Amharic Quran
Chapters/Surah

ሱረቱ ሁድ (የሁድ ምዕራፍ)

11:1
አ.ለ.ረ. (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርአን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰከኩ፣ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፤ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው።

Alif, Lam, Ra. [This is] a Book whose verses are perfected and then presented in detail from [one who is] Wise and Acquainted.

11:2
(እንዲህ በላቸው) ፦ አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ እኔ ለናንተ ከርሱ (የተላክሁ) አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ።

[Through a messenger, saying], "Do not worship except Allah . Indeed, I am to you from Him a warner and a bringer of good tidings,"

11:3
ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፤ ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ፤ እስከ ተወሰነም ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋልና፤ የትሩፋትንም ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳውን) ይሰጠዋል፤ ብትሸሹም እኔ በናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።

And [saying], "Seek forgiveness of your Lord and repent to Him, [and] He will let you enjoy a good provision for a specified term and give every doer of favor his favor. But if you turn away, then indeed, I fear for you the punishment of a great Day.

11:4
መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

To Allah is your return, and He is over all things competent."

11:5
ንቁ፣ እነሱ ከርሱ (ከአላህ) ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ፤ ንቁ ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትን የሚገልጹትንም ሁሉ ያውቃል፤ እርሱ በደረቶች ውስ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነውና።

Unquestionably, they the disbelievers turn away their breasts to hide themselves from Him. Unquestionably, [even] when they cover themselves in their clothing, Allah knows what they conceal and what they declare. Indeed, He is Knowing of that within the breasts.

11:6
በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢሆን እንጂ፤ ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል፤ ሁሉም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው።

And there is no creature on earth but that upon Allah is its provision, and He knows its place of dwelling and place of storage. All is in a clear register.

11:7
እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች የፈጠረው ነው፤ ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር፤ የትኛችሁ ሥራው አማረ መሆኑን ይፈትናችሁ ዘንድ (ፈጠራቸው) ፦ እናንተ ከሞት በኋላ በእርግጥ ተቀስቃሳሾች ናችሁ ብትልም እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ ይደለም ይላሉ። (1)
(1) ይህ ቃል ብልሹ በመሆን እንደ ድግምት ነው ይላሉ።


And it is He who created the heavens and the earth in six days - and His Throne had been upon water - that He might test you as to which of you is best in deed. But if you say, "Indeed, you are resurrected after death," those who disbelieve will surely say, "This is not but obvious magic."

11:8
ቅጣቱንም ወደ ተቆጠሩ (ጥቂት) ጊዜያቶች ከነርሱ ብናቆይላቸው (ከመውረድ) የሚከለክለው ምንድነው? ይላሉ፤ ንቁ በሚመጣባቸው ቀን ከነሱ ላይ ተመላሽ አይደለም፤ በርሱ ይሳለቁበት የነበሩትም (ቅጣት) በነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል።

And if We hold back from them the punishment for a limited time, they will surely say, "What detains it?" Unquestionably, on the Day it comes to them, it will not be averted from them, and they will be enveloped by what they used to ridicule.

11:9
ሰውንም ከኛ ችሮታን ብናቀምሰው ከዚያም ከርሱ ብንወስዳት፣ እርሱ በእርግጥ ተስፋ ቆራጭ ክሕደተ ብርቱ ነው።

And if We give man a taste of mercy from Us and then We withdraw it from him, indeed, he is despairing and ungrateful.

11:10
ካገኘችውም ችግር በኋላ ጠጋዎችን ብናቀምሰው ችግሮች ከኔ ላይ ተወገዱ ይላል፤ (አያመሰግንም)እርሱ ተደሳች ጉረኛ ነውና።

But if We give him a taste of favor after hardship has touched him, he will surely say, "Bad times have left me." Indeed, he is exultant and boastful -

11:11
ግን እነዚያ የታገሡ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ እነዚያ ለነሱ ታላቅ ምንዳ አላቸው።

Except for those who are patient and do righteous deeds; those will have forgiveness and great reward.

11:12
በርሱ ላይ የገንዘብ ድልብ ለምን አልተወረደም ወይም ከርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም ማለታቸውንም በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በርሱም ልብህ ጠባብ ሊኾን ይፈራልሃል፤ አንተ አስፈራሪብቻ ነህ፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው።

Then would you possibly leave [out] some of what is revealed to you, or is your breast constrained by it because they say, "Why has there not been sent down to him a treasure or come with him an angel?" But you are only a warner. And Allah is Disposer of all things.

11:13
ግን እነዚያ የታገሡ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ እነዚያ ለነሱ ታላቅ ምንዳ አላቸው።

Or do they say, "He invented it"? Say, "Then bring ten surahs like it that have been invented and call upon [for assistance] whomever you can besides Allah , if you should be truthful."

11:14
በርሱ ላይ የገንዘብ ድልብ ለምን አልተወረደም ወይም ከርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም ማለታቸውንም በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በርሱም ልብህ ጠባብ ሊኾን ይፈራልሃል፤ አንተ አስፈራሪብቻ ነህ፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው።

And if they do not respond to you - then know that the Qur'an was revealed with the knowledge of Allah and that there is no deity except Him. Then, would you [not] be Muslims?

11:15
ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) በርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን፤ እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎደልባቸውም።

Whoever desires the life of this world and its adornments - We fully repay them for their deeds therein, and they therein will not be deprived.

11:16
እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፤ የሠሩትም ሥራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ፤ (በቅርቢቱ ዓለም) ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው።

Those are the ones for whom there is not in the Hereafter but the Fire. And lost is what they did therein, and worthless is what they used to do.

11:17
ከጌታው ከአስረጅ ጋር የሆነ ሰው ከርሱም (ከአላህ) የሆነ መስካሪ የሚከተለው ከርሱ በፊትም የሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲሆን (የመሰከረለት) የቅርቢቱን ሕይወት እንደሚሻው ሰውነውን? እነዚያ በርሱ (በቁርአን) ያምናሉ፤ ከአሕዛቦቹም በርሱ የሚክድ ሰው እሳት መመለሻው ናት፤ ከርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትኹን፤ እርሱ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም።

So is one who [stands] upon a clear evidence from his Lord [like the aforementioned]? And a witness from Him follows it, and before it was the Scripture of Moses to lead and as mercy. Those [believers in the former revelations] believe in the Qur'an. But whoever disbelieves in it from the [various] factions - the Fire is his promised destination. So be not in doubt about it. Indeed, it is the truth from your Lord, but most of the people do not believe.

11:18
በአላህ ላይ እብለትን ከሚቀጣጥፍም ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ በጌታቸው ላይ ይቀረባሉ፤ መስካሪዎቹም፦ እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹ ናቸው ይላሉ፤ ንቁ የአላህ ርግማን በበዳዮች ላይ ይኹን።

And who is more unjust than he who invents a lie about Allah ? Those will be presented before their Lord, and the witnesses will say, "These are the ones who lied against their Lord." Unquestionably, the curse of Allah is upon the wrongdoers

11:19
(እነሱም) እነዚያ ከላህ መንግድ የሚከለከሉ መጥመሟንም የሚፈልጓት ናቸው፤ እነሱም መጨረሻይቱን ዓለም እነሱ ከሐዲዎች ናቸው።

Who averted [people] from the way of Allah and sought to make it [seem] deviant while they, concerning the Hereafter, were disbelievers.

11:20
እነዚያ በምድር ውስጥ (ከአላህ) የሚያመልጡ አልነበሩም፤ ከአላህም ሌላ ለነሱ ረዳቶች አልነበሯቸውም፤ ለነሱ ቅጣቱ ይደራረብላቸዋል፤ (እውነትን) መስማትን የሚችሉ አልነበሩም፣ የሚያዩም አልነበሩም።

Those were not causing failure [to Allah ] on earth, nor did they have besides Allah any protectors. For them the punishment will be multiplied. They were not able to hear, nor did they see.

11:21
እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ከነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር የጠፋቸው ናቸው።

Those are the ones who will have lost themselves, and lost from them is what they used to invent.

11:22
እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም በጣም ከሳሪዎቹ እነሱ መሆናቸው ጥርጥር የለውም።

Assuredly, it is they in the Hereafter who will be the greatest losers.

11:23
እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸውም የተዋረዱት፣ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፤ እነሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።

Indeed, they who have believed and done righteous deeds and humbled themselves to their Lord - those are the companions of Paradise; they will abide eternally therein.

11:24
የሁለቱ ክፍሎች (1) ምሳሌ እንደ ዕውርና እንደ ደንቆሮ እንደሚያይና እንደሚሰማም ብጤ ነው፤ በምሳሌ ይተካከላሉን? አትገሠጹምን?
(1) የከሐዲዎችና የምዕመናን


The example of the two parties is like the blind and deaf, and the seeing and hearing. Are they equal in comparison? Then, will you not remember?

11:25
ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክን፤ (አላቸውም)፦ እኔ ለናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ።

And We had certainly sent Noah to his people, [saying], " Indeed, I am to you a clear warner

11:26
አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ እኔ በናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።

That you not worship except Allah . Indeed, I fear for you the punishment of a painful day."

11:27
ከሕዝቦቹም እነዚያ የካዱት መሪዎቹ ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም፤ እነዚያም እነሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም፤ ለናንተም በ እኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም፤ ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን አሉ።

So the eminent among those who disbelieved from his people said, " We do not see you but as a man like ourselves, and we do not see you followed except by those who are the lowest of us [and] at first suggestion. And we do not see in you over us any merit; rather, we think you are liars."

11:28
፦ ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ብሆን ከርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ (ነቢይነት) ቢሰጠኝና፣ በናንተ ላይ ብትደበቅባችሁ፣ እናንተ ለርሷ ጠይዎች ስትሆኑ እርሷን (በመቀበል) እናስገድዳችኋለን? አላቸው።

He said, "O my people have you considered: if I should be upon clear evidence from my Lord while He has given me mercy from Himself but it has been made unapparent to you, should we force it upon you while you are averse to it?

11:29
ሕዝቦቼም ሆይ! በርሱ (በተላክሁበት ማድረስ) ላይ ገንዘብን አልጠየቃችሁም፤ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፤ እኔም እነዚያን ያመኑትን አባራሪ አይደለሁም፤ እነርሱ ጌታቸውን የሚገናኙ ናቸውና፤ ግን እኔም የምትሳሳቱ ሕዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ።

And O my people, I ask not of you for it any wealth. My reward is not but from Allah . And I am not one to drive away those who have believed. Indeed, they will meet their Lord, but I see that you are a people behaving ignorantly.

11:30
ሕዝቦቼም ሆይ ባባርራቸው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማን ነው? አትገሠጹምን?

And O my people, who would protect me from Allah if I drove them away? Then will you not be reminded?

11:31
ለእናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አልሉ፣ ሩቅንም ዐውቃለሁ አልላችሁም፤ ለነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው፣ አላህ ደግ ነገርን (እምነትን) አይሰጣቸውም አልልም፤ አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር ዐዋቂ ነው፤ እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና (አላቸው)።

And I do not tell you that I have the depositories [containing the provision] of Allah or that I know the unseen, nor do I tell you that I am an angel, nor do I say of those upon whom your eyes look down that Allah will never grant them any good. Allah is most knowing of what is within their souls. Indeed, I would then be among the wrongdoers."

11:32
፦ ኑሕ ሆይ በእርግጥ ተከራከርከን፤ እኛን መከራከርህንም አበዛኸው፣ ከእውነተኞቹም እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው አሉ።

They said, "O Noah, you have disputed us and been frequent in dispute of us. So bring us what you threaten us, if you should be of the truthful."

11:33
፦ እርሱን የሚያመጣባችሁ የሻ እንደሆነ አላህ ብቻ ነው፤ እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም አላቸው።

He said, " Allah will only bring it to you if He wills, and you will not cause [Him] failure.

11:34
ለናንተም ልመክራችሁ ብሻ አላህ ሊያጠማችሁ ሽቶ እንደ ሆነ ምክሬ አይጠቅማችሁም፤ እርሱ ጌታችሁ ነው፤ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፤ (አላቸው)።

And my advice will not benefit you - although I wished to advise you - If Allah should intend to put you in error. He is your Lord, and to Him you will be returned."

11:35
ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? ብቀጥፈው ኃጢአቴ (ቅጣቱ) በኔ ላይ ነው፤ እኔም ከምታጠፉት (ጥፋት) ንጹሕ ነኝ በላቸው።

Or do they say [about Prophet Muhammad], "He invented it"? Say, "If I have invented it, then upon me is [the consequence of] my crime; but I am innocent of what [crimes] you commit."

11:36
ወደ ኑሕም እነሆ ፦ ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር (ወደፊት) አያምኑም፤ ይሠሩትም በነበሩት (ክሕደት) አትዘን ማለት ተወረደ።

And it was revealed to Noah that, "No one will believe from your people except those who have already believed, so do not be distressed by what they have been doing.

11:37
(አላህም) በጥበቃችንና በትእዛዛችንም ሆነህ መርከቢቱን ሥራ፤ በነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ እነሱ በእርግጥ የሚሰጠሙ ናቸውና (አለው)።

And construct the ship under Our observation and Our inspiration and do not address Me concerning those who have wronged; indeed, they are [to be] drowned."

11:38
ከወገኖቹም መሪዎቹ፣ በርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር ከርሱ እየተሳለቁ፣ መርከቢቱን ይሠራል። ከኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን ከናንተ እንሳለቅባችኋለን አላቸው።

And he constructed the ship, and whenever an assembly of the eminent of his people passed by him, they ridiculed him. He said, "If you ridicule us, then we will ridicule you just as you ridicule.

11:39
የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን ሰው (ማን እንደ ሆነ) ወደፊት ታውቃላችሁ (አላቸው)።

And you are going to know who will get a punishment that will disgrace him [on earth] and upon whom will descend an enduring punishment [in the Hereafter]."

11:40
ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ፣ በርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት፣ (ወንድና ሴት) ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን አልነው፤ ከርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም።

[So it was], until when Our command came and the oven overflowed, We said, "Load upon the ship of each [creature] two mates and your family, except those about whom the word has preceded, and [include] whoever has believed." But none had believed with him, except a few.

11:41
፦መኼዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው፣ እያላችሁም በውስጧ ተሳፈሩ፤ ጌታዬ መሐሪ አዛኝ ነውና አላቸው።

And [Noah] said, "Embark therein; in the name of Allah is its course and its anchorage. Indeed, my Lord is Forgiving and Merciful."

11:42
እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በነርሱ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትሆን፣ (በአላህ ስም ተቀመጡባት)፤ ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ፦ ልጄ ሆይ ከኛ ጋር ተሳፈር፣ ከከሐዲዎቹም አትሁን ሲል ጠራው።

And it sailed with them through waves like mountains, and Noah called to his son who was apart [from them], "O my son, come aboard with us and be not with the disbelievers."

11:43
(ልጁም) ፦ ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ አለ፤ (አባቱም) ፦ ዛሬ ከአላህ ት እዛዝ ምንም ጠባቂ የለም፤ (እርሱ) ያዘነለት ካልሆነ በቀር አለው፤ ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ፤ ከሰጣሚዎቹም ሆነ።

[But] he said, "I will take refuge on a mountain to protect me from the water." [Noah] said, "There is no protector today from the decree of Allah , except for whom He gives mercy." And the waves came between them, and he was among the drowned

11:44
ተባለም ፦ ምድር ሆይ ውሃሽን ዋጪ፤ ሰማይም ሆይ (ዝናምሽን) ያዢ፤ ውሃውም ሠረገ፤ ቅጣቱም ተፈጸመ፤ ጁዲይ በሚባልም ተራራ ላይ (መርከቢቱ) ተደላደለች፤ ለከሐዲዎችም ሰዎች ጥፋት ተገባቸው (ጠፉ) ተባለ።

And it was said, "O earth, swallow your water, and O sky, withhold [your rain]." And the water subsided, and the matter was accomplished, and the ship came to rest on the [mountain of] Judiyy. And it was said, "Away with the wrongdoing people."

11:45
ኑሕም ጌታውን ጠራ፤ አለም ፦ ጌታዬ ሆይ ልጄ ከቤተሰቤ ነው፤ ኪዳንህም እውነት ነው፤ አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነህ።

And Noah called to his Lord and said, "My Lord, indeed my son is of my family; and indeed, Your promise is true; and You are the most just of judges!"

11:46
(አላህም) ኑሕ ሆይ እርሱ ከቤተ ሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱ ሰዎች እንዳትሆን እገሥጽሃለሁ አለ።

He said, "O Noah, indeed he is not of your family; indeed, he is [one whose] work was other than righteous, so ask Me not for that about which you have no knowledge. Indeed, I advise you, lest you be among the ignorant."

11:47
፦ ጌታዬ ሆይ በርሱ ለኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ፤ ለኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎች እሆናለሁ አለ።

[Noah] said, "My Lord, I seek refuge in You from asking that of which I have no knowledge. And unless You forgive me and have mercy upon me, I will be among the losers."

11:48
፦ ኑሕ ሆይ ከኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች (ትውልድ) ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ፤ (ከነሱው ዘሮች የሆኑ) ሕዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን፤ ከዚያም ከኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይነካቸዋል ተባለ።

It was said, "O Noah, disembark in security from Us and blessings upon you and upon nations [descending] from those with you. But other nations [of them] We will grant enjoyment; then there will touch them from Us a painful punishment."

11:49
ይህቺ ከሩቅ ወሬዎች ናት፤ ወደ አንተ እናወርዳታለን፤ አንተም ሕዝቦችህም ከዚህ በፊት የምታውቋት አልነበራችሁም፤ ታገሥም፤ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ናትና።

That is from the news of the unseen which We reveal to you, [O Muhammad]. You knew it not, neither you nor your people, before this. So be patient; indeed, the [best] outcome is for the righteous .

11:50
ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን (ላክን) አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፤ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።

And to 'Aad [We sent] their brother Hud. He said, "O my people, worship Allah ; you have no deity other than Him. You are not but inventors [of falsehood].

11:51
ሕዝቦቼ ሆይ በርሱ (በማድረሴ) ላይ፣ ምንዳን አልጠይቃችሁም፤ ምንዳዬ በዚያ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፤ አታውቁምን?

O my people, I do not ask you for it any reward. My reward is only from the one who created me. Then will you not reason?

11:52
ሕዝቦቼም ሆይ ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፤ ከዚያም ወደርሱ ተጸጸቱ፤ ዝናምን በናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና፤ ወደ ኀይላችሁም ኀይልን ይጨምርላችኋል፤ አመጠኞችም ሆናችሁ አትሽሹ።

And O my people, ask forgiveness of your Lord and then repent to Him. He will send [rain from] the sky upon you in showers and increase you in strength [added] to your strength. And do not turn away, [being] criminals."

11:53
አሉ፦ ሁድ ሆይ በአስረጅ አልመጣህልንም፤ እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም፤ እኛም ለአንተ አማኞች አይደለንም።

They said, "O Hud, you have not brought us clear evidence, and we are not ones to leave our gods on your say-so. Nor are we believers in you.

11:54
ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር (በዕብደት) ለክፈውሃል እንጂ ሌላን አንልም (አሉ)፤ እኔ አላህን አስመሰክራለሁ፤ ከምታጋሩትም፣ እኔ ንጹሕ መሆኔን መስክሩ አላቸው።

We only say that some of our gods have possessed you with evil." He said, "Indeed, I call Allah to witness, and witness [yourselves] that I am free from whatever you associate with Allah

11:55
ከርሱ ሌላ (አማልክትን ከምታጋሩት ንጹሕ ነኝ)፤ ሁላችሁም ሆናችሁ፣ ተንኮልን ሥሩብኝ፤ ከዚያም አታቆዩኝ፤

Other than Him. So plot against me all together; then do not give me respite.

11:56
እኔ በጌታዬና በጌታችሁ በአላህ ላይ ተጠጋሁ፤ በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም እርሱ አናትዋን የያዛት ብትሆን እንጂ፤ ጌታዬ (ቃሉም ሥራውም) በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነው፣ (አላቸው)።

Indeed, I have relied upon Allah , my Lord and your Lord. There is no creature but that He holds its forelock. Indeed, my Lord is on a path [that is] straight."

11:57
ብትዞሩም፣ በርሱ ወደናንተ የተላክሁበትን ነገር በእርግጥ አድርሼላችኋለሁ፤ ጌታዬም፣ ሌላችሁን ህዝብ ይተካል፤ ምንም አትጎዱትምም፤ ጌታዬ በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና (አላቸው)።

But if they turn away, [say], "I have already conveyed that with which I was sent to you. My Lord will give succession to a people other than you, and you will not harm Him at all. Indeed my Lord is, over all things, Guardian."

11:58
ትእዛዛችንም በመጣ ጊዜ፣ ሁድንና እነዚያን ከሱ ጋር ያመኑትን፣ ከኛ በሆነው ችሮታ አዳን፤ ከብርቱ ቅጣትም አዳናቸው።

And when Our command came, We saved Hud and those who believed with him, by mercy from Us; and We saved them from a harsh punishment.

11:59
ይህች (ነገድ) ዓድ ናት፤ በጌታቸው ታምራት ካዱ፤ መልክተኞቹንም አምመጡ፤ የኅያል ሞገደኛን ሁሉ ትእዛዝም ተከተሉ።

And that was 'Aad, who rejected the signs of their Lord and disobeyed His messengers and followed the order of every obstinate tyrant.

11:60
በዚች በቅርቢቱ ዓለምም ርግማን እንዲከተላቸው ተደረጉ፤ በትንሣኤም ቀን (እንደዚሁ)፤ ንቁ፣ ዓዶች ጌታቸውን ካዱ፤ ንቁ፣ የሁድ ሕዝቦች ለሆኑት ዓዶች፣ (ከእዝነት) መራቅ ይገባቸው።

And they were [therefore] followed in this world with a curse and [as well] on the Day of Resurrection. Unquestionably, 'Aad denied their Lord; then away with 'Aad, the people of Hud.

11:61
ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን)፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም፤ እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ፤ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ፤ ምሕረቱንም ለምኑት፤ ከዚህም ወደርሱ ተመለሱ፤ ጌታዬ ቅርብ (ለለመነው) ተቀባይ ነውና አላቸው።

And to Thamud [We sent] their brother Salih. He said, "O my people, worship Allah ; you have no deity other than Him. He has produced you from the earth and settled you in it, so ask forgiveness of Him and then repent to Him. Indeed, my Lord is near and responsive."

11:62
፦ ሷሊህ ሆይ ከዚህ በፊት በኛ ውስጥ (መሪ ልትሆን) በእርግጥ የምትከጅል ነበርክ፤ አባቶቻችን የሚግገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን? እኛም ወደርሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በኾነ መጠራጠር ውስጥ ነን አሉ።

They said, "O Salih, you were among us a man of promise before this. Do you forbid us to worship what our fathers worshipped? And indeed we are, about that to which you invite us, in disquieting doubt."

11:63
፦ ሕዝቦቼ ሆይ ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ብሆን፣ ከርሱም የሆነን ችሮታ (ነቢይነት) ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማነው? ከማሳሳትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም አላቸው።

He said, "O my people, have you considered: if I should be upon clear evidence from my Lord and He has given me mercy from Himself, who would protect me from Allah if I disobeyed Him? So you would not increase me except in loss.

11:64
ሕዝቦቼም ሆይ ይህቺ ለናንተ ታምር ስትኾን የአላህ ግመል ናት፤ ተውዋትም፤ በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ በክፉም አትንኳት፤ ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና (አላቸው)።

And O my people, this is the she-camel of Allah - [she is] to you a sign. So let her feed upon Allah 's earth and do not touch her with harm, or you will be taken by an impending punishment."

11:65
ወግተው ገደሏትም፤ (ሷሊህ) በአገራችሁም ሦስትን ቀናት (ብቻ) ተጠቀሙ ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው አላቸው።

But they hamstrung her, so he said, "Enjoy yourselves in your homes for three days. That is a promise not to be denied."

11:66
ትእዛዛችንም በመጣ ጊዜ፣ ሷሊህንና እነዚያን ከሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳን፤ ከዚያም ቀን ውርደት (አዳንናቸው)፤ ጌታህ እርሱ ብርቱው አሸናፊው ነውና።

So when Our command came, We saved Salih and those who believed with him, by mercy from Us, and [saved them] from the disgrace of that day. Indeed, it is your Lord who is the Powerful, the Exalted in Might.

11:67
እነዚያንም የበደሉትን ጩኸት ያዛቸው፤ በቤቶቻቸውም ውስጥ፣ የተንበረከኩ ሆነው ሞተው አነጉ።

And the shriek seized those who had wronged, and they became within their homes [corpses] fallen prone

11:68
በሷ ውስጥ እንዳልኖሩባት ኾኑ፤ ንቁ፣ ሠሙዶች፣ ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ፤ ንቁ፤ ለሠሙዶች፣ (ከአላህ እዝነት) መራቅ ተገባቸው።

As if they had never prospered therein. Unquestionably, Thamud denied their Lord; then, away with Thamud.

11:69
መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በ(ልጅ) ብስራት በእርግጥ መጡት፤ ሰላም አሉት፤ ሰላም አላቸው፤ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፤

And certainly did Our messengers come to Abraham with good tidings; they said, "Peace." He said, "Peace," and did not delay in bringing [them] a roasted calf.

11:70
እጆቻቸውም ወደርሱ የማይደርሱ መሆናቸውን ባየ ጊዜ፣ ሸሻቸው፤ ከነሱም ፍርሃት ተሰማው፤ ፦ አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና አሉት።

But when he saw their hands not reaching for it, he distrusted them and felt from them apprehension. They said, "Fear not. We have been sent to the people of Lot."

11:71
ሚስቱም የቆመች ስትሆን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፤ በኢስሐቅም አበሰርናት፤ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)።

And his Wife was standing, and she smiled. Then We gave her good tidings of Isaac and after Isaac, Jacob.

11:72
(እርሷም) ዋልኝ! እኔ አሮጊት፣ ይህም ባሌ ሽማግሌ ኾኖ ሳለ እወልዳለሁን? ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው አለች፤

She said, "Woe to me! Shall I give birth while I am an old woman and this, my husband, is an old man? Indeed, this is an amazing thing!"

11:73
፦ ከአላህ ትእዛዝ ትደነቂያለሽን? የአልህ ችሮታና በረከቶቹ በናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን፣ እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና አሉ።

They said, "Are you amazed at the decree of Allah ? May the mercy of Allah and His blessings be upon you, people of the house. Indeed, He is Praiseworthy and Honorable."

11:74
ኢብራሂም፣ ፍራቻው በኼደለትና ብስራት በመጣችለትም ጊዜ በሉጥ ሕዝቦች (ነገር) ይከራከረን ጀመር።

And when the fright had left Abraham and the good tidings had reached him, he began to argue with Us concerning the people of Lot.

11:75
ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ፣ አልቃሻ፣ መላሳ ነውና።

Indeed, Abraham was forbearing, grieving and [frequently] returning [to Allah ].

11:76
፦ ኢብራሂም ሆይ ከዚህ (ክርክር) ተው፤ እነሆ፣ የጌታህ ትእዛዝ በእርግጥ መጥቷል፤ እነሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው፣ (አሉት)።

[The angels said], "O Abraham, give up this [plea]. Indeed, the command of your Lord has come, and indeed, there will reach them a punishment that cannot be repelled."

11:77
መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ፣ በነሱ (ምክንያት) አዘነ፤ ልቡም ተጨነቀ፤ ይህ ብርቱ ቀን ነውም፣ አለ።

And when Our messengers, [the angels], came to Lot, he was anguished for them and felt for them great discomfort and said, "This is a trying day."

11:78
ሕዝቦቹም ወደርሱ እየተጣደፉ መጡት፤ ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር፤ ፦ ሕዝቦቼ ሆይ እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው፤ እነሱ ለናንተ ይልቅ በጣም የጠዱ ናቸው፤ (አግቧቸው)፤ አላህንም ፍሩ፤ በእንግዶቼም፣ አታሳፍሩኝ፤ ከናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለምን? አላቸው።

And his people came hastening to him, and before [this] they had been doing evil deeds. He said, "O my people, these are my daughters; they are purer for you. So fear Allah and do not disgrace me concerning my guests. Is there not among you a man of reason?"

11:79
፦ ከሴቶች ልጆችህ ለኛ ምንም ጉዳይ የለንም፤ አንተም የምንሻውን በርግጥ ታውቃለህ አሉት።

They said, "You have already known that we have not concerning your daughters any claim, and indeed, you know what we want."

11:80
፦ በናንተ ላይ ለኔ ኅይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር) አላቸው።

He said, "If only I had against you some power or could take refuge in a strong support."

11:81
ሉጥ ሆይ እኛ የጌታህ ምልክተኞች ነን፤ (ሕዝቦችህ) ወደ አንተ (በክፉ) አይደርሱብህም፤ ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ኺድ፤ ከናንተም አንድም (ወደ ኋላው) አይገላመጥ፤ ሚስትህ ብቻ ስትቀር፤ እነሆ እርሷን የሚያገኛቸው ስቃይ ያገናታልና፤ ቀጥሯቸው እንጋቱ ላይ ነው፤ ንጋቱ ቅርብ አይደለምን? አሉት።

The angels said, "O Lot, indeed we are messengers of your Lord; [therefore], they will never reach you. So set out with your family during a portion of the night and let not any among you look back - except your wife; indeed, she will be struck by that which strikes them. Indeed, their appointment is [for] the morning. Is not the morning near?"

11:82
ትእዛዛችንም በመጣ ጊዜ (ከተማይቱን) ላያዋን ከታችዋ አደረግን፤ (ገለበጥናት)፤ ተከታታይም የሆነ የሸክላ ድንጊያ በርሷ ላይ አዘነምን።

So when Our command came, We made the highest part [of the city] its lowest and rained upon them stones of layered hard clay, [which were]

11:83
ከጌታህ ዘንድ፣ ምልክት የተደረገባት ስትሆን (አዘነምናት) እርሷም ከበደለኞች ሩቅ አይደለችም።

Marked from your Lord. And Allah 's punishment is not from the wrongdoers [very] far.

11:84
ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ (ላክን)፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፤ ስፍርንና ሚዛንንም አታጉድሉ፤ እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ፤ እኔም በናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።

And to Madyan [We sent] their brother Shu'ayb. He said, "O my people, worship Allah ; you have no deity other than Him. And do not decrease from the measure and the scale. Indeed, I see you in prosperity, but indeed, I fear for you the punishment of an all-encompassing Day.

11:85
ሕዝቦቼም ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ምሉ፤ ሰዎችንም አንዳቾቻቸውን አታጉድሉባቸው፤ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ።

And O my people, give full measure and weight in justice and do not deprive the people of their due and do not commit abuse on the earth, spreading corruption.

11:86
አላህ ያስቀረላችሁ (1) ለናንተ የተሻለ ነው፤ ምእመናን እንደሆናችሁ፣ (አላህ በሰጣችሁ ውደዱ)፣ እኔም (መካሪ እንጅ) በናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።
(1)ስፍርንና ሚዛንን ሞልታችሁ የተረፈው ሲሳይ


What remains [lawful] from Allah is best for you, if you would be believers. But I am not a guardian over you."

11:87
፦ ሹዐብይ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚግገዙትን ጣዖታት እንድንተው፣ ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መስራትን፣ (እንድንተው) ታዝሃለችን? አንተ በእርግጥ ታጋሹ ቅኑ (1) አንተ ነህና አሉት።
(1) መቀጣጠባቸው ነው።


They said, "O Shu'ayb, does your prayer command you that we should leave what our fathers worship or not do with our wealth what we please? Indeed, you are the forbearing, the discerning!"

11:88
፦ ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ፤ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ብሆንና ከርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ፣ (በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን?) ከርሱ ወደ ከለልኳችሁም ነገር ልለያችሁ (1) አልሻም፤ በተቻለኝ ያክል ማበጀትን እንጂ አልሻም፤ (ለደግ ሥራ) መገጠሜም በአላህ እንጂ በሌላ አይደለም፤ በርሱ ላይ ተመካሁ፤ ወደርሱም እመለሳለሁ፤ አላቸው።
(1) እናንተን ከልክየ እኔ ልሠራው


He said, "O my people, have you considered: if I am upon clear evidence from my Lord and He has provided me with a good provision from Him... ? And I do not intend to differ from you in that which I have forbidden you; I only intend reform as much as I am able. And my success is not but through Allah . Upon him I have relied, and to Him I return.

11:89
ወገኖቼም ሆይ! እኔን መከራከራችሁ፣ የኑሕን ሕዝቦች፣ ወይም የሁድን ሕዝቦች፣ ወይም የሷሊህን ሕዝቦች ያገኛቸው (ቅጣት) ብጤ፣ እንዲያገኛችሁ አይገፋፋችሁ፤ የሉጥም ሕዝቦች ከናንተ ሩቅ አይደሉም።

And O my people, let not [your] dissension from me cause you to be struck by that similar to what struck the people of Noah or the people of Hud or the people of Salih. And the people of Lot are not from you far away.

11:90
ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፤ ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ፤ ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነውና (አላቸው)።

And ask forgiveness of your Lord and then repent to Him. Indeed, my Lord is Merciful and Affectionate."

11:91
፦ ሹዐይብ ሆይ! ከምትለው ነገር ብዙውን አናውቀውም፤ እኛም አንተን በኛ ውስጥ ደካማ ሆነህ እናይሃለን፤ ጎሶችህም ባልኖሩ ኖሮ፣ በወገርንህ ነበር፤ አንተም በኛ ላይ የተከበርህ አይደለህም አሉት።

They said, "O Shu'ayb, we do not understand much of what you say, and indeed, we consider you among us as weak. And if not for your family, we would have stoned you [to death]; and you are not to us one respected."

11:92
ሕዝቦቼ ሆይ! ጎሶቼ በናንተ ላይ ከአላህ ይልቅላህን) ከኋላችሁ ወደ ጀርባ አድርጋችሁም ያዛችሁት፤ ጌታዬ በምትሠሩት ሁሉ ከባቢ ነው አላቸው።

He said, "O my people, is my family more respected for power by you than Allah ? But you put Him behind your backs [in neglect]. Indeed, my Lord is encompassing of what you do.

11:93
ሕዝቦቼም ሆይ! በችሎታችሁ ልክ ሥሩ፤ እኔ ሠሪ ነኝና፤ የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትና፣ እርሱ ውሸታም የኾነው ማን እንደሆነ ወደፊት ታውቃላችሁ፤ ጠብቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ተጠባባቂ ነኝና (አላቸው)።

And O my people, work according to your position; indeed, I am working. You are going to know to whom will come a punishment that will disgrace him and who is a liar. So watch; indeed, I am with you a watcher, [awaiting the outcome]."

11:94
ትእዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሹዐብይንና እነዚያን ከርሱ ጋር ያመኑትን ከኛ በሆነው ችሮታ አዳን፤ እነዚያን የበደሉትንም (የጅብሪል) ጩኸት ያዘቻቸው፤ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ።

And when Our command came, We saved Shu'ayb and those who believed with him, by mercy from Us. And the shriek seized those who had wronged, and they became within their homes [corpses] fallen prone

11:95
በርሷ ውስጥ እንዳልነበሩ ሆኑ፤ ንቁ፤ ሠሙድ (ከአላህ እዝነት) እንደ ራቀች መድየንም ትራቅ።

As if they had never prospered therein. Then, away with Madyan as Thamud was taken away.

11:96
ሙሳንም በታምራታችንና በግልጽ ብርሃን በእርግጥ ላክነው።

And We did certainly send Moses with Our signs and a clear authority

11:97
ወደ ፈርዖንና ወደ ሰዎቹ (ላክነው)፤ የፈርዖንንም ነገር (ሕዝቦቹ) ተከተሉ፤ የፈርዖን ነገርም ቀጥተኛ አልነበረም።

To Pharaoh and his establishment, but they followed the command of Pharaoh, and the command of Pharaoh was not [at all] discerning.

11:98
በትንሣኤ ቀን ሕዝቦቹን ይቀድማል፤ ወደ እሳትም ያወርዳቸዋል፤ የሚገቡትም አገባብ ምንኛ ከፋ!

He will precede his people on the Day of Resurrection and lead them into the Fire; and wretched is the place to which they are led.

11:99
በዚችም (በቅርቢቱ ዓለም) እርግማንን አስከተልናቸው፤ በትንሣኤም ቀን (እንደዚሁ) የተሰጡት ስጦታ ምንኛ ከፋ!

And they were followed in this [world] with a curse and on the Day of Resurrection. And wretched is the gift which is given.

11:100
ይህ (የተነገረው) ከከተሞቹ ወሬዎች ነው፤ ባንተ ላይ እንተርከዋለን፤ ከርሷ ፋናው የቀረና ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ አልለ።

That is from the news of the cities, which We relate to you; of them, some are [still] standing and some are [as] a harvest [mowed down].

11:101
እኛም አልበደልናቸውም፤ ግን ነፍሶቻቸውን በደሉ፤ የአላህም ትእዛዝ በመጣ ጊዜ፣ እነዚያ ከአላህ ሌላ የሚግገዙዋቸው አማልክቶቻቸው በምንም አላዳኑዋቸውም፤ ከማክሰርም በቀር ምንም አልጨመሩላቸውም።

And We did not wrong them, but they wronged themselves. And they were not availed at all by their gods which they invoked other than Allah when there came the command of your Lord. And they did not increase them in other than ruin.

11:102
የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው፤ ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።

And thus is the seizure of your Lord when He seizes the cities while they are committing wrong. Indeed, His seizure is painful and severe.

11:103
በዚህ (1) ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሠጫ አለ። ይህ (የትንሣኤ ቀን)፣ ሰዎች በርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው፤ ይህም የሚጣዱት ቀን ነው።
(1) ባለፈው ሰባት ታሪክ


Indeed in that is a sign for those who fear the punishment of the Hereafter. That is a Day for which the people will be collected, and that is a Day [which will be] witnessed.

11:104
(ይህንን ቀን) ለተቆጠረም ጊዜ እንጂ አናቆየውም።

And We do not delay it except for a limited term.

11:105
በሚመጣ ቀን ማንኛዋም ነፍስ በርሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትናገርም፤ ከነሱም መናጢና ዕድለኛም አለ።

The Day it comes no soul will speak except by His permission. And among them will be the wretched and the prosperous.

11:106
እነዚያ መናጢ የሆኑትማ፣ በእሳት ውስጥ ናቸው፤ ለነርሱ በርሷ ውስጥ ማናፋትና መንሰቅሰቅ አላቸው።

As for those who were [destined to be] wretched, they will be in the Fire. For them therein is [violent] exhaling and inhaling.

11:107
ጌታህ ከሻው (ጭማሬ) ሌላ ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ (በእሳት ይኖራሉ)፤ ጌታህ የሚሻውን ሠሪ ነውና።

[They will be] abiding therein as long as the heavens and the earth endure, except what your Lord should will. Indeed, your Lord is an effecter of what He intends.

11:108
እነዚያም ዕድለኞቹማ ጌታህ ከሻው (ጭማሬ) ሌላ ሰማያትና ምድር እስከዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሆነው በገነት ውስጥ ይኖራሉ፤ የማይቋረጥ ስጦታን ተሰጡ።

And as for those who were [destined to be] prosperous, they will be in Paradise, abiding therein as long as the heavens and the earth endure, except what your Lord should will - a bestowal uninterrupted.

11:109
እነዚህ (ከሐዲዎች) ከሚግገዙት ጣዖት በመጠራጠር ውስጥ አትኹን፤ አባቶቻቸው ከዚህ በፊት እንደሚግገዙት እንጂ አይግገዙም፤ እኛም (እነዚህን) ፈንታቸውን የማይጓደል ሲሆን የምንሞላላቸው ነን።

So do not be in doubt, [O Muhammad], as to what these [polytheists] are worshipping. They worship not except as their fathers worshipped before. And indeed, We will give them their share undiminished.

11:110
ለሙሳም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፤ በርሱም ተለያዩበት፤ ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ፣ በመካከላቸው (አሁን) ይፈረድ ነበር፤ እነሱም ከርሱ (ከቁርአን) አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ናቸው።

And We had certainly given Moses the Scripture, but it came under disagreement. And if not for a word that preceded from your Lord, it would have been judged between them. And indeed they are, concerning the Qur'an, in disquieting doubt.

11:111
ሁሉንም፣ ጌታህ ሥራዎቻቸውን (ምንዳቸውን) በእርግጥ ይሞላላቸዋል፤ እርሱ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነውና።

And indeed, each [of the believers and disbelievers] - your Lord will fully compensate them for their deeds. Indeed, He is Acquainted with what they do.

11:112
እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፤ ከአንተ ጋር ያመኑትም (ቀጥ ይበሉ)፤ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና።

So remain on a right course as you have been commanded, [you] and those who have turned back with you [to Allah ], and do not transgress. Indeed, He is Seeing of what you do.

11:113
ወደነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ፤ እሳት ትነካችኋለችና፤ ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም፤ ከዚያም አትረዱም።

And do not incline toward those who do wrong, lest you be touched by the Fire, and you would not have other than Allah any protectors; then you would not be helped.

11:114
ሶላትንም በቀን ጫፎች፤ (1) ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፤ መልካም ሥራዎች ኅጢአቶችን ያስወግዳሉና፤ ይህ ለተገሣጮች ግሣጤ ነው።
(1) ጥዋትና ከቀትር በኋላ


And establish prayer at the two ends of the day and at the approach of the night. Indeed, good deeds do away with misdeeds. That is a reminder for those who remember.

11:115
ታገሥም፤ አላህ የበጎ ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና።

And be patient, for indeed, Allah does not allow to be lost the reward of those who do good.

11:116
ከናንተም በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ቀሪ ሥራዎች ባለቤቶች ለምን አልነበሩም፤ ግን ከነሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ፣ (ከለከሉና ዳኑ)። እነዚያም የበደሉት ሰዎች (አልከለከሉም)፤ በርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ፤ አመጠኞችም ነበሩ።

So why were there not among the generations before you those of enduring discrimination forbidding corruption on earth - except a few of those We saved from among them? But those who wronged pursued what luxury they were given therein, and they were criminals.

11:117
ጌታህም ከተሞችን ባለ ቤቶቻቸው መልካም ሠሪዎች ሆነው ሳሉ፣ በመበደል የሚያጠፋቸው አልነበረም።

And your Lord would not have destroyed the cities unjustly while their people were reformers.

11:118
ጌታህም በሻ ኖሮ፣ ሰዎችን ሁሉ አንድ ሕዝብ ባደረጋቸው ነበር፤ የተለያዩም ከመሆን አይወገዱም።

And if your Lord had willed, He could have made mankind one community; but they will not cease to differ.

11:119
ጌታህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር፤ (ከመለያየት አይወገዱም)፤ ለዚሁም ፈጠራቸው፤ (1) የጌታህም ቃል፣ ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ በማለት ተፈጸመች።
(1) መጨረሻው ይህ ኾነ።


Except whom your Lord has given mercy, and for that He created them. But the word of your Lord is to be fulfilled that, "I will surely fill Hell with jinn and men all together."

11:120
ከመልክተኞቹም ዜናዎች (ተፈላጊውን) ሁሉንም ልብህን በርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን፤ በዚችም (ሱራ) እውነቱ ነገር ለምእመናን ግሣጼና ማስታወሻ መጥቶልሃል።

And each [story] We relate to you from the news of the messengers is that by which We make firm your heart. And there has come to you, in this, the truth and an instruction and a reminder for the believers.

11:121
ለነዚያም ለማያምኑት፦ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሥሩ፤ እኛ ሠሪዎች ነንና በላቸው።

And say to those who do not believe, "Work according to your position; indeed, we are working.

11:122
ተጠባበቁም እኛ ተጠባባቂዎች ነንና (በላቸው)።

And wait, indeed, we are waiting."

11:123
በሰማያትና በምድርም ያለው ምስጢር ሁሉ፣ የአላህ ነው፤ ነገሩ ሁሉም ወደርሱ ይመለሳል፤ ስለዚህ ተገዛው፤ በርሱም ላይ ተጠጋ፤ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም።

And to Allah belong the unseen [aspects] of the heavens and the earth and to Him will be returned the matter, all of it, so worship Him and rely upon Him. And your Lord is not unaware of that which you do.

Copyright 2013, AmharicQuran.com