱ ጊዜ፦ አባታችን ሆይ! (ወንድማችንን እስከምንወስድ) ስፍር ከኛ ተከልክሏል፤ ስለዚህ ወንድማችንን ከኛ ጋር ላከው፤ ይሰፈርልናልና እኛም ለርሱ ጠባቂዎች ነን አሉ።

So when they returned to their father, they said, "O our father, [further] measure has been denied to us, so send with us our brother [that] we will be given measure. And indeed, we will be his guardians."

12:64
፦ ከአሁን በፊት በወንድሙ ላይ እንዳመንኳችሁ እንጅ በርሱ ላይ አምናችኋለሁን? አላህም በጠባቂነት (ከሁሉ) የበለጠ ነው፤ እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው፤ አላቸው።

He said, "Should I entrust you with him except [under coercion] as I entrusted you with his brother before? But Allah is the best guardian, and He is the most merciful of the merciful."

12:65
ዕቃቸውንም በከፈቱ ጊዜ ሸቀጣቸውን ወደነርሱ ተመልሳ አገኙ፦ አባታችን ሆይ! ምን እንፈልጋለን? ይህቺ ሸቀጣችን ናት፤ ወደ እኛ ተመልሳልናለች፤ (እንረዳባታለን) ለቤተሰቦቻችንም እንሸምታለን፤ ወንድማችንንም እንጠብቃለን፤ የግመልንም ጭነት እንጨምራለን፤ ይህ (በንጉሡ ላይ) ቀላል ስፍር ነው፣ አሉ።

And when they opened their baggage, they found their merchandise returned to them. They said, "O our father, what [more] could we desire? This is our merchandise returned to us. And we will obtain supplies for our family and protect our brother and obtain an increase of a camel's load; that is an easy measurement."

12:66
፦ ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን በእርግጥ የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃል ኪዳን መተማመኛ እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ ጋር ፈሞ አልልከውም አላቸው፤ መተማመኛቸውንም በሰጡት ጊዜ ፦ አላህ በምንለው ሁሉ ላይ ምስክር ነው አላቸው።

[Jacob] said, "Never will I send him with you until you give me a promise by Allah that you will bring him [back] to me, unless you should be surrounded by enemies." And when they had given their promise, he said, " Allah , over what we say, is Witness."

12:67
አለም፦ ልጆቼ ሆይ! ባንድ በር አትግቡ፤ ግን በተለያየ በሮች ግቡ፤፤ ከአላህም (ፍርድ) በምንም አልጠቅማችሁም፤ (አልመልስላችሁም)፤ ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፤ በርሱ ላይ ተመካሁ፤ ተመኪዎችም ሁሉ በርሱ ብቻ ይመኩ።

And he said, "O my sons, do not enter from one gate but enter from different gates; and I cannot avail you against [the decree of] Allah at all. The decision is only for Allah ; upon Him I have relied, and upon Him let those who would rely [indeed] rely."

12:68
አባታቸውም ካዘዛቸው ስፍራ በገቡ ጊዜ ከአላህ (ፍርድ) ምንም ነገር ከነርሱ የሚከለክላቸው አልነበረም፤ ግን በያዕቆብ ነፍስ ውስጥ የነበረች ጉዳይ ናት፤ ፈጸማት፤ እርሱም ስላሳወቅነው የዕውቀት ባለቤት ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።

And when they entered from where their father had ordered them, it did not avail them against Allah at all except [it was] a need within the soul of Jacob, which he satisfied. And indeed, he was a possessor of knowledge because of what We had taught him, but most of the people do not know.

12:69
በዩሱፍ ላይ በገቡ ጊዜም ወንድሙን ወደርሱ አስጠጋው፦ እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ ይሠሩት በነበሩትም ሁሉ አትቆላጭ አለው።

And when they entered upon Joseph, he took his brother to himself; he said, "Indeed, I am your brother, so do not despair over what they used to do [to me]."

12:70
ዕቃቸውንም ባዘጋጀላቸው ጊዜ፤ ዋንጫይቱን (1) በወንድሙ ዕቃ ውስጥ አደረገ፤ ከዚያም፦ እላንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በርግጥ ሌቦች ናችሁ ሲል ጠሪ ተጣራ።
(1) መጠጫና መስፈሪያውን


So when he had furnished them with their supplies, he put the [gold measuring] bowl into the bag of his brother. Then an announcer called out, "O caravan, indeed you are thieves."

12:71
ወደነሱ ዞረውም፦ ምንድን ጠፋችሁ? አሉ።

They said while approaching them, "What is it you are missing?"

12:72
፦ የንጉሡ መስፈሪያ ጠፍቶናል፤ እርሱንም ላመጣ ሰው የግመል ጭነት አለው፤ እኔም በርሱ ተያዥ ነኝ አለ።

They said, "We are missing the measure of the king. And for he who produces it is [the reward of] a camel's load, and I am responsible for it."

12:73
፦ በአላህ እንምላለን በምድር ላይ ለማጥፋት እንዳልመጣን በእርግጥ ዐውቃችኋል፤ ሌቦችም አልነበርንም አሉ።

They said, "By Allah , you have certainly known that we did not come to cause corruption in the land, and we have not been thieves."

12:74
፦ ውሸታሞች ብትሆኑ ቅጣቱ ምንድነው? አሏቸው።

The accusers said, "Then what would be its recompense if you should be liars?"

12:75
ቅጣቱ (በያዕቆብ ሕግ) ዕቃው በጓዙ ውስጥ የተገኘበት ሰው (ራሱ መወሰድ) ነው፤ እርሱም ቅጣቱ ነው እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን፤ አሉ።

[The brothers] said, "Its recompense is that he in whose bag it is found - he [himself] will be its recompense. Thus do we recompense the wrongdoers."

12:76
(ምርመራውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት በዕቃዎቻቸው ጀመረ፤ ከዚያም (ዋንጫይቱን) ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት፤ እንደዚሁ ለዩሱፍ ብልሃትን አስተማርነው፤ አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሡ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባውም ነበር፤ የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን ከዕውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም ዐዋቂ አልለ።

So he began [the search] with their bags before the bag of his brother; then he extracted it from the bag of his brother. Thus did We plan for Joseph. He could not have taken his brother within the religion of the king except that Allah willed. We raise in degrees whom We will, but over every possessor of knowledge is one [more] knowing.

12:77
፦ ቢሰርቅ ከአሁን በፊት የርሱው ወንድም በእርግጥ ሰርቋል አሉ፤ ዩሱፍም (ይህችን ንግግር) በነፍሱ ውስጥ ደበቃት፤ ለነሱም አልገለጣትም፤ (በልቡ)፦ እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው፤ አላህም የምትሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነው አለ።

They said, "If he steals - a brother of his has stolen before." But Joseph kept it within himself and did not reveal it to them. He said, "You are worse in position, and Allah is most knowing of what you describe."

12:78
አንተ የተከበርከው ሆይ! ፦ ለርሱ በእርግጥ ታላቅ ሽማግሌ አባት አለው፤ ስለዚህ በርሱ ስፍራ አንደኛችንን ያዝ፤ እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ እናይሃለንና አሉት።

They said, "O 'Azeez, indeed he has a father [who is] an old man, so take one of us in place of him. Indeed, we see you as a doer of good."

12:79
፦ ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ሌላን ከመያዝ በአላህ እንጠበቃለን፤ እኛ ያን ጊዜ በእርግጥ በዳዮች ነን፤ አለ።

He said, "[I seek] the refuge of Allah [to prevent] that we take except him with whom we found our possession. Indeed, we would then be unjust."

12:80
ከርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ፤ ታላቃቸው አለ፦ አባታችሁ በናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መታመኛ ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የምስርን ምድር አልለይም፤ እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።

So when they had despaired of him, they secluded themselves in private consultation. The eldest of them said, "Do you not know that your father has taken upon you an oath by Allah and [that] before you failed in [your duty to] Joseph? So I will never leave [this] land until my father permits me or Allah decides for me, and He is the best of judges.

12:81
ወደ አባታችሁ፣ ተመለሱ፤ በሉትም ፦ አባታችን ሆይ! ልጅህ ሰረቀ ባወቅነውም ነገር እንጂ አልመሰከርንም፤ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን) ዐዋቂዎች አልነበርንም፤

Return to your father and say, "O our father, indeed your son has stolen, and we did not testify except to what we knew. And we were not witnesses of the unseen,

12:82
ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ፤ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን።

And ask the city in which we were and the caravan in which we came - and indeed, we are truthful,"

12:83
(ያዕቆብ) ፦ አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለናንተ ሸለሙላችሁ፤ (ሠራችሁትም) መልካምም ትዕግሥት (ማድረግ) አለብኝ፤ እነርሱን፣ (ሦስቱንም) የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፤ እነሆ እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና አላቸው።

[Jacob] said, "Rather, your souls have enticed you to something, so patience is most fitting. Perhaps Allah will bring them to me all together. Indeed it is He who is the Knowing, the Wise."

12:84
ከነሱም ላይ ዘወር አለና ፦ በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ! አለ፤ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ፤ እርሱም በትካዜ የተመላ ነው።

And he turned away from them and said, "Oh, my sorrow over Joseph," and his eyes became white from grief, for he was [of that] a suppressor.

12:85
(እነርሱም) ፦ በአላህ እንምላለን፤ ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ፣ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም፤ አሉ።

They said, "By Allah , you will not cease remembering Joseph until you become fatally ill or become of those who perish."

12:86
፦ ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማስሙተው፣ ወደ አላህ ብቻ ነው፤ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ፤ አላቸው።

He said, "I only complain of my suffering and my grief to Allah , and I know from Allah that which you do not know.

12:87
ልጆቼ ሆይ! ኺዱ፤ ከዩሱፍና ከወንድሙም (ወሬ) ተመራመሩ፤ ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ እነሆ ከአላህ እዝነት ከሐዲዎች ሕዝቦች እንጂ፣ ተስፋ አይቆርጥም (አለ)።

O my sons, go and find out about Joseph and his brother and despair not of relief from Allah . Indeed, no one despairs of relief from Allah except the disbelieving people."

12:88
በርሱም ላይ በገቡ ጊዜ አንተ የተከበርከው ሆይ! እኛንም ቤተ ሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን፤ ርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል፤ ስፍርንም ለኛ ሙላልን፤ በኛም ላይ መጽውት አላህ መጽዋቾችን ይመነዳልና አሉት።

So when they entered upon Joseph, they said, "O 'Azeez, adversity has touched us and our family, and we have come with goods poor in quality, but give us full measure and be charitable to us. Indeed, Allah rewards the charitable."

12:89
፦ እናንተ የማታውቁ በነበራችሁ ጊዜ በዩሱፍና በወንድሙ ላይ የሠራችሁትን ግፍ ዐወቃችሁን? አላቸው።

He said, "Do you know what you did with Joseph and his brother when you were ignorant?"

12:90
፦ አንተ በእርግጥ ዩሱፍ ነህን? አሉት፤ እኔ ዩሱፍ ነኝ ይህም ወንድሜ ነው አላህ በኛ ላይ በእርግጥ ለገሰልን፤ እነሆ! የሚጠነቀቅና የሚታገሥ ሰው (አላህ ይክሰዋል)፤ አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና፣ አለ።

They said, "Are you indeed Joseph?" He said "I am Joseph, and this is my brother. Allah has certainly favored us. Indeed, he who fears Allah and is patient, then indeed, Allah does not allow to be lost the reward of those who do good.

12:91
፦ በአላህ እንምላለን፤ አላህ በኛ ላይ በእርግጥ አበለጠህ፤ እኛም በእርግጥ አጥፊዎች ነበርን አሉ።

They said, "By Allah , certainly has Allah preferred you over us, and indeed, we have been sinners."

12:92
፦ ዛሬ በናንተ ላይ ወቀሳ የለባችሁም፤ አላህ ለናንተ ይምራል፤ እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው፣ አላቸው።

He said, "No blame will there be upon you today. Allah will forgive you; and He is the most merciful of the merciful."

12:93
ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ኺዱ፤ በአባቴ ፊትም ጣሉት የሚያይ ሆኖ ይመጣልና፤ ቤተሰቦቻችሁንም ሰብስባችሁ አምጡልኝ፣ (አላቸው)።

Take this, my shirt, and cast it over the face of my father; he will become seeing. And bring me your family, all together."

12:94
ግመል ጫኞቹም (ምስርን) በተለዩ ጊዜ አባታቸው ፦ እኔ የዩሱፍን ሽታ በእርግጥ አገኛለሁ፤ ባታቄሉኝ ኖሮ (ታምኑኝ ነበር) አለ።

And when the caravan departed [from Egypt], their father said, "Indeed, I find the smell of Joseph [and would say that he was alive] if you did not think me weakened in mind."

12:95
፦ በአላህ እንምላለን፤ አንተ በእርግጥ በቀድሞው ስሕተትህ ውስጥ ነህ፤ አሉት።

They said, "By Allah , indeed you are in your [same] old error."

12:96
አብሳሪውም በመጣ ጊዜ፣ (ቀሚሱን) በፊቱ ላይ ጣለው፤ ወዲያውም የሚያይ ሆነ፤ እኔ ለናንተ፦ ከአላህ በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ አላልኳችሁምን? አላቸው።

And when the bearer of good tidings arrived, he cast it over his face, and he returned [once again] seeing. He said, "Did I not tell you that I know from Allah that which you do not know?"

12:97
፦ አባታችን ሆይ ለኀጢአቶቻችን ምሕረትን ለምንልን፤ እኛ ጥፋተኞች ነበርንና አሉ።

They said, "O our father, ask for us forgiveness of our sins; indeed, we have been sinners."

12:98
፦ ወደፊት ለናንተ ጌታዬን ምሕረትን እለምንላችኋለሁ እነሆ! እርሱ መሐሪው አዛኙ ነውና አላቸው።

He said, "I will ask forgiveness for you from my Lord. Indeed, it is He who is the Forgiving, the Merciful."

12:99
በዩሱፍ ላይም በገቡ ጊዜ. ወላጆቹን ወደርሱ አስጠጋቸው፤ በአላህም ፈቃድ ጥብቆች ስትሆኑ ምስርን ግቡ፣ አላቸው።

And when they entered upon Joseph, he took his parents to himself and said, "Enter Egypt, Allah willing, safe [and secure]."

12:100
ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው፤ ለርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት፤ አባቴም ሆይ ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፤ ጌታዬ በእርግጥ እውነት አደረጋት፤ ከወህኒ ቤትም ባወጣኝና ሰይጣንም በኔና በወንድሞቼ መካከል ከአበላሸ በኋላ እናንተን ከገጠር ባመጣችሁ ጊዜ፣ በእርግጥ ለኔ መልካም ዋለልኝ፤ ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው፤ እነሆ እርሱ ዐዋቂው ጥበበኛው ነው፤ አለ።

And he raised his parents upon the throne, and they bowed to him in prostration. And he said, "O my father, this is the explanation of my vision of before. My Lord has made it reality. And He was certainly good to me when He took me out of prison and brought you [here] from bedouin life after Satan had induced [estrangement] between me and my brothers. Indeed, my Lord is Subtle in what He wills. Indeed, it is He who is the Knowing, the Wise.

12:101
ጌታዬ ሆይ! ከንግስና በእርግጥ ሰጠኸኝ፤ ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ፤ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ፤ ሙስሊም ሆኜ ግደለኝ፤ በመልካሞቹም አስጠጋኝ፤ (አለ)።

My Lord, You have given me [something] of sovereignty and taught me of the interpretation of dreams. Creator of the heavens and earth, You are my protector in this world and in the Hereafter. Cause me to die a Muslim and join me with the righteous."

12:102
(ሙሐመድ ሆይ) ይህ ወዳንተ የምናወርደው ሲሆን፤ ከሩቅ ወሬዎች ነው፤ አንተም እነርሱ (በዩሱፍ) የሚመክሩ ሆነው፣ ነገራቸውን በቆረጡ ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም።

That is from the news of the unseen which We reveal, [O Muhammad], to you. And you were not with them when they put together their plan while they conspired.

12:103
አብዛኛዎቹም ሰዎች (ለማመናቸው) ብትጓጓም የሚያምኑ አይደሉም።

And most of the people, although you strive [for it], are not believers.

12:104
በርሱም (በቁርአን) ላይ ምንም ዋጋ አትጠይቃቸውም፤ እርሱ ለአለማት ግሣጼ እንጂ ሌላ አይደለም።

And you do not ask of them for it any payment. It is not except a reminder to the worlds.

12:105
በሰማያትና በምድርም ካለችው ምልክት፣ ብዙይቱ እነሱ ከርሷ ዘንጊዎች ሆነው በርሷ ላይ ያልፋሉ።

And how many a sign within the heavens and earth do they pass over while they, therefrom, are turning away.

12:106
አብዛኞቻቸውም፤ እነሱ አጋሪዎች ሆነው እንጂ በአላህ አያምኑም።

And most of them believe not in Allah except while they associate others with Him.

12:107
ከአላህ ቅጣት ሸፋኝ አደጋ የምትመጣባቸው ወይም ሰዓቲቱ እነሱ የማያውቁ ሲሆኑ በድንገት የምትመጣባቸው መሆንዋን አይፈሩምን?

Then do they feel secure that there will not come to them an overwhelming [aspect] of the punishment of Allah or that the Hour will not come upon them suddenly while they do not perceive?

12:108
፦ ይህች መንገዴ ናት፤ ወደ አላህ እጠራለሁ፤ እኔም የተከተለኝም ሰው በግለጽ ማስረጃ ላይ ነን፤ ጥራትም ለአላህ ይገባው፤ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም በል።

Say, "This is my way; I invite to Allah with insight, I and those who follow me. And exalted is Allah ; and I am not of those who associate others with Him."

12:109
ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደነርሱ ራዕይ የምናወርድላቸው የሆኑን ወንዶችን እንጂ አልላክንም፤ በምድር ላይ አይኼዱምና የነዚያን ከነሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ አይመለከቱምን? የመጨረሻይቱም አገር፣ ለነዚያ ለተጠነቀቁት በእርግጥ የተሻለች ናት፤ አታውቁምን?

you [as messengers] except men to whom We revealed from among the people of cities. So have they not traveled through the earth and observed how was the end of those before them? And the home of the Hereafter is best for those who fear Allah ; then will you not reason?

12:110
መልክተኞቹም ተስፋ በቆረጡና እነርሱ በእርግጥ የተዋሹ መሆናቸውን በተጠራጠሩ ጊዜ እርዳታችን መጣላቸው፤ (እኛ) የምንሻውም ሰው እንዲድን ተደረገ፤ ቅጣታቸንም ከአጋሪዎቹ ሕዝቦች ላይ አይመለሰም።

[They continued] until, when the messengers despaired and were certain that they had been denied, there came to them Our victory, and whoever We willed was saved. And Our punishment cannot be repelled from the people who are criminals.

12:111
በታሪካቸው ውስጥ፣ ለአእምሮ ባለ ቤቶች በእርግጥ መገሠጫ ነበረ፤ (ይህ ቁርአን) የሚቀጣጠፍ ወሬ አይደለም፤ ግን ያንን በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ለነገርም ሁሉ ገላጭ፣ ለሚያምኑ ሕዝቦችም መሪና ችሮታ ነው።

There was certainly in their stories a lesson for those of understanding. Never was the Qur'an a narration invented, but a confirmation of what was before it and a detailed explanation of all things and guidance and mercy for a people who believe.

Copyright 2013, AmharicQuran.com